YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በቦሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት በለይቶ ማቆያ ያሉ ዜጎች ወደ አገር ውስጥ ከገባን 21 ቀን ቢሞላንም እስካሁን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ አልተደረገልንም አሉ፡፡

ከውጭ መተው 21 ቀን የሞላቸው በማቆያ ቦታ የሚገኙ ዜጎች እስካሁን ድረስ ምንም አይነት የኮሮና ምርመራ እንዳልተደረገላቸው ነው የተናገሩት፡፡

ዜጎቹ እንደሚሉት ከሆነ ከገባን ጀምሮ ምንም ትኩረት አልተሰጠንም እንደ ዜጋም እየተቆጠርን አይደለም ብለዋል፡፡

15ቀን ሲሞላችሁ የኮሮና ምርመራ ተደርጎላችሁ ወደ ቤታችሁ ትሄዳላችሁ ብንባልም ከመጣን 21 ቀን አስቆጥረናል ግፍ እየተሰራብን ነውም ብለዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የቅሬታ አቅራቢዎቹን ጥያቄ ይዞ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን ጠይቋል፡፡

#በኢንስቲትዩቱ የኮቪድ 19 ምክትል አስተባባሪ አቶ ዘውዱ አሰፋ እንደሚሉት ሰዎቹ እስካሁን ለምን መመርመር እንዳልተቻለ እናጣራለን ቅሬታቸውንም በአፋጣኝ እንፈታለን ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

Via:- Ethio FM
Photo :- የኮሮና ምልክት አለማሳየታቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት #የኔቲዩብ

@Yenetube @Fikerassefa