ለኦሮሞ መብት ተሟጋቹ #ጃዋር_መሀመድ ድጋፋቸውን እና #ተቃውሟቸውን ለመግለፅ ዛሬ በርካታ ኢትዮጵያውያን በጀርመን ኑርንበርግ ከተማ አደባባይ ወጥተዋል።
ለኦሮሞ መብት ተሟጋቹ ጃዋር መሀመድ ድጋፋቸውን እና ተቃውሟቸውን ለመግለፅ ዛሬ በርካታ ኢትዮጵያውያን በጀርመን ኑርንበርግ ከተማ አደባባይ ወጥተዋል። ጃዋር መሀመድ በዩናይትድ ስቴትስ ከተሞች እና በአውሮፓ ሀገራት እየተዟዟረ ከደጋፊዎቹ ጋር የሚያደርገውን ውይይት ቀጥሏል። ዛሬ በኑርንበርግ ከተማ ድጋፋቸውን ለመግለፅ አደባባይ የወጡት ኢትዮጵያውያን የኦነግን ጨምሮ የሌሎች ክልሎችን ባንዲራዎችም ይዘው ተስተውሏል።
ተቃውሟቸውን ለማሰማት የከተማዋ ባቡር ጣቢያ አካባቢ የወጡት ደግሞ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ያለውን ባንዲራ ይዘው ነበር። ተቃዋሚዎች በቅርቡ ጃዋር መሀመድ መንግሥት ጠባቂዎቼን ሊያነሳብኝ ነው የሚል መልዕክት ለደጋፊዎቹ ማስተላለፉን ተከትሎ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለሞቱ 86 ሰዎችም የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት አድርገዋል። ጃዋርም ለፍርድ ይቅረብ የሚል ጥሪ አስተላልፈዋል።
Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa