#የኤርትራ ውስጣዊ ነባራዊ ሁኔታ ባለመለወጡ እና ሐገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናት ድንበር በመከፈቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚሰደዱ ኤርትራዉያን #ቁጥር መጨመሩን የአውሮፓ ሕብረት አስታወቀ።
የሕብረቱ ኮሚሽን እንደሚለዉ ሁለቱ ሐገራት የአዋሳኝ ድንበሮቻቸዉን ከከፈቱ ወዲሕ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ኤርትራውያን ቁጥር በፊት ከነበረዉ በአራት እጥፍ ጨምሯል።
የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ድረ-ገፅ የጠቀሰዉ የትግራዩ የሽሬ ዞን-አስተዳደር እንዳስታወቀዉ በቅርቡ 15 ሺሕ ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል።
ከነዚሕ መሐል ዘመድ ወዳጅ ለመጠየቅ እና ሸቀጦች ለመግዛት ድንበር የተሻገሩ መኖራቸውን መረጃው ጠቅሶ፤ አብዛኞቹ ግን እዚያው ኢትዮጵያ የሚቆዩ ናቸው ብሏል።
ኮሚሽኑ በትናትናው ዕለት ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራውያን ቁጥር 175 ሺሕ ደርሷል። እንደ ኮሚሽኑ ገለፃ አብዛኞቹ ብቻቸዉን የተሰደዱ ታዳጊዎች ናቸው።
ሽሬ የሚገኙት ኤርትራዉያን የስደተኝነት ከለላ እናጣለን፤ የኤርትራ መንግሥትም የበቀል እርምጃ ዒላማ እንሆናለን የሚል ሥጋት እንዳላቸው ኮሚሽኑ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መሪዎች ዕርቅ ማውረዳቸውን ያስታወቁት ባለፈው ሐምሌ ቢሆንም ሁለቱን አገሮች የሚያገናኙ መንገዶች ለአገልግሎት የተከፈቱት ባለፈዉ መስከረም 1 ነበር።
©DW
@yenetube @mycase27

አስር ያህል #የኤርትራ ካቢኔ ሚንስትሮች ሀገራቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የተፈራረመቻቸውን ስምምነቶች አስመልክቶ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠየቁ።
ሚንስትሮቹ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ እንዲስጧቸው ዛሬ አርብ ቀጠሮ ለመያዝ ሲሞክሩ ነበር።
ሚንስትሮቹ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር ውይይት ማድረግ መጀመራቸውን ለስርዓቱ ቅርበት ያላቸው ግለሰቦች እየገለፁ ነው።
በቅርቡ የሀገሪቱ የቀድሞ የፋይናንስ ሚንስትር ተይዞ መታሰር፣ የህዝቡ የተሻለ መብት ጥያቄዎች ተደማምረው በርካታ ኤርትራውያን ለውጥ እንዲኖር ፍላጎት አላቸው።
©ዋዜማ ራዲዮ
@YeneTube @Fikerassefa