YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#update ጨፌ ኦሮሚያ ⤵️⤵️

ጨፌ ኦሮሚያ የክልሉን አስፈጻሚ አካላት መልሶ ለማደራጀትና ስልጣንና ሃላፊነታቸውን ለመወሰን የወጣውን አዋጅ #አፀደቀ

የጨፌ ኦሮሚያ በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው 4ኛ ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ነው የክልሉን አስፈጻሚ አካላት መልሶ ለማደራጀትና ስልጣንና ሃላፊነታቸውን ለመወሰን የወጣው አዋጅ ያፀደቀው።

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ #ለማ መገርሳ በዚሁ ወቅት አንዳሉት፥ የአደረጃጀት ለውጥ ማድረግ ያስፈለገው ባለፉት ጊዜያት በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዳሉ በመለየት የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎች ቢሰሩም የህዝብን ቅሬታ መፍታት እና እርካታን መፍጠር ስላልተቻለ ነው።

ይህም በተለይም ከስራ ፍጥነት እና ጥራት ያለው አገልግሎት ከመስጠት ጋር በተያያዘ ክፍተት በማሳየቱ እንዲሁም ተሃድሶ ተብለው የተጀመሩ ስራዎችም የአመራሩን እና የሰራተኛውን አመለካከት ከማደስ ባለፈ እርካታን ባለመፍጠራቸው ነው ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ የሚሰራበት መንገድ መለወጥ እንዲሁም የተጀመሩ ለውጦቸን ለማስቀጠል የሚያስችሉ የመዋቅር እና የአደረጃጀት ለውጥ ማምጣቱ አስፈልጓል ብለዋል።

አዲሱ አደረጃጀተም በዋናነት ህዝቡን ማእከል ባደረገ መልኩ ሰፊውን ህዝብ ማግኘት የሚቻልበትን ቀበሌን ማእከል በማድረግ መስራት የሚያስችል መሆኑንም ገልፀዋል።

እንዲሁም ችግር የሚስተዋልበትን የአስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት፣ የሰው ሀይልና በጀት አጠቃቀም ላይ የሚስተዋለውን ሰፊ ክፍተት የሚቀርፍ መሆኑንም አንስተዋል።

ከዚህ በፊት በነበረው አደረጃጀት በክልል ደረጃ 42 የነበሩ ቢሮዎች በዛሬው እለት በፀደቀው አዋጅ መሰረት ወደ 38 ዝቅ እንዲደረጉ መወሰኑንም ርእሰ መስተዳደሩ አቶ ለማ መገርሳ ገልፀዋል።

በአዲሱ አደረጃጀት መሰረትም፦
1. የርእሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት
2. የእርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ
3. የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ
4. የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ
5. የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ
6. የትምህርት ቢሮ
7. የጤና ጥበቃ ቢሮ
8. የፀጥታ እና አስተዳደር ቢሮ
9. የውሃ እና ኢነርጂ ልማት ቢሮ
10. የመሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ቢሮ
11. የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
12. የንግድ ቢሮ
13. የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ
14. የባህልና ቱሪዝም ቢሮ
15. የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
16. የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ
17. የኢንተርፕራይዝና ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ
18. የትራንስፖረት ባለስልጣን
19. የመንገዶች ባለስልጣን
20. የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን
21. የአካባቢ፣ የደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን
22. የኮንስትራክሽን ባለስልጣን
23. የማእድን ልማት ባለስልጣን
24. የግብርና ግብአቶች ቁጥጥር ባለስልጣን
25. የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና መገናኛ ባለስልጣን
26. የአርብቶ አደር አካባቢዎች ልማት አስተባባሪ ኮሚሽን
27. የእቅድና ኢኮኖሚ ልማት ኮሚሽን
28. የኢንቨስትመንት ኮሚሽን
29. ፖሊስ ኮሚሽን
30. የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን
31. የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን
32. ስፖርት ኮሚሽን
33. የህብረት ስራዎች ማስፋፊያ ኤጀንሲ
34. የእንስሳት ሀብት ልማት ኮሚሽን
35. የገበያ ልማት ኮሚሽን
36. የግብርና ጥናት ኢንስቲቲዩት
37. የከተሞች ፕላን ኢኒስቲቲዩት
38. የመንግስት ህንፃዎች አስተዳደር በመሆን በአዲስ መልክ ተደራጅተዋል።

📌እንዲሁም በዞን፣ በወረዳ እና በቀበሌ ደረጃ የነበሩ አደረጃጀቶችም በአዲስ መልክ እንዲዋቀሩ ተወስኗል።
ምንጭ ፦ FBC
@yenetube @mycase27
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምርጫ #ቦርድን_እንደገና ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ #አፀደቀ

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ ልዩ ስብሰባው በአዋጁ ላይ የምክር ቤቱ የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርትን እና የውሳኔ ሀሳብን ተመልክቷል።

በአዋጁ ላይ ብሄርንና ፆታን በተመለከተ በተቻለ መጠን አካታች እንዲሆን የተቀመጠው ክፍል “በተቻለ መጠን” የሚለው አስገዳጅ በሆነ ሀረግ ቢቀመጥ የሚል ሀሳብ ቢነሳም ቀድሞ የነበረው አገላለፅ እንዲሆን ወስኗል።

ዜግነትን በተመለከተ ኢትዮጵያዊ በሚል የተቀመጠው ለትርጉም የተጋለጠ በመሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ የኢትዮጵያ ዜግነት ያለው በሚል እንዲቀመጥ አቅርቧል።

የቦርድ አባላት ከቦርድ አባልነት ከተነሱ በኋላ ለሁለት ዓመት ምንም ዓይነት ሹመት እንዳይሰጣቸው የሚል የውሳኔ ሀሳብንም አካቷል።

በአዋጁ እና ውሳኔ ሀሳቡ ላይ የተወያየው ምክር ቤቱ በአራት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አዋጁን አፅድቆቷል።

ምክር ቤቱ በተጨማሪም የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴርን የ8 ወራት ሪፖርትን ካዳመጠ በኋላ የተሰሩትን ጠንካራና ደካማ ተግባራትን በዝርዝር ገምግሟል።

ምንጭ:- FBC
@YeneTube @FikerAssefa