YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
"የትምህርት ስረአታችን ከቀኝ-ግዛት ተፅእኖ ነፃ ማውጣት አለብን" ሲሉ የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታው ኮራ ጡሽኔ ተናገሩ

ሚኒስትር ዲኤታው እንደገለፁት አብዛኛው የአፍሪካ የትምህርት ሥርዓት ሙሉ በሙሉ የተወሰደው ከምዕራባውያን ሀገሮች እና ከባህላቸው ነው ፤ በዚህም ምክንያት በተለያየ መንገድ የቅኝ ግዛት ተፅእኖው አሁንም አለ።

ከቀኝ ግዛት ነፃ መውጣት ማለት... ባህላዊ እሴቶቻችንን በትምህርት ስረአታችን ውስጥ በማካተት ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን መፈለግ ነው" በማለት አመለካከታችንም ጭምር ነፃ መውጣት እንዳለበት  ከኢኖቬሽን 2025 የሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።


@Yenetube @Fikerassefa
👍44😁168👎3👀3
Instagram የራሱን የቪድዮ ኢዲት ማድረጊያ መተግበሪያ አስተዋወቀ።

Instagram "Edits" ሲል የሰየመውን የediting መተግበሪያ ከቀናት በፊት አስተዋውቋል። ይህም ከቲክቶኩ የኢዲቲንግ መተግበሪያ Capcut ጋር በርካታ ተመሳሳይ features አሉት።

ይህ መተግበሪያ በAI የተደገፉ tools ስላሉት ለcontent creators ስራ አቅላይ ነውም ተብሏል።

አሁን ላይ ያን ያህል ከሌሎች የኢዲቲንግ መተግበሪያዎች ጋር መፎካከር የሚያስችለው features ባይኖሩትም ወደፊት ጥሩ features/አገልግሎቶች እንደሚያካትትም ተገልጿል።

መተግበሪያውን ከplay store ለማውረድ edits

Via:- Big habesha
@Yenetube @Fikerassefa
👍456😁1
🔒 በHulugram ውስጥ የግል ውይይቶችን እንዴት መደበቅ ይችላሉ? 🔒

📱 ውይይቶችዎን በሚስጥር መጠበቅ ይፈልጋሉ? Hulugram ቀላል ያደርገዋል! 💯

ማንኛውንም ውይይት በጥቂት ቀላል ደረጃዎች እንዴት መደበቅ እንደሚችሉ እነሆ:

1️⃣ የሚፈልጉትን ውይይት ላይ ረጅም ጊዜ ተጭነው ይያዙ 👆

2️⃣ በሚታየው menu ውስጥ "More options" ላይ ይንኩ ⋮ 👉📋

3️⃣ ከአማራጮቹ ውስጥ "Hide" ን ይምረጡ 🙈


🔐 የመጀመሪያ ጊዜ ወይይቶን እየደበቁ ነው? 🔐

ለጥበቃ የይለፍ ቁጥር እንዲያዘጋጁ ይጠየቃሉ! 🔑🛡️

የይለፍ ቁጥርዎን ካዘጋጁ በኋላ:
ግላዊ እንዲሆኑ የሚፈልጓቸውን ማንኛውንም ውይይቶች መደበቅ ይችላሉ! 🤫👀

Download Here 👉 https://play.google.com/store/apps/details?id=plus.ride.huluchat 🔄📥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍91
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵዊያን ሰራተኞች የኑሮ ሁኔታ፤ አሁንም አሳሳቢነቱ ቀጥሏል ሲል የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ተናገረ፡፡

ኮንፌዴሬሽኑ በመጪው ሀሙስ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ136ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሰራተኞች ቀንን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ኢሰማኮ በመግለጫውም የዋጋ ግሽበት የደመወዝ ተከፋዩን የመግዛት አቅም በእጅጉ እንዳዳከመው ነውም ብሏል፡፡

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እስካሁን አለመወሰኑን ያስታወሰው ኮንፌዴሬሽኑ ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ አነስተኛ ሆኖ እያለ ከፍተኛ የገቢ ግብር ስለሚቆረጥባቸው መሰረታዊ ፍላጎታቸውን እንዳያሟሉ አድርጓቸዋል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ አንዳንድ አሰሪዎች፣ የማህበር መሪዎች ለአባሎቻቸው ስለቆሙ ወይም ለአባሎቻቸው መብት ስለተከራከሩ ብቻ ከስራ ይባረራሉ፣ ይዋከባሉ ወይም ራቅ ወዳለ ቦታ እንዲዘዋወሩ ይደረጋሉ ብለዋል፡፡

አቶ ካሳሁን ኑሮ የከበዳቸውን ተቀጣሪ ሰራተኞችን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተላኩ ጥያቄዎችን በተመለከተ በተደረገው ውይይት ጥያቄያችን ተቀባይነት አግኝቶ ለሚመለከታቸው ሚኒስትሮች ተላልፎ ተሰጥቷቸዋል፤ ሆኖም የተወሰኑ ጥያቄዎች ምላሽ ያገኙ ቢሆንም መሰረታዊና ቁልፍ የሆኑ የሰራተኛ ጥያቄዎች አልተመለሱም ብለዋል፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
👍51😭133
#ትሊዴፓ

" ከብልጽግና ጋር ልክ እንደሌሎቹ በአገር ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ተባብሮ ለመሥራት ይችላል እንጂ የሚያገናኘው ነገር የለም፤ ገለልተኛ እና ነጻ ፓርቲ ነው " - የቀድሞ የህወሓት አመራር


በጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ከህወሓት የተከፈለው ቡድን አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም በሂደት ላይ መሆኑን ከአመራሮቹ መካከል አንዱ ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ገልጸዋል።

የፖለቲካ ፓርቲው በሊብራል ዴሞክራሲ ጽንሰ ሃሳብ የሚመራ ሲሆን " ትግራይ ሊብራል ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ " በማለት ለመጠራት ውስኗል።

" ስሜ አይጠቀስ " ያሉ አንድ የቀድሞ የህወሓት አመራር ስለ ፓርቲው ምስረታ ምን አሉ ?

- " የፓርቲው ስያሜ የፖለቲካ ፓርቲውን ለመመሥረት በእንቅስቃሴ ላይ ባሉ ሰዎች የተመረጠ እንጂ ከምርጫ ቦርድ እውቅና ስላላገኘ ጉባዔ ሲካሄድ ሊቀየር ወይንም ሊሻሻል ይችላል። "

- " የህወሓት ሕጋዊነት ስለሚያበቃ የህወሓት የፖለቲካ ዓላማዎችን ለማሳካት የሚያስችለን አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመሥረት ተገድደናል። "

-  " የፓርቲው ሕገ ደንብ እና ፕሮግራሞቻችን አርቅቀን ጨርሰናል። "

- " አሁን ላይ የደጋፊዎችን ፊርማ በማሰባሰብ ላይ እንገኛለን። "

- " የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች ገና ስላልተሟሉ እስካሁን ድረስ ለቦርዱ በይፋ የቀረበ ጥያቄ የለም። "

- " የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ቡድኑ ለምዝገባ እየሄደበት ያለውን ሂደት ያውቃል። "

- " ፓርቲው ክልላዊ ፓርቲ ነው። ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በግንቦት የመጀመሪያ ወር ላይ ቅድመ እውቅና እናገኛለን ብለን እንጠብቃለን። "

- " የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአንድ ዓመት ጊዜ ካበቃ በኋላ ክልላዊ መንግሥትን ለመመሥረት በሚደረገው ምርጫ እንሳተፋለን። "

- " ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እውቅና ካገኘን በኋላ ከባለሀብቶች እስከ የቀን ሠራተኞች ድረስ በአባልነት እና በአመራርነት ተቀላቅለው ሊሳተፉበት ይችላሉ። "

- " ትግራይ ሊብራል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ከብልጽግና ጋር ልክ እንደሌሎቹ በአገር ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ተባብሮ ለመሥራት ይችላል እንጂ የሚያገናኘው ነገር የለም፤ ገለልተኛ እና ነጻ ፓርቲ ነው።
"

የትግራይ ሊብራል ዴሞክራቲክ ፓርቲ እየመሠረቱ ካሉተ አንጋፋ ሰዎች መካከል ፦
• የቀድሞ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣
• የህወሓት ፖሊት ቢሮ አባል የነበሩት እና የትዕምት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በየነ መክሩ
• ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት እንደሚገኙበት ታውቋል። (ፕሮፌሰር ክንደያ በቅርቡ በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል)

በሁለት ተከፍሎ እርስ በእርሱ ሲካሰስ የቆየው ህወሓት የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው ቀነ ገደብ ጉባዔ ማካሄድ ባለመቻሉ ከፓርቲነት ሊሰረዝ እንደሚችል ቦርዱ ማስታወቁ ይታወሳል።

የመሰረዝ አደጋ የገጠመው በደብረፂዮን (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ተደራድሮ የፕሪቶሪያ ስምምነትን እንደፈረመ ድርጅት እንደ አዲስ በቦርዱ መመዝገቡ ተገቢ አለመሆኑን ሲገልጽ ቆይቷል።

የህወሓት መሰረዝ ስጋት የፈጠረባቸው በአቶ ጌታቸው የሚመራው የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ከሳምንታት በፊት ባወጡት መግለጫ በደብረፂዮን (ዶ/ር) ለሚመራው ቡድን በጋራ ጉባዔ ለማካሄድ ጥሪ አቅርበው የነበረ ቢሆንም በጎ ምላሽ አለማግኘታቸውን ገልጸዋል።

በመሆኑም " የህወሓት ሕጋዊነት ስለሚያበቃ የህወሓት የፖለቲካ ዓላማዎችን ለማሳካት የሚያስችለን አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመሥረት ተገድደናል " ብለዋል።

የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ዜና
👍25😁311👎1
"ስዩም ተሾመ የተባለውን ግለሰብ የፌደራል ፖሊስ ማቅረብ ካልቻለ እና ስማችንን ማጉደፍ የሚቀጥል ከሆነ ስራችንን ልናቆም እንገደዳለን"- የከፍተኛ የፍርድ ቤት ዳኞች

- ፌደራል ፖሊስ ለሶስተኛ ግዜ አክቲቪስቱን ማግኘት አልቻልኩም ብሏል፣ ዳኞች በበከላቸው ለፍትህ ስርዐቱ ያለውን ንቀት ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል

(መሠረት ሚድያ)- ስዩም ተሾመ የተባለው አክቲቪስት የአቶ ዮሐንስ ቧያሌው እና የአቶ ክርስቲያን ታደለን የክስ ሂደት አስመልክቶ በችሎቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እየፈጠረ ነው በሚል ፍርድ ቤቱ ግለሰቡን ሥነ-ሥርዓት እንዲያሲዘው መጠየቃቸውን አስመልክቶ በቅርቡ መዘገባችን ይታወሳል።

ጉዳዩን እየተመለከተው የሚገኘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሽብር ወንጀል ችሎት አክቲቪስቱ ቀርቦ መልስ እንዲሰጥ ለፌደራል ፖሊስ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።

ይሁን እንጂ ስዩም ተሾመ የተባለውን ግለሰብ በዛሬው እለትም ለሦስተኛ ጊዜ የፌደራል ፖሊስ ግለሰቡን አላገኘሁትም በሚል ምላሽ ሰጥቷል።

የችሎቱ ዳኞች በበኩላቸው "የፌደራል ፖሊስ ግለሰቡን ለደህንነቱ ሲባል እጀባ እያደረገለት እንደሆነ ይታወቃል።ነገር ግን ፍርድ ቤቱ እንዲያቀርበው ትዕዛዝ ሲደርሰው አላገኘሁትም የሚል ምላሽ መስጠቱ በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ያለውን ንቀት የሚያሳይ ነው" ብለዋል።

አክለውም "ግለሰቡ መሀል አዲስ አበባ ተቀምጦ የፍርድ ቤቶችን ዳኞች ስም ሲያጎድፍ እየዋለ ነው። ከችሎቱ አቅም በላይ ሆኗል። ስለዚህ የፍርድ ቤቱ የበላይ አመራሮች ጉዳዩን ለማስቆም አለመሞከራቸው ያሳዝናል" ብለው በዛሬው ችሎት ላይ እንደተናገሩ የመሠረት ሚድያ ምንጮች ጠቁመዋል።

"አሁንም ግለሰቡ በፖሊስ ተይዞ ካልቀረበ እና የዳኞችን ስም የሚያጎድፍ ከሆነ ስራችንን ለማቆም እንገደዳለን" ሲሉ ተናግረዋል።

አቤቱታውን ያቀረቡት አቶ ዮሐንስ ቧያሌው በበኩላቸው "የዓቃቢ ሕግ ምስክሮች ለደኅንነታቸው ሲባል የስም ዝርዝራቸው እንዳይደርሰን ተከልክለን እያለ በዓቃቢ ሕግ አቶ ኢዮሲያድ አበጀ በኩል ለአቶ ስዩም ተሾመ ተሰጥቶት በማሕበራዊ ሚዲያ ማን እንደ ሚመሰክርብን ነግሮናል። ፍርድ ቤቱ የሚቀጣንንም ቅጣት ከወዲሁ ግለሰቡ እየነገረን ነው። እኛ በሕግ ቁጥጥር ስር እያለን ይሄ ሁሉ ዘመቻ ሲፈፀምብን ፍርድ ቤቱ ለምን ማስቆም አልቻለም?" ሲሉ አቤት ብለዋል።

ችሎቱ በበኩሉ "አሁን ጉዳዩ ከእናንተ ወጥቶ የፍርድ ቤቱ ጉዳይ ሆኗል። ከዚህ ችሎትም አልፎ አጠቃላይ የፍትሕ ሥርዓቱን የሚመለከት እየሆነ ነው። ለፌደራል ፖሊስ ደጋግመን መፃፋችንን ታውቃላችሁ። ማቅረብ የሚችለው ፖሊስ ነው። ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ካልፈፀመ የፍትሕ ሥርዓቱ ጥያቄ ውስጥ እንዳለ ይጠቁማል። ለጊዜው ይሄ ችሎት ማለት የሚችለው ይህንን ብቻ ነው" ሲሉ ዳኞች በምሬት ተናግረዋል።

የፌደራል ፖሊስ ለአራተኛ ጊዜ ስዩም ተሾመን አስገድዶ ፍርድ ቤት እንዲያቀርብ ችሎቱ ለሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍66😁25😭96
Forwarded from YeneTube
🌏IAT & IAIC INTERNATIONAL STUDENT FAIR🌎

Ready to study abroad and change your life?

🎓This is your chance to meet top university representatives from:

USA 🇺🇸 Canada 🇨🇦 Sweden 🇸🇪
Germany 🇩🇪 France 🇫🇷 Finland 🇫🇮 Denmark 🇩🇰 and more!

📆 May 3 & 4
🕐 3:00 - 10:00 (LT)
📍Ghion Hotel

Don’t forget to bring:
🪪Passport or Birth certificate
📚Transcripts or Student copy

Entrance Fee: FREE!!

💡Opportunities:
- Study loan options
- Learn about the scholarships offered

🏆Don’t miss this golden opportunity to take your future global!

🆓No entrance fee — just register now!

Click the link below to book your spot: 🔗
https://forms.gle/81ZueGK5d9R9Cg9P6
👍5
Forwarded from YeneTube
⭐️ ⭐️ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ።  ⭐️ ⭐️

የበዓል ስጦታ በማይታመን ዋጋ!!!

📍 ሳር ቤት ላይ አፖርትመንቶችን

በካሬ 64,200 ብር ብቻ

ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ

ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ አፖርትመንቶችን

ለመኖሪያ ምቹ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት አዋጭ!!!

ታድያ ይህ እድል እንዳያመልጥዎ
ፈጥነዉ ይደዉሉ!!!

+251 950 05 56 55

ወይም በቴሌግራም

TG  @Davehomes

What’s up https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1
👍53
🇪🇹በአምናው በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የደረሰው መኪና አደጋ በቁጥር ሲገለፅ;

👉3,111 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አልፏል;

👉በቀን በአማካኝ 9 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል;

👉67, 633 ተሽከርካሪዎች ወደ ሃገር የገቡ ሲሆን 46, 571 ተሽከርካሪዎች ላይ አደጋ ደርሷል;

👉ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል;

👉68 በመቶ የተከሰቱት አደጋዎች በአሽከርካሪዎች ጥፋት ነው።
😭18👍91👎1
የተባበሩት_አረብ_ኤምሬትስ #ቢትኮይን ኩባንያ በ #ኢትዮጵያ የማይኒንግ አቅሙን በ52 ሜጋ ዋት ኣሳደገ

የተባበሩተ አረብ ኤምሬትስ የቢትኮይን ማይኒንግ ኩባንያ የሆነው ፎኒክስ ግሩፕ፤ በኢትዮጵያ ባለው የማይኒንግ አቅም ላይ 52 ሜጋ ዋት ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል።

ኩባንያው ትናንት ሚያዚያ 21 ቀን 2017 እንዳስታወቀው፤ አዲስ ተግባራዊ ካደረገው ጭማሪ ጋር በኢትዮጵያ የፎኒክስ የቢትኮይን ማይኒንግ አቅም 132 ሜጋ ዋት ደርሷል። የኩባንያው አጠቃላይ አቅም አሁን ከ500 ሜጋ ዋት በላይ መሻገሩ ተገልጿል።

የፎኒክስ ተባባሪ መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሙናፍ አሊ፤ የኩባንያው ስትራቴጂ "የተትረፈረፈ እና ዝቅተኛ ኃይል ወጭ ያላቸውን ዋና ዋና አካባቢዎች ማገኘት ላይ የተመሠረተ ነው" ብለዋል።

"በኢትዮጵያ ያደረግነውን የቅርብ ጊዜ መስፋፋታችን የመሳሰሉ ተነሳሽነቶች ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው፣ ዛሬ ከፍተኛ ዋጋ በመፍጠር ብቻ ሳይሆን አቋማችንን በማጠናከር ላይም ይገኛሉ" ሲሉም መናገራቸውን ኮይንቴሌግራፍ ዘግቧል።

ይህ ማስፋፊያ ዜና የተሰማው የ #አቡ_ዳቢው ክሪፕቶማይኒንግ ኩባንያ ፎኒክስ ግሩፕ የ80 ሜጋ ዋት ኃይል ግዥ ስምምነት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር መፈራረሙን ተከትሎ ነው። በወቅቱ ኩባንያው በ2025 ሁለተኛው ሩብ አመት ስራ እንደሚጀምር ገልጿል።

ፎኒክስ ኩባንያ በአቡዳቢ ኢንተርናሽናል ሆልዲንግ ኩባንያ (IHC) የሚደገፍ ሲሆን፣ በመላው #ኤምሬትስ#አሜሪካ እና #ካናዳ ውስጥ የክሪፕቶ ማይኒንግ ስራዎችን ያከናውናል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍373👎2😁1
ኢትዮጵያ በወጪ ንግድ ታሪኳ ከፍተኛ የሆነ ገቢ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ማግኘቷ ተነገረ።

በጊዜ ማዕቀፉ ከ5.3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ከወጪ ንግድ ተገኝቷል ተብሏል።ኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ከ5.3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ከ ወጪ ንግድ ማግኘቷ ተነግሯል።

ይህን ያህል ገቢ ሲገኝ በኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ታሪክ የመጀመሪያው እንደሆነ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሣሁን ጎፌ ተናግረዋል።በቢሾፍቱ እየተካሄደ ባለው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ዘርፍ የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ነው ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ታሪክ ከፍተኛው ገቢ ነው ያሉት።

በ2016 ሙሉ የበጀት ዓመት #ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ ያገኘችው 3 ነጥብ 8 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደነበር በጊዜው ተነግሯል።በቀዳሚው የ2015 ሙሉ የበጀት ዓመት ደግሞ 3.7 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር መገኘቱ ይታወሳል።ኢትዮጵያ ያደረገችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ከወጪ ንግድ የሚገኘው ገቢ በየጊዜው ዕድገት እንዲያሳይ ማገዙ ተደጋግሞ ይጠቀሳል።

ማሻሻያውቅ የላኪዎችን የረጅም ጊዜ ጥያቄ የመለሰና በዘርፋ ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ነው ሲል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተናግሯል።ቀደም ሲል ግን ዘርፉ የተወሳሰቡ ችግሮች ያሉበት ሆኖ ቆይቷል።

የምርት ጥራት መጓደል ፤ የመዳረሻ ቦታዎች ማነስ ፤ እሴት ተጨምሮባቸው የሚላኩ ምርቶች ብዙ አለመሆን ፤ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እና አለም አቀፍ ጉዳዮች የዘርፉ ችግሮች ተብለው በተደጋጋሚ ሲጠቀሱ የቆዩ ናቸው፡፡ህገ ወጥ ንግድና በዘርፉ የተሰማሩ አካላት የስነ ምግባር ጉድለቶችም የዘርፉ ተጨማሪ ምክንያቶች በሚል ይነሳሉ ቡና ፤ የጥራጥሬ እና የቅባት እህሎች እንዲሁም የቁም እንስሳት ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ልካ ገቢ ከምታገኙባቸው መካከል ሲጠቀሱ ወርቅ እና ጫትም ሌሎቹ ናቸው፡፡

በዘጠኝ ወሩ የተገኘው ገቢ ኢትዮጵያ ከውጪ ለምትገዛቸው ምርቶች ከምታወጣው ዶላር አንጻር ሲታይ ግን አሁንም አነስተኛ የሚባል ነው፡፡ነዳጅ፣ የአፈር ማደበርያ እና የተለያዩ ምርቶች ከውጭ ለማስገባት በየዓመቱ በአማካይ 13 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደምታወጣ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
😁33👍202👀1
YeneTube
Photo
#Update

ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በመኖሪያ ቤታቸው ተአቅበው እንዲቆዩ ቋሚ ሲኖዶስ ወሳኔ አሳለፈ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከቤተክርስቲያኗ የነገረ ማርያም አስተምህሮ ውጪ በፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር አዳራሽ የሰጡትን ትምህርትና በማኅበሩ ሚዲያ የተላለፈበትን ሁኔታ በተመለከተ በዛሬ መደበኛ ጉባኤ ተወያይቶ ለመወሰን በያዘው ቀጠሮ መሰረት ውይይት ካደረገ በኋላ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም ፦

1. ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማህበር በተለያዩ ጊዜያት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮ ውጪ በሚዲያው ያስተላለፈው የስሕተት ትምህርት የቤተክርስቲያኗን አባቶች፣ ሊቃውንቱንና መላው ሕዝበ ክርስቲያኑን ያሳዘነ በመሆኑ በማህበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ በኩል ጊዜያዊ የእገዳ ደብዳቤ እንዲደርሰው እና በመምሪያው በኩል አስፈላጊው ጥብቅ ክትትል እንዲደረግ ሆኖ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ መስጠት ይቻል ዘንድ 5 አባላት ያሉት ኮሚቴ እንዲቋቋም አድርጓል።

ቋሚ ሲኖዶስ ያቋቋማቸው አጣሪ ልዑካን አጠቃላይ የማህበሩን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እና በሚዲያው ያስተላለፋቸውን የስህተት ትምህርቶች በተመለከተ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና ከማህበራት ምዝገባ፣ ቁጥጥርና ክትትል መምሪያ ጋር በመነጋገር በሚገባ መርምርውና አጣርተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከውሳኔ ሐሳብ ጋር ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርቡ ወስኗል።

2. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል “ ማርያም ቤዛዊተ ዓለም ” አትባልም በማለት ከቤተ ክርስቲያኗ የነገረ ማርያም አስተምህሮ ውጪ የሰጡት ሕጸጽ ያለበት ትምህርት በሊቃውንት ጉባኤ በኩል በሚገባ ተመርምሮና ተጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጋር ለቋሚ ሲኖዶስ በአስቸኳይ እንዲቀርብ ብፁዕነታቸውም ጉዳዩ ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በተአቅቦ እንዲቆዩ ወንሷል።

3. ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት እና ብፁዕ አቡነ በርናባስ የደቡብ ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ያስተላለፏቸው የስሕተት ትምህርቶችና በሌሎችም መምህራን የተላለፉ ነቀፋ ያለባቸው ትምህርቶች ካሉ የሊቃውንት ጉባኤ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ አንጻር በሚገባ መርምሮና አጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርብ ወስኗል።

4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኝ ብዙኃን ስርጭት ድርጅት ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማህበር ሚዲያ የአየር ሰዓት የሰጠበትን ዝርዝር ሁኔታና ከማኅበሩ ጋር በተያያዘ አየር ላይ ያዋላቸውን ትምህርቶች የሚያሳይ ሪፖርት እንዲያቀርብ እንዲደረግ ወስኗል።

መረጃው የቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

@Yenetube @Fikerassefa
👍98😁25👎154
ተከሰሱ

18 ከፍተኛ የትግራይ አመራሮች በዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሰሱ

ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤልን ጨምሮ 18 ከፍተኛ የትግራይ የፖለቲካ እና የጦር መሪዎች በፌደራል መንግስት በተሾሙ 64 የጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች እና ሰራተኞች ላይ ከጥቅምት 2013 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 2015 ዓ.ም ድረስ በነበረው የትግራይ ደም አፋሳሽ ጦርነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

ሚያዝያ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና ለጠቅላይ የምርመራ መምሪያ የቀረበው የጽሁፍ ክስ እንዳመለከተው የተጠቀሱት ተከሳሾች በጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮች እና ሰራተኞች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል።

ክሱ የቀረበው በአቶ አበራ ንጉስ የተባሉ የህግ ምሁር እና ጠበቃ እንዲሁም ከጥቅምት እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም በፌደራል መንግስት በተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር የፍትህ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ያገለገሉ ግለሰብ ናቸው።

@Yenetube @Fikerassefa
😁37👍282
ተጨማሪ ⤴️

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን
ለወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ

አዲስ አበባ
😁26👍86🔥3👀1