Dn Abel Kassahun Mekuria
15.2K subscribers
535 photos
46 videos
1 file
841 links
ይህ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የተለያዩ ትምህርቶችን የሚያገኙበት በባለቤቱ የተከፈተ ቻነል ነው።

ይወዳጁን

ለፌስቡክ ገጽ
https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12?mibextid=ZbWKwL

ለyoutube
https://youtu.be/s6Cn-jMYjrk?si=Tw7lXr62xkGQtL9_

ለInstagram
https://www.instagram.com/abelkassahunm?igsh=OW
Download Telegram
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ኃምሌ አምስት ቅዱሱ ሰማዕትነት በተቀበለበት እለት እጃችሁ ትገባለች!!!
418🔥16👏14👍12❤‍🔥8🙏4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቅዱስ ጳውሎስ እና ደማስቆ!
145👍10👏1
ፀሐይ ናላ በምታዞርበት እና ሁሉም ለማረፍ ወደ አልጋው በሚሽቀዳደምበት በቀትር ሰዓት አብርሃም ግን በድንኳኑ ደጃፍ ላይ ተቀምጦ እንግዳ በተስፋ ይጠባበቅ ነበር።(ዘፍ 18) በዚህ የቃጠሎ ጊዜ (ስድስት ሰዓት) መንገድ ላይ የሚገኝ ሰው ወይ ምንም ማረፊያ የሌለው ምስኪን ነው፣ አለዚያ ደግሞ እንደዚያች ሳምራዊት ሴት ከሰው የተገለለ ብቸኛ ነው።(ዮሐ 4፥6) አብርሃም ድንኳኑን ያሰናዳው ያማረ ለለበሱ፣ ብድር ለሚመልሱ፣ በመልክም በገንዘብም ዓይን ውስጥ ለሚገቡ ሰዎች ሳይሆን፣ ሰው ለሸሻቸው መጠጊያ ለሌላቸው እና በፀሐይ ንዳድ እየተንገበገቡ ማረፊያ ፈልገው ለሚዞሩ አስታዋሽ አልባ ምስኪኖች ነበር።

አብርሃም በደጁ የሚያልፉ ምስኪን እንግዶቹን “ና እስኪ” ብሎ በማቃለል ቃል አይጠራቸውም። እየሮጠ ወደ እነርሱ ሄዶ “ጌቶች (እመቤት) እባካችሁ ወደ ቤቴ ግቡልኝ” ብሎ በትሕትና ይለምናቸዋል እንጂ።

ይህንን ግን በምን አወቅን? በሦስት ሰዎች ተመስለው ወደ ቤቱ ቅድስት ሥላሴ በመጡ ጊዜ አብርሃም እነርሱን ያስተናገደበትን መንገድ አይተን ተረዳን። አብርሃም በዚህች ቀን ተዘጋጅቶ ይጠብቅ የነበረው ሰውን እንጂ እግዚአብሔርን አልነበረም። እግዚአብሔር ግን አብርሃም ለምስኪናኑ ያሳይ የነበረው ቸርነቱን አይቶ በቤቱ ሊስተናገድ ወደደ።

አብርሃም ለድሆች ሲል በከፈተው በር በኩል በመካንነት ምክንያት የተዘጋውን የሣራን ማኅፀን የሚከፍት የሠራዊት ጌታ ገባለት።

የአንተን የብዙ ዓመታት ጥያቄ ለመመለስ እግዚአብሔር ወደ ሕይወትህ የሚገባው፣ ለሌሎች ሰዎች ብለህ በከፈትኸው የመልካምነት እና የቅንነት በር በኩል ነው።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ሐምሌ ቅድስት ሥላሴ -2017 ዓ.ም.
https://tttttt.me/Dnabel

እንኳን አደረሳችሁ!
203🙏50🔥7🥰6
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሐምሌ 11 እጅዎ ይገባል።

#ባኮስ መጻሕፍት ቤት
#ሰርዲኖስ መጻሕፍት ቤት
#አርጋኖ መጻሕፍት ቤት

ያገኙታል!
158👍13🙏7🥰1
የልደቴን ቀን አስመልክቶ በጎ ምኞታችሁን ለገለጻችሁልኝ እና ምነው ዕድሜዬም እንዲህ በረዘመ የሚያስብል ረጃጅም ምርቃት ለመረቃችሁኝ ሁሉ መድኃኔዓለም የዕድሜ ጎዳናውን ይስጥልኝ። ለሐምሌ አምስት ታስቦ የነበረው ማስፈሰኪያ (ቅዱስ ጳውሎስ) ወደ ልደት ቀኔ እየተሳበ መድረሱ ደግሞ ቀኑን የማይረሳ አድርጎልኛል። ሐምሌ ዘጠኝን ሁለት ጊዜ አከበርኩት። እናንተም ደግሞ ነገ እንድታከብሩት ተሰናድቶ ይጠብቃችኋል። ከወዲሁ መልካም ንባብ!
265🙏17🥰14👍5👏1
147👍15👏1
Channel photo updated
308🥰24👍11🙏9🔥6
+++ የሚያክም መጽሐፍ +++

የአሁን ዘመን ፈተና ትኩረትን መረጃ ላይ ማድረግ ነው። ሰው የሚያነበው መረጃ ለመሰብሰብ ለማከማቸት ሆኗል። ይህ ደግሞ ያደግንበት እና የተማርንበት ተጽዕኖ ሊሆን ይችላል። ነገሩ ሲደጋገም ደግሞ ዕውቀት ይህ ብቻ ይመስለናል። ንባባችን ሁሉ መረጃን ለመቃረም እንደ ሆነ ማሰብ እንጀምራለን። እንዲህ ከሆነ ደግሞ እጅግ እንጎዳለን።

መጻሕፍት በጥሩ ጥናት በደንብ የተጣራ መረጃ እና ወደ ሕይወታችን ልንመልሳቸው የሚገቡ ተግባራዊነት ያላቸው እዝናት ሊይዝ ይገባዋል። ብዙ ጊዜ የሚዘጋጁ መጻሕፍት ግን ወደ አንዱ ሲያጋድሉ እንታዘባለን። የመምህር አቤል መጽሐፍ እንደ ዕድል ሆኖ ሁለቱን አስተባብሮ በመያዝ የነፍሳችንን ጥያቄ ይመልስልናል። መጽሐፉ ንባብም ሕይወትም አለው። ሕይወቱ ደግሞ የቅዱስ ጳውሎስ ነው።
 
አሁን ላይ ከአባቶች የራቅነው በዘመን ብቻ አይመስለኝም። በአስተሳሰብም ጭምር ነው። ይህን የምንረዳው የቀደሙትን አባቶች መጽሐፍ ስናነብ ነው። ሐሳባቸው፣ ሥነ ጽሑፋቸው፣ ንግግራቸው፣ አገላለጻቸው፣ አንባቢው ላይ የሚፈጥሩት ስሜት ለየት ያለ ነው። አንባቢው ከእነርሱ ጋር ያለውን የቦታ እና የጊዜ ርቀት የሚያስረሳ ነው። ለምሳሌ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ጳውሎስ መልዕክታት ሲጽፍ፣ ይህንን ስሜት ያጋባብናል። መረጃ ከመሰብሰብ ይልቅ፣ በመንፈስ ይወስደናል፣ ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር በሕይወቱ ሳለ የተገናኘን ያህል ይሰማናል። ይህንን የመሰለ ተዋሕዶ ለማግኘት አንድ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ እና በቀደሙት አባቶች ድርሰት ውስጥ ራሱን ቀንና ማታ ማጥመቅ አለበት።

በተለይ ደግሞ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ስንመጣ የበለጠ ተመስጦ ያስፈልጋል፣ ብዙዎችም ሞክረውት አልተሳካም። ጳውልስን ለመረዳት እንደነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዓይነት የመንፈስ ልዕልና ይፈልጋል። መምህር አቤል ከአባቶቹ እግር ተጠግቶ ይህን መልካሙን ዜና፣ ምርጡን ዘር አቅርቦልናል። መምህር አቤል ከቅዱስ ዮሐንስ አፈውርቅ፣ ከቅዱስ ኤፍሬም፣ ከቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ጋር ባደረገው ተመስጦ ለቅዱስ ጳውሎስ ራሱን ሲያዘጋጅ ቆይቶ ኖሯል። አሁን ይህን የመጽሐፍ ማር ጋግሮ እነሆ ብሉ ይለናል።

ይህ መጽሐፍ ዝም ብሎ የሚነበብ መጽሐፍ አይደለም። ራሱን ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ማዛመድ ለሚፈልግ ሁሉ የተሰጠ መስኮት ነው። በዚህ መስኮት ቅዱስ ጳውሎስን ከልጅነት ጅምሮ አብረነው እናድጋለን። በመካከልም ቆም እያልን ልክ እንደ 3D ፊልም፣ ታሪኩን ቃኘት ቃኘት እናደርጋለን። ስለዚህ ለተመስጦ የሚመች ቦታ እና ጊዜ መድቦ የሚነበብ መሆን አለበት። ቤተክርስቲያን ሁሌም ከቅዱሳን ጋር ኅብረት እንዳለን ታስተምረናለች። ይህን እውነታ በደንብ የተረዳሁት በዚህ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ነጥቆ ከ2ሺ ዓመት በፊት ይወስድና ከጳውሎስ ጋር ያገናኘናል። ቅዱስ ጳውሎስ በተከላቸው አብያተ ክርስቲያናት አብረነው እንድንጓዝ ያደርገናል። በዚህ ጉዞውም ውስጥ የጳውሎስ መልዕክታት ፍንትው ብለው ይገለጻሉ። ጳውሎስን በጥቅሶቹ ብቻ ሳይሆን ከነአንድምታው ያጠጣናል። አሁን እኛ ጥቅስ በመማዘዝ ሐዋርያውን ካልተረዱት ወገኖች ጋር ክርክር በመግጠማችን የቅዱስ ጳውሎስን አሳዛኝ ሕይወት እንዳንመረምር የዓይን ሞራ የመሰለ ግርዶሽ ተጥሎብናል። ይህ መጽሐፍ የዓይን ሐኪም ሆኖ እንዳናስተውል የተጋረደብንን ሞራ ይገፍልናል። መጽሐፉ ጳውሎስን ማሳየት ብቻ ሳይሆን፣ በጉዞው ውስጥ አብረን ከድካሙ፣ ከደስታው፣ ከኀዘኑ ጋር እንድንካፈል ዕድል ይሰጠናል። ልቡን ለከፈተ ሰው ደግሞ የጳውሎስን ልብ ከልቡ ከፍቅሩን ከፍቅሩ እንዲዋሐድ ያደርገዋል።
 
ጥሪው እኔም ደርሶኛል።
እናንተም:- ኑ የጳውሎስ የፍቅሩ ማኅበርተኛ እንሁን።

መልካም ንባብ!

ዲ/ን ዶ/ር ቶማስ ሺመልስ
95👏2
171👍6
በምክር ቤቱ የተቀመጡት ሽማግሎች ትኩር ብለው ሲመለከቱት ፊቱ (የቅዱስ እስጢፋኖስ) እንደ መልአክ ሲያበራ አዩ፡፡(ሐዋ 6፥15) በሸንጎው የተሰየሙት አይሁድ ከዚህ ቀደም እንዲህ ያለው የፊት ብርሃን በማን ላይ ተስሎ እንደ ነበር በንባብ በደንብ ያውቁታል፡፡ ለዚህም ይመስላል እንደ መልአክ ያበራባቸውን ፊቱን ትኩር ብለው በአስተውሎት የተመለከቱት፡፡ ነገር ግን የሙሴን ሕግ ይሳደባል ያሉትን እስጢፋኖስ ከሲና ሲወርድ የፊቱ ቁርበት እንዳበራው ሙሴ ‹‹ተሸፈንልን ›› ማለት አልፈለጉም፡፡ ስለዚህ ነጸብራቁ ዓይናቸውን እንደ በዘበዘው ፍርሃታቸውን አምቀው በዝምታ ተቀመጡ፡፡(ዘጸ 34፥30) ቅዱሱ በሐሰት ተከሶ ገጻቸው በጥላቻ በጠቆረ ቃየናውያን ጉባኤ መካከል ቢቆምም እርሱ ግን መልካም አድራጊ ነውና ፊቱ በፍቅር እንደ መልአክ ያበራባቸው ነበር፡፡(ዘፍ 4፥7)”

ቅዱስ ጳውሎስ፣ ገጽ: 22

ቅዱስ ጳውሎስ እንዴት ይዟችኋል?
224👍7🥰6🤔1
+++ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" +++

ያኔ የገዳሙ መጋቢ የነበሩት አባ ተጠምቀ በጭንቀት ተውጠዋል። ከአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እግር ስር ወድቀው "ግድ የልዎትም አባ የዛሬው ጉዞ ይቆይዎ። እኔ ጥሩ ሕልም አላየሁም። እባክዎ እግርዎን ከዚህ ቤት አያንሡ፤ እንደው እባክዎ" እያሉ ይለምኗቸዋል። አቡነ ጎርጎርዮስ ግን ወደ መቂ ጊዮርጊስ ለአገልግሎት ለመሄድ ቆርጠው ተነሥተው ነበርና ሳልሄድ አላድርም ብለው እምቢ አሉ። በእርግጥ በዚያች የጉዞ ቀን ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ቀድመው ሳይረዱት ቀርተው አይመስልም። ምክንያቱም "ዛሬ ጥሩ ሕልም አላየሁምና አይሂዱ" ላሏቸው አባ ተጠምቀ " እኔስ ብሆን አንዳች ምልክት ያላየሁ ይመስልሃል። ዛሬ ጠዋት ሱሬን ስታጠቅ ሰባት ጊዜ መልሶ ሲፈታብኝ ነበር" ሲሉ መልሰውላቸዋል። ይሁን እንጂ በመቂ የሚገኝ እጅግ ሕመም የጸናበት አንድ የሚያውቁት ክርስቲያን ስለ ነበር ከራሳቸው ሕይወት ይልቅ ለዚያ ሰው ነፍስ ዋጋ ሰጥተው "ኸረ ሳላቆርበው እንዳይሞትብኝ" እያሉ አባ ጎርጎርዮስ ወደ መኪናው ፈጥነው ወጡ። ነገር ግን ከዚያ መኪና በሕይወት አልወረዱም። ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጭኖ ከመጣ ተሽከርካሪ ጋር እርሳቸው ያሉበት መኪና ተጋጭቶ እሑድ ኃምሌ 22 ቀን ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ እኛ ደግ እና ባለ ብዙ ራእይ አባት አረፉ።

ብፁዕነታቸው ከማረፋቸው ከአንድ ሳምንት በፊት በአላጌ ሕፃናት አምባ የልጆች ማሳደጊያ ተገኝተው በዚያ ቦታ ለሚሠራ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ካኖሩ በኋላ "ሰው የሚፈልገውን ከሠራ የሚጠብቀው ሞቱን ነው" ብለው ተናግረው ነበር። በውስጣቸውም የነበረው የአገልግሎት እሳት ገና እየተቀጣጠለ ቢሆንም በዚህች ምድር የሚቀራቸው የእንግድነት ዘመን ግን ጥቂት መሆኑን ስለተረዱ በዚያ ለነበሩት መንፈሳዊ ልጆቻቸው እየደጋገሙ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" ይሏቸው ነበር። ከዚህች ክፋት ከነገሠባት ዓለም ጠልቀው ፈጣሪያቸው ካለበት መንፈሳዊ አገር የሚወጡበት ጊዜ መቃረቡን ቀድመው የተረዱ አባት ነበሩ።

አቡነ ጎርጎርዮስ ከዘመናቸው ቀድመው የኖሩ፣ ትውልዱ ሃይማኖቱን ያቆዩለትን አባቶች እንዲያውቅና የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነቱንም ታሪክ ከመሠረቱ ተረድቶ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያፈቅር በቃልም በመጽሐፍም የተጉ አባት ናቸው። ቅዱስ አባታችን የነበሩበትን ዘመን አልፎ በሚሄደው ተራማጅ አሳቢነታቸውና ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገት ያሳዩት በነበረው ትጋት አሁን ላይ ላሉትና ወደ ፊትም ለሚነሡ በእውነት ለሚደክሙ ቅን አገልጋዮች ሁሉ ትልቅ አርአያ ይሆናሉ።

የአገልግሎት ድካማቸው በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን። እኛንም የአባቶቻችን ልጆች ያድርገን!!!

(*የያኔው አባ ተጠምቀ የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሣልሳይ የምሥራቅ ሸዋ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው።)

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ሐምሌ 22፣ 2014 ዓ.ም.
ዝዋይ (ብፁዕነታቸው ብዙ ሥራ በሠሩበት ክፍለ አገር ሆኜ)
86
206👍14💔7🙏3👏2🥰1👌1
+የአቤል መሥዋዕት+
(አጭር ትውውቅ)

✔️ከዲ/ን አቤል ጋር ዘለግ ያለ ጉዞ አብረን እናቀናለን። በጉዟችን የምናጠናው በየመንገዱ ምዕራፍ የምናወሳው ደግሞ የክርስቶስ እስረኛ ስለሆነው ቅዱስ ጳውሎስ ነው።

--------------------፩ኛ--------------------

🔴የመጀመርያው የጉዟችን ምዕራፍ ውስጥ መሪያችን ወደ ኢየሩሳሌም ይዞን ይጓዛል። በዛም ሳለን ክርስቶስ ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት እያደሩ የቃሉን ትምህርት እየሰሙ የእጆቹን ተአምራት እየተመለከቱ የኖሩ የቅዱሳን ሐዋርያትን ኅብረት ፈተና "የተፈተነው ኅብረት" በሚል መሪ ቃል ልብን ሰቅዞ በሚይዝ የቃል አወራረድ ወደ መጀመርያው ክፍል ይዞን ይገባል። በዚህ የመጀመርያው ምዕራፍ ነገርን ከሥሩ እንዲሉ የቅዱስ ጳውሎስ ሕይወት መቅድም የሚሆኑ ጉዳዮችን እንጂ ቀጥታ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ጉዳይ አልወሰደንም ነበር። ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ድርሰቱ በመጀመርያ ክፍሉ ከእመቤታችን አስቀድሞ ስለ አባቷ አዳም ስለ እናቷ ሔዋን መናገርን እንዳስቀደመ እንዲሁ ዲያቆን አቤልም ኢየሩሳሌም የባታው ክርስትናን ሐዋርያት ሊያስፋፉት ሲሉ የገጠማቸውን ፈተና በማስታወስ ይዘልቃል።"ሐዋርያዊ መፍትሄ" በሚል መርገፍ ደግሞ እዛው የመጀመርያ የጉዟችን ምዕራፍ ውስጥ ሆኖ ከሐዋርያት ሳይወጣ ሐዋርያት ለኅብረቱ መፈተን የሰጡትን መፍትሄ በማንሳት ስብከታዊ ትንተና በማከል ያስጉዘናል። የመፈተሄያቸው ቁልፍ ጉዳይ ስለሆኑት ሰባቱ ዲያቆናትና ሐዋርያዊው መፍትሔ ምን ያክል ስኬታማ እንደሆነ በማይጎረብጡ ቃላቶች ያስቃኝናል። የቅዱስ ጳውሎስ ሕይወት ሲነሳ ከሚነሱ ታላላቅ የተመረጡ ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው እስጢፋኖስን "የአንድ ብዙው ዲያቆን" በሚል እና በሌሎች ንዑሳን ርዕሶች ውስጥ ጣዕም ባለው ትምህርታዊ ስብከት ያነሳሳዋል።

--------------------፪ኛ--------------------

🔴የቅዱስ ጳውሎስን ጉዳይ አብዝቶ የነገረን ከምዕራፍ አንድ ጉዟችን በኋላ ነው። በሁለተኛው የጉዞ ምዕራፍ በቅዱሱ ታሪክ ውስጥ ሳትነሳ የማታልፈው ወደ አንዲት ስመ ጥር ከተማ ይወስደናል እርሷም ጠርሴስ ነበረች። ስለ እርሷ ዝና እና ከቅዱሱ ጋር ያላትን ግንኙነት በጉልህና በተረዳ ነገሮናል። በኋላም በጉዟችን ውስጥ በቅዱሱ ዙርያ ሁለት ጉዳዮችን አንስቶ አብራርቶልናል። የመጀመርያው " እኔ ደግሞ እስራኤላዊና ከአብርሃም ዘር ከብንያምም ወገን ነኝና።" የሚለውን የራሱን የሐዋርያውን ቃል ማንሻ አረጉ ነገዱን ቆጥሮ ያመጣልናል። በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 22 ላይ ተመዝገቡ የምናገኝውን "ይህ ሰው ሮማዊ ነው" የሚለውን የመቶ አለቃውን ንግግር በመያዝ ደግሞ የቅዱሱን ሮማዊ ዜግነት አስመልክቶ ጥሩ ማመሳከርያዎችን ይዞ ይመግበናል። ስለ ውልደቱ ስለ ዜግነቱና የዘረ ሐረጉን በተመለከተ በማስረጃና በጥሩ የማብራራት ስልት ይዞን መጥቱ ከዚሁ ምዕራፍ ብዙ ሳንጓዝ "ተማሪው ሳዋል" በሚል የትምህርት ሁኔታውን እንዲሁም ከዚሁ ጋር በማያያዝ የአይሁድ ትምህርት ቤቶችንም ያስጠናናል። ነገር አድርሶት የቅዱሱን የኦሪት መምህር የገማልያንም ጉዳይ የማናቃቸውን ነገሮች ጨምሮ ያሳውቀናል። መሪያችን የቅዱሱን ትምህርታዊ ሁኔታ ብቻ አንስቶ አላበቃም "ድንኳን ሰፊው" በሚል ርዕስ ሐዋርያው የነበረውን የእጅ ጥበብና እንዴት ከየት እንዳገኝው ይገልጻል። በጉዟችን ሁለተኛ ምዕራፍ የመጨረሻው ትምህርት አድርጎ የሰጠን የቅዱስ ጳውሎስ የጋብቻ ሁኔታ በተመለከት ነበር በዚህ ርእስ ውስጥ የሊቃውንትን ማመሳከርያ ማጣቀሻ በማድረግ ያብራራልናል።

--------------------፫ኛ--------------------

🔴የጉዟችን ሦስተኛ ምዕራፍ ደርሰናል...ዘለግ ያለው የቅዱስ ጳውሎስ ታሪክና ተጋድሎ ላይ ደርሰናል ከዚህ ወዲህ ቅዱስ ጳውሎስን በብዙ እንድንረዳው የሚያደርጉ ሰፋ ያሉ ገለጻዎች ተመልክተናል። የዚህ የጉዟችን ሦስተኛ ምዕራፍ የትምህርቱ ዐቢይ ምዕራፍ "የተጠመደው ትልቁ አሣ" የሚል ነው። ይህ ትልቁ አሣ ማነው? እንዴት ተጠመድ ? የት ተጠመደ ? ከተጠመደ በኋላስ ለምን አገልግሎት ዋለ? ጥያቂያችን ነው። የጉዟችን መሪ የሆነው ዲ/ን አቤል ካሳሁን በርዕስ ደረጃ ልዮ የሆነውን ጉዳይ ያብራራልናል። በዚህ ምዕራፍ አብዛኛውን በሚባል ሁኔታ ደማስቆ ላይ ያስቆየናል።"ልብስ ጠባቂው ሳዎል" የሚልና "የሞት ጽዋ ጠማቂው" በሚሉ ርዕሶች ቅዱሱ ቀድሞ የነበረው ግብርና ጥፋት ምን እንደነበር ልብ ላይ በሚያርፋ ትረካዎች ያስቃኝናል። ከዚህ ወዲህ ምን አልባት ከዚህ በፊት የምናቃቸው የሚመስሉን ከርእስ አሰጣጣቸው ጀምሮ ግን ለየት ያሉ ትምህርታዊ ስብከታዊ ትንተናዎች ነው ምናገኝው። የጳውሎስን ጉዞ ከባኩስ ጉዞ ጋር ያነጻጽራል የደማስቆ ኩነቶች ምን እንደነበሩ ከ6 በላይ ዓይነ ግቡ በሆኑ ንዑስ ርዕሶች ያስጎበኝናል። የሶርያ ራስ ደማስቆ በ ቅዱስ ጳውሎስ ህይወት ውስጥ ሰፊ ድርሻ እንዳላት ቃኝተናል።

--------------------፬ኛ--------------------

🔴ደማስቆን ከጎበኝን በኋላ አራተኛው የጉዟችን ምዕራፍ ደረስን። ከምዕራፍ ምዕራፍ ሳይደክመው ቀደመው ከነበሩ መረጃዎች በላይ ሌሎች መረጃዎችንና ማጣቀሻዎችን እያከለ ያስጎበኝናል። በአራተኛው ምዕራፋችን የቅዱስ ጳውሎስ ሰብእና ቦታውን ይዟል። የቅዱስ ጳውሎስ መልክ ገጽታ አቋም እና የመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ቀደምት ድርሳናትን እና የሊቃውንትን አተያይ እያነሳ መልክአ ጳውሎስን በልባችን ይስልብናል። ግዘፍ ነስቱ እየተመለከትነው እንደሆነ እስክናስብ ድርስ መልኩን በቃላቶች አስውቦ ይስለዋል። በዚህ ምዕራፍ ሰፊ ትንተናዎች ቢኖሩትም ብዙ አያስቆየንም "ተንቀሳቃሽ ፍቅር" እና "ትህትና ለባሽ" በሚሉ ንዑስ ርዕስ ውስጥ መልካም መዓዛ እንዳለው ሽቶ የተወደደውን የቅዱስ ጳውሎስን ሰብእና በብዙ መደነቅ ያስቃኝናል።

--------------------፭ኛ--------------------

🔴የጉዟችን የመጨረሻ ምዕራፉች በቅዱስ ጳውሎስ ዙርያ አዳዲስ እውቀቶች ሸክፈዋል። ካለፉት ምዕራፉች በጣም ሰፊና ብዙ ርእሰ ጉዳዮች ተንሸራሽረውበታል። በምዕራፍ አምስት ብቻ ከገጽ 176 እስከ ገጽ 342 ድረስ የሚዘልቅ ትንናዎች 20 የሚያክሉ ሳቢ ርእሶች ይዟል። የዚህ ምዕራፍ የጉዞ መዳረሻ ከደማስቆ በኋላ የነበረውን የቅዱሱን አገልግሎት ያስቃኛል። ቅዱሱ ያደረጋቸውን ጉዞዎች አብረነው እንድንጓዝ እድል ይሰጠናል። በየሄደበት የገጠሙት ፈተናዎችና ህመሞች ያስታውሰናል። ስለ ሃያውም ንዑስ ርእሶች ጊዜ ይገድበናል እንጂ ብናነሳ በወደድን ነበር። ቅዱስ ጳውሎስን ተጋድሎውን ለማጥናት የተመረጠ ምዕራፍ ይህ ነው።

--------------------6ኛ--------------------

🔴ጉዟችን ሊገባደድ አንድ ምዕራፍ ቀረን። ከኢየሩሳሌም የጀመረው ጠርሴስን ደማስቆን ያቋረጠው ቅዱሱ የተጓዘባቸውን ሀገሮች ያካለለው ቅዱስ ጳውሎስን እንድናጠናው ከእርሱ ጋር ያስጓዘን መጸሐፍ ስድስተኛው ምዕራፍ ላይ ያበቃል። ይህ ምዕራፍ እንደ አምስተኛው ምዕራፍ ሰፊ ርእሰ ጉዳዮች ታሪኮች ትንተናዎች ይዟል። የቅዱስ ጳውሎስን የመጨረሻ ሰዓቶች ከ10 በላይ በሆኑ ማንሻ ርእሶች ስለ ስራው እያደነቅን ስለ ገጠመው ሁሉ እያዘንን የቅዱስ ጳውሎስን የመጨረሻ የስንብት ግሩም ቃሎች እያሰብን እዚህ ላይ እናገባድዳለን። ሀሉም ምዕራፉች አስተማሪዎች ሆነው ሳለ ምዕረፍ አምስትና ስድስት በጉዞዬ ቅዱስ ጳውሎስን ያገኝውባቸው ድንቅ ምዕራፉች ናቸው።
26
--------------------ተፈጸመ--------------------

🔴ተመልሰናል... ቅዱስ ጳውሎስን ፍለጋ ከዲያቆኑ ጋር ጉዞ ጀመርን በየተጓዝንበትም ሁሉ ቅዱሱን አገኝነው ደስም አለን። ለመብላት የሚመች ገብቶ የማያውክ የአቤል ምሠዋዕት እነሆ።

ኦርቶዶክሳውያን መጻሕፍትን እናንብ እናስነብብ

ዲ/ን ሞገስ አብርሃም
ሐምሌ 2017
✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️

"...እንደኣርመው ተሰጥቶኝ የታረምሁበትን መጽሐፍ ላኣሳያችሁ፡፡ እጃችሁ ላይ ያለው መጽሐፍ “የአንድ ብዙ ነው” ታሪክ፣ ወግ፣ ትርጓሜ፣ ባህል ያለበት መጽሐፍ ነዋ! በጉባኤ ቤት የሰማኋቸውን ታሪኮች አድራሻ እንዳገኝላቸው ረድቶኛል። ተጀምረው የቀሩትን ጨርሶልኛል። ታሪክ ጸሐፊዎች ከተርጓሚዎች፣ ከተመራማሪዎች እንዴት እንደሚስማሙና የሁሉንም ምስክርነት በመቀበል አንዲት እውነትን ለሰዎች የተገለጠች እንድትሆን መጽሐፋ የሄደበት ጥበብ የሚያስገርም ነው። ዲያቆን አቤል በገነት ካሉ አፍላጋት መካከል አንዱንም ሳንቀምሰው እንዳንቀርአራቱን የገነት አፍላጋት መፍሰሻቸውን በዚህ መጽሐፍ ውስጥ አድርጎልናል። ከተወደደው መምህራችን ከቅዱስ ጳውሎስ በቀር አራቱን አፍላጋት የሚመስል ማነው?" ሊቀ ሊቃውንት ስምዓኮነ
68👍2👏2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“ቅዱስ ጳውሎስ” መጽሐፍን ፈልጌ አጣሁት? የሚሉ መልእክታት ለላካችሁልን ሁሉ፣ መጽሐፉ ዳግመኛ ከኅትመት ቤት ወጥቶ ከነገ ጀምሮ በሁሉም መጻሕፍት መደብር እና ሐሙስ (ነገ) በኤግዝቢሽን ማዕከል በሚደረገው “የንባብ ለሕይወት” የአራት ቀናት የመጻሕፍት ዐውደ ርእይ ላይ በስፋት ታገኙታላችሁ።

ኑ የጳውሎስ የፍቅሩ ማኅበርተኛ እንሁን!!!
102