#ትሊዴፓ
" ከብልጽግና ጋር ልክ እንደሌሎቹ በአገር ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ተባብሮ ለመሥራት ይችላል እንጂ የሚያገናኘው ነገር የለም፤ ገለልተኛ እና ነጻ ፓርቲ ነው " - የቀድሞ የህወሓት አመራር
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ከህወሓት የተከፈለው ቡድን አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም በሂደት ላይ መሆኑን ከአመራሮቹ መካከል አንዱ ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ገልጸዋል።
የፖለቲካ ፓርቲው በሊብራል ዴሞክራሲ ጽንሰ ሃሳብ የሚመራ ሲሆን " ትግራይ ሊብራል ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ " በማለት ለመጠራት ውስኗል።
" ስሜ አይጠቀስ " ያሉ አንድ የቀድሞ የህወሓት አመራር ስለ ፓርቲው ምስረታ ምን አሉ ?
- " የፓርቲው ስያሜ የፖለቲካ ፓርቲውን ለመመሥረት በእንቅስቃሴ ላይ ባሉ ሰዎች የተመረጠ እንጂ ከምርጫ ቦርድ እውቅና ስላላገኘ ጉባዔ ሲካሄድ ሊቀየር ወይንም ሊሻሻል ይችላል። "
- " የህወሓት ሕጋዊነት ስለሚያበቃ የህወሓት የፖለቲካ ዓላማዎችን ለማሳካት የሚያስችለን አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመሥረት ተገድደናል። "
- " የፓርቲው ሕገ ደንብ እና ፕሮግራሞቻችን አርቅቀን ጨርሰናል። "
- " አሁን ላይ የደጋፊዎችን ፊርማ በማሰባሰብ ላይ እንገኛለን። "
- " የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች ገና ስላልተሟሉ እስካሁን ድረስ ለቦርዱ በይፋ የቀረበ ጥያቄ የለም። "
- " የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ቡድኑ ለምዝገባ እየሄደበት ያለውን ሂደት ያውቃል። "
- " ፓርቲው ክልላዊ ፓርቲ ነው። ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በግንቦት የመጀመሪያ ወር ላይ ቅድመ እውቅና እናገኛለን ብለን እንጠብቃለን። "
- " የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአንድ ዓመት ጊዜ ካበቃ በኋላ ክልላዊ መንግሥትን ለመመሥረት በሚደረገው ምርጫ እንሳተፋለን። "
- " ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እውቅና ካገኘን በኋላ ከባለሀብቶች እስከ የቀን ሠራተኞች ድረስ በአባልነት እና በአመራርነት ተቀላቅለው ሊሳተፉበት ይችላሉ። "
- " ትግራይ ሊብራል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ከብልጽግና ጋር ልክ እንደሌሎቹ በአገር ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ተባብሮ ለመሥራት ይችላል እንጂ የሚያገናኘው ነገር የለም፤ ገለልተኛ እና ነጻ ፓርቲ ነው። "
የትግራይ ሊብራል ዴሞክራቲክ ፓርቲ እየመሠረቱ ካሉተ አንጋፋ ሰዎች መካከል ፦
• የቀድሞ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣
• የህወሓት ፖሊት ቢሮ አባል የነበሩት እና የትዕምት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በየነ መክሩ
• ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት እንደሚገኙበት ታውቋል። (ፕሮፌሰር ክንደያ በቅርቡ በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል)
በሁለት ተከፍሎ እርስ በእርሱ ሲካሰስ የቆየው ህወሓት የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው ቀነ ገደብ ጉባዔ ማካሄድ ባለመቻሉ ከፓርቲነት ሊሰረዝ እንደሚችል ቦርዱ ማስታወቁ ይታወሳል።
የመሰረዝ አደጋ የገጠመው በደብረፂዮን (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ተደራድሮ የፕሪቶሪያ ስምምነትን እንደፈረመ ድርጅት እንደ አዲስ በቦርዱ መመዝገቡ ተገቢ አለመሆኑን ሲገልጽ ቆይቷል።
የህወሓት መሰረዝ ስጋት የፈጠረባቸው በአቶ ጌታቸው የሚመራው የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ከሳምንታት በፊት ባወጡት መግለጫ በደብረፂዮን (ዶ/ር) ለሚመራው ቡድን በጋራ ጉባዔ ለማካሄድ ጥሪ አቅርበው የነበረ ቢሆንም በጎ ምላሽ አለማግኘታቸውን ገልጸዋል።
በመሆኑም " የህወሓት ሕጋዊነት ስለሚያበቃ የህወሓት የፖለቲካ ዓላማዎችን ለማሳካት የሚያስችለን አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመሥረት ተገድደናል " ብለዋል።
የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ዜና

👍25😁3❤2⚡1👎1