YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
🚀 ቡስትግራም: ተመልካቾች እና ፎሎወሮች ያግኙ።

📣🔥👀📹👍


📹የቲክቶክ : ቪዲዮዎችዎ ብዙ ቪውስ፣ ላይኮች፣ ፎሎወሮች እና ኮመንቶች ያግኙ።

📷የኢንስታግራም: ፎሎወሮች፣ ላይኮች፣ ቪውስ እና ኮመንቶች ያግኙ።

📹የዩቲዩብ: ሰብስክራይበሮች እና ቪዲዮ ቪውስ በፍጥነት ያግኙ።

✈️ቴሌግራም: ቻነል መምበሮች፣ ፖስት ቪውስ፣ ላይኮች እና ሪአክሽኖች ይጨምሩ።

ቡስትግራም - የሶሻል ሚዲያ ገፅታዎን መገንባት አሁን በጣም ቀላል ሆኗል!`

📹 📷 📹 ✈️

LINK - 🔗 👉 OPEN BOOSTGRAM 🕯📈
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍15😁21
Forwarded from YeneTube
⭐️ ⭐️ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ።  ⭐️ ⭐️

የበዓል ስጦታ በማይታመን ዋጋ!!!

📍 ሳር ቤት ላይ አፖርትመንቶችን

በካሬ 64,200 ብር ብቻ

ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ

ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ አፖርትመንቶችን

ለመኖሪያ ምቹ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት አዋጭ!!!

ታድያ ይህ እድል እንዳያመልጥዎ
ፈጥነዉ ይደዉሉ!!!

+251 950 05 56 55

ወይም በቴሌግራም

TG  @Davehomes

What’s up https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1
👍31
ሁቲዎች የአሜሪካ አውሮፕላን አጓጓዦች መርከቦች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን አስታወቁ

ሁቲዎች በሁለት የአሜሪካ ኢላማዎች ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን የየመን ቡድን ወታደራዊ ቃል አቀባይ ያህያ ሳሬ ተናግረዋል። "በአሽኬሎን እና በኡሙ አል ራሽራሽ ሁለት ኢላማዎች ላይ ወታደራዊ እርምጃን በድሮኖች ወስደናል" ሲሉ ሳሬ ይፋ አድርገዋል። የአሜሪካን አውሮፕላን አጓጓዥ የሆኑት ትሩማን እና ቪንሰን እንዲሁም የባህር ኃይል መርከቦቻቸው ተመተዋል።

ቀደም ሲል የአሜሪካ ጦር በየመን ታዋቂ የሆነውን የገበያ ቦታ ላይ በቦምብ በመምታት ቢያንስ 12 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። የትራምፕ አስተዳደር ጥቃቱ ቡድኑ ለአለም አቀፍ የንግድ ልውውጥ ዋነኛ መተላለፊያ በሆነው በቀይ ባህር ላይ የሚደርሰውን ማስፈራሪያ እንዲያቆም ለማስገደድ ያለመ ነው ብሏል። እ.ኤ.አ. ከኖቬምበር 2023 ጀምሮ ሁቲዎች እስራኤል በጋዛ ላይ ላካሄደችው ጦርነት እና ከፍልስጤማውያን ጋር ለመተባበር ሲሉ ከእስራኤል ጋር በተገናኙ መርከቦች ላይ ጥቃት እየሰነዘሩ ይገኛል።

በጥር ወር በሃማስ እና በእስራኤል መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ከተካሄደ በመርከቦቹ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እንደሚያቆም አስታውቀው ነበር።
በሌላ መረጃ የእስራኤል ወታደሮች ባለፉት 24 ሰዓታት በፈፀሙት ጥቃት 39 ፍልስጤማውያንን ገድለዋል።

በእስራኤል የአየር ጥቃት በጋዛ ባለፉት 24 ሰዓታት ቢያንስ 39 ፍልስጤማውያን መሞታቸውንና ባለፉት 18 ወራት ጦርነት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 51,240 መድረሱን የጋዛ ሰርጥ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የሚኒስቴሩ መግለጫ እንዳስታወቀው ሌሎች 62 ሰዎች በደረሰባቸው የአካል ጉዳት ወደ ሆስፒታሎች የገቡ ሲሆን በአጠቃላይ የቆሰሉ ሰዎች ቁጥርን 116 ሺ 9 መቶ 31 አድርሶታል።


Via:- ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
👍215😭3
ለ20ኛ ጊዜ የተደረገው የግድያ ሙከራ ከሸፈ

በቡርኪናፋሶ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ ላይ ያነጣጠር ግድያ ከሽፏል።

የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው በርካታ ወታደራዊ አባላትን ያሳተፈ እንደነበር የሀገሪቱ የደህንነት ሚኒስትር ማሃማዱ ሳና አስታውቀዋል።

የሀገሪቱ የደህንነት አገልግሎት ተቋማት የሴራው አካል በሆኑ የቡርኪናቢ ወታደሮች እና የታጣቂ ቡድን መሪዎች መካከል የነበረውን ግንኙነት በመጥለፍ የሚገኙበትን ቦታ እና የወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ዝርዝር ሁኔታ እንዳገኙ ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ላይ የተሴረው መፈንቅለ መንግሥት በመጀመሪያ ሚያዝያ 8 ቀን ለማካሄድ ታቅዶ እንደነበር ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የውጪ ዜጎችን ጨምሮ ዘጠዥ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ከዚህ ጀርባ የፈረንሳይ እጅ እንዳለበት ተዘግቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍686🔥4
ሞቃዲሾ

ወደ ሞቓዲሾ እየገሰገሰ የነበረውን የአልሸባብ እንቅስቃሴ ለመግታት የቱርክ መከላከያ ሰራዊትን የያዙ 2 የጦር አውሮፕላኖች ሶማሊያ ሞቃዲሾ አርፈዋል።

በዚህም በመጀመሪያ 500 የቱርክ ኮማንዶ ከስፍራው ደርሰዋል።

ባለፉት ቀናት ውስጥ አልሸባብ በሶማሊያ ጦር ላይ ከፍተኛ የማጥቃት ዘመቻ መጀመሩን ተከትሎ የሶማሊያ ጦር የመፈራረሰ አደጋ ውስጥ መግባቱን የተመለከተችው ቱርክ በሁለት አንቶኖቭ አውሮፕላን 500 ሰራዊት ከበቂ መሳሪያ ጋር ወደ ሞቃዲሾ ልካለች።

@Yenetube @Fikerasefa
👍5911😁9👀2
በዓልን አስመልክቶ ስጦታ መስጠት የምትፈልጉ በውስጥ መስመር ያናግሩ።

@Fikerassefa ያናግሩን የተለዩ ፓኬጆች አሉን።
👍10👀1
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩቢዮ ያቀዱትን የአዲስ አበባ ጉብኝት ሰረዙ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በአዲስ አበባ እና በናይሮቢ ለማድረግ ያቀዱትን ጉብኝት መሰረዛቸው ተዘግቧል። ይህ የሆነው የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በዛሬዉ ዕለት ለአምስት ቀናት ጉብኝት ወደ ቻይና ካቀኑ ከሰዓታት በኋላ ነው።

እንደ አፍሪካ ኢንተለጀንስ ዘገባ ከሆነ ሩቢዮ በአፍሪካ በሚያደርጉት በዚህ የመጀመሪያ ጉብኝት የፀጥታ እና የንግድ ጉዳዮችን የሚሸፍን እንደነበር የተገለፀ ሲሆን አሁን ግን ላልተወሰነ ጊዜ አራዝመዋል።

ኢትዮጵያ በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በተጣለው አስከፊ የንግድ ታሪፍ  ከተጣለባቸው 185 ሀገራት መካከል አንዷ ነች። ከኤፕሪል 5 ቀን 2025 ጀምሮ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ለሚገቡ ሁሉም ምርቶች 10 በመቶ የመነሻ ታሪፍ መጣሉ ይታወቃል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍39😁863👀3
⭐️ ⭐️ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ።  ⭐️ ⭐️

የበዓል ስጦታ በማይታመን ዋጋ!!!

📍 ሳር ቤት ላይ አፖርትመንቶችን

በካሬ 64,200 ብር ብቻ

ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ

ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ አፖርትመንቶችን

ለመኖሪያ ምቹ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት አዋጭ!!!

ታድያ ይህ እድል እንዳያመልጥዎ
ፈጥነዉ ይደዉሉ!!!

+251 950 05 56 55

ወይም በቴሌግራም

TG  @Davehomes

What’s up https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1
4👍1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለካሜሩን ሃጅ ተጓዦች የተቀላጠፍ አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት ገለፀ

በካሜሩን የግዛት አስተዳደር ሚኒስትርና የሃጅ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች ጎብኝቷል።

ልዑኩ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ጋር ፍሬያማ ውይይት እንዳካሄደ አየር መንገዱ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ያወጣው መረጃ ያሳያል።

በውይይቱ ወቅት አየር መንገዱ ከካሜሩን ለሚመጡ የሐጅ ተጓዦች አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጧል። በተጨማሪም ወደ ያውንዴ እና ዱአላ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ የበለጠ አጠናከሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍16😁101
በስልጤ ዞን አገባሻለዉ ብሎ በማታለል አስገድዶ የደፈረዉ ግለሰብ በጽኑ እስራት ተቀጣ      

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን  በምስራቅ ስልጢ ወረዳ በሰዳጎራ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሱንዱዳ ተብሎ በሚጠራ አካበቢ ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓ ም አዋል ከይሬ  የተባለዉ ግለሰብ ስሜቱን ባልተገባ  መንገድ ለማርካት በማሰብ የግል ተበዳይ የሆነችዋን ወይዘሪት ራህመት ጠይብ የተባለችን ወጣት  አገባሻለው ብሎ እያታለለ ሰዓቱ እንዲመሽባት ካደረገ በኋላ ጨለማና ምቹ ሁኔታ መኖሩን በማረጋገጥ የአስገድዶ መድፋር ወንጀል ፈጽሞባት ጥሏት መሄዱን የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት እና ሚዲያ ጉዳዮች ዲቪዥን ሀላፊበ ኮማንደር ከድር ኤርጎሻ  ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቭዥን ጨገልፀዋል።

ይህን ወንጀል መፈፀሙን የሰሙ ግለሰቦች ለምስራቅ ስልጢ ወረዳ ፖሊስ ጥቆማ በማድረሳቸው ፖሊስም ፈጥኖ በመድረስ ተጎጂዋን  ለሕክምና በመላክ ስለድርጊቱ አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን በማሰባሰብና ተጠርጣሪውን ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር አዉሏል፡፡ ምርመራ አጣርቶ መዝገብ በማደራጀት ለምስራቅ ስልጢ ወረዳ ዓ/ህግ ያቀረበ ሲሆን ዓ/ህግም ከፖሊስ የቀረበለትን መዝገብ አይቶና ፈትሾ ተከሳሹ በ1996 ዓ/ም የወጣውን  የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.  የወንጀል ህግ አንቀጽ  620 ንዑስ አንቀፅ 2 (ሀ)  ላይ   የተደነገገውን   በመተላለፍ  በፈጸመው   የአስገድዶ መድፈር  ወንጀል ክስ መስርቶ  ለምስራቅ ስልጢ ወረዳ ፍ/ቤት አቅርቧል።  ፍርድ ቤቱ  ከአቃቤህግ የቀረበለትን ይህንን ሴትን ልጅ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል  ክስ ከተገቢ ማስረጃዎች ጋር  አገናዝቦ ከመዘነ በኋላ ተከሳሹ ጥፋተኛ መሆኑን ብይን ሰጥቷል።
  
በዚህም መሠረት  የምስራቅ ስልጢ ወረዳ ፍርድ ቤት ሚያዚያ 6 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት  ተከሳሹን ያርማል ሌሎችን ያስተምራል በማለት ተከሳሽ አወል ከይሬ በ6 ዓመት ከ 6ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲል ኮማንደር ከድር ኤርጎሻ የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት እና ሚዲያ ጉዳዮች ዲቪዥን ሀላፊ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍39👎65😭3😁2
🚀 ቡስትግራም: ተመልካቾች እና ፎሎወሮች ያግኙ።

📣🔥👀📹👍


📹የቲክቶክ : ቪዲዮዎችዎ ብዙ ቪውስ፣ ላይኮች፣ ፎሎወሮች እና ኮመንቶች ያግኙ።

📷የኢንስታግራም: ፎሎወሮች፣ ላይኮች፣ ቪውስ እና ኮመንቶች ያግኙ።

📹የዩቲዩብ: ሰብስክራይበሮች እና ቪዲዮ ቪውስ በፍጥነት ያግኙ።

✈️ቴሌግራም: ቻነል መምበሮች፣ ፖስት ቪውስ፣ ላይኮች እና ሪአክሽኖች ይጨምሩ።

ቡስትግራም - የሶሻል ሚዲያ ገፅታዎን መገንባት አሁን በጣም ቀላል ሆኗል!`

📹 📷 📹 ✈️

LINK - 🔗 👉 OPEN BOOSTGRAM 🕯📈
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2👍6🔥21
Forwarded from In Africa Together
🌏IAT እና IAIC ያዘጋጀው ታላቅ ኢንተርናሽናል የተማሪዎች ኢቨንት 🌎

በውጭ ሀገር ለመማር እና ህይወትዎን ለመቀየር ዝግጁ ኖት?

ከ አሜሪካ 🇺🇸 ካናዳ 🇨🇦 ስዊድን 🇸🇪 ጀርመን 🇩🇪 ፈረንሳይ 🇫🇷 ፊንላንድ 🇫🇮 ዴንማርክ 🇩🇰 እና ሌሎችም!

🎓የአለም ሀገራት የተውጣጡ የዮኒቨርሲቲ ተወካዮች በአካል የሚገኙበት

📆 ሚያዝያ 25 እና 26
🕐 ከ3:00 እስከ 10:00 ሰዐት
📍በጊዮን ሆቴል

አስፈላጊ ዶክመንቶች ፡-
🪪ፓስፖርት ወይም የልደት ሰርተፍኬት
📚ትራንስክሪፕት

💡ኢቨንቱ ላይ ከሚያገኟቸው መረጃዎች በጥቂቱ፡-
የብድር አማራጮች መረጃ የሚያገኙበት
ስለሚሰጡት ስኮላርሺፖ የሚያውቁበት

🏆ወደውጭ ሀገር ሄዶ የመማር ፍላጎቶትን ለማሳካት ይህን ወርቃማ እድል እንዳያመልጥዎ!

🆓 መግቢያ በነፃ - አሁኑኑ ይመዝገቡ!

ቦታዎን ለማስያዝ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ፡ 🔗 https://forms.gle/81ZueGK5d9R9Cg9P6
👍7😁1
ብርቱካን ተመስገንን ጨምሮ በሽብር ወንጀል ተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀን የክስ መመስረቻ ጊዜ ተፈቀደ

ፖሊስ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት እስካሁን በተጠርጣሪዎች ላይ ያሰባሰባቸውን መረጃዎች እና ቀሪ የምርመራ ሥራዎችን አጠናቅቆ አቅርቧል፡፡

ብርቱካን ተመስገንን አስመልክቶ በመገናኛ ብዙኃን ከተላለፈው ሐሰተኛ ዘጋቢ ፊልም ጋር በተያያዘ ብርቱካን ተመስገን፣ ነብዩ ጥዑመልሳን የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሥራ አስኪያጅ፣ ታሪኩ ኃይሌ የአዲስ ምዕራፍ ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ፣ ደረጀ ሉቃሌ፣ ኅሊና ታረቀኝ፣ ንጥር ደረጀ እና መታገስ ዓለሜ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወሳል።

በተጠርጣሪዎቹ ላይም ስልጣንን በኃይል ለመያዝ፣ የጦር መሣሪያ በመታጠቅ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ በመደራጀት፣ በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሰ ከሚገኘው ጽንፈኛና ፀረ ሰላም ቡድን አመራሮች ጋር በጥቅም በመመሳጠር፣ መንግሥት የሕዝብ ተቀባይነት እንዲያጣና ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ እንዲደረግበት በማሰብ፣ ተዋድደውና ተከባብረው በሚኖሩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መካከል ቅራኔ በመፍጠርና ወደ ግጭት እንዲገቡ ለማድረግ፣ በውጭ ሀገር ከሚገኝ የፀረ ሰላም የቡድን አመራሮች ጋር በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች በመገናኘት እና ተልዕኮ በመቀበል የሥራ ባህሪያቸውን እንደመልካም አጋጣሚ መጠቀም የሚሉ የምርመራ የጥርጣሬ መነሻዎች ለችሎቱ ቀርበዋል፡፡

የምርመራ ሥራውን በሰውና በሠነድ ማስረጃ በስፋት በማጠናከር የፎረንሲክ እና የቴክኒክ ምርመራዎችን በተሰጠው 12 ቀናት አጠናቅቆ ለዓቃቤ ሕግ ማስረከቡን ፖሊስ አስረድቷል።

የተከሳሽ ጠበቃዎች በበኩላቸው÷ ተጠርጣሪዎቹ  ቋሚ አድራሻ ያላቸው እና መረጃም የማያጠፉ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ የዋስትና መብታቸው ሊከበር ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

ዓቃቤ ሕግ ተጠርጣዎቹ የዋስትና መብት ቢፈቀድላቸው መረጃ ሊሰውሩ እንደሚችሉና ምስክሮችንም በጥቅም ሊደልሉብኝ ይችላሉ ሲል ተቃውሟል፡፡

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱም ጠበቆች ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለዓቃቤ ሕግ የ14 ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቅዷል፡፡

Via:- FMC
@Yenetube @Fikerassefa
👍27👎223😁2😭2🔥1👀1
በምዕራብ ኦሞ ዞን በተከሰተ የአባ ሠንጋ በሽታ ሰባት ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ፣ በሽታው የቤት እንስሳትንም ገድሏል

በደቡብ ምዕራብ #ኢትዮጵያ ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን በተቀሰቀሰ የአባ - ሠንጋ በሽታ ሰባት ሰዎችን ጨምሮ የቤት እንስሳት መሞታቸውን የዞኑ መስተዳድር አስታወቀ፡፡

የአባ - ሠንጋ በሽታው በምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ ኮካ በተባለ ቀበሌ ውስጥ የተከሰተው ከባለፈው ሀሙስ ጀምሮ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከዞኑ የአርብቶ አደር እና የጤና መምሪያ የተውጣጣ ቡድን ሚያዚያ 13 ቀን 2017 ዓ.ም በሽታው ታይቶበታል ወደተባለው አካባቢ መድረሱን የምዕራብ ኦሞ ዞን አርብቶ አደር መምሪያ አስታውቋል።

ቡድኑ ባደረገው ምርመራ በሽታው አባ-ሠንጋ / አንትራክስ / መሆኑን ማረጋገጥ መቻሉን የመምሪያው ሃላፊ አቶ በለጠ ግርማ መናገራቸውን ከጀርመን ድምጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በሽታው እስከአሁን በሰው ሕይወትና በእንስሳት ላይ ጉዳት ማድረሱንም ሃላፊው ገልጸዋል ያለው ዘገባው “በበሽታው 7 ሰዎች እና 15 የቤት እንስሳት መሞታቸውን ማረጋገጥ ተችሏል“ ማለታቸውንም አካቷል።

በሽታው ወደ ሌሎች አጎራባች ወረዳዎች እንዳይስፋፋ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ እየተሰጠ መሆኑን እና “አሁን ላይ በባለሙያዎች የህክምና መድኃኒት የመስጠት እና የእንስሳት ክትባት ሥራ መጀመራቸውን የአርብቶ አደር መምሪያ ሃላፊው መናገራቸውን ዘገባው አስታውቋል።

የዞኑ መስተዳድር በሽታውን በራሱ አቅም እየተከላከለ እንደሚገኝ እና በቀጣይ ሂደቱን በመገምገም ከክልል ድጋፍ የምንጠይቅበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል ሲሉ መናገራቸውን አመላክቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍144😭2
ኬንያ በ2025 የምስራቅ አፍሪካን ትልቁን ኢኮኖሚ በመሆን ኢትዮጵያን ልትቀድም ነው - አይኤምኤፍ

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ባወጣው አዲስ ትንበያ መሰረት ኬንያ በ2025 የምስራቅ አፍሪካ ትልቁን ኢኮኖሚ በመሆን ኢትዮጵያን ልትቀድም ትችላለች።

ትላንት የወጣዉ አዲሱ ትንበያው እንደሚያመለክተው የኬንያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) በ2025 ወደ 132 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ሲሆን ይህም የኢትዮጵያን 117 ቢሊዮን ዶላር ይበልጣል።

ይህ ትንበያ የወጣው የኢትዮጵያ ብር ምንዛሪ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መውደቁን ተከትሎ መሆኑ ተዘግቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍35😁17😭72👎1
የአሜሪካ ኢንባሲ ማስጠንቀቂያ ለኢትዮጵያውያን።

በቪዛዎ ከተፈቀደሎት ጊዜ በላይ ከቆዩ ወደፊት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለመጓዝ ቋሚ እገዳ ሊጣልቦትና በህግ ሊያስጠይቅ ይችላል።
የቆንስላ ኦፊሰሮች የኢሚግሬሽን ሙሉ ታሪክዎን ማግኘት ይችላሉ።  በተጨማሪም ከዚህ በፊት የተላለፉት የኢሚግሬሽን ሕግ ጥሰቶች ካሉም የቆንስላ ኦፊሰሮች ያውቃሉ።
ቪዛዎን በትክክል መጠቀም የእርስዎ ኃላፊነት ነው"ብሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍29😭10👎3😁32
በምሥራቅ ጎጃም በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው ታወቀ


(T.me/Yenetube) - ፈጣን የዜና ምንጭ

በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ሐሙስ ሚያዝያ 9/2017 ዓ.ም. በትምህርት ቤት ዙሪያ በደረሰ የድሮን ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ።

በዞኑ እናርጅ እናውጋ ወረዳ ገደብ በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ የትምህርት ቤት አጥር ለማጠር እና ቤት ለመሥራት 'ለልማት ሥራ' የወጡ "ሰላማዊ ሰዎች" በጥቃቱ መገደላቸውን ገልፀዋል።

የአካባቢው አስተዳደር ግን ጥቃቱ በአካባቢው ተሰብስበው በነበሩ የፋኖ ታጣቂዎች ላይ እንጂ በንፁሃን ነዋሪዎች ላይ አለመፈጸሙን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተፈጸመ ስለተባለው ጥቃት ክትትል እያደረገ መሆኑን አመልክቷል። ነዋሪዎች እንደተናገሩት "ተሰብስበው" በከተማዋ ያለው ገደብ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት አጥርን እያጠሩ በነበሩ የሰዎች ላይ ነው ጥቃቱ የተፈፀመው።
ጥቃቱ በተፈፀመበት አካባቢ በቅርብ ርቀት ላይ እንደነበሩ የተናገሩ ሌላ የዓይን እማኝ ወዲያው ጩኸት፣ ግርግር እና ድንጋጤ መፈጠሩን ጠቁመው "የሆነውን አናውቀውም" ሲሉ በቅፅበቱ የነበረውን ሁኔታ ገልፀዋል። እሳቸውን ጨምሮ ሥራ ላይ የነበሩ ሰዎች ጥቃቱ ወደተፈፀመበት አካባቢ ሲጠጉ "ሰው የሚባል አይለይም" ሲሉ ስለ ጉዳቱ ተናግረዋል።

"እንዳለ በሙሉ ጥቁር ነገር ነው የሆነው። አካባቢው በሙሉ ሰው የሚባል ነገር የለም። ከወደቀው ውስጥ የሚጮህ አለ፤ የሚንከባለል አለ። የተፈጠረው ነገር ይዘገንናል። ሰው ለሆነ እጅግ የሚዘገንን ድርጊት ነው" ብለዋል።

የፈረሰውን የትምህርት ቤቱን አጥር እያጠሩ እያለ ቀኝ እጃቸውን ተመትተው መቁሰላቸውን የተናገሩ ሌላ ነዋሪ "ከባድ ፍንዳታ" መከሰቱን ጠቅሰው "ብዙ ሰው ነው የተጎዳው" ብለዋል።

"ባሕር ዛፍ የሚቆርጥ፤ ሚስማር የሚመታ አለ፤ ማገር የሚቆርጥ አለ፤ የሚይዝ አለ" ሲሉ ማኅበረሰቡ መሰባሰቡን የገለፁ ሌላ የዓይን እማኝ የሟቾቹን ቁጥር "ብዛት ይኖረዋል" በማለት ገልፀዋል። አስከሬን ስለማንሳታቸው የተናገሩ ሌላ እማኝ ደግሞ አብዛኛው የጥቃቱ ተጎጂዎች ወዲያው ሕይወታቸው ማለፉን ገልፀው፤ ሟቾቹ በአብዛኛው ወጣቶች ናቸው ብለዋል።

ከ24 በላይ ቁስለኞችንም ወደ ሕክምና መወሰዳቸውን የገለፁት እማኞች፤ አብዛኞቹ በከተማዋ ወደሚገኘው ገደብ ጤና ጣቢያ ከደረሱ በኋላ ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

ከ70 በላይ አስከሬን አንስተው በባጃጅ ወደ ቤተ ክርስቲያን ማመላለሳቸውን የተናገሩ አንድ የዓይን እማኝ፤ ታዳጊዎችን እና ሽማግሌዎችን ጨምሮ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 120 እንደሚደርስ ገልፀዋል። "ከ115 እስከ 120 የሚሆን አስከሬን ነው የተቀበረው። ያልታወቀም ይኖራል ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም ድንጋጤ ውስጥ ስለነበርን" ብለዋል።

ሌላ የዓይን እማኝ በበኩላቸው 57 አስከሬን እስከሚነሳ ድረስ እንደነበሩ ጠቁመው የሟቾቹ ቁጥር ከ100 በላይ እንደሚሆን ገምተዋል። አስከሬኖቹ ላይ ከባድ ጉዳት በመድረሱ ሟቾችን መለየት ከባድ እንደነበር የተናገሩት እማኞች በዚህ ምክንያት እና በስጋት እስከ ቀትር 08፡00 ድረስ ገደብ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በጅምላ እንደተቀበሩ ገልፀዋል።

"አሞራ እንዳይበላቸው ቅበሩ ሲባል ማኅበረሰቡ በፍጥነት አምስት የሚሆን መቃብር ውስጥ ነው የቀበራቸው" ሲሉ አንድ ነዋሪ ተናግረዋል።

የመንግሥት ኃይሎች ጥቃቱ ከደረሰ በኋላ ወደ ከተማዋ መግባታቸውን ተከትሎ ስጋት ያደረባቸው አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች መሸሸታቸውን የተናገሩ አንድ ነዋሪ፤ ተጨማሪ ጥቃቶች መፈፀማቸውንም ጠቁመዋል።

ማኅበረሰቡ ከተረጋጋ በኋላ ለሟቾቹ ድንኳን እንደተጣለ እና ከቀናት በኋላ በአካባቢው "ፍራጅ" የሚባለው ማስተዛዘኛ መርሃ ግብር እንደተደረገም ነዋሪዎች ተናግረዋል። "ሰሞኑን ሲሸበር ነበር። ሕዝቡ በሙሉ ሽብር ላይ ነው ያለው" ሲሉ ዳግም የድሮን ጥቃት ይደርሳል በሚል የፋሲካ በዓልን በስጋት ማሳለፋቸውን "በዓል የሚባል ነገር የለም" ብለዋል።

"ከባድ ሐዘን ውስጥ ነው ያለው። በዓል ምንም አይመስልም ነበር። ለበዓል ከከተማ የሚመጡ ልጆች አልመጡም" ሲሉ አካባቢው በሐዘን ድባብ ውስጥ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ግጭት በ2015 ዓ.ም. መጨረሻ ከተቀሰቀሰ ወዲህ ከተማዋ በፋኖ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር እንደሆነች ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃቱ ሲፈፀም ግን የፋኖ ታጣቂዎች ከተማዋ ውስጥ እንዳልነበሩ እና በአካባቢው ግጭት እንዳልነበረ ጠቁመዋል።

ታጣቂዎቹ "አንዳንድ ሥራ ለመሥራት ካልመጡ በቀር ከተማው ውስጥ አይታዩም" ሲሉ አንድ ነዋሪ ተናግረዋል።
ነጋዴ እንደሆኑ የተናገሩ አንድ የዓይን እማኝ ሟቾቹ ንፁሃን ስለመሆናቸው ሲናገሩ "በርካቶቹን በንግድ ሥራቸው" የሚያውቋቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።

"የፋኖ አባላት ቢሆኑ [አስከሬን ሲነሳ] ታጣቂ እናገኝ ነበር። ፋኖዎችን እና ማኅበረሰቡን [ለይተን] እናውቃቸዋለን። [ፋኖዎች] በአንድ ላይ ነው የሚንቀሳቀሱት" ሲሉ ሌላ ነዋሪ ተናግረዋል።

ሌላ ነዋሪ በበኩላቸው "የተሰበሰው አጥር የሚያጥረው እና ቤት የሚሠራው ሰው በቀረፃው [የድሮን ቅኝት] የፋኖ ስብስብ ነው ተብሎ ታስቦ ይሁን ያወቅነው ነገር የለም። ምንአልባት ሲሰበሰብ ፋኖ ነው ተብሎ ታስቦ [ይሆናል] እንደዚያ ነው እኛ የተረዳነው" ሲሉ ጥቃት ሊፈጸም የቻለበትን ምክንያት ግምታቸውን ገልፀዋል።

የእናርጅ እናውጋ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሙሉ ጌቴ ንፁሃን ሰዎች ተገደሉ መባሉን "የጠላት ወሬ" ያሉ ሲሆን፤ እርምጃው "ፅንፈኛ" ያሏቸው የፋኖ ታጣቂዎች ላይ መወሰዱን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

"እዚህ አካባቢ ቁጥሩ በርከት ያለ የኃይል ስብስብ አለ። ሰብስበው ሥልጠና ጭምር [እንደሚሰጡ] መረጃው አለኝ። የትምህርት ቤት አጥር፤ ቤት ሥራ የሚባለው ነገር ማሳመሪያ ነው . . ." በማለት ንፁሃን በፍንጣሪም ቢሆን አልተገደሉም ሲሉ አስተባብለዋል።

የፋኖ ታጣቂዎች በበኩላቸው በወረዳው በስፋት እንደሚንቀሳቀሱ ጠቁመው ገደብ ከተማ አካባቢ ላይ ግን በወቅቱ "ምንም ዓይነት የታጠቀ ኃይል" አልነበረም በማለት በጥቃቱ የተገደለ አባል እንደሌላቸው ተናግረዋል።

አካባቢውን ለሥልጠና እንደማይጠቀሙት የተናገሩት የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ሰብሳቢ አቶ አስረስ ማረ ዳምጤ "ሁሉም ግድያው የተፈፀመባቸው ሲቪሊያን ናቸው። አንድም የታጠቀ ኃይል በቦታው ላይ አልነበረም" በማለት ግድያውን ማኅበረሰቡን ከማሸበር ጋር አያይዘውታል።

ምንጭ: ቢቢሲ አማርኛ

@Yenetube @Fikerassefa
😭66👍508👀3
ራሺያ ለቡርኪናፋሶ

የቡርኪናፋሶ መሪ በሆነው ኢብራሂም ትራኣሬ ላይ ከቀናት በፊት ለ19ኛ ጊዜ የተቀነባበረ የግድያ ሙከራ መደረጉን ተከትሎ ትራኦሬ ለራሺያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስቸኳይ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንዲደረግለት መጠየቁን እና ራሺያም የጦር መሳሪያ በአስቸኳይ ወደ ቡርኪናፋሶ ለመላክ ቁርጠኛ መሆኗን የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

(T.me/Yenetube) ፈጣን የዜና ምንጭ

የግድያ ሙከራው በፈረንሳይ የሚደገፍ በመሆኑ እና በሀገሪቱ የታጠቁ ቡድኖች ከፍተኛ ስጋት መፍጠራቸውን ተከትሎ ራሺያ ለቡርኪናፋሶ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንደምታደርግ ይጠበቃል።
ራሺያ እና ቡርኪናፋሶ በባለፈው ጥቅምት ወር በወታደራዊ ጉዳዮች በትብብር ለመስራት መስማማታቸው የሚታወስ ነው።
ትራኦሬ "ሀገሬ እና ህዝቤ ነፃ እስከሚወጣ ድረስ እዋጋቸዋለሁ" ብለዋል።


@Yenetube @Fikerassefa
👍12115🔥9