#ዛሬ_ይተላለፋል #በረከት_ስምዖን ከአምሓራ ቴሌቪዥን ጋር ያደረገው ቆይታ
አሁን አማራ ቴሌቪዥን በተላላፊ ማስታወቂያ እንዳስነበበው ከአሁን ከሚተላለፋ ፕሮግራም በመቀጠለ የአቶ በረከት ስምዖን ፕሮግራም እንደ ሚያስተላልፍ አስታውቋል።
#Yenetube @Fikerassefa

#በረከት ስምኦን ቃሉን አጠፋ ቀጣዩ ዘገባ ያመለክታል Reyot እንደዘገበው⬇️⬇️
አቶ በረከት ስምኦን ለርዕዮት ቃለምልልስ ለመስጠት የገቡትን ቃል አጠፉ፡፡
ውድ ታዳሚዎቻችን፣ ሰሞኑን አቶ በረከት በየመገናኛ ብዙሀን እየወጡ የመግለጫ ዘመቻ ማድረጋቸውን ተከትሎ እጅግ በርካታ ተከታታዮቻችን ርዕዮት ከአቶ በረከት ስምኦን ጋር ቃለምልልስ እንዲያካሂድ ጠይቃችሁናል፡፡
ይህንን በመመርኮዝናአቶ በረከት ሊቀርቡላቸው የሚገቡ እውነተኛ ጥያቄዎች መኖራቸውን በመረዳት ከቀናት በፊት እርሳቸው ጋር ደውለን ቃለምልልስ እንዲሰጡን ጠየቅን፡፡ ፈቃደኝነታቸውን ገልጸው ቃለምልልሱ ዛሬ August 31 2018 ከምሽቱ 3 ሰአት ላይ ሊደረግ ቀጠሮ ከሰጡን በኋላ በቀጠሮው መሰረት ስንደውል ቃላቸውን አጥፈው ቃለምልልሱን ሊሰጡን እንደማይችሉ ገልጠውልናል።
©Reyot FB Page
@YeneTube @Fikerassefa

አቶ በረከትና አቶ ታደሰ ፍርድ ቤት ቀረቡ
አቶ #በረከት_ስምዖንና አቶ #ታደሰ_ካሳ በተጠረጠሩበት የጥረት ኮርፖሬት የሀብት ብክነት ጉዳይ ዛሬ በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ በውጭ ሆነው እንዲከራከሩና ጉዳዩ አዲስ አበባ እንዲታይላቸውም ጠይቀዋል፡፡ በምክንያትነት ደግሞ የጤና ችግርና የቤተሰብን ድጋፍ በቅርበት ለማግኘት በሚል አቅርበዋል፡፡
ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ‹‹ተመዘበረ›› ካለው የሀብት መጠን ከፍተኛነት አንጻር ዋስትና እንዳይሰጣቸውና እንዲሁም የተጠረጠሩበት ወንጀል የተፈጸመው በአማራ ክልል በመሆኑ ጉዳያቸው በባሕር ዳር እንዲታይ ለፍርድ ቤቱ ጠይቋል፡፡ ምሥክሮችን በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ስለሚያቀርብም የጉዳዩን በባሕር ዳር መታዬት ተገቢነት ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ የዋስትና መብታቸውን ከልክሎ በጥብቅ ጥበቃ በማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ወስኗል፡፡ የተጠረጠሩበት ወንጀል ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ ዋስትና የከለከለው ፍርድ ቤቱ የተመዘበረው ሀብት በአማራ ክልል ስለሆነ ጉዳዩ መታዬት ያለበት በባሕር ዳር እንደሆነም ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡
በጥብቅ ጥበቃ እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱ የወሰነው ከነበራቸው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት አንጻር መሆኑንም ችሎቱ አስታውቋል፡፡ የተጠረጠሩበትን ጉዳይ ዐቃቤ ሕግ አጠናክሮ እንዲያቀርብ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶ የዛሬ ውሎውን ችሎቱ አጠናቅቋል፡፡
ምንጭ፦ አምሓራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት