YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አንጋፋዉ #አርቲስት_ደበበ_እሸቱ «#ኢትዮጵያዊነት አማራጭ የማይገኝለት ነዉ።

ልክ እንደሙዚቃዉ ህብር ያለዉ ነዉ። ሙዚቃን አዳምጠነዉ ቋንቋዉም ባይገባን በሙዚቃዎቹ ምት ስሜታችን ረክቶ ሊደነቅ የሚቻል ጥበብ ነዉ።

በመድረኩ ግጥም ያቀረቡት ባለሞያዎች ልጆችም ቢሆኑ፤ #ኢትዮጵያ እያለች ግጥምን ካቀረበችዉ #ታዳጊ_ልጅ ጀምሮ፤ ኢትዮጵያ ብላ ልታወድስ የቻለችዉ ያ መድረክ በመዘጋጀቱ ነዉ። ሕብረት ያስፈልጋል፤ አንድ መሆን ያስፈልጋል፤ ኢትዮጵያ አደጋ ዉስጥ እንዳትገባ የሁላችንም ተሳትፎ አስፈላጊ ነዉ ብሎአል።

ደራሲና ገጣሚ #ዶክተር_በድሉ_ዋቅጅራ በበኩላቸዉ
«ብዙዎች የዘረፉትን አስመላሽ፣ ገድለው የጣሉትን አፈላላጊ ያፈናቀሉትን ዜጋ አስፋሪ ሆነዋል። ማህበረሰባችን የስነ ምግባር አረም ለማብቀል ተስማሚ ሆኗል። በየትምርት ቤቱ የሥነ- ምግባር ትምህርት የለም። በዝያ ፋንታ ልጆች የሚማሩት ፖለቲካ ነዉ። ሥነ ምግባርን በማስተማር ረገድ ቤተ-ክህነት አቋም ልትይዝ ይገባል። ቤተ ክርስትያን አሁን የተቸገረ ማደርያ አይደለም ፤ ቤተ ክርስትያን የሚጠበቀዉ መስቀል በያዘ ቄስ ሳይሆን፤ ጠመንጃ በያዘ ፌደራል ነዉ። ቤተ-ክህነቶቹ አከራይተዉ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ገቢ ያገኛሉ። በአንፃሩ ገጠር ያሉት ቤተ-ክርስትያናት የሚያስቀድሱበት ጧፍ የላቸዉም። ይሄን ይሄን ስናይ የማኅበረሰቡ የአኗኗር ዘይቤ ተበላሽቶአል፤ ዘቅጦአል።

ስለዚህ ቆጭ ብለን፤ ቤተ-ክርስትያንን እንደተቋም፤ ትምህርትን እንደተቋም የመገናኛ ብዙኃንን እንደተቋም ልናዋቅር በፖሊሲ ልነድፍ ይገባል።» ብለዋል።

ምንጭ:- Dw
@YeneTube @FikerAssefa