YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በሕብረተሰቡ ላይ ያልተገባ ክፍያ የሚጠይቁ ሕገ-ወጥ ጫኝ እና አውራጆች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ!

ከዚህ በፊት ሕብረተሰቡን ላልተገባ ግጭት እና ለከፍተኛ ወጭ ሲዳርጉ በነበሩ ሕገ-ወጥ ጫኝ እና አውራጆች ላይ በወጣው መመሪያና ደንብ መሠረት እርምጃ በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ሚደቅሳ ከበደ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ በከተማዋ የአገልግሎት አሰጣጡ የተሳለጠ እንዲሆን በሕገ-ወጥ ጫኝና አውራጆች ላይ ሕጋዊ እርምጃ በመወሰዱ በዘርፉ የተሰማሩ ግለሰቦች ቁጥር ቀንሷል፡፡

በዚህም አሰራት መሠረት ከሕብረተሰቡ ጋር ተግባብተው የሚሰሩ ሕጋዊ ጫኝና አውራጆችን መፍጠር መቻሉን አክለዋል።

"በዘርፉ ሕዝቡ እፎይ ያለበት አገልግሎት ቢሆንም፤ አሁንም በአንድ አንድ አካባቢዎች ከአቅም በላይ ገንዘብ በመጠየቅ ሕዝቡን የሚያማርሩ ሕገ-ወጥ ጫኝ እና አውራጆች መኖራቸውን ባደረግነው የዳሰሳ ጥናት አረጋግጠናል" ሲሉም አቶ ሚደቅሳ ለአሐዱ ገልጸዋል።

ሕጋዊ የሆነ ፍቃድ ያላቸው ጫኝና አውራጆች ሕግን ተላልፈው ሲገኙ፤ የጥፋት ደረጃው ተገምግሞ የወሰዱትን ፍቃድ እስከመሰረዝ ብሎም በሕግ ቁጥጥር ሥር የሚውሉበት ሁኔታ እንዳለም ጠቁመዋል።

ከከተማ ውጭ የሚሰራ ሥራ እና አሳቻ ሰዓትን ጠብቀው እየሰሩ ያሉ ሕገ-ወጥ ጫኝ እና አውራጆች በዘርፉ ላይ ተግዳሮት መሆናቸውን አስረድተዋል።ሁሉም ሰው ለሠላም ዘብ እንድቆም እና ሕብረተሰቡ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት መረጃን በመስጠት የጎላ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ የቢሮው ምክትል ኃላፊ ሚደቅሳ ከበደ ጠይቀዋል።

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
👍493😁3
🚀 ቡስትግራም: ተመልካቾች እና ፎሎወሮች ያግኙ።

📣🔥👀📹👍


📹የቲክቶክ : ቪዲዮዎችዎ ብዙ ቪውስ፣ ላይኮች፣ ፎሎወሮች እና ኮመንቶች ያግኙ።

📷የኢንስታግራም: ፎሎወሮች፣ ላይኮች፣ ቪውስ እና ኮመንቶች ያግኙ።

📹የዩቲዩብ: ሰብስክራይበሮች እና ቪዲዮ ቪውስ በፍጥነት ያግኙ።

✈️ቴሌግራም: ቻነል መምበሮች፣ ፖስት ቪውስ፣ ላይኮች እና ሪአክሽኖች ይጨምሩ።

ቡስትግራም - የሶሻል ሚዲያ ገፅታዎን መገንባት አሁን በጣም ቀላል ሆኗል!`

📹 📷 📹 ✈️

LINK - 🔗 👉 OPEN BOOSTGRAM 🕯📈
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1🔥75👍357
⭐️ ⭐️ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ።  ⭐️ ⭐️

የበዓል ስጦታ በማይታመን ዋጋ!!!

📍 ሳር ቤት ላይ አፖርትመንቶችን

በካሬ 64,200 ብር ብቻ

ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ

ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ አፖርትመንቶችን

ለመኖሪያ ምቹ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት አዋጭ!!!

ታድያ ይህ እድል እንዳያመልጥዎ
ፈጥነዉ ይደዉሉ!!!

+251 950 05 56 55

ወይም በቴሌግራም

TG  @Davehomes

What’s up https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1
👍13
የሻረግ ቅመማ-ቅመም 👌 
#ምርቶቻችንን ከ :-
🥣 ሸዋ ሾፒንግ 
🥣 በሽ ገበያ
🥣 ባምቢስ(ልዊስ)
🥣 ሎሚያድ
🥣 ጋራ ማርት
🥣 ዴይሊ ሚኒማርት
🥣 ጋራድ ሱፐርማርኬት
እና በሌሎች ሱፐር ማርኬቶች ያገኙናል። 

🥣 መልካም በዓል   / 2017 ዓ.ም 🥣
#ጥራት እና ዋጋ ቅናሽ መለያችን ነው !!
📲 0911 664775 / 0911 872827
👍31
በዘጠኝ ወራት ውስጥ  ከአንድ ሺህ ሰባት መቶ በላይ  አቤቱታዎችን  መቀበሉን የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ

በ2017 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት  ዉስጥ 2,890 አቤቱታዎችን  ለመቀበል  አቅዶ  1,716  አቤቱታዎች ብቻ ነው የቀረበልኝ ብሏል፡፡

እናም የዕቅዴን  60% ብቻ ነው ማሳካት የቻልኩት ሲል በ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱ  ገልጧል፡፡

በበጀት እጥረት ተቋሙን የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ ባለመሆኑ፣ የተቋሙ ነጻ የቅሬታ መቀበያ በሚፈለገው መልኩ አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑና የተቋሙ የማስፈጸም አቅም በበጀት፣ ቁሳቁስና የሰው ሀይል የተሟለ አለመሆን ለስኬቱ  ማነስ ምክንያት መሆናቸውን ጠቅሷል፡፤

ከቀረቡት  1,716 አቤቱታዎች ውስጥ 564  አቤቱታዎች ተቀባይነት ባለማግኘታቸው (በተቋሙ ስልጣን ስር የማይወድቁ ማለትመ በፍርድ ቤት የታዩ፣የወንጅል  ጉዲዮች ላይ የቀረቡ አቤቱታዎች በመሆናቸው)

ተገቢው የህግ ምክር አገልግሎት ተሰጥቷቸው ተሸኝተዋል ይላል ሪፖርቱ፡፡

469  አቤቱታዎች ደረጃቸውን ያልጠበቁ  ቀሪ 683 አቤቱታዎች  ደግሞ ምርመራ እንዲካሄድባቸው ለመርማሪዎች  የተመሩ መሆኑን ጣያችን ከሪፖርቱ ተመክልቷል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
👍131😁1
ጋዛ

ምንም ዓይነት ሰብአዊ እርዳታ ወደ ጋዛ አይገባም ሲሉ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ተናገሩ።

የእስራኤል ፖሊሲ ግልፅ ነው እናም ምንም ዓይነት ሰብአዊ እርዳታ ወደ ጋዛ አይገባም ሲሉ የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትስ በኤክስ ገፅ ላይ ባወጡት መግለጫ አጋርተዋል።

የሰብአዊ እርዳታ ወደ ጋዛ ሰርጥ እንዳይገባ መከልከል "ሀማስ ይህን ድጋፍ በህዝቡ ላይ እንዳይጠቀም ከሚከለክሉት ዋና የግፊት መሳሪያዎች አንዱ ነው" ሲሉ ካትዝ አክለዋል። "አሁን ባለው እውነታ ማንም ሰው ወደ ጋዛ ምንም አይነት ሰብአዊ እርዳታ ለማስገባት ፈቃደኛ አይደለም፤ እናም ማንም ወደዚህ አእርዳታ ለማስገባት ዝግጁ አይደለም ብለዋል።

የእስራኤል ባለስልጣናት ቀድሞውንም በጋዛ ያለውን አስከፊ ሰብአዊ ሁኔታ በማባባስ ሁሉንም እርዳታ ወደ ጋዛ እንዳይገባ ለአንድ ወር ያህል አግደዋል።

ድንበር የለሹ የሀኪሞች ቡድን ወይም ኤምኤስኤፍ የምግብ የነዳጅና የህክምና ክምችቶችን ያሟጠጠውን የጋዛን ሙሉ ከበባ አውግዟል።የእስራኤል ኃይሎች በጋዛ ውስጥ በማንኛውም መልኩ በጊዜያዊ ወይም በቋሚ ሁኔታ በጠላት እና በእስራኤል ማህበረሰቦች መካከል እንደ ሊባኖስና ሶሪያ ሁሉ በፀጥታ ቀጠና ውስጥ ይቆያሉ ሲሉ ካትዝ አክለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
😭33👍30👎151
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቅቡልነት አሽቆልቁሎ 42 በመቶ ደረሷል ተባለ።

ዘ ኢኮኖሚስት እና ዩጎቭ ያካሄዱት የሕዝብ አስተያየት ጥናት 52 በመቶ ምላሽ ሰጪዎች ለትራምፕ የእስካሁን አፈጻጸም አሉታዊ አመለካከት እንዳላቸው አሳይቷል።

በተመሳሳይ በሕዝብ አስተያየቱ መሠረት በጥናቱ የተሳተፉ 35 በመቶ ሴቶች ትራምፕን ሲቃወሙ፤ 49 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች ፕሬዝዳንቱን ይደግፋሉ።

ከሚያዚያ 5 እስከ 7 በተደረገው ጥናት 1 ሺህ 512 ሰዎች ተሳትፈዋል።

ዎል ስትሪት ጆርናል በቅርቡ አካሂዶት በነበረው የሕዝብ አስተያየት መስጫ የትራምፕ ቅቡልነት 46 በመቶ እንደነበር ገልጿል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍213🔥2👀2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትግራይ

በርካታ የትግራይ ሰራዊት ከካምፕ እያመለጡ ወደ ሌላ አደረጃጀት እየገቡ ይገኛሉ

በደብረጺዮን ክንፍ የሚመራው ህወሃት የትግራይ ሰራዊትን በመጠቀም በክልሉ ግጭት ለመቀስቀስ እየሰራ ነው መባሉን ተከትሎ በበርካቶች ዘንድ ተቃውሞ ተነስቶበታል።
በዚህም በርካታ የሰራዊቱ አባላት ከካምፕ እያመለጡ ይገኛሉ፡፡ 

በአሁን ሰዓት የትግራይ ሰራዊት ታጣቂዎች ቀድሞ ከነበሩት ወታደራዊ ክፍል እየጠፉ “ ነፃ መሬት “ ብለዉ ወደ ሰየሙት ያልታወቀ ቦታ በመሸሽ እስካሁን 21 ሺህ የሚጠጋ ታጣቂ ያለው የሀይል አደረጃጀት ማቋቋሟቸዉን ከትግራይ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Via:- አዩዘሀበሻ
@YeneTube @Fikerassefa
👍316😁3👀1
በዓልን አስመልክቶ ስጦታ መስጠት የምትፈልጉ በውስጥ መስመር ያናግሩ።

@Fikerassefa ያናግሩን የተለዩ ፓኬጆች አሉን።
👍6
የለማ መገርሳ ቤተሰቦች ታሰሩ:- ጅዋር ማህመድ

የለማ መገርሳ ቤተሰብ አባላት መታሰራቸውን ፖለቲከኛው ጃዋር አረጋግጬአለሁ አለ። ከፖለቲካ ውጭ የሆኑ ቤተሰቡ መታሰራቸው ነውር ነው ብሏል። ለማ ለምን ዝም አለን ተብሎ እንዴት ቤተሰቡ ይታሰራሉ ብሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
😁22👍165😭5👀4
በትግራይ በባህላዊ የማዕድን ሥራ ላይ የተሰማሩ እስከ 10 ሚሊዮን ብር እንደሚቀጡ ተገለፀ!

በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በቅርቡ በወጣው የተሻሻለ የማዕድን አስተዳደር ደንብ መሠረት በባህላዊ የማዕድን ማምረት ሥራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች  እስከ 10 ሚሊዮን ብር እንደሚቀጡ ተገለጸ።

ረቡዕ ሚያዚያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም. ተግባራዊ እንዲደረግ በክልሉ ለሚገኙ ለመሬትና ማዕድን እንዲሁም ለሚመለከታቸዉ የመንግስት መ/ቤቶች በተላከዉ ደብዳቤ ይህኑን ደንብ እንዲያስፈፅሙ መጠየቁን ካፒታል ተመልክቷል።

ደንቡ በባህላዊ እና አነስተኛ ደረጃ የማዕድን ሥራዎች ላይ እንደ ሜርኩሪ እና ሳይናይድ ያሉ ጎጂ ኬሚካሎችን መጠቀም እንዲሁም ብረትና ብረት ነክ ማዕድናትን ያለዕሴት መጨመር መላክ ወይም መሸጥን በግልጽ ይከለክላል።

ይህን ጣሰ ማንኛውም ሰው ከ15 እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ሊቀጣ የሚችል ሲሆን በተጨማሪም እስከ 10 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ሊጣልበት ይችላል።

ከዚህም በላይ ጥፋተኛው ከማዕድን ሥራው ጋር የተያያዙ ማሽነሪዎችና ሌሎች መሣሪያዎች እንዲሁም ያመረተው ማዕድን ይወረሳል፤ ድርጅቱም ዝግ የሚሆን ከመሆኑም በላይ ለወደፊቱ በማንኛውም የማዕድን ሥራ እንዳይሳተፍ ይታገዳል።

የክልሉ መንግሥት ይህንን ደንብ ያወጣው በፌዴራል መንግሥት በተሰጠው ሥልጣን መሠረት መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን ዓላማውም የአካባቢን ደህንነት መጠበቅ፣ የሰዎችንና የእንስሳትን ጤና መከላከል እንዲሁም ማዕድናት በአግባቡ ተጨምሮባቸው ለሀገር ጥቅም እንዲውሉ ማድረግ ነው ተብሏል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👍46😁2212👎1
በሲዳማ ክልል የተለያዩ የጤና ባለሙያዎች መታሰራቸው ተሰማ።

የስምንት ወር ዲውቲ አልተከፈለንም ያሉ ዶክተሮች ለእስር መዳረጋቸው ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የኔቲዩብ ቤተሰቦቸው ጠቁመውናል።

በሲዳማ ክልል፤ ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ በሚገኘዉ ሀንጣጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች መታሰራቸው ለጉዳዩ ቅርብ ይሆኑ መረጃውን አጋርተውናል።

ከተሳሩ ባለሙያዎች ስም ዝርዝር እና ፎቶዎች በከፊል እነኚህ ናቸው።

ዶ/ር ሰመረ ፍቃዱ
ዶ/ር ዪሴፍ ጤናዬ
ዶ/ር አማኑኤል
ዶ/ር ብሩክ
ነርስ ደምሴ
አቶ አባቡ
አቶ ታሪኩ ኪምቢቻ
አቶ ጥላሁን

ፋርማሲስቶች

አቶ ወገን
አቶ ድምሩ
አቶ መኖር
አቶ አዱኛ



ይህ መልዕክት ለሚመለከተው እንዲደርስ ሼር ያድርጉ።
😭56👍3112🔥1
Forwarded from YeneTube
⭐️ ⭐️ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ።  ⭐️ ⭐️

የበዓል ስጦታ በማይታመን ዋጋ!!!

📍 ሳር ቤት ላይ አፖርትመንቶችን

በካሬ 64,200 ብር ብቻ

ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ

ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ አፖርትመንቶችን

ለመኖሪያ ምቹ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት አዋጭ!!!

ታድያ ይህ እድል እንዳያመልጥዎ
ፈጥነዉ ይደዉሉ!!!

+251 950 05 56 55

ወይም በቴሌግራም

TG  @Davehomes

What’s up https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1
👍71👎1
Forwarded from YeneTube
የሻረግ ቅመማ-ቅመም 👌 
#ምርቶቻችንን ከ :-
🥣 ሸዋ ሾፒንግ 
🥣 በሽ ገበያ
🥣 ባምቢስ(ልዊስ)
🥣 ሎሚያድ
🥣 ጋራ ማርት
🥣 ዴይሊ ሚኒማርት
🥣 ጋራድ ሱፐርማርኬት
እና በሌሎች ሱፐር ማርኬቶች ያገኙናል። 

🥣 መልካም በዓል   / 2017 ዓ.ም 🥣
#ጥራት እና ዋጋ ቅናሽ መለያችን ነው !!
📲 0911 664775 / 0911 872827
👍32
እግዱ ተሻረ

አዲሱ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌ/ጀኔራል ታደሰ ወረደ በቀድሞው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕ/ት በአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዚያዊ እግድ የተላለፈባቸውን ሦስት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችን ከሚያዝያ 7/2017 ዓ.ም ጀምሮ እግዱ መነሳቱን ከሦስት ቀን በፊት በቀን 08/08/2017 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ አሳውቀዋል።
በቀድሞው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተጣለባቸው ጊዚያዊ እግድ የተነሳላቸው ሦስቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ስም ዝርዝር፦
1.ሜጀር ጄነራል ዮወሃንስ ወልደጊዮርጊስ፣
2. ብርጋዴር ጄነራል ምግበይ ሃይለ እና
3. ሜጀር ጄነራል ማሾ በየነ ናቸው።

@Yenetube @Fikerassefa
👍27😁8👎21