YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ስልጣናቸውን ለአባ ለአበ ገዳ ጎበና ሆላ ኢሬሶ #አስረከቡ

ትናንት ምሽት በተካሄደ የስልጣን ርክክብ (ባሊ ርክክብ) ስነ ስርዓት ነው የስልጣን ጊዜያቸውን ያጠናቀቁት አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ስልጣናቸውን #በሰላማዊ መንገድ ያስረከቡት።

የስልጣን ርክክቡ የተካሄደውም የኦሮሞ ህዝብ ለዘመናት በዴሞክራሲያዊ መንገድ በየ8 ዓመቱ ስልጣን ሲረካከብበት በነበረው በገዳ ስርዓት መሰረት ነው።

በዚህም መሰረት ነው ላለፉት #8 ዓመታት ሲመሩ የነበሩት የቢርመጂ ቱለማ አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ለአዲሱ የሜልባ አባ ገዳ ጎበና ሆላ ኢሬሶ ስልጣናቸውን ያስረከቡት።

አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ከአዲሱ የሜልባ አባ ገዳ ጎበና ሆላ ኢሬሶ ጋር ተመራርቀው በሰላማዊ መንገድ ስልጣን ተረካክበዋል።
©fbc
@yenetube @mycase27