#update አዲስ አበባ
በሱሉልታ እና ቡራዩ በኩል ወደ አዲስ አበባ የገቡ የኦነግ ደጋፊዎች በፖሊስ ታጅበው ወደ የመጡበት ተመለሱ፡፡
ከሰዓት በኋላ በፒያሳ፣ ቡራዩና አዲሱ ገበያ አካባቢ ውጥረትና የግጭት ሥጋት ሠፍኖ ውሏል፡፡
በቡራዩ በኩል ወደ አዲስ አበባ ለመግባት የሞከሩ ወጣቶች ዘልቀው እንዳይገቡ በፌደራል ፖሊስ አባላት ታግደዋል፡፡
በሱሉልታ በኩል የገቡት በአድማ በታኞች ታጅበው ተመልሰዋል፡፡
📌በዊንጌትና አዲሱ ገበያ አካባቢ ሱቆችና የንግድ ቤቶች ተዘግተው ውለዋል፤ ከሕዝብ ትራንስፖርት ውጪ የመኪና እንቅስቃሴ አነስተኛ ነበር፡፡
📌የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ዳይሬክተር #ጃዋር መሐመድ በፌስቡክ ገጹ “ሕዝቡን ዋና ከተማህ አትገባም ማለት ትልቅ ድፍረት ነው፤ ፖሊስ በፍጥነት መንገድ ከፍቶ ሕዝቡ በሠላም ገብቶ እንዲወጣ ካላመቻቸ ሕዝቡ ጥሶ መግባቱ አይቀሬ ነው” ሲል ጽፏል፡፡
©ዋዜማ ራዲዮ
@yenetube @mycase27

#ጃዋር
ጃዋር መሐመድ የኢትዮጵያ የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታ «ግልፅ ያልሆነ፣ በቂ ጥናትና በቂ ውይይት ያልተካሔደበት» ነው ሲል ተቸ። በ2013 ዓ.ም. ሥራ ላይ ይውላል ተብሎ የሚጠበቀው ፍኖተ-ካርታ «ተድበስብሶና ተምታቶ የቀረበ» ነው ሲል ወርፎታል።
ለኦኤምኤን በሰጠው ማብራሪያ «የትምህርት ፍኖተ-ካርታ ከሀገር ግንባታ ጋር የተያያዘ ነው። የሀገር ግንባታ ደግሞ ፖለቲካዊ ፕሮጀክት ነው። ስለዚህ የትምህርት ፍኖተ-ካርታው ካገሪቷ የፖለቲካ ፍኖተ-ካርታ ጋ መዋሐድ መቻል አለበት» ብሏል።
Via:- Eshet bekele
@YeneTube @FikerAssefa

#ጃዋር መሃመድ ከAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት ጋር ባደረገው ቆይታ ያነሳቸው ሀሳቦች:
📌 እስካሁን ሊገባኝ ያልቻለው ለምን በለሊት ጥበቃ ማንሳት እንደተፈለገ ነው። ከፌደራል ፖሊስም ሆነ ከደህንነት ተቋማት ጋር የነበረኝ ግንኙነት ጥሩ የሚባል ነበር።
📌 የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ትናንት "ጥበቃዎቹ እንዲነሱ የተፈለገው የፀጥታ ችግር ስለሌለ ነው" ብሎ ነበር። እውነታው ግን ከሁለት ሳምንት በፊት እንቅስቃሴያችንን እንድንቀንስ እና በርካታ ህዝብ ከሚሰበሰብበት ቦታ ከመሄድ እንድንታቀብ ተነግሮን ነበር። እንደውም ተጨማሪ ሀይል ለመጨመር ሀሳብ እንዳላቸው ነግረውን ነበር። ስለዚህ ይህ እየተባለ የፀጥታ አካላቱን ለማንሳት መፈለጋቸው ግር የሚል ነበር።
📌 ለምን ይህ እንደተከሰተ ሊናገር የሚፈልግ የለም። ጣት መጠቋቆም ብቻ ነው ያለው፣ ይህም የሰው ህይወት እንዲጠፋ ምክንያት ሆኗል።
📌 ከጠ/ሚሩ ጋርም ሆነ ከሌሎች አመራሮች ጋር ቁጭ ብለን ማውራት እንችላለን። እኔ ለዛ ዝግጁ ነኝ።
📌 ጠ/ሚሩ በፓርላማ ያረጉት ንግግር ግርታን ፈጥሮብኛል። ልዩነት ቢኖረንም ጥሩ ግንኝነት ነው ያለን። ከሀገር ከወጡ በሁዋላ በስልክ አላወራንም። ሲመለሱ ግን በሆኑት ጉዳዮች ላይ ብናወራ ፍላጎቴ ነው።
📌 ሚኔሶታ ስንገናኝ የመንግስት ጥበቃ እንዲኖረኝ የነገሩኝ ጠ/ሚሩ ናቸው። እንደውም መንግስት እንዲህ አይነት ጥበቃ ከመንግስት አካላት ውጭ ላሉ ሰዎች እንደሚሰጥ አላውቅም ነበር። አሁን ላይ ምን እንደተፈጠረ አላውቅም።
📌 "መደመር" መፅሀፍን አንብቤዋለሁ። ሀሳቡ ጥሩ ነው፣ ሊሻሻልም ይችላል። ግን እንደ እኛ ላለ ሀገር ፖሊሲ ሲነደፍ ሁሉም ሊመክርበት ይገባል። አሁን እየተሄደበት ያለው መንገድ ግን ግለኝነት ያለበት ይመስላል። መለስ የሰራው አይነት ስህተት ማለት ነው። አብዮታዊ ዴሞክራሲ መጥፎ ሀሳብ አልነበረም፣ ግን ተቃዋሚዎችን ያማከለ አልነበረም ስለዚህ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት አጣ። አሁንም ያ ሁኔታ እንዳይከሰት እሰጋለሁ።
📌 የመሪው ፓርቲ አንድ መሆን ጉዳይ ግን የተቻኮለ ይመስለኛል። አሁን ላይ አስፈላጊም አይመስለኝም። እንዲሁም (ጠ/ሚሩ) የፖለቲካ ስርአቱን አሀዳዊ ለማድረግ ያላቸው ዝንባሌ ላይ ሊያስቡበት ይገባል።
📌 ውጪ እያለሁ የሆነ ግዜ ፖለቲካውን ትቼ፣ የፌስቡክ አካውንቴን ዘግቼ ወደ ትምህርት እንደማደላ አስብ ነበር። ያ ግን እስካሁን አልሆነም። ዋናው ነገር ግን እኔ እዚህ የመጣሁት ላግዛቸው ነበር፣ ሳግዛቸውም ነበር።
📌 አሁን ግን ዳር ላይ ሆኜ መቀጠል እንደሌለብኝ እየተሰማኝ ነው። ፖለቲካው ላይ እንድሳተፍ የህዝብ ፍላጎትም አለ። ይህ ተቃዋሚዎችን መርዳት ይሁን፣ ተቃዋሚዎችን እና ገዢው ፓርቲን ማቀራረብ ይሁን እስካሁን አልወሰንኩም። ይህ በቅርብ የመጣ ሀሳብ ነው፣ በተለይ ባለፉት 24 ሰአታት። ከተቃዋሚዎችም፣ ከዢው ፓርቲ ሰዎችም እንዲሁም ከሌሎች ጋር አወራበታለሁ። ዋናው ግን ለሀገር የሚጠቅም ነገር መስራት እፈልጋለሁ።
📌 አሁን ላይ ሀገሪቱ ባለችበት ሁኔታ ምርጫ ማካሄድ እጅግ አደገኛ ነው ብዬ አስባለሁ። ጠ/ሚሩ እንዲሁም አንዳንድ ምርጫውን እናሸንፋለን ብለው የሚያስቡ ፓርቲዎች ምርጫው እንዲካሄድ እንደሚፈልጉ አውቃለሁ። ምርጫውን ማሸነፍ ይቻላል፣ ሀገር ግን ይጎዳል።
📌 ዛሬ ከተለያዩ የፖለቲካ አመራሮች እና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር አብረን በመሆን መረጋጋት እንዲኖር በአንድ ላይ መግለጫ ሰጥተናል።
Via Elias Meseret

ለኦሮሞ መብት ተሟጋቹ #ጃዋር_መሀመድ ድጋፋቸውን እና #ተቃውሟቸውን ለመግለፅ ዛሬ በርካታ ኢትዮጵያውያን በጀርመን ኑርንበርግ ከተማ አደባባይ ወጥተዋል።
ለኦሮሞ መብት ተሟጋቹ ጃዋር መሀመድ ድጋፋቸውን እና ተቃውሟቸውን ለመግለፅ ዛሬ በርካታ ኢትዮጵያውያን በጀርመን ኑርንበርግ ከተማ አደባባይ ወጥተዋል። ጃዋር መሀመድ በዩናይትድ ስቴትስ ከተሞች እና በአውሮፓ ሀገራት እየተዟዟረ ከደጋፊዎቹ ጋር የሚያደርገውን ውይይት ቀጥሏል። ዛሬ በኑርንበርግ ከተማ ድጋፋቸውን ለመግለፅ አደባባይ የወጡት ኢትዮጵያውያን የኦነግን ጨምሮ የሌሎች ክልሎችን ባንዲራዎችም ይዘው ተስተውሏል።
ተቃውሟቸውን ለማሰማት የከተማዋ ባቡር ጣቢያ አካባቢ የወጡት ደግሞ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ያለውን ባንዲራ ይዘው ነበር። ተቃዋሚዎች በቅርቡ ጃዋር መሀመድ መንግሥት ጠባቂዎቼን ሊያነሳብኝ ነው የሚል መልዕክት ለደጋፊዎቹ ማስተላለፉን ተከትሎ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለሞቱ 86 ሰዎችም የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት አድርገዋል። ጃዋርም ለፍርድ ይቅረብ የሚል ጥሪ አስተላልፈዋል።
Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa

በአማራና ኦሮሚያም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮች ዋነኛ ምክንያት የፖለቲካ ልሂቃን የሚፈጥሩት ያልተገባ ፉክክር ነው ሲሉ አክቲቪስት #ጃዋር_መሃመድ አስታወቁ።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa