YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በህገ ወጥ መንገደ ሲዘዋወር የነበረ 72,900 #ዶላር #በአዳማ ከተማ ተያዘ።

በመምሪያው የፀጥታ ማስከበር የስራ ሂደት አስተባባሪ ምክትል ኮማንደር አለምእሸት ሀይሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ ህገ ወጥ ገንዘቡ ትናንት ምሽት ነው የተያዘው።

ገንዘቡ በቆጥጥር የዋለውም በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ እየተዘዋወረ መሆኑን ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሆኑንም ተናግረዋል።

ከአዲስ አበባ በተነሳው ተሽከርካሪ ውስጥ ስምንት ሰዎች የተሳፈሩ ሲሆን፥ በድርጊቱ ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ሰር መዋሉን ጠቅሰዋል። ተጠርጣሪው ከከተማ ሳይወጣ በቁጥጥር ስር ለመዋሉ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ እንደነበር ያነሱት ምክትል ኮማንደር አለም እሸት የህብረተሰቡ ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

ምንጭ:- ፋና ብሮድካስቲንግ
@YeneTube @Fikerassefa