YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
📌 ከነጆ መንዲ የሚወስደው መንገድ በታጣቂዎች በመዘጋቱ ግጭት ከተፈጠረባቸው #የካማሸ ዞን ወረዳዎች ጋር ግንኙነት ተቋርጧል።

#መንግስት የዕለት ደራሽ እርዳታ #በሂሊኮፍተሮች ማቅረብ ጀምሯል።
@YeneTube @Fikerassefa
#በአማራና ትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶችን ለመፍታት የፌደራሉ መንግስት ጣልቃ እንዲገባ የአማራ ክልል #መንግስት ጠየቀ።

ግጭቱ ለግዜው በአንድ አካባቢ ብቻ የተፈፀመ ይሁን እንጂ ወደተለያዩ አካባቢዎች የመዛማት ዕድል ስላለው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብሏል #ክልሉ
ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@yenetube @mycase27
#መንግስት_በጅምላ_እያሰረ_ይገኛል - DW


መንግሥት በግድያው እጃቸው አለበት ብሎ የጠረጠራቸውን ግለሰቦች በጅምላ እያሰረ መሆኑ ይሰማል።

ፍርድ ቤት የቀረቡም አሉ።ይህም ባለፈው አንድ ዓመት በሀገሪቱ በወንጀል የሚጠረጠሩ ለምን አይያዙም ለሚሉ ተደጋጋሚ አቤቱታዎች«ሳናጣራ በጅምላ አናስርም» ይል የነበረውን መንግሥት ለትችት መዳረጉ አልቀረም።ጥቃቱን የተከተለው የመንግሥት እርምጃ እያነጋገረ ነው ከሁለት ሳምንት በፊት በባህርዳር እና በአዲስ አበባ የተፈጸመው የከፍተኛ ባለሥልጣናት ግድያ  ባለፈው አንድ ዓመት ኢትዮጵያ  ውስጥ በነበረው አንጻራዊ ነጻነት ላይ ጥላ ያጠላ ይመስላል።

ግድያው ያስከተለው ድንጋጤና እና አለመረጋጋት ከቀን ወደ ቀን እየቀነሰ በመሄድ ላይ ቢሆንም ስጋቱ ግን የጠፋ አይመስልም።መፈንቅለ መንግሥት የተባለው የባህር ዳሩ ግድያ እና የአዲስ አበባው ጥቃት ግንኙነት አለው ሲሉ የነበሩት የመንግሥት ባለሥልጣናት ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ግን ግንኙነት ይኑረው አይኑረው እየተጣራ ነው ብለዋል።

ይሁንና የዛሬ 15 ቀን ስለሆነው ብዙ መልስ ያላገኙ ጥያቄዎች እና መላ ምቶችም በየአቅጣጫው መሰንዘራቸው ቀጥሏል። መንግሥት በግድያው እጃቸው አለበት ብሎ የጠረጠራቸውን ግለሰቦች አማራ ክልል እና አዲስ አባባን ጨምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች በጅምላ እያሰረ መሆኑ ይሰማል።

ፍርድ ቤት የቀረቡም አሉ።ይህ ደግሞ ባለፈው አንድ ዓመት በሀገሪቱ በወንጀል የሚጠረጠሩ ለምን አይያዙም ለሚሉ ተደጋጋሚ አቤቱታዎች«ሳናጣራ በጅምላ አናስርም» ይል የነበረውን መንግሥት ለትችት መዳረጉ አልቀረም።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው እንደተናገሩት መንግሥት አሁን ትዕግስቱ አልቋል። እርምጃውም እንደበፊቱ ለዘብተኛ ሳይሆን ይጠናከራል። ከዛሬ ሁለት ሳምንቱ ጥቃት በኋላ መንግሥት በመውሰድ ላይ ያለው  እና ወደፊትም እወስደዋለሁ የሚለው  እርምጃ እያነጋገረ ነው። ከዛሬ ሁለት ሳምንቱ ግድያ በኋላ የተከተሉ ሁነቶች እና አንድምታቸው የመወያያ ርዕሳችን ነው።

 ሦስት እንግዶች ጋብዘናል፣እነርሱም አቶ መሱድ ገበየሁ የኢትዮጵያ የመብት ድርጅቶች ህብረት ሃላፊ እና የሕግ ባለሞያ፣አቶ ፍስሀ ተክሌ በዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ተመራማሪ እንዲሁም  አቶ ያሬድ ጥበቡ አሜሪካን የሚኖሩ የፖለቲካ ተንታኝ ናቸው።

Via:-DW
@YeneTube @FikerAssefa
አፋር ክልል በተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬም እንደቀጠለ ነው።

ባሳለፍነው ሳምንት ሰርጎ ገቦች ድንበር አልፈው የአፋር ህዝብ ላይ ጥቃት መዘንዘራቸው ይታወሳል። በዚህ ጥቃት ሳቢያ የ17 ሰው ህይወት ማለፉ ይታወሳል ይህንን አስመልክቶ አፋር ክልል በተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል እንዲሁም #መንግስት ዝምታን መርጧል።

@YeneTube @Fikerassefa