YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በድሬዳዋ አስተዳደር መልካ ጀብዱ በተባለ አካባቢ የተቀሰቀሰ #ብሄር ተኮር ግጭት አራት ስዎች #ተገድለው በርካቶች ቆስለዋል።

የፌደራል ፖሊስና መከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው ዘልቀው ለማረጋጋት እየሞከሩ መሆኑን የአስተዳደሩ ፖሊስ #አስታውቋል
ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@Yenetube @Mycase27
#update ቤኒሻንጉል ክልል ⤵️⤵️

#ከቤኒሻንጉል ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል እርዳታ የጫኑ 9 መኪኖች በጸጥታ ችግር #ምክንያት ወደ ካማሺ ዞን መንቀሳቅስ አልቻሉም ተባለ።

ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በአሶሳ ከተማ ቆመው የሚገኙት እኒህ መኪኖች 2, 358 ኩንታል ስንዴ፣ በቆሎና የተለያዩ አልሚ ምግቦችን የጫኑ #ናቸው

የብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከቤኒሻንጉል የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮና ከመከላከያ ጋር በመተባበር መኪኖቹን ወደ ቦታው ለማንቀሳቀስና ወደ ተፈናቃዮቹ ለማድረስ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብሏል።

በተያያዝ ዜናም የቤኒሻንጉሉን ግጭት የሚያጣራው ኮሚሽንም በመንገድ መዘጋት ምክንያት ስራ አለመጀመሩን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን #አስታውቋል

የደረሰውን ሰብዓዊ ቀውስ ለማጣራት የተቋቋምው ኮሚቴ ወደ ቦታው ለመደረስ አለመቻሉን የኮሚሽኑ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ቅርንጫፍ ሃላፊ ኮሚሽነር ዶክተር #አታክልቲ ገብረህይወት አስታውቀዋል።

ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ ምርመራውን #እንደሚጀምርም ጨምረው ተናግረዋል።
ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@yenetube @mycase27