Forwarded from YeneTube
የ5 ሚሊየን ቅናሽ ተደረገ 😳😳
📍አሚስኮ ሪልስቴት(AMISCO RealEstate)
ለቡ ሙዚቃ ሰፈር
👍👍ለ 5 ቤት ብቻ የተደረገ ልዩ ቅናሽ
☎️09-89-26-43-80
🏠🏠 በካሬ 75ሺ ብር ብቻ (በከፊል ማጠናቂያ)
✅ 100% ለሚከፍል በካሬ=65ሺብር
📌ባለ 3መኝታ 183.7ካሬ
👍ጠቅላላ = 13,777,500 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,133,250ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =11.9ሚሊየን ብር
📌ባለ 3መኝታ 192.69ካሬ
👍ጠቅላላ = 14,451,750 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,335,525ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =12.5ሚሊየን ብር
ሳይቱ የሚያሟላቸው ነገሮች
👉B+G+12+terrace
👉 90% የተጠናቀቀ
👉በ6 ወር የምትረከቡት
👉 ምቹ መኖሪያ ሰፈር
👉የተሟላ እና በቂ ፓርኪንግ
👉 የጋራ አዳራሽ
👉 የደህንነት መጠበቂያ ካሜራ
👉 የከርሰ ምድር ውሃ
👉 ዋና ገንዳ
👉 የልጆች መጫወቻ
👉 ደህንነቱ የተጠበቀ የመኖሪያ መንደር
👉 የቆሻሻ ማስወገጃ
👉እሳት አደጋ ማጥፊያ
👉 ተጠባባቂ ጀነሬተር
👉 ሊፊት
👉ሰፊ ቴራስ
👉6500 ካሬ ላይ ያረፈ ጊቢ
👉ግሪን ጋርደን
👉በ100ሜ ርቀት የእምነት ተቋማት
የሚያስፈልግዎትን ሁሉ በአቅራቢያዎ የሚያገኙበት
እድሉን ለመጠቀም
☎️09-89-26-43-80
Whatsup: 09-89-26-43-80
Telegram: @fiyami11
Email:hiwottadi22@icloud.com
📍አሚስኮ ሪልስቴት(AMISCO RealEstate)
ለቡ ሙዚቃ ሰፈር
👍👍ለ 5 ቤት ብቻ የተደረገ ልዩ ቅናሽ
☎️09-89-26-43-80
🏠🏠 በካሬ 75ሺ ብር ብቻ (በከፊል ማጠናቂያ)
✅ 100% ለሚከፍል በካሬ=65ሺብር
📌ባለ 3መኝታ 183.7ካሬ
👍ጠቅላላ = 13,777,500 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,133,250ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =11.9ሚሊየን ብር
📌ባለ 3መኝታ 192.69ካሬ
👍ጠቅላላ = 14,451,750 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,335,525ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =12.5ሚሊየን ብር
ሳይቱ የሚያሟላቸው ነገሮች
👉B+G+12+terrace
👉 90% የተጠናቀቀ
👉በ6 ወር የምትረከቡት
👉 ምቹ መኖሪያ ሰፈር
👉የተሟላ እና በቂ ፓርኪንግ
👉 የጋራ አዳራሽ
👉 የደህንነት መጠበቂያ ካሜራ
👉 የከርሰ ምድር ውሃ
👉 ዋና ገንዳ
👉 የልጆች መጫወቻ
👉 ደህንነቱ የተጠበቀ የመኖሪያ መንደር
👉 የቆሻሻ ማስወገጃ
👉እሳት አደጋ ማጥፊያ
👉 ተጠባባቂ ጀነሬተር
👉 ሊፊት
👉ሰፊ ቴራስ
👉6500 ካሬ ላይ ያረፈ ጊቢ
👉ግሪን ጋርደን
👉በ100ሜ ርቀት የእምነት ተቋማት
የሚያስፈልግዎትን ሁሉ በአቅራቢያዎ የሚያገኙበት
እድሉን ለመጠቀም
☎️09-89-26-43-80
Whatsup: 09-89-26-43-80
Telegram: @fiyami11
Email:hiwottadi22@icloud.com
❤5
የዓለም ጤና ድርጅት በ2025 የጤና ዕርዳታ እስከ 40% ሊቀንስ እንደሚችል አስጠነቀቀ!
የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በ2025 ዓ.ም. ለጤና ዘርፍ የሚሰጠው ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድጋፍ እስከ 40 በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል ትንበያውን ይፋ አድርጓል።ይህ ቅነሳ በውጭ ዕርዳታ ላይ ከፍተኛ ጥገኝነት ባላቸው በርካታ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገሮች ላይ ከባድ ተጽዕኖ እንደሚያሳድርና ዜጎች ለጤና አገልግሎት ከራሳቸው ኪስ የሚያወጡት ወጪ በእጅጉ እንዲጨምር እንደሚያደርግ ተገልጿል።
ይህ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ከሁለት ሳምንት በፊት በእስያ ልማት ባንክ በተዘጋጀው ኢንስፓየር ፎረም ላይ የዓለም ጤና ድርጅት ባቀረበው ግምት መሠረት ነው።ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው፣ ለጤና የሚውለው ኦፊሴላዊ የልማት እርዳታ (ODA) በ2025 ከ2023 ደረጃ ጋር ሲነፃፀር ከ25 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወደ 15 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ ሊቀንስ ይችላል።
ይህ አኃዝ እኤአ በ2015 ዓ.ም. ከነበረው 18 ቢሊዮን ዶላር የጤና ኦዲኤ ፈንድ በታች በመሆን፣ ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይደርሳል ተብሏል።የዚህ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ቅነሳ ዋነኛ ምክንያት፣ ለዓለም አቀፍ ጤና ዕርዳታ ከሚሰጡ ትልልቅ ለጋሽ አገሮች መካከል፣ እንደ አሜሪካ እና ሌሎች በርካታ አገሮች የገንዘብ ድጋፋቸውን በእጅጉ መቀነሳቸው እንደሆነ ተጠቁሟል።
Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa

❤7
በትግራይ ክልል አፈሳ መጀመሩን ተከትሎ የክልሉ ወጣቶች ክልሉን ለቀው እየወጡ መሆኑ ተገለጸ!
በትግራይ ክልል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ የመጣው የፖለቲካ አለመግባባት ስጋት በመፍጠሩና ለጦርነት አፈሳ መጀመሩን ተከትሎ፤ ወጣቶች ክልሉን ለቀው እየወጡ መሆኑን ለአሐዱ አስታውቀዋል።"እኛ ጦርነት አንፈልግም" ያሉት ወጣቶቹ፤ "ከየትኛውም በኩል ኢትዮጵያዊነታችንን ለመግፋት የሚደረግ ጫና ተቀባይነት የለም" ብለዋል፡፡
"ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በክልሉ ያለው አለመረጋጋት ስጋት ስላሳደረብን፤ ደህንነቱ ወደ ተጠበቀ ቦታ ለቀን እየወጣን ነው" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል።
"በክልሉ እስር፣ ግድያና ማስፈራራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ መጥቷል" የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ "ችግሩን የሚፈታ ሳይሆን የሚባባስ እየሆነ በመሄዱ ስጋት እየተፈጠረብን ነው። በዚህም ምክንያት ሕይወታችንን ለመታደግ ስደትን እየመረጥን ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
"እኛ በአሁኑ ወቅት ወደ ጦርነት የሚያስገባን ጉዳይ የለንም። ከሆነም በንግግር መፍታት ነው የምንፈልገው" ያሉም ሲሆን፤ "ሆኖም ይህንን እንድናደርግ ዕድል የሚሰጠን ባለማግኘታችን በቂ ገንዘብ ያላቸው ጓዳኞቻችን ተመቻችቶላቸው ከሀገር አስቀድመው ወጥተዋል" ብለዋል።
አሐዱም ስለጉዳዩ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለማናገር ያደረገው ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ አልተሳካም።
ነገር ግን በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ አብዮታዊ ሕዝቦች (ኢህአፓ) ፓርቲ ዋና ሥራ አስኪያጅና የትግራይ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ወኪል ይሳቅ ወልዳይን እና የቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች ኢትዮጵያ ምክትል ፕሬዝዳንት መብሪህ ብርሃንን አነጋግሯል።
የኢሕአፓ ዋና የሥራ አስፈፃሚ አባሉና የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ተወካይ የሆኑት አቶ ይሳቅ ወልዳይ በሰጡት ምላሽ፤ ህወሓትና የፌደራሉ መንግሥት ወደ ጦርነት በመግባታቸው የትግራይ ወጣት ከኢትዮጵያዊን ወንድም እና እህቶቹ ጋር እንዲዋጋ ሆኗል" ሲሉ አስታውሰዋል።
"እንደ በፊቱ የትግራይ ወጣት ጦርነት አይፈልግም" ያሉት የሥራ አስፈፃሚ አባሉ፤ "አሁን የሚፈልገው ስደት ሳይሆን መማር እና መስራት ወደቀደመው ሕይወቱ መመለስ ነው" ብለዋል።
"የትግራይ ወጣቶች በአሁኑ ሰዓት ለስራ አጥነት፣ ለከፋ ችግር፣ ለጦርነት እና ለግጭት በመጋለጡ ስደትን እየመረጠ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የቅድሚያ ለሰብዓዊ መብት ኢትዮጵያ ምክትል ፕሬዝዳንት መብሪህ ብርሃነ በሰጡት ምላሽ፤ "በክልሉ በሚንቀሳቀሱ ወታደራዊ አመራሮችና በፌደራል መንግሥቱ መካከል በተፈጠረው ፖለቲካዊ አለመግባባት ሰብዓዊ ድጋፍ ለመስጠትም ተግዳሮት ሆኗል" ሲሉ ገልጸዋል።
"ወጣቱ ትውልድ በአሁኑ ወቅት ወደ ሳዑዲ አረቢያና በሌሎች ሀገራት በባህር እየተሰደደ ነው፡፡ ይህን ደግሞ እልባት ሊሰጠው ይገባል" ሲሉ አሳስበዋል።
"አሁን ላይ የክልሉ ሕዝብ የሚፈልገው ጦርነት ሳይሆን ሰብዓዊ አቅርቦት ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
ለአሐዱ ቅሬታቸውን የገለጸት የትግራይ ክልል ወጣቶች በበኩላቸው፤ "የሚመለከተው አካል በሀገራችን በሰላማዊ መንገድ ሰርተን የምንቀየርበትን መንገድ እንዲፈጥርልን እንጠይቃለን" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
Via Ahadu

❤50👎3🔥2👀2😁1😭1
የኢትዮጵያ እና የሳዑዲአረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሁለትዮሽ ግንኙነት እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙርያ ተወያዩ!
የሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ጋር ትናንት አርብ ሐምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም በስልክ መወያየታቸውን የሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስትሮቹ በሁለትዮሽ ግንኙነታቸው ዙርያ ወይይት ያደረጉ ሲሆን፤ በቀጠናው ያሉትን ተግዳሮቶች ለመፍታት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ጨምሮ፣ በቅርብ ጊዜ በተከሰቱ ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያላቸውን አስታየት ተለዋውጠዋል ተብሏል።

❤12😁5🔥2
የጎንደሯ ነዋሪ የሽቱ ምስጋናው በኢትዮጵያ ሎተሪ ታሪክ ከፍተኛ የሆነውን 50 ሚሊዮን ብር ሎተሪ አሸናፊ ሆነች።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የሚሊዮን ሎተሪ እና የቶምቦላ እጣ ባለዕድለኞችን በዛሬው እለት ሸልሟል።ብሔራዊ ሎተሪ ያዘጋጀው የ50 ሚሊዮ ብር ሎተሪ እጣ ግንቦት 30/2017 ዓ.ም መውጣቱ ይታወሳል፡፡
በተመሳሳይ የቤት እና የመኪና ዕጣዎችም ከተጨማሪ የገንዘብ ሽልማት ጋር ያቀረበው ቶምቦላ ሎተሪ ባለፈው ሰኔ 29 አሸናፊዎቹ ይፋ ማድርጉ ይታወቃል፡፡በዚህም የ50 ሚሊዮን ሎተሪ እና የቶምቦላ ሎተሪ አሸናፊወች ሽልማታቸውን ዛሬ ተረክበዋል፡፡
የሚሊዮን ሎተሪ ዕድለኞች የአንደኛ እጣ አሸናፊ የሆነችው የሽቱ ምስጋናው ከጎንደር 50 ሚሊዮን ብር አሸናፊ ሆናለች፣ ሽልማቷንም ተቀብላለች።
ካሳ አለሙ አባይ የተባሉ ከትግራይ ነዋሪ ደግሞ 25 ሚሊዮን አሸናፊ ሆነዋል፣ ሽልማታቸውንም ተቀብለዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ በቶምቦላ ሎተሪ ነጋልኝ አበራ ብሩ ከኦሮሚያ ም/ሸዋ 1ኛ ዕጣ ባለ 3 መኝታ መኖሪያ ቤት ከተጨማሪ ለ3 ዓመት 60ሺህ አሸናፊ ሆነዋል።ሌሎችም አሸናፊዎች ሽልማቶቻቸውን ዛሬ ተቀብለዋል።
Via Sheger

❤55🔥5😭3😁2⚡1
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ላይ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ተከሰተ!
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ላይ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ተከስቷል።
የአደጋው መንስኤ ባይታወቅም የአካባቢው ማሕበረሰብ ከከተማው እሳት አደጋ መከላከያ እና ፀጥታ አካላት ጋር በመሆን እሳቱን ለመቆጣጠር እየተረባረበ ነው።ሆስፒታሉ አንጋፋ እና ከወላይታ ዞን ውጪ በአጎራባች ዞኖች ላሉ ነዋሪዎች ጭምር አገልግሎት ሲሰጥ የቆየም ነው።
Via EBC

❤7😭3👎1👀1
#Update
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተከሰተው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ሥር ዋለ!
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ላይ የተከሰተውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተችሏል።አደጋው ከቀኑ 8:00 ሰዓት አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ መንስኤው እየተጣራ ይገኛል።
እሳቱን ለመቆጣጠር ሕብረተሰቡ እና የጸጥታ አካላት የተቀናጀ ብርቱ ጥረት ያደረጉ ሲሆን፤ በአደጋው የሆስፒታሉ ቀዶ ሕክምና፣ የውስጥ ደዌ ሕክምና እና ተመላላሽ ሕክምና ክፍሎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተጠቁሟል።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀድሞ ስሙ ኦቶና ሆስፒታል አንጋፋ እና ከወላይታ ዞን ውጪ በአጎራባች ዞኖች ላሉ ነዋሪዎች ጭምር አገልግሎት የሚሰጥ ሆስፒታል ነው።
Via FBC

❤24😭3
ሕወሓት፣ ፌደራል መንግሥቱና ወታደራዊ አመራሮቹ አኹንም የትግራይን ሕዝብ በማስፈራራት ተጠምደዋል ሲል ዛሬ ባወጣው ሳምንታዊ መልዕክቱ ከሷል።
የመንግሥት ዛቻዎች ትግራይን ለቀጣይ ጥፋት ሰበብ ለማድረግ የሚካሄዱ ናቸው ያለው ሕወሃት፣ የትግራይ ሕዝብና መሪ ድርጅቱ ፍላጎት ግን የትግራይን ጥቅም ለማስጠበቅ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ልዩነቶችን መፍታት ነው ብሏል። ዓለማቀፉ ኅብረተሰብም፣ ፌደራል መንግሥቱ የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት ተግባራዊ እንዲያደርግ ግፊት እንዲፈጥርም ሕወሓት ጠይቋል።

❤55👎33😁13
የቤንዚል፣ የነጭ ናፍጣ እና የኬሮሲን ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ተባለ!
የነሐሴ ወር የቤንዚል፣ የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲን እና የአውሮፕላን ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል አለ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፡፡ሚኒስቴሩ ከዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነሐሴ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም መሰረት የቤንዚል፣ የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲንና የአውሮፕላን ነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ብሏል፡፡
በሌላ በኩል ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 127 ነጥብ 22 ብር እንዲሁም ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 124 ነጥብ 55 ብር ብቻ እንዲሸጥ መወሰኑን የሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ወንድሙ ፍላቴ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎችም በነዳጅ ውጤቶች ግብይት በአዋጁና በአሠራር መመሪያው መሠረት ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

❤39🔥3
Forwarded from YeneTube
👀👀👀👀👀👀👀👀👀👀
"አስቸኳይ ክፍት የስራ ማስታወቂያ"
ቀን 18/11/17 የወጣ
0997473781/ 0997470384
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ:ነርስ ጂፒ ዶክተር ነርስ,ላብራቶሪ ቴክኒሻን
♦️ት/ት ደረጃ:diploma/degree
♦️ልምድ:0-5
♦️ደሞዝ:በድርጅቱ እስኬል
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ #አካዉንታንት ለ ድርጅቶች እና ሆቴሎች ላይ /ለአስመጭ/ለፍብሪካ
♦️የት/ደረጃ' ዲግሪ/ዲፕሎማ
♦️የስራ ልምድ'0-6ዓመት
♦️ደሞዝ' 6000-15000
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅NGO
♦️የት/ት ደረጃ ኤኒ ዲግሪ /ዲፕሎማ
♦️የስራ ልምድ 0አመት
♦️ደሞወዝ 25000 30000+
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራመደብ: ስልክ ኦፕሬተር በፈረቃ
♦️ት/ት ደረጃ:10/12/ዲፕሎማ
♦️ልምድ: 0አመት
♦️ደሞዝ: 9800 +
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
የስራ መደብ: የሽልማት አስተባባር
♦️የት/ደረጃ' ዲግሪ/ዲፕሎ
♦️የስራ ልምድ '0አመት
♦️ደሞወዝ 13500
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ:# ጥፍር እና አይላሽ
♦️ት/ት ደረጃ: 10
♦️ልምድ: 0አመት
♦️ደሞወዝ 12000 +
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ #አየር መንገድ ውስጥ ሽያጭ
♦️የት/ደረጃ' 10/ ዲፕሎማ/ዲግሪ
♦️የስራ ልምድ' 0 ዓመት
♦️ደሞዝ' 10,000 +
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ #Reception ለሆቴል ,ድርጅቶች እና ለ ገስት ሀውስ/ለክሊኒክ/ሆስፒታል/ለድርጅት
♦️የት/ደረጃ 10/ degree/dip
♦️ፃታ' /ሴ
♦️የስራ ልምድ'0~1 ዓመት
♦️ደሞዝ' 7000+
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ ሆስተስ
♦️የት/ደረጃ' 10+
♦️ፆታ' /ሴ
♦️ደሞዝ' 15000/ 20000
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ:# ሹፌር ህ1/ደረቅ1
♦️ት/ት ደረጃ 8/10
♦️ልምድ:የሰራ
♦️ደሞዝ:11.000
♦️ፆታ:ሴት
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ:#ካሸር ለድርጅት እና ለትለያዩ ተቁአማት##ለሆቴል#ለሱፕርማርኬት
♦️የት/ደረጃ' 10-ዲግሪ
♦️ልምድ:0-1
♦️ፆታ' ሴ
♦️ደሞዝ' 5500-10000+
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ #በያጅ GMF
♦️የት/ደረጃ'/10/ሰርተፉኬት
♦️ልምድ: የሰራ
♦️ደሞዝ' ማራኪ
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ: ጉዳይ አስፈፃሚ
♦️የት/ደረጃ' 10+
♦️የስራ ልምድ '0አመት
♦️ፆታ' ወ/ሴት
♦️ደሞዝ: 10500
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
⭐️የስራ መደብ:#የእሸጋ ሰራተኛ
✨የት/ት ደረጃ:10/ሰርተፍኬት
✨ልምድ:0አመት
✨ደሞዝ:በስምምነት
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
☎️ አድራሻ መገናኛ መተባበር
ህንጻ 4 ፎቅ ቢሮ ቁ B421
📞 0997470384
📞 0997473781

🎁ከተወዳጁ የሂል ሳይድ መንደር ውስጥ ለሽያጭ የመጨረሻ በሆነው የዲያስፓራ ብሎክ ቁጥር 3 ላይ ከባለ አንድ እስከ ባለ አራት መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች
🏡በ 8% ቅድመ ክፍያ ብቻ
የቤቱን 60% ደግሞ እየኖሩበት ወይም አከራይተውት በ20 አመት ቀስ ብለው መክፈል የሚችሉት
💎 ባለ 1 መኝታ በ 487,000 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 825,982 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 854,221 ሺ ብር
💎ባለ 4 መኝታ በ 1,157,787 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
🛍️🛒ሱቆች ከ 70 ካሬ ጀምሮ ይምጡ የግሎ ያድርጉ
- ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 3 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው
-እንዲሁም በ ግሩፕ ሆነው ለሚመጡ ደንበኞች ዳጎስ ያለ ቅናሽ አዘጋጅተን እየጠበቅኖት ነው
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelDMCRealtor)
#WhatsApp

❤2
Forwarded from YeneTube
የ5 ሚሊየን ቅናሽ ተደረገ 😳😳
📍አሚስኮ ሪልስቴት(AMISCO RealEstate)
ለቡ ሙዚቃ ሰፈር
👍👍ለ 5 ቤት ብቻ የተደረገ ልዩ ቅናሽ
☎️09-89-26-43-80
🏠🏠 በካሬ 75ሺ ብር ብቻ (በከፊል ማጠናቂያ)
✅ 100% ለሚከፍል በካሬ=65ሺብር
📌ባለ 3መኝታ 183.7ካሬ
👍ጠቅላላ = 13,777,500 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,133,250ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =11.9ሚሊየን ብር
📌ባለ 3መኝታ 192.69ካሬ
👍ጠቅላላ = 14,451,750 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,335,525ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =12.5ሚሊየን ብር
ሳይቱ የሚያሟላቸው ነገሮች
👉B+G+12+terrace
👉 90% የተጠናቀቀ
👉በ6 ወር የምትረከቡት
👉 ምቹ መኖሪያ ሰፈር
👉የተሟላ እና በቂ ፓርኪንግ
👉 የጋራ አዳራሽ
👉 የደህንነት መጠበቂያ ካሜራ
👉 የከርሰ ምድር ውሃ
👉 ዋና ገንዳ
👉 የልጆች መጫወቻ
👉 ደህንነቱ የተጠበቀ የመኖሪያ መንደር
👉 የቆሻሻ ማስወገጃ
👉እሳት አደጋ ማጥፊያ
👉 ተጠባባቂ ጀነሬተር
👉 ሊፊት
👉ሰፊ ቴራስ
👉6500 ካሬ ላይ ያረፈ ጊቢ
👉ግሪን ጋርደን
👉በ100ሜ ርቀት የእምነት ተቋማት
የሚያስፈልግዎትን ሁሉ በአቅራቢያዎ የሚያገኙበት
እድሉን ለመጠቀም
☎️09-89-26-43-80
Whatsup: 09-89-26-43-80
Telegram: @fiyami11
Email:hiwottadi22@icloud.com
📍አሚስኮ ሪልስቴት(AMISCO RealEstate)
ለቡ ሙዚቃ ሰፈር
👍👍ለ 5 ቤት ብቻ የተደረገ ልዩ ቅናሽ
☎️09-89-26-43-80
🏠🏠 በካሬ 75ሺ ብር ብቻ (በከፊል ማጠናቂያ)
✅ 100% ለሚከፍል በካሬ=65ሺብር
📌ባለ 3መኝታ 183.7ካሬ
👍ጠቅላላ = 13,777,500 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,133,250ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =11.9ሚሊየን ብር
📌ባለ 3መኝታ 192.69ካሬ
👍ጠቅላላ = 14,451,750 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,335,525ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =12.5ሚሊየን ብር
ሳይቱ የሚያሟላቸው ነገሮች
👉B+G+12+terrace
👉 90% የተጠናቀቀ
👉በ6 ወር የምትረከቡት
👉 ምቹ መኖሪያ ሰፈር
👉የተሟላ እና በቂ ፓርኪንግ
👉 የጋራ አዳራሽ
👉 የደህንነት መጠበቂያ ካሜራ
👉 የከርሰ ምድር ውሃ
👉 ዋና ገንዳ
👉 የልጆች መጫወቻ
👉 ደህንነቱ የተጠበቀ የመኖሪያ መንደር
👉 የቆሻሻ ማስወገጃ
👉እሳት አደጋ ማጥፊያ
👉 ተጠባባቂ ጀነሬተር
👉 ሊፊት
👉ሰፊ ቴራስ
👉6500 ካሬ ላይ ያረፈ ጊቢ
👉ግሪን ጋርደን
👉በ100ሜ ርቀት የእምነት ተቋማት
የሚያስፈልግዎትን ሁሉ በአቅራቢያዎ የሚያገኙበት
እድሉን ለመጠቀም
☎️09-89-26-43-80
Whatsup: 09-89-26-43-80
Telegram: @fiyami11
Email:hiwottadi22@icloud.com
❤2
2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ!
ኢትዮጵያ እና ጣልያን በጋር ያዘጋጁት 2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።በመዲናዋ እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ የጣሊያን ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ፣ የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሃመድ፣ የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ፣ የዓለምአቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) ፕሬዝዳንት አልቫሮ ላሪዮ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በተጨማሪም የተባበሩት መንግሥታት ረዳት ዋና ፀሐፊና የዩኤንዲፒ የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ፣ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ፣ የኬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶን ጨምሮ በርካታ ሚኒስትሮችና ባለድርሻ አካላት የጉባኤው ተሳታፊ ናቸው።
የምግብ ሥርዓት ጉባኤው አጀንዳዎች በዓለም የምግብ ሥርዓት ላይ በተገኙ ለውጦችና ተግዳሮቶች ላይ እንደሚሆን ተገልጿል። ሀገራት የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽንን ያገኟቸውን ስኬቶችና ያጋጠሟቸው ተግዳሮቶች ላይ ሪፖርት ያቀርባሉ፤ በሮሙ ጉባኤ የገቧቸው ቃሎች የደረሱበትን ደረጃ ይገመግማል እንዲሁም አቅጣጫዎችንም ያሰቀምጣል ተብሏል።
ለምግብ ስርዓት ሽግግር ስራዎች በአነስተኛ ወለድ የፋይናንስ አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግ፣ አማራጭ የፋይናንስ ምንጮችን መጠቀም እና ሀገር በቀል የፋይናንስ መሰብሰብ አቅምን ማጎልበት ላይ ምክክሮች እንደሚደረግ ኢፕድ ዘግቧል።ከጉባኤው ጎን ለጎን የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብሮች፣ የሁለትዮሽ ውይይቶችና ጉብኝቶች ይደረጋሉ ተብሎም ይጠበቃል።

❤14🔥1
አልሸባብ የኢትዮጵያ ጦር ያስለቀቀውን ከተማ ከሶማሊያ ሠራዊት መልሶ ተቆጣጠረ!
የሶማሊያው ታጣቂ ቡድን አልሸባብ ከ11 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ጦር እንዲለቅ የተደረገውን እና በሶማሊያ መንግሥት ሠራዊት ስር የነበረችውን ማሃስ ከተማ ዳግም በቁጥጥሩ ስር ማስገባቱ ተሰማ።ቢቢሲ ሶማሊኛ ዛሬ ማለዳ ባወጣው ዘገባ መሠረት በማዕከላዊ ሶማሊያ ሂራን ክልል ውስጥ የምትገኘው ማሃስ ትናንት እሁድ ከባድ ውጊያ ተካሂዶባታል።
በከተማዋ በመንግሥት ወታደሮች እና ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው በሚነገርለት በአልሸባብ ታጣቂዎች መካከል በተካሄደው ከባድ ውጊያ በርካቶች መሞታቸው ተሰምቷል።አልሸባብ በከተማዋ ላይ ጥቃት የፈጸመው ተቀጣጣይ ፈንጂ በጫኑ መኮኖች በመታገዝ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ሶማሊኛ ተናግረዋል።
የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስቴር በአካባቢው ስላለው ግጭት ባወጣው አጭር መግለጫ የአካባቢ እና የመንግሥት ኃይሎች በርካታ የአልሸባብ ታጣቂዎችን መግደላቸውን ገልጿል።ነገር ግን ሚኒስቴሩ ምን ያህል ታጣቂዎች እንደተገደሉ የገለፀው ነገር የለም።የአከካባቢው ነዋሪዎች በአልሸባብ እና በመንግሥት ወታደሮች መካከል በነበረው ውጊያ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።ነገር ግን የደረሰውን ጉዳት ለማረጋገጥ የሚያስችል የገለልተኛ ወገን መረጃ የለም።
Via BBC

😁10❤7👍4🔥1
በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ የሚገኙ 14 ወረዳዎች ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ የተወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና እና ቦረና ዞኖች ሕዝባዊ ተቃዉሞ መቀስቀሱን ዋዜማ ሰምታለች።
ይህ ውሳኔ የተወሰነው የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ሰሞኑን ባካሄደው ዓመታዊ ጉባኤው ላይ መሆኑን ያስረዱት ምንጮች፣ ይህንኑ ተከትሎ በቅርቡ እንደ አዲስ በተዋቀረው የምስራቅ ቦረና ዞን መቀመጫ ነጌሌ ቦረና ከተማ እና የቦረና ዞን መቀመጫ በሆነችው ያቤሎ ከተማ፣ እንዲሁም በሌሎች ወረዳዎች ከዛሬ ማለዳ አንስቶ የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሄዱ መሆኑን ዋዜማ የደረሳት መረጃ ያመልክታል።
ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ በምክር ቤቱ የተወሰኑት 14ቱ ወረዳዎች በሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ በሚገኙት ቦረና፣ ባሌ፣ ሐረርጌ እንዲሁም ከድሬደዋ አካባቢዎች ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ ውሳኔ የተሰጠባቸው እንደሆኑ ምንጮች ነግረውናል።ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 21፣ 2017 ዓ፣ም እኩለ ቀን ድረስ በፌዴራልም ሆነ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት በኩል በጉዳዩ ላይ የተባለ ነገር የለም።
[ዋዜማ]

❤24⚡2😁2😭2👀1