Yismake Worku
20.5K subscribers
334 photos
9 videos
1 file
69 links
Bilingual content in English & Amharic, author tips, book reviews, behind-the-scenes writing insights, and interactive community discussions.

Buy ads: https://telega.io/c/yismakeworku
Download Telegram
ነገሮች አልሳካ ብለው አስቸገሯችሁ!? መልፋት ሰርክ የምታደርጉት ቢሆንም ቅሉ እረፍት ፊቱን ነስቷችኋል!?
እንግዲያውስ እምነትን ጨብጡ፣ ለፈጣሪ ሁሉን ነገር ሥጡት። ንገሩት፣ ተነፍሱለት። የነገራችሁት አምላክ አብዛኛውን ነገር እንደሸፈነላችሁና እናንተ ትንሽ ጥረት ብቻ እንደሚቀራችሁ በማመን ነገሮችን ለማሳካት ሞክሩ። ይሳካል! እመኑኝ።
ስለዚህ ተነሱ!
አቅዱ!
ንገሩት!
#እስከመቼ የሚለውን ስንኝ ይዛችሁ ስኬት የተባለ ሀረግ እስከሚመጣላችሁ ግጥሙ!
@yismakeworku
የግድግዳ ሰዓትን አስተውላችሁ ታውቃላችሁ።
የሰዓት እና የደቂቃ መቁጠሪያዎችን ግዝፈት ከሴኮንድ ቆጣሪ ይልቃል።
ያቺ ደካማ የምትመስል ነገር ግዙፎችን ታሽከረክራለች፣ ትዘውራለች።
እንግዲህ ሠዓትን ስኬት፣ የሴኮንድ መቁጠሪያን ደሞ ልፋትን ትወክላለች።

የሠዓት መቁጠሪያን ያክል ግዙፍ ለመሆን አትቸኩሉ። ስኬት በአንዴ አይገኝም። የሴኮንድ መቁጠሪያ ሁኑ። የሴኮንድ መቁጠሪያ ሺ ጊዜ ለፍታ፣ ስትሽከረከር ነው ሰዓትን የምትሰጠን።

#እስከመቼ በሉ!
@yismakeworku
👍3