#update አንዋር መስጊድ⤵️⤵️
አንዋር መስጊድ ቅጥር ግቢ #ታህሳስ 1 ቀን 2008 ዓ.ም በግምት ቦንብ በመወርወር የሽብር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በ11 ዓመት ጽኑ እስራት #ተቀጣ።
ተከሳሽ አህመድ ሙስጠፋ አብዶሽ የራሳቸውን ሃይማኖታዊ ዓላማን ለማራመድ በማሰብ፣ በመንግስት ላይ ተፅእኖ ለማሳደርና ህብረተሰቡን ለማሸበር እንዲሁም በኢፌዲሪ ህገ-መንግስት የተረጋገጠውን የሃይማኖት ነጻነት በመቃረን ከራሳቸን አስተሳሰብና አስተምህሮት እምነት ውጪ ሌላ አስተምህሮት መኖር የለበትም የሚል ዓላማ በመከተል ቀኑና ወሩ ባልታወቀ
በ2007 ዓመተ ምህረት ተከሻሽ በሚጠቀምበት የሞባይል ስልክ ቁጥር በማህበራዊ ድረ-ገጽ ላይ የተዋወቀውንና ያልተያዘውን ግብረ-አበሩን #ሼክ አሊ ሀይደር ጋር በመነጋገር ሀበሽ እስላም አይደለም ይህን ተግባር ካሳካህልኝ 100 ሺህ አሰጥሃለሁ በማለት #ተከሳሽ ከሚኖርበት ሶማሌ ክልል ልዩ ቦታው ኤረር ጎታ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በመነሳት አዲስ አበባ ሂዶ በአንዋር መስጊድ ላይ ቦንብ እንዲያፈነዳ በግብረ አበሩ በኩል ተልዕኮ እንደተሰጠው የወንጀል ዝርዝሩ ያስረዳል ፡፡
ተከሳሽም ተልዕኮውን ለመፈጸም አዲስ አበባ በመግባት የአንዋር መስጊድን ሁኔታ አጥንቶ ለግብረ አበሩ ማህበራዊ ድረ-ገጽ መልዕክት የላከለት ሲሆን ፥ ታህሳስ 1 ቀን 2008 ዓመተ ምህረት #በአንዋር_መስጊድ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመግባት በመስጊዱ ውስጥ ተሰብስበው በዝየራ ላይ በነበሩት ሰዎች ላይ ቦንቡን በመወርወር በ24 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት በማድረሱ በሽብርተኝነት ወንጀል ድርጊት በመፈጸም ክስ ተመስርቶበት ቆይቷል።
የፌደራል ዐቃቤ ህግም በጉዳዩ ላይ 30 ሰዎችን የምስክርነት ቃልና የተጎጂዎችን የህክምና ማስረጃ እንዲሁም የተከሳሽን የእምነት ቃል #ለፍርድ ቤቱ ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት የ11 ዓመት ፅኑ እስራት እንደበየነበት የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል።
©FBC
@yenetube @mycase27

ለአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሞት ተጠያቂ የሆኑ አካላት #ለፍርድ ይቀርባሉ- ዶክተር ደብረጽዮን
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ለአንድ ተማሪ #ህልፈት ምክንያት የሆኑ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ #መጀመሩን የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገለጹ።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ዛሬ ከሰዓት በኋላ #በሰጡት_መግለጫ ላይ በተማሪው ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።
ህይወቱ ላለፈው ተማሪ ቤተሰቦችና ጓደኞች መፅናናትን የተመኙት ዶክተር ደብረጽዮን፥“ድርጊቱ አስነዋሪ ነው” ብለዋል።
“ትግራይ የብሄሮችና ብሄረሰቦች መኖሪያ መሆኗን አምኖ ለመጣ ተማሪ እንዲህ አይነት ተግባር መፈፀም ሰላም ወዳዱን የክልሉን ህዝብ ባህልና ታሪክ የማይገልፅ ነው” ብለዋል።
ድርጊቱን የፈፀሙ ተማሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር መጀመሩን አስረድተው፥ ተጠርጣሪዎቹ ጥፋታቸውን በማጣራት የክልሉ መንግስት ወደ ህግ የሚያቀርባቸው መሆኑን ገልፀዋል።
በመስዋእትነት የተረጋገጠው ሰላም በጥቂት ግለሰቦች አይደፈርስም ያሉት ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ፥ “ህብረተሰቡ ሰላሙን ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ መነሳት ይኖርበታል” ነው ያሉት።
በክልሉ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለይም በአክሱም ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ የጠየቁት ዶክተር ደብረጽዮን፥ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ጠቁመዋል።
ምንጭ፦ ኤዜአ
@YeneTube @FikerAssefa