YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምርጫ #ቦርድን_እንደገና ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ #አፀደቀ

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ ልዩ ስብሰባው በአዋጁ ላይ የምክር ቤቱ የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርትን እና የውሳኔ ሀሳብን ተመልክቷል።

በአዋጁ ላይ ብሄርንና ፆታን በተመለከተ በተቻለ መጠን አካታች እንዲሆን የተቀመጠው ክፍል “በተቻለ መጠን” የሚለው አስገዳጅ በሆነ ሀረግ ቢቀመጥ የሚል ሀሳብ ቢነሳም ቀድሞ የነበረው አገላለፅ እንዲሆን ወስኗል።

ዜግነትን በተመለከተ ኢትዮጵያዊ በሚል የተቀመጠው ለትርጉም የተጋለጠ በመሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ የኢትዮጵያ ዜግነት ያለው በሚል እንዲቀመጥ አቅርቧል።

የቦርድ አባላት ከቦርድ አባልነት ከተነሱ በኋላ ለሁለት ዓመት ምንም ዓይነት ሹመት እንዳይሰጣቸው የሚል የውሳኔ ሀሳብንም አካቷል።

በአዋጁ እና ውሳኔ ሀሳቡ ላይ የተወያየው ምክር ቤቱ በአራት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አዋጁን አፅድቆቷል።

ምክር ቤቱ በተጨማሪም የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴርን የ8 ወራት ሪፖርትን ካዳመጠ በኋላ የተሰሩትን ጠንካራና ደካማ ተግባራትን በዝርዝር ገምግሟል።

ምንጭ:- FBC
@YeneTube @FikerAssefa