#የአማራ ክልል ምክር ቤት አዳዲስ የካቢኔ አባላትን ሹመት #አጸደቀ
ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ ለክልሉ #የተለያዩ ቢሮዎች በእጩነት የቀረቡ ሃላፊዎችን ሹመት አጽድቋል።
በዚህም መሰረት
📌አቶ ላቀ አያሌው - ምክትል ርዕሰ መስተዳድር
📌አቶ መላኩ አለበል - በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደረጃ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ
📌ዶክተር ቦሰና ተገኘ - የግብርና ቢሮ ሃላፊ
📌አቶ ሻምበል ከበደ - የቴክኒክና ሙያ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሃላፊ -
📌ወይዘሮ ብዙአየሁ ቢያዝን - የገቢዎች ቢሮ ሀላፊ
📌አቶ ፍርዴ ቸሩ - ጠቅላይ አቃቤ ህግ
📌ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ - የሰላም ግንባታና የህዝብ ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ
📌አቶ ንጉሱ ጥላሁን - በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደረጃ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ
📌ዶክተር ሙሉነሽ አበበ - የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ
📌ወይዘሮ አስናቁ ድረስ - የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ቢሮ ሀላፊ
ምንጭ ፦ኤፍ ቢ ሲ
@yenetube @mycase27

#አብን_ኦነግ‼️
በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የሚንቀሳቀስ የታጠቀ ኃይል እንደሌለው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አስታወቀ። የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቶሌራ አደባ "የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ምንም አይነት የታጠቀ ኃይል በዚያ አካባቢ አልነበረውም፤ የለውምም" ሲሉ ተናግረዋል።
ከወራት በፊት በኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ እና በኦሮሞ ነፃነት ግንባር መካከል ዕርቅ ለማውረድ የአባገዳዎች ኅብረት ጣልቃ በገባበት ወቅት አቶ በየነ ሰንበቶ የኦነግ ጦር "በሰሜን ሸዋ፤ ከሜሴና እና በከረዩ አለ።" ብለዉ ነበር። አቶ በየነ ሰንበቶ "ወሎ ከሚሴ ያሉትን ከአማራ ክልል ጋር እንነጋገራለን" ሲሉም ተናግረው ነበር።
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አዳባ ግን "እኛ እየሰራን ያለንው የፖለቲካ ሥራ ብቻ ነው። የምናዘው በእኛ ስር የሚታዘዝ ምንም ሰራዊት የለም" ሲሉ መልሰዋል።
አጣዬ፣ ማጀቴ፣ ሰንበቴ እና ካራ ቆሬ በተባሉ አካባቢዎች ከተፈጸሙ ጥቃቶች በኋላ በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ባለሥልጣናት የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን ተጠያቂ አድርገዋል። አቶ ቶሌራ ግን በአካባቢዎቹ ለተፈጸሙት ጥቃቶች ተጠያቂው #የአማራ,ብሔራዊ_ንቅናቄ (አብን) የተባለው የፖለቲካ ፓርቲ ነው ሲሉ ወንጅለዋል። አቶ ቶሌራ ጥቃቱን ያደረሱት "አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንዲራ የፌድራልም ያልሆነ ወይንም የክልሉም [የአማራ ክልል] ያልሆነ ባንዲራ ይዘው ነው የሚሔዱት። እንደሚመስለኝ በዚያ አካባቢ የሚንቀሳቀስ ተፎካካሪ ፓርቲ #አብን_የሚሉት ነው የሚመስለኝ" ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ቃል አቀባይ አቶ ክርስቲያን ታደለ በበኩላቸው ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር በኩል የቀረበውን ወቀሳ ፈፅሞ አይቀበሉም። አቶ ክርስቲያን "ጥቃቱን እና ወረራውን የፈጸሙ ኃይሎች የኦነግን አርማ የያዙ፤ ራሳቸውን የኦነግ አባላት ነን ብለው የሚናገሩ፤ ጥቃት በሚፈፅሙባቸው መሳሪያዎች ጭምር የኦነግን አርማ አድርገው የሚታገሉ ናቸው። ይህ በሆነበት ሁኔታ አንድም እንኳ የጦር መሳሪያ የሌለው፤ ሰላማዊ ትግል እያደረገ ያለውን አብንን መኮነን በአደባባይ የሰሩትን ነውር ለመሸፋፈን የሚያደርጉት ጥረት ሆኖ ነው የምናገኘው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ሰሞኑን በሰሜን ሸዋና የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች በተፈጸመው ጥቃት የሞቱ እና የቆሰሉ ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር አሁንም በግልፅ አይታወቅም።
በትናንትናው ዕለት በአካባቢው ያለውን የጸጥታ መደፍረስ ለማረጋጋት የፌደራል እና የክልል የጸጥታ አስከባሪ ተቋማት እርምጃ እንዲወስዱ ታዘዋል።
የጸጥታ ኃይሎቹ “አስፈላጊውን ህጋዊ እና ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ” ትዕዛዝ መተላለፉን ያስታወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት ነው።
ምንጭ:- DW
@YeneTube @FikerAssefa

ትዴት #የአማራ_እና_ትግራይ ወጣቶች የወዳጅነት መድረክ ሊያዘጋጅ ነው።
የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) «ቀጣይ ትውልድ» በሚል መሪ ቃል የአማራና ትግራይ ክልል ወጣቶች የሚሳተፉበት የወዳጅነት መድረክ በባህር ዳር፣ ቆቦ፣ አላማጣ፣ አዲስ አበባ እና መቀሌ ከተሞች በመስከረም 2012 መካሄድ እንደሚጀመር አስታወቀ።የትዴት ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉ ብርሃን ኃይለ፣ ዝግጅቱን በቀጣዩ መስከረም ወር ላይ ለመጀመር ፈቃደኛ ከሆኑ ግለሰቦች ገንዘብ ማሰባሰብ መጀመራቸውን ለአዲስ ማለዳ ገልጸው፣ የትዴት ድጋፍ እንዳለ ሆኖ ከአማራ ክልል መንግስትም የገንዘብ ድጋፍ መጠየቃቸውን አውስተዋል።
ምንጭ: አዲስ ማለዳ