YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ደቡብ_አፍሪካ የዜጎቻችን ጉዳይ ⤵️

በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዜጎችን ችግር ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገለጸ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስቸኳይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎችን ለመደገፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመስራት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

ኤምባሲው ከስራ ቦታቸው የተፈናቀሉ የኢትዮጵያውያ ማህበረሰብ አባላትን ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ለማድረግም ጥረት ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡

ትናንት የተፈፀመውን ክስተት ተከትሎም ጉዳዩ ላይ ውይይት ማድረጉን ጠቅሷል፡፡

በዚህም ከደቡብ አፍሪካና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት በመስራት ለችግሩ እልባት ለመስጠት የሚያግዝ እቅድ በማዘጋጀት ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬም በሶዌቶ እና በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በድጋሚ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
©FBC
@YeneTube @Fikerassefa
#ደቡብ_አፍሪካ በሌሎች ሀገር ዜጎች ላይ ያነጣጠረው ጥቃት በኢትዮጵያውያን ላይ ብቻ ያነጣጠረ ባይሆንም በዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት ከሀገሪቱ መንግስት ጋር ተወያይተው መፍትሄ እንደሚፈልጉ ኘሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ::

ፕሬዘዳንቷ በደቡብ አፍሪካከሚኖሩ የዲያስፖራ አባላት ጋር ተወያይተዋል:: አባላቱ በስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እንዳሰጋቸው እና መንግስት ከመንግስት ጋር ውይይት አድርገው መፍትሄ እንዲፈልጉላቸው ጠይቀዋል። በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን በ28ኛው የዓለም አቀፍ ምጣኔ ሀብት ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ ያሉት ፕሬዘዳንቷ ከዚህ ጎን ለጎን ነው ከኢትዮዽያውያኑ ጋር የተወያዩት።ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በጉባኤው ላይም በወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ እና በሰላም ዙሪያ ባተኮረው ውይይት ላይ ተሳትፈዋል።

ፕሬዝደንቷ የስራ እድል ፈጠራን ለማሳደግ ከፖሊሲ ማውጣት እና ከአዳራሽ ውስጥ ውይይት ባለፈ እታች ድረስ ወደ ህዝቡ ወርዶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።ወጣቶች በስደት ለሚኖሩበት ሀገር እንደ ስጋት ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦም እንዳላቸው መታየት እንዳለበት ገልጸዋል።በሰላም መፍትሄ አመንጪነት ዙሪያ ሴቶችም በሀላፊነት ደረጃ ሊሳተፉ እንደሚገባ ፕሬዝደንቷ ጠቁመዋል።እንደ ፕሬዝደንቷ አገላለጽ የልማት ጉዳይ እና የሰላም አጀንዳዎች ተነጣጥለው የሚታዩ መሆን የለባቸውም።

ምንጭ:የፕሬዘዳንት ፅ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
#Update

በኮሮና ቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም የተባሉ 4 ሰዎች በአዲስ አበባ ተገኙ!!

የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ በኮሮና ቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም የተባሉ አራት ሰዎች በኢትዮጵያ መገኘታቸውን አሳውቋል።

አራቱም ኢትዮጵያዊያን መሆናቸው የተነገረ ሲሆን፤ #ሦስቱ_ቫይረሱ ከተከሰተበት ዉሃን ግዛት ተማሪ የነበሩ ናቸው ተብሏል።

ጤና ጥበቃ አሁን እየሰጠ ባለው መግለጫ የደም ናሙናው ወደ #ደቡብ_አፍሪካ መላኩን አስታውቋል።

ምንጭ:- BBC አማርኛ
@YeneTube @Fikerassefa