Dn Abel Kassahun Mekuria
15.2K subscribers
534 photos
45 videos
1 file
841 links
ይህ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የተለያዩ ትምህርቶችን የሚያገኙበት በባለቤቱ የተከፈተ ቻነል ነው።

ይወዳጁን

ለፌስቡክ ገጽ
https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12?mibextid=ZbWKwL

ለyoutube
https://youtu.be/s6Cn-jMYjrk?si=Tw7lXr62xkGQtL9_

ለInstagram
https://www.instagram.com/abelkassahunm?igsh=OW
Download Telegram
📕 የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የአንባብያን ኅብረት
በ2014 ዓ.ም. ለአንባብያን ታላቅ የምሥራች 📘

ከወርኃዊው የመጻሕፍት ዳሰሳ ጋር በአንድ ላይ የሚካሄድ አንባብያንን የሚያነቃቃ ባለ 12 ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር መስከረም 30 ይጀምራል:: ቅዱስ ፊልጶስ ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ያቀረበውን "የምታነብበውን ታስተውለዋለህን?" የሚለውን ወርቃማ ጥያቄ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ለዚህ ዘመን አንባቢዎች ድጋሚ ለማቅረብና ስለሚያነብቡአቸው መጻሕፍት ያላቸውን ማስተዋልና መረዳት ለመለካት "ፊልጶስ እና ባኮስ" የተሰኘ እጅግ ደማቅ የጥያቄና መልስ ውድድር አዘጋጅቶአል::

📚 ተወዳዳሪዎች

የጥያቄና መልስ ውድድሩ ላይ ለመሳሣተፍ አንባብያን ሁሉ የተጋበዙ ሲሆን ለተወዳዳሪነት የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት በየወሩ የመጀመሪያ አምስት ቀናት በGoogle form መመዝገብ ይቻላል:: ተወዳዳሪዎች ቅጹን እንደሞሉበት ቅደም ተከተል በውድድሩ ላይ የመካፈል ዕድል የሚያገኙ ሲሆን በዚህ የውድድር ዓመት በ12 ዙር የ ፊልጶስ እና ባኮስ ጥያቄና መልስ ውድድር ላይ የሚካፈሉት በየዙሩ 6 በጠቅላላው 72 ተወዳዳሪዎች ይሆናሉ::

📚 የጥያቄና መልሱ ይዘት

ፊልጶስና ባኮስ የጥያቄና መልስ ውድድር ዲያቆኑ ፊልጶስ እና ጃንደረባው ባኮስ እንደተጠያየቁበት "ትንቢተ ኢሳይያስ" ሁሉ ጥያቄና መልሱ የሚያጠነጥነው በአንድ የተመረጠ መጽሐፍ ላይ ብቻ ነው::

ለምሳሌ :- ለመስከረም 30፣ 2014 ዓ.ም. ለ"ፊልጶስ እና ባኮስ ጥያቄና መልስ ውድድር" የተመረጠው መጽሐፍ :- የዲያቆን ያረጋል አበጋዝ "ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕይወቱና ትምህርቱ" የተሰኘው መጽሐፍ ሲሆን በውድድሩ ላይ የሚወጡት ጥያቄዎችም ሙሉ በሙሉ ከዚህ መጽሐፍ ላይ ብቻ ይሆናሉ::

በዚህ መሠረት በየወሩ በፊልጶስና ባኮስ የጥያቄና መልስ ውድድር ላይ የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች አስቀድሞ በወሩ መጀመሪያ ላይ ከምዝገባው ጋር ይፋ የሚሆነውን የተመረጠውን መጽሐፍ ከጫፍ እስከጫፍ አንብበው ለውድድሩ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል::

📚 ሽልማቶች :-

በፊልጶስና ባኮስ ወርኃዊ የጥያቄና መልስ ውድድር ላይ በየዙሩ የሚሣተፉና ከ1-3 የሚወጡ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ዕለት እዚያው ሽልማት ያገኛሉ:: በዚህም መሠረት :-

1ኛ ለሚወጡ :- የአንድን የጥንት ወይም የቅርብ መንፈሳዊ መጽሐፍ ደራሲ ሁሉንም ሥራዎች ስብስብ (Full collection)

2ኛና 3ኛ ለሚወጡ :- የዚያኑ ደራሲ አንድ አንድ መጻሕፍት ይሸለማሉ::

በ12ቱ ዙሮች ተወዳድረው አንደኛ የሚወጡ አንባብያን ደግሞ ለአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር የሚቀርቡ ሲሆን በመጨረሻው ዙር አሸናፊዎች :-

1ኛ ለሚወጣ (ለምትወጣ):- በብዙ መጻሕፍት የተሞላ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የመጽሐፍ መደርደሪያ ሼልፍ

2ኛ ለሚወጣ (ለምትወጣ) :- በሶፍት ኮፒ መጻሕፍት የተሞላ የመጽሐፍ ማንበቢያ ኪንድል (Kindle)

3ኛ ለሚወጣ :- በማይክሮ ፊልም በተነሡ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት የተሞላ ሀርድ ዲስክ የሚሸለሙ ይሆናል::

መስከረም 30 የሚካሔደው የመጀመሪያው ዙር የፊልጶስና ባኮስ የጥያቄና መልስ ውድድር ላይ ለመካፈል ለምትፈልጉ አንባብያን ምዝገባው ከመስከረም 1-5 ባሉት ቀናት መሆኑን እንገልጻለን::

#የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው?

ለመመዝገብ ይህንን ይጫኑ

https://forms.gle/hS8YCaMJC6GGSpTA8

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ
+ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የመጻሕፍት ጉባኤ በሐዋሳ ሊጀመር ነው! +

ለአንድ ዓመት ያህል በአዲስ አበባ ብቻ ተወስኖ የነበረው በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የሚካሔደው የጃንደረባው የመጻሕፍት ጉባኤ ሠረገላ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ በመገስገስ ከአዲስ አበባ ውጪ የመጀመሪያውን ጉባኤ በሐዋሳ ሊያደርግ ዝግጅቱን አጠናቅቆአል:: ከወራት በፊት ከሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ጋር በመተባበር በኢጃት ፕሮጀክቶች ላይ ውይይት ያደረጉት የሐዋሳ አገልጋዮች በንቃት የሚሳተፉበትን ይህንን ልዩ የመጻሕፍት አንባቢያን ጉባኤ በሐዋሳና አካባቢዋ ያላችሁ ሁሉ እንድትታደሙ ተጋብዛችኁዋል::

በዕለቱ የሐዋሳ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ አንባቢያን ኅብረት (Book Club) በይፋ ይመሠረታል:: የጃንደረባውን ባኮስ ዜና ጥምቀት የሚተርከው "ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ" መጽሐፍ ዳሰሳ ቀርቦበት ውይይት ይካሔዳል::

"ጃንደረባውም ደስ ብሎት መንገዱን ይሔድ ነበር" ሐዋ. 8:39
#የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው?