YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
(Novemeber 24 )የፊታችን እሁድ በመዲናች አዲስ አበባ ሜክሲካ አከባቢ የመኪና ውድድር ይካሄዳል።

ከጠዋቱ አንድ ሁለት ሰዐት ጀምሮ የሚካሄዳውን የመኪና ውድድር አስመልክቶ መንገዶች ከጠዋት አንድ ሰዐት ጀምሮ መንገዶች ዝግ ይሆናሉ የሚዘጉ መንገዶ #ሜክሲኮ_ቶታል አከባቢ #ለገሀር እንዲሁም #ብሄራዊ አከባቢ መንገዶች ዝግ እንደሚሆኑ አዘጋጁ ጠቁሞናል።

የውድድሩ አዘጋጅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሞተር ስፖርት አሶሴሽን መሆኑን ሰምተናል።

መረጃውን ያደረሰን drive Addis ነው።
@Yenetube @Fikerassefa
በሰሜን ሸዋ በፀጥታ ችግር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተራዘመ!

የሰሜን ሸዋ ዞን በወቅታዊ የሰላም ችግር ምክንያት የትምህርት ዘርፉ ስራ በታቀደለት ጊዜ ለመፈፀም አስቸጋር ሁኔታዎች እንደነበሩበት በማስታወቅ ያለውን ችግር በተመለከት ከመምህራንና ርዕሰ መምህራን ጋር ውይይት በማድረግ የሚገኙትን አማራጮች በመጠቀም ስራው ሲያከናውን መቆየቱን ገልጻል።

የ12ኛ ክፍል #ብሄራዊ ፈተና ከግንቦት ወደ ሃምሌ እንዲገፋ እንዲሁም የ6ኛና 8ኛ ክፍል ወደ ሰኔ እንዲገፋ መደረጉን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ታደሰ ሸዋፈራ አስታውቀዋል።

የ6ኛ፣ 8ኛና 12 ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን በሚመለከት ለ2 ወራት የሚቆይ የተቀናጀ ለፈተና የማብቃት ዘመቻ ተጀምሯል ሲሉ ገልጸው የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና አመራሮች ጋር በመሆን ተማሪዎችን የማብቃት መርኃ ግብር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።ምክትል ሃላፊው በተጨማሪ “በዞኑ መማር ከነበረባቸው ተማሪዎች ውስጥ 63 በመቶ የሚሆኑት በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው” ሲሉ ገልጸዋል።

በአጠቃላይ 354ሺ ተማሪዎችን ዞኑ ማስተማር የነበረበት ቢሆንም፤ 230ሺ (63 ነጥብ 5 በመቶ) የሚሆኑት በትምህርት ገበታ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ይህ አፈፃፀም ከ1ኛው ወሰነ ትምህርት አሁን የተሻለ መሆኑን ያነሱት ኃላፊው፤ 59ሺ ተማሪዎች ጭማሪ አድርጓል ነው ያሉት፡፡

በነዚህ ዘግይተው ትምህርት የገቡ ተማሪዎች ምክንያት የትምህርት የማጠናቀቂያ ሰዓቱን ለማራዘም ታስቦ እየተሰራም እንደሆነም ነው ምክትል ኃላፊው ያነሱት፡፡በአሁኑ ሰዓት በዞኑ በ1ኛ ደረጃ ካሉት 1190 የትምህርት ተቋማት ውስጥ 840 የሚሆኑት በማስተማር ላይ መሆናቸውን ጠቁሞ በ2ኛ ደረጃ ደግሞ ከ59 ትምህርት ቤቶች 54ቱ በማስተማር ላይ ናቸው ብለዋል።

በዞኑ በ1ኛ ደረጃ ከ228ሺ ተማሪዎች ውስጥ 150ሺ (66 በመቶ) እየተማሩ ነው ያሉት ሃላፊው በ2ኛ ደረጃ ከ46ሺ 635 ተማሪዎች ውስጥ 36ሺ (39 በመቶ) የሚሆኑት እንዲሁም፤ ቅድመ መደበኛ ከ73ሺ123 ተማሪዎች ውስጥ 42ሺ (60 በመቶ) እየተማሩ መሆኑን ምክትል ኃላፊው ገልፀዋል፡፡የሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርት መምሪያ የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የቀጣይ ጊዜ የ6ኛ፣ 8ኛና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና ቅድመ ዝግጅትን በሚመለከት ውይይት ማካሄዱን ከክልሉ የትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍192👎1