Yismake Worku
20.5K subscribers
334 photos
9 videos
1 file
69 links
Bilingual content in English & Amharic, author tips, book reviews, behind-the-scenes writing insights, and interactive community discussions.

Buy ads: https://telega.io/c/yismakeworku
Download Telegram
Dertogada Part 9
#ዴርቶጋዳን_በትረካ
.
ክፍል 9/፱፣ ይህ ትረካ 33ደቂቃዎችን እና 3.8ሜጋባይትን አጠቃሎ ይዟል።
@Yismakeworku
Dertogada Part 10
#ዴርቶጋዳን_በትረካ
.
ክፍል 10/፲፣ ዴርቶጋዳ በ31ደቂቃ እና በ3.5MB እንዲህ ቀርቧል
@yismakeworku
@yismakeworku
እደግልኝ ልጄ - የሚታዘዝ ልጅ ይስጥህ
@yismakeworku
ከእለታት ባንዱ እኔና አለምፀሀይ ወዳጆ
@yismakeworku
🥰1
Dertogada Part 11
#ዴርቶጋዳን_በትረካ
.
ክፍል ፲፩/11፣ በ33ደቂቃ እና 3.8MB በትረካ ይቀርባል
@yismakeworku
@yismakeworku
በወቅቱ ካልተነገሩ በስተቀር፣ በሁዋላ የሚረሱ ሀሳቦቼን
እነሆ፡፡
.በጂማ ከተማ ሰሞኑን የኦህዴድ ስብሰባ ነበረ፡፡ እና
ከአማራ፣ የብአዴን ተወካይ ንግግር አድርገው ነበር፡፡
የህውሓትም እንዲሁ፡፡ (ያው ቴሌቪዥን ማየት በአንድ ጎኔ
ተኝቼ ሆኗል ሥራየ) ...እና የብአዴኑ ተወካይ ጥቂት
ኦሮምኛ ቃላት ወረወረ፡፡ የህውሀቱም እንደዛው፡፡
በጉባኤው የተገኙትም ሰዎች አዳራሹን በሳቅ ቀውጢ
አደረጉት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ፡፡ እኔ ግን
እየተሳቀቅኩ ነበር፡፡ ይመስገኑና ጠቅላይ ሚኒስትራችን፣
ግብፅ ሄደው በአማርኛ፣ ትግራይ መጥተው በትግርኛ፣
ኦሮምያ በኦሮምኛ፣ ሶማሌ ሄደው በሶማሊኛ ሲናገሩ
ነበር፡፡ ቀላል አይደለም ይሄ፡፡ ግን የብአዴኑ እና የህውሀቱ
ተወካዮች ሳቅ የመነጨው ከምንድን ነው? ሳቁባቸው
ወይስ ሳቁላቸው፡፡ የእነርሱ አነጋገር አንድ እንግሊዛዊ
መጥቶ በኦሮምኛ የተናገረ ይመስላል፡፡ የቋንቋ ጉዳይ
ሲነሳ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡፡
.የሆኑ ሰውዬ ነበሩ አሉ፡፡ (ኢትዮጵያዊ ናቸው) ስማቸውን
አልጠቅስም፡፡ የተባበሩት መንግሥታትን ድርጅት በመሪነት
ለመመረጥ ቅስቀሳ ያደርጉ ነበር፡፡ዞረው ዞረው ሌሎቹን
ሀገራት አዳርሰው "ሩሲያ"ደረሱ፡፡ ሞቅ ደመቅ ብሎ ህዝቡ
በአደባባይ ወጥቶ ጠበቃቸው፡፡ ንግግር ጀመሩ
ኢትዮጵያዊው፡፡ ሰፊ ንግግር ካደረጉ በሁዋላ ግን "ሆባይ"
የሚል ቋንቋ ከአንድ ሩሲያዊ ተሰማ፡፡ ሁሉም ተቀበሉት፡፡
"ሆባይ"
"ሆባይ"
"ሆባይ"
"ሆባይ"
"ሆባይ"
እያሉ የተሰበሰቡት ሰዎች አቀለጡት፡፡ ከዛ ወደ ኢትዮጵያ
መጡ ሰውየው፡፡ በቃ የተባበሩት መንግስታት መሪ ሆንኩ
አሉ እንደደረሱ፡፡ ሁሉንም ቦታ ቀስቅሻለሁ፡፡ መልካም
አቀባበልም ነበረኝ አሉ፡፡ የመጨረሻውማ ለጉድ ነው ሲሉ
ገለፁ፡፡ እንዲያውም ቀስቅሼ ስጨርስ "ሆባይ" ነው ያሉኝ
በጥንት የሩሲያ ቋንቋ፡፡ "መሪያችን"ማለት ነው፡፡
"አይ...." አሉ አንድ ሌላ ኢትዮጵያዊ ሰውዬ፡፡ "ዝንጆሮ"
ማለት ነው "ሆባይ" ማለት አሉት፡፡ "በሀገርህ ቋንቋ
በግዕዝ ነው ያናገሩህ፡፡ አየኸው ፈተናቸውን? አንተ
አማርኛ በሚመስል እንግሊዝኛ ስትናገር፣ ሩሲያኖች
በሀገርህ ቋንቋ ጣሉህ"
አ...ል...ተ...መ...ረ...ጡ..ም!
በቋንቋቸው ተሰድበው እርፍ!
(ማስታወቂያ፡- "ግዕዝን ካላወቁ" እኔን ይቅጠሩኝና
ለጠቅላይ ሚንስትሩ እኔ አፌ ሲፈታ አስተምራለሁ፡፡)
@yismakeworku
@Yismakeworku
ከፀሀዬ ጋር
.
@yismakeworku
የሰው ልጅ መገኛ (አሁን የሰው፣ እንደ ጴጥሮስ ቁልቁል
መሰቀያ)፣ ከሆነችው ሀገራችን ላይ እስካሁን
የሚገርመኝ አንድ ነገር አለ፡፡ የሚወጡት አፅሞች የሴት
መሆናቸው ነው፡፡ ሉሲ!!! ሰላም!!! አርዲ!!! ወንድ
አልነበረም? (ኧረ የወንድ ያለሽ?) የሚል ሙዚቃ እውቁ
ሙዚቀኛ ፀሐዬ ዮሐንስ እንዲዘፍነው ካዘጋጀሁት
ሙዚቃ ላይ በውስን የተወሰደ፡፡
@yismakeworku
ስለ ጥንታዊ መጻሂፍታችን እነግራችኋለሁ ብዬ በመጥፋቴ ይቅርታ እየጠየቅኩ በቅርቡ ግን ለማሳወቅ እንደምሞክር ሳሳውቅ በደስታ ነው።
@yismakeworku
@yismakeworku
ብዝዎች በድርሰቶቼ ጋር አብዝቼ ስለምዘክራት "ቶ" ፊደል ትርጉም እንዳስረዳቸው ሲጎተጉቱኝ ኑረዋል። እነሆ እኔም ረዘም ቢልም ልመልስላችሁ አስባለሁ።
የእርስዎም ጥያቄ ነው?
አዎ
አይደለም
@yismakeworku
ስለ "ቶ" ረዘም የሚለውን ዳሰሳዬ ለመንገር በክፍል በክፍል ካላቀረብኩት ይንዛዛል። በቻልኩት መጠን አሳጥሬ ነገር ግን ይዞቱን ሳለቅ ስለምንነቱ እንዲህ ዘግቤዋለሁ።

ክፍል ፩
"አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል" [መስቀሌን በመስቀሌ
ላይ አኑር/አስቀምጥ]
የዚህን እጅግ የረቀቀ አባባል የምንረዳው በትርጓሜ እና
በምርምር ነው። መስቀል ከእየሱስ በፊት የነበረ እና ያለ
ነው። ምሳሌነቱም የሰው ልጅ የቁጥር መልክ ነው።
ስለሆነም "ተ" ን ሰብእ ድረስ ስንቆጥረው "ቶ" ሳብኡን
ወይንም ሰባተኛውን እናገኛለን። ይህንን ነው እንግዲ
ምንም መነሻና መድረሻ ቃል ሳይጨምሩ ከነአጠራሩ
በግዕዙ "አንቅህ" [ankh] ወይም የህይወት ምልክት
በማለት የሚጠሩት ። "ቶ" ራስ ያለው ሰው ወይም ሰብእ
ማለት ነው። ሰብእ ማለት ሰው ማለት ነው ይህውም
ከሰባት ባህርያት ከአራቱ የሥጋ በህርያት ውሃ፣ አፈር፣
እሳት፣ ነፍስ እንዲሁም ከሶስቱ የነፍስ ባህርያት ህያውነት፣
ልባዊነት፣ ንባባዊነት የተፈጠረ ነው።ከእየሱስ ክርስቶስ
ልደት በፊት ኢትዮጵያውያን ነገስታት መስቀል በትረ
መንግስታቸው ወይም መለያቸው ነበር።በቀደሙ ዘመናት
ደግሞ ኢትዮጵያውያን ነገስታት በሄዱበት እና በተቀመጡበት
ቦታ ሁሉ በእጃቸው ይይዙት ነበር።ይህም የበትረ መንግስት
ቀዳሚ ምሳሌ መሆኑ ነው። በርግጥ በሮማውያን ዘመን
ደግሞ የወንጀለኛ መቅጫ ወይንም የሰው መስቀያ ሁኖ
ቆይቷል በምርምርም ስንረዳው ሰውን በሰው መግደል
ወይም ማጥፍት መሆኑን እንረዳለን።
(ይቀጥላል...)
@yismakeworku
@yismakeworku
👍3
ወዳጄ። የልብ ጓደኛዬ።
እንዲህ አለኝ "ይስምሽ አንድ ነገር አስቢያለሁ! በቴሌግራም ቁምነገር ለመስራት አስቢያለሁ" ግራ ስለገባኝ የግንባሬን ውጥር ቆዳ በማኮማተር እንዳልገባኝ ላሳየው ሞከርኩ። ስለገባው ማብራራቱ ቀጠለ... "ምን መሰለህ! በቴሌግራም የምችላትን የእንግሊዘኛ ቋንቋ በማካፈል ለወዳጆች ለማስተማር ነው! ሆኖም ግን ከአንተ እርዳታ እሻለሁ ማለትም ቻናሉን በቻናልህ አስተዋውቅልኝ" አለኝ።
ለጥሩ ነገር ስለሆነ እና ለወዳጆቼም ልጋብዝ ስለምሻ ምን ገዶኝ በማለት ጭንቅላቴ ከታች ወደላይ ነቀነቅኩለት። ፈገግ አለ።

ስለዚህ ጓደኞቼ የእንግሊዘኛን ቋንቋ እጅግ በቀላሉ ለማወቅና ለመማር ከፈለጉ ይሄን ቻናል መቀላቀል ይችላሉ
@Ethioenglizegna ይላል ማስፈንጠሪያው።
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEz1L5EX2Ip3StgxBQ
👍3
ይህ የኔ፣ ያንተ፣ ያንቺ፣ የእናንተ፣ የኛ ጣና ነው።
ጣና ታሟል! የሀገሬ ባለስልጣናት ችላ ብለውታል።
እባካችሁ እባካችሁ ጣናን አታጨልሙብን
ይህንን ፅሁፍ በየ "ግሩፑ" በየ "ቻናሉ" #ሼር በማድረግ ድምፃችንን ላልሰሙት በማሰማት ሀላፊነትህን ተወጣ።
@yismakeworku
@yismakeworku
👍1
የመጀመሪያውን እንግሊዘኛ ቋንቋን በቴሌግራም የማስተማር ስራዬ ተጀመረ ይለኛል ወዳጄ። ያሳቀኝም "እንዳትፎርፉ ነገ ትምህርት አለ" ብሎ ሀሳቡን ሲዘጋ ነው ሃሃሃሃ።

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርቱን በ @ethioenglizegna መከታተል እንደምትችሉ ጋብዟል።

መልካም!