Yismake Worku
20.5K subscribers
334 photos
9 videos
1 file
69 links
Bilingual content in English & Amharic, author tips, book reviews, behind-the-scenes writing insights, and interactive community discussions.

Buy ads: https://telega.io/c/yismakeworku
Download Telegram
‹‹……………ተው ብዬህ አልነበረም?......ክፉ ቀን ማለፊያ
ጥበብን አልገርሁህም ነበር?.........ክፉ ቀንን በጥበብ
ከማለፍ በላይ ጥበብ የለም! ይች ደም መላስ የለመደች
ሀገር የምትለወጥ መስሎሃል!
#ቴዎድሮስን በላች፣ አልተለወጠችም፡፡
#ገብርዬን በላች፣ አልተለወጠችም፡፡
#ሚኒሊክ ደከመላት፣ አልተለወጠችም፡፡
#ፋሲልን በላች፣ አልተለወጠችም፡፡
#አሉላን በላች፣ አልተለወጠችም፡፡
#አንተንም በላች፣ አልተለወጠችም፡፡
#የበላይን ደም ጠጣች፣ ይኸው አልተለወጠችም፡፡
ስንት ጀግኖች ሞቱላት፣ አ ል ተ ለ ወ ጠ ች ም፡፡
አልነገርኩህም?….አልነገርኩህም?…አልነገርኩህም?
አትሰማም! አትሰማማ!
ተው እያልኩህ ሞትህ!......ሞ ት ህ!
…….>>
@yismakeworku ቃለ ዲዲሞስ፥ ዴርቶጋዳ