YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ባለፉት ሁለት #ሳምንት ባልሞላ ጊዜ በአድስ አበባ ውስጥ በተፈጠሩ ግጭቶች ወደ #28 ሰዎች መሞታቸዉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሜጀር ጄነራል #ደግፌ በዲ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ #ገልፀዋል

ከነዚህ ዉስጥ በፀጥታ ኃይሉ የሞቱት #ሰባት ሲሆኑ ቀሪዎቹ በድንጋይ ተደብድበው እና #በስለት ተወግተው እንደሞቱም አክለውበታል።

ሰልፍ በተካሄደ ጊዜም ወደ ሕገወጥ ተግባራት የገቡ 1, 204 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አድርገው ለሕንፀት ወደ ጦላይ እስር ቤት እንደተወሰዱም ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

ከተያዙት ዉስጥ ምንም አይነት የአዲስ አበባ መታወቂያ የሌላቸዉ እንደሚገኙበትም ተናግረዋል።

📌ታሳሪዎችን አስመልክቶ ሰሞኑን በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን «የሚናፈሱ» ያሏቸውን ጉዳዮች እዉነት አይደሉም ሲሉም አጣጥለዋል።

©DW
@yenetube @mycase27
በዋልታ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሀሰተኛ ዘገባ በማሰራጨት የተጠረጠሩ #ሰባት ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በዋልታ ቴሌቪዥን ማህበራዊ ሚድያ ላይ “የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ባልታወቀ ሁኔታ ተገደሉ” የሚል የሀሰት መረጃ ሰርተዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደባቸው መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ጋር በመሆን እያጣራ ባለው በዚህ ወንጀል ከድረ ገፁ ስራ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት ያላቸው፣ የድረ ገፁ የይለፍ ቃል ያላቸውን እና በኃላፊነት ደረጃ የሚጠረጠሩ ሰባት ተጠርጣሪዎችን መያዙን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የተደራጁ እና ልዩ ልዩ ወንጀሎች ዳይሬክተር ኮማንደር አበራ ቡሊና ገልፀዋል።

ዳይሪክተሩ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የሀሰተኛ ወሬው እንዴት ሊሰራጭ እንደቻለ ምርመራ ሲደረግ መቆየቱን ጠቁመው ከጉዳዩ ጋር ቅርበት አላቸው ተብሎ የተጠረጠሩ ወደ ሰባት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብለዋል።

Via:- EBC
@YeneTube @Fikerassefa