YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#update አንዋር መስጊድ⤵️⤵️

አንዋር መስጊድ ቅጥር ግቢ #ታህሳስ 1 ቀን 2008 ዓ.ም በግምት  ቦንብ በመወርወር የሽብር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በ11 ዓመት ጽኑ እስራት #ተቀጣ

ተከሳሽ አህመድ ሙስጠፋ አብዶሽ የራሳቸውን ሃይማኖታዊ ዓላማን ለማራመድ በማሰብ፣ በመንግስት ላይ ተፅእኖ ለማሳደርና ህብረተሰቡን ለማሸበር እንዲሁም በኢፌዲሪ ህገ-መንግስት የተረጋገጠውን የሃይማኖት ነጻነት በመቃረን ከራሳቸን አስተሳሰብና አስተምህሮት እምነት ውጪ ሌላ አስተምህሮት መኖር የለበትም የሚል ዓላማ በመከተል ቀኑና ወሩ ባልታወቀ

በ2007 ዓመተ ምህረት ተከሻሽ በሚጠቀምበት የሞባይል ስልክ ቁጥር በማህበራዊ ድረ-ገጽ ላይ የተዋወቀውንና ያልተያዘውን ግብረ-አበሩን #ሼክ አሊ ሀይደር ጋር በመነጋገር ሀበሽ እስላም አይደለም ይህን ተግባር ካሳካህልኝ 100 ሺህ  አሰጥሃለሁ በማለት #ተከሳሽ ከሚኖርበት ሶማሌ ክልል ልዩ ቦታው ኤረር ጎታ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በመነሳት አዲስ አበባ ሂዶ በአንዋር መስጊድ ላይ ቦንብ እንዲያፈነዳ በግብረ አበሩ በኩል ተልዕኮ እንደተሰጠው የወንጀል ዝርዝሩ ያስረዳል ፡፡

ተከሳሽም ተልዕኮውን ለመፈጸም አዲስ አበባ በመግባት የአንዋር መስጊድን ሁኔታ አጥንቶ ለግብረ አበሩ ማህበራዊ ድረ-ገጽ መልዕክት የላከለት ሲሆን ፥ ታህሳስ 1 ቀን 2008 ዓመተ ምህረት #በአንዋር_መስጊድ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመግባት በመስጊዱ ውስጥ ተሰብስበው በዝየራ ላይ በነበሩት ሰዎች ላይ ቦንቡን በመወርወር በ24 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት በማድረሱ በሽብርተኝነት ወንጀል ድርጊት በመፈጸም ክስ ተመስርቶበት ቆይቷል።

የፌደራል ዐቃቤ ህግም በጉዳዩ ላይ 30 ሰዎችን የምስክርነት ቃልና የተጎጂዎችን የህክምና ማስረጃ እንዲሁም የተከሳሽን የእምነት ቃል #ለፍርድ ቤቱ ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት የ11 ዓመት ፅኑ እስራት እንደበየነበት የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል።
©FBC
@yenetube @mycase27