ጠቅላይ አቃቢ ህግ ዛሬ በሰጠው መግለጫ #አቶ_ጌታቸው_አሰፋን ጨምሮ በሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በሌሎች ወንጀሎች የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ የእስር ማዘዣ እንደወጣባቸው አስታውቋል፡፡
እስካሁን በቁጥጥር ስር ሊዉሉ ያልቻሉት በተጠረጠሩበት ወንጀል ውስብስብነት እና በፊት ከነበራቸው ከፍተኛ የአመራርነት ቦታ አንጻር መሆኑን አቃቤ ህግ ገልጿል፡፡
ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡ የሚኖሩበት አካባቢ እና ስለተጠረጠሩበት ጉዳይ መረጃዎች ሲሰበሰቡ ቆይተዋልም ተብሏል፡፡
ህብረተሰቡ ጠቃሚ መረጃዎችን ለፖሊስ እያደረሰ እንደሆነም ተነግሯል፡፡
#ብሔርን_ሽፋን_አድረገው የተደበቁ ግለሰቦች #በትግራይ ክልል ብቻ ሳይሆን #በሌሎችም አካባቢዎች እንደሚስተዋሉ አቃቤ ህግ አሳዉቋል፡፡ ማንም ከህግ ዉጭ ሊሆን እንደማይችል እና በቅርቡ ግለሰቦቹ ለፍርድ እንደሚቀርቡ መግለጫውን የሰጡት የጠቅላይ አቃቢ ህግ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዝናቡ ቱኑ ገልጸዋል፡፡
ምንጭ:- አምሓራ ማስ ሚዲያ
@YeneTube @Fikerassefa