YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ሐሰት መሆኑ አረጋግጧል መንግስት

ኢትዮጵያ ጦሯን ከኤርትራ ድንበር እያነሳች ነው ተብሎ የተሰራጨው መረጃ #ሐሰት ነው ሲል መንግሥት አስተባበለ፡፡

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አካባቢ በኢትዮጵያና በኤርትራ ድንበር በተለይም በሽራሮ ግንባር የሚገኘው ጦሯን ኢትዮጵያ እያነሳች እንደሆነ፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው አውቶብሶችና ኦራል ወታደራዊ የጭነት ተሽከርካሪዎች ጦሩን ሲያጓጉዙ መታየታቸውን፣ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲሰራጭ ነበር፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ የተጠየቁት የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ መረጃው ሐሰት ነው ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

‹‹እውነት ነው ሽራሮ ግንባር ላይ እንቅስቃሴዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን የተለመደ አሠራር ነው ሲሉ፤›› ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራ ላለፉት 20 ዓመታት ከነበሩበት የጥላቻ መንፈስ ተላቀው ሰላም ካወረዱ ጥቂት ወራት እየተቆጠሩ ሲሆን፣ በመካከላቸው ያለውን የጠላትነት ስሜት አጥፍተው በሰላም ለመኖር መስማማታቸው ይታወሳል፡፡ ከዚህ ባለፈ የኢኮኖሚ ትስስር ለመፍጠር፣ በተለይም ኢትዮጵያ የኤርትራን ወደቦች መጠቀም የሚያስችላት ስምምነት መደረጉ አይዘነጋም፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በኤርትራ ድንገተኛ ጉብኝት ካደረጉ በኋላ፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

‹‹ሁለቱ አገሮች ድንበር ላይ ያሉ ወታደሮቻቸውን ለማንሳት እስካሁን የተፈራረሙት ስምምነት የለም ሲሉ፤›› አቶ ሞቱማ አክለዋል፡፡

ሁለቱ አገሮች እንደገና ወዳጅነት የጀመሩት የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የአልጀርስ ስምምነትን ሙሉ በሙሉ መቀበሉን ካስታወቀ በኋላ ነበር፡፡ እስካሁን ድረስ ይኼንን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ የተጀመረ ሥራ ባለመኖሩ፣ ከድንበር ላይ ጦር የማንሳት እንቅስቃሴ ሊኖር አይችልም ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

©ሪፖርተር
@Fikerassefa @Yenetube
#ሐሰት #ሀዋሳ ላይ የጦር መሳሪያ ተያዘ ተብሎ የተሰራጨው ዜና ውሸት ነው።

"ሀዋሳ መጠኑ ያልታወቀ የህገውጥ መሳሪያ ተያዘ ተብሉ በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጩች ዜናዎች ያልተጣራ መሆኑ አረጋግጫለሁ።

በራሴ ጥረት ለማረጋገጥ እንደሞከርኩት የፌዴራል ፓሊስ እና የክልሉ ፓሊስ አረብ ሰፋር ላቀጭ ግሮሰሪ አከባቢ ማረጋጋት ስራ ሲሰሩ ነው የሚያሳይ ፎቶ እንጂ። ህገውጥ መሳሪያ አለመሆኑ ላረጋግጥላችሁ ፍልጋለሁ።

ሁከቱም የተነሳው ከሶስት ወር በፊት የተፋናቀሉት ዜጎች የተሰጠ ብር በቂ አይደለም በማለት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሲሞኩሩ የክልሉ ፓሊስ እና የፎዴራል ፓሊስ በቀላሉ አረጋግተዋል።

©Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa