YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ፖሊስ የአዲስ ስታንዳርድ ጋዜጠኞችን ለእስር መዳረጉን እና የኤሌክትሮኒክስ ንብረቶችን መውሰዱን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

በእስር ላይ የነበሩ የተቋማችን ሰራተኞች ምሽት ላይ ከተለቀቁ በኋላ ንብረቶቻችሁ ከማክሰኞ ሚያዚያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በኋላ ሊመለሱላችሁ ይችሉ ይሆናል ተብለናል።

ተቋማችን አዲስ ስታንዳርድ ሚዲያ በግልጽ ለህዝብ ማሳወቅ የሚፈልገው የተቋማችን ዋነኛ የዲጂታል መገልገያችን (main digital credentials) ምንም አይነት ጥቃት እንዳይደርስበት በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲገኝ ያደረግን መሆኑን ነው።

ነገር ግን ከዚህ ውጭ ፖሊስ ባካሄደው ብርበራ በግዳጅ ከተወሰዱብን የኤሌክተሮኒክስ እቃዎች በተለይም ከስልኮቹ እና ኮምፒዩተሮቹ በተናጠል የሚላኩ ማናቸውም መልዕክቶች፣ ኢሜይሎች እንዲሁም ግንኙነቶች ተቋማችንን እንዲሁም ሰራተኞቻችንን የማይወክሉ መሆናቸውን ነው።

በተቋማችን ላይ ፖሊስ ብርበራ ካካሄደ በኋላ ባሉት ጊዜያት እነዚህ ኮምፒዩተሮች እና ስልኮች የሚገኙት በጸጥታ ሀይሎቹ እጅ ሲሆን በእነዚህ ኮምፒዩተሮች እና ስልኮች ምን እየተከናወነባቸው እንደሆነ የተረጋገጠ ነገር መግለጽ አንችልም።

ሆን ተብሎ በፋሲካ ዋዜማ እንዲህ አይነት ድርጊት በተቋማችን ላይ የተፈጸመው አፋጣኝ ምላሽ እንዳንሰጥ እና ሰራተኞቻችን ግራ እንዲጋቡ ለማድረግ መሆኑን መረዳት አያዳገትም።

በዚህ አጋጣሚ ህጋዊ እና ሰላማዊ የሆነ አካሄድን አሟጦ በመጠቀም የሰራተኞቻችን ደህንነት እና የኤሌክተሮኒክስ ንብረቶቻችንን ያለምንም ጥቃት መመለስ ለማረጋገጥ እንደምንሰራ ለማሳወቅ እንወዳለን።

በዚህ ፈታኝ ጊዜ የሚዲያ ተቋማችን ወዳጆች ሁኔታዎቹን እንድትረዱልን እያሳሰብን፣ ቀጣይነት ላለው ድጋፋችሁ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

በየጊዜው የሚኖሩ ሁኔታዎችን እየተከታተልን እንደምናሳውቅ እንገልጻለን።


@Yenetube
👍548😭5
ድምጻዊ ያሬድ ነጉ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ያሉ ታራሚዎችን ጎበኘ

ድምጻዊ ያሬድ ነጉ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ያሉ ሴት ታራሚዎችን ለፋሲካ በዓል መጎብኘቱን ዳጉ ጆርናል ከአርቲስቱ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ተመልክቷል።

ያሬድ ነጉ ለታራሚዎች ሶስት ሰንጋ በሬ በማበርከት ነዉ በዓሉን ከነእርሱ ጋር ያከበረዉ። ያሬድ የሙዚቃ ስራም ለታራሚዎቹ አቅርቧል።

ያሬድ ነጉ ለታራሚዎቹ ያቀረበዉ የሙዚቃ ድግስ በራሱ የዩቲዩብ ገጽ ላይ ተለጥፏል።
@Yenetube @Fikerassefa
71👍27😁12👀3
አርቲስት ገነት ንጋቱ :- በፀሎት አስብኑን ይህው በትንሳኤው እለት በልጆቻችን ፊት ድጋሚ በሰርግ ተጋብተናል::

ሰርግ ❤️💍

ከ14 ዓመት መለያየት በኃል አርቲስት ገነት ንጋቱ እና አርቲስት ሙሉጌታ ጀዋሬ ዛሬ

* በልጆቻቸው
* በጎደኞቻቸው እና
* በዘመድ አዝማድ

ፊት ድጋሚ ተሞሽረዋል::

ሁሉቱም በማልቀስ ደስታቸውን የገለፁ ሲሆን ሁሉም ነገር ለፈጣሪ ሰጥተን ድጋሚ ትዳርን አንድ ብለን ጀምረናል ያሉት ጥንዶች መልካም ምኞታችሁን ተመኙልን ብለዋል::

ብዙ ኢትዮጵያውያን ሲፍልጉ የነበረው
አንድነት አሁን እውን ሆኗል::

* አይለያችሁ ጥንዶች

* መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ

* መልካም የትዳር ዘመን
👍222😁5521👎8🔥3
Forwarded from YeneTube
⭐️ ⭐️ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ።  ⭐️ ⭐️

የበዓል ስጦታ በማይታመን ዋጋ!!!

📍 ሳር ቤት ላይ አፖርትመንቶችን

በካሬ 64,200 ብር ብቻ

ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ

ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ አፖርትመንቶችን

ለመኖሪያ ምቹ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት አዋጭ!!!

ታድያ ይህ እድል እንዳያመልጥዎ
ፈጥነዉ ይደዉሉ!!!

+251 950 05 56 55

ወይም በቴሌግራም

TG  @Davehomes

What’s up https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1
👍121
ድንገተኛ ሞት

ሁሉም ዜሮ ዜሮ በሚለው ዘፈኑ የሚታወቀው አርቲስት ሰለሞን በዛሬው እለት ህይወቱ ማለፉን የመረጃ ምንጮቻችን ከወደ አሜሪካ ገልፀውልናል።

ኑሮውን በሃገረ አሜሪካ  በአትላንታ ከተማ አድርጐ የነበረው ሰለሞን የፋሲካ በዓልን ከቤተሰቦቹ ጋር ካሳለፈ በኋላ አመሻሽ ላይ ትንሸ ህመም ተሰማችኝ ብሎ ወደ ሆስፒታል እንደሄደና በዛው ህይወቱ እንዳለፈ አክለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
😭45👍224😁2👀1
መኖሪያ ቤት ሰብሮ በመግባት በሬ የሰረቀዉ ግለሰብ ከሶስት ቀን ፍለጋ በኃላ ከሰረቀዉ በሬ ጋር እጅ ከፍንጅ ተያዘ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዳውሮ ዞን ታርጫ ዙሪያ ወረዳ ጎዞ ሻሾ ቀበሌ ሚያዝያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ጨለማን ተገን በማድረግ  የግለሰብ መኖሪያ ቤት በሌሊት  ሰብሮ በመግባት በሬዉን ከታሰረበት ፈቶ በመውሰድና  ጫካ ዉስጥ ማሰሩን የዞኑ ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስም  ሚያዚያ 10 ቀን 2017 ዓ.ም በታርጫ ዙሪያ ወረዳ ኮይሻ ቀበሌ በሬዉን ከታሰረበት በመፍታት እየጎተተ ሲወስድ ፍለጋ ከወጡ የመንደሩ ነዋሪዎች ጋር ፊት ለፊት መገናኘቱን በማሳወቃቸው ግለሰቡ በቁጥጥር ስር መዋሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ  ተናግረዋል።

በዞኑ በዓል ወቅት ከሚፈፀሙ ወንጀሎች መካከል የእርድ እንስሳት በመሆኑ ህብረተሰብ ሊጠነቀቅ ይገባል ተብሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
😁23👍202
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በ88 ዓመታቸው አረፉ!

የሮም ፓትርያርክና የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ የነበሩት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በ88 ዓመታቸው ማረፋቸውን ቫቲካን በይፋ አስታውቋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በ2013 የቀድሞ ጳጳስ በነዲክቶስ 16ኛ ከሥልጣናቸው ከለቀቁ በኋላ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ ሆነው ተሹመዋል።

የእርሳቸውን ማረፍ በተመለከተ ካርዲናል ኬቨን ፋረል በቫቲካን በኩል በላኩት የሐዘን መግለጫ ላይ "ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ በከባድ ሐዘን ቅዱስ አባታችን ፍራንሲስ ማረፋቸውን ላሳውቃችሁ እወዳለሁ" ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የካቶሊክ አማኞች ዘንድ ያላቸው ፍቅርና ተቀባይነት ከፍተኛ እንደነበር ይታወቃል ።

@YeneTube @FikerAssefa
👍44😭19😁4👀21
በ3 ሀገራዊ ቋንቋዎች የመንጃ ፈቃድ ስልጠና እንዲሰጥ ተፈቀደ!

በአፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛ እና ሶማልኛ ቋንቋዎች የመንጃ ፈቃድ ስልጠና እንዲሰጥ መፈቀዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡ባለሥልጣኑ በሪፎርም ሒደት ውስጥ እንደሚገኝ እና ለረጅም ግዜ ሲጠየቁ የነበሩ በርካታ የተገልጋዮቻችን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እየፈታ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

ተቋሙ ከሚሰጣቸው በርካታ አገልግሎቶች ውስጥ አዲስ መንጃ ፍቃድ አገልግሎት አንዱ ሲሆን÷ የእጩ አሽከርካሪዎች የንድፈ ሃሳብ ስልጠና እና ፈተና በአማርኛ ቋንቋ ብቻ ሲሰጥ እንደነበር ተጠቅሷል።በአፍ-መፍቻ ቋንቋቸው በአማራጭነት ቢሰለጥኑ እና ቢፈተኑ የተሻለ ውጤት ሊያመጡ እንደሚችሉ ለረጅም ጊዜ ሲጠየቅ የነበረ የመልካም አስተዳድር ጥያቄ መሆኑን የባለስልጣኑ መረጃ አመልክቷል፡፡

ይህን ተከትሎም ተቋሙ በዝርዝር ጉዳዩን ፈትሾ የአካታችነት ጥያቄው አሳማኝ መሆኑንና የተሟላ የካሪኩለም ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁን በማንሳት ለመንጃ ፍቃድ ስልጠና በ3 ሀገራዊ ቋንቋዎች ስልጠና እንዲሰጥ መወሰኑን አስታውቋል፡፡በዚህም ፍቃድ ከሰጣቸው 137 ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ከአማርኛ በተጨማሪ በአፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛ እና ሶማልኛ ቋንቋዎች ለማሰልጠን ፍቃደኛ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ስለሆነም ሞዴል ተቋማት ለሆኑ 12 ማሰልጠኛ ተቋማት ፍቃድ መሰጠቱ ነው የተጠቆመው፡፡በሌላ በኩል ዕጩ አሽከርካሪዎች ከአማርኛ በተጨማሪ በቀረቡት የቋንቋ አማራጮች መሰልጠን እና መፈተን እንደሚችሉ ባለስልጣኑ አስገንዝቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍32😁115
በሀዋሳ ከተማ በህብረተሰቡ ጥቆማ በ82 እንጀራ አቅራቢ ነጋዴዎች ላይ እገዳ ማድረጉን የሀዋሳ ከተማ ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ

መምሪያው ‎ከባዕድ ነገር በተቀለቀሉና ጊዜው ያለፈባቸው ለምግብነት በሚውሉ ምርቶች ጋር በተያያዘ እየተደረገ ያለው የቁጥጥር ስራ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል።

‎የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባና ንግድን ገበያ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ አጋና ኔቶ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ‎ከህዝብ የሚመጡ ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ በዘመቻ በተሰራ ስራ 82  እንጀራ የሚያቀርቡ ነጋዴዎች ላይ እገዳ የተጣለ መሆኑንም ገልፀዋል።

‎ከነዚህ ውስጥ የ7 ናሙናዎች ወደ ኢትዮጵያ ምግብና መጠጥ ባለስልጣን የተላከ ሲሆን 5ቱ በሰው ልጅ ጤና ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ንጥረ ነገር መገኘቱን ተናግረዋል።‎በመሆኑንም አምስቱ ላይ ክስ የተጀመረ ሲሆን የሌሎችም ውጤት ተጠናቆ ሲመጣ እርምጃው የሚተገበር ይሆናል ሲሉ አቶ አጋና ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

‎ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶች እንደ በርበሬ፣ ጨው፣ ብስኩት፣ ለስላሳ መጠጦችንና ሌሎቸም ከ6 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት በ8 ወራት ውስጥ ከገበያ እንዲወጡ የተደረገ መሆኑን ሀላፊው ገልጸዋል።‎ህጋዊ ሆኖ የሚሰራን ነጋዴ እያበረታታን ህገ ወጥ የሆኑት ላይ የህግ የበላይነትን በማስከበር  በሸማቾች ጥበቃ አዋጅ 813/2006 ቀጣይነት ያለው ግንዛቤ በመፍጠር ጭምር ተጠናክሮ የሚሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

‎ደረቅ እንጀራ በሚያቀርቡ አምስቱ ነጋዴዎች ለጤና ጎጂ ንጥረ ነገር መገኘቱን አረጋግጠው ህብረተሰቡ በሚሰጠን ጥቆማ በመታገዝ  ጤናውንና ጥራቱን የጠበቀና የአገሎግሎት ጊዜው ያላለፈበትን ምርትን ለህብረተሰቡ የማቅረብ ስራ እንሰራለን ሳሉ አስረድተዋል።


@Yenetube @fikerassefa
👍45😁43👎1
ሴኔጋል የኤሌክትሪክ ዋጋን በ 50% ቀንሳለች
👉ይህ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ አሜሪካ ከምታስከፍለው ዋጋ ያነሰ ነው።


የሴኔጋል የኢነርጂ፣ ፔትሮሊየም እና ማዕድን ሚኒስትር ቢራሜ ሱሌዬ ዲዮፕ፣ የኤሌክትሪክ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን፣ በአንድ ኪሎዋት ሰዓት (kWh) ዋጋ ከ D14 ወደ D7 ዝቅ ማለቱን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ይህንን ስኬት ለዜጎች ቅልጥፍና እና ተደራሽነት ለማሳደግ የታለመው በኢነርጂ ሴክተር ውስጥ መዋቅራዊ ለውጦችን በማምጣት ነው ብለዋል ።

"እነዚህ ማሻሻያዎች የተነደፉት የምርት ወጪን ለመቀነስ፣ የስርዓት አፈጻጸምን ለማሻሻል እና ኃይል ለእያንዳንዱ ሴኔጋላዊ ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ ነው" ሲል ዲዮፕ ተናግሯል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍103😭149🔥1
Forwarded from HuluPay Community
በTelegram ላይ የተረጋገጠ ምልክት (Verified Checkmark) ለማግኘት የእርስዎን አካውንት አሁን Premium ያድርጉት
- 4GB እስከሆኑ ፋይሎችን ይጫኑ
- በፍጥነት ያውርዱ
- የእርስዎን online status ከሌሎች ይደብቁ
- እስከ 4 accounts ድረስ ይጠቀሙ
- ልዩ ስቲከሮች እና ኢሞጂዎች
🎭
- የድምፅ መልእክቶችን ጽሁፍ ያድርጉ
- ልዩ badges ያግኙ

- ማስታወቂያዎችን ያስወግዱ


አሁኑኑ ይቀላቀሉ እና የእርስዎን Telegram ተሞክሮ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግሩ! 🚀

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍83🔥1
በፑንትላንድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት የአልሸባብ ታጣቂዎች ሳይሆኑ አይቀሩም በተባሉ ታጣቂዎች ተገደሉ

በሱማሊያዋ ፑንትላንድ ራስ ገዝ የኢትዮጵያ ቆንስላ ውስጥ ተመድበው ይሠሩ የነበሩት ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ፋራህ አይዲድ ጃማ ከሱማሌላንድ ራስ ገዝ በቅርቡ በተነጠለችው "ኤስ ኤስ ካቱሜ" ግዛት ላስ አኖድ ከተማ ውስጥ በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው ማለፉን የሱማሊያ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

የግዛቲቷ ባለሥልጣናት፣ ግድያውን የፈጸሙት ለጊዜው ታጣቂዎች የአልሸባብ አባላት ሳይኾኑ አይቀርም የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው ዘገባዎቹ መባሉን ዳጉ ጆርናል ከዋዜማ ዘገባ ተመልክቷል። በዲፕሎማቱ ሕልፈት ዙሪያ የግዛቲቱ ባለሥልጣናት ምርመራ እያደረጉ እንደኾነ ተገልጧል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በዲፕሎማቱ ሕልፈት ዙሪያ በይፋ ያለው ነገር የለም።

የሱማሊያ ፌደራል መንግሥት፣ ከሶማሌላንድ መገንጠል እንፈልጋለን ያሉ የጎሳ ሚሊሻዎች ከደም አፋሳሽ ውጊያ  በኋላ የመሠረቷትን "ኤስ ኤስ ካቱሜ" ግዛት፣ ባለፈው ሳምንት የፌደሬሽኑ አባል ግዛት አድርጎ መቀበሉን ማወጁ ይታወሳል።

Via ዋዜማ
@Yenetube @Fikerassefa
👍46😭124🔥2
አዲሱ ህግ ፀደቀ

ተራ አስከባሪ ግብር እንዲከፍሉ ተወሰነ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የታክሲ ተራ አስከባሪ ማኅበራት ከገቢያቸው 20 በመቶውን ለመንግሥት እንዲሰጡ የሚያስገድድ ደንብ አጽድቋል።

ደንቡ ማኅበራቱ “ዝግ እና መደበኛ የባንክ አካውንት" እንዲከፍቱና ከሁለት ዓመት በኋላ “ወደ ሌላ የሥራ ዘርፍ እንዲሸጋገሩ” ግዴታ ይጥላል።

“የተርሚናል አገልግሎት አሠራርና ቁጥጥር” የተሰኘው ደንብ፣ ኢንተርፕራይዝ በማለት የሠየማቸው ማኅበራት የሚደራጁት በከተማዋ የሥራና ክህሎት ቢሮ መስፈርት መኾኑን ታውቋል።

ኢንተርፕራይዞቹ 30 በመቶ  “የግዴታ ቁጠባ” መቆጠብ፣ 50 በመቶውን በተንቀሳቃሽ የባንክ ሒሳብ ማስቀመጥና ያንድ ዓመት ውል መፈረም እንዳለባቸውም ይደነግጋል።

@Yenetube @Fikerassefa
😁88👍5513😭8👀1