YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
እህታማቾቹ ላይ የመኪና አደጋ በማድረስ የተሰወረዉ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ⤵️

ተፈላጊው የፖሊስ አባል #በቁጥጥር ስር ዋለ። መስከረም 01 ቀን 2011 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ሲሆን በቂርቆስ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ቦልጋሪያ (የድሮ በግ ተራ) ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዕድሜያቸው የ19 እና የ20 ዓመት የሆኑ እህትማማቾችን የመኪና አደጋ በማድረስ የተሰወረው የፖሊስ መኪና አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል፤ ምርመራውን በማጣራት ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ሲሆን #ተከሳሹ አደጋውን ካደረሰ በኋላ ላለፉት 19 ቀናት ተሰውሮበት ከነበረው ከምስራቅ ጎጃም በክትትል መያዙ ታውቋል፡፡ ተጠርጣሪውን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ አድካሚ ፍለጋ ማድረጉንም ተገልጧል፡፡ ህብረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች ከሚጻፉት ጉዳዮች ይልቅ፤ ወደ ኮሚሽኑ በመምጣት መረጃ ማግኘት የሚችል መሆኑ ተገልፀዋል፡፡

©የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
@YeneTube @Fikerassefa