YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዩቱበሮች እና ቲክቶከሮች ግብር ሊከፍሉ ነው

በመይነ መረብ ወይም በተለያዩ መተግበሪያዎች ላይ በክፍያ የሚቀርቡ ወይም በሚያቀርቡት አገልግሎት ገንዘብ ከሚያገኙ ሰዎች ላይ መንግሥት የተጨማሪ እሴት ታክስ ለመሰብሰብ ማቀዱ ታውቋል።

በድረገፅ ከሚቀርቡ የዜና አገልግሎቶች፣ከፖድካስት፣ከፊልሞች፣እና ሙዚቃን ጨምሮ በሚቀርቡ አገልግሎቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ይጣልባቸዋል።

በደንበኝነት ምዝገባ ላይ የተመሰረተ የሚዲያ አገልግሎት የሚሰጡ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲከፍሉ የሚያስገድደው አሰራር በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ በሚቀርብ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲጣል ያስገድዳል።
በአዲሱ አዋጅ በበይነ መረብ የሚተላለፍ podcast፣blogs፣journal፣በመይነመረብ የሚሸጥ መፅሀፍ፣ በመይነ መረብ የሚሰጥ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመንግሥት ታክስ  መክፈል እንዳለባቸው ይደነግጋል።
በመይነ መረብ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት የደረሰኝ አገልግሎት የመስጠት ሀላፊነት አለባቸው።

@Yenetube @Fikerassefa
😁90👍40😭83👀3👎1
👍4
YeneTube
Photo
EBS አስቸኳይ ማብራሪያ ሰጠ

👉ስህተት ተፈጥሯል ብሏል።

እንደሚታወቀው ጣቢያችን ኢቢኤስ ቴሌቭዥን መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም እሁድን በኢቢኤስ በተሰኘው የመዝናኛ ዝግጅታችን ውስጥ በሚተላለፈው የ "አዲስ ምዕራፍ " ፕሮግራማችን በተላለፈ አንድ ዝግጅት በርካታ አስተያየቶች ና ጥያቄዎች ከተለያዩ አቅጣጫዎች እየደረሰን ይገኛል።

ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ማህበራዊ ና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዪቻችንን ወደ መድረክ በማምጣትና የመፍትሄ አካል በመሆን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚተጋ የህዝብ ሚድያ ነው።
ሚድያው ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ታሪክ በማቅረብ የበኩሉን ድጋፍ በማድረግ ና ህዝብን በማሳተፍ ግለሰባዊ ብሎም ሃገራዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚቻለውን ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል ። በዚህም ፍሬ ያፈራ ስራ ስንሰራ ቆይተናል።

በቀጣይም ይህን ተግባር መስራታችንን እንቀጥላለን።
የአዲስ ምዕራፍ ዝግጅ ቻችን ከዚህ አላማም በመነሳት መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣት ብርቱካን ተመስገን ደረሰብኝ ባለችው ፆታዊ ጥቃት ከትምህርት ገበታዋ ተለይታ፤ በወጣትነትዋ የወለደችውን ልጇንም ለማሳደግ አቅም የሌላት መሆኑን በመግለፅ ድጋፍ እንዲደርግላት ተማፅና ወደ ጣቢያችን በአካል በመምጣት በሃዘን ና በእንባ ችግሯን ገልፆለች። ይህም በሴቶች ላይ እየደረሰ ካለው ፆታዊ ጥቃት ና በዚህም ህይወታቸው መራራ የሆነባቸውን እህቶችና እናቶችን በመርዳት ላይ ባተኮረ አላማ በመነሳት ይህን ፕሮግራም ወደተመልካች ለማድረስ ሞክርናል።

ሆኖም ፕሮግራሙ ከተሰራጨ በኃላ ፍፁም ኢሞራላዊ በሆነ መልኩ ይህን የሰብአዊ ተግባር ያለውን ፕሮግራም አሳስቶ በመጠቀም እኛንም ሆነ ተመልካቾችን በረቀቀ መንገድ በማዛባት የተሳሳተ መረጃ እንድናቀርብ የተሰራ እንደሆነ ከስርጭቱ በኋላ በወጡ መረጃዎች ለመረዳት ችለናል። ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጉዳዪን በጥልቀት እየመረመረ ይገኛል።

በወቅቱ በአካል መጥታ ችግሯን የተናገረችው ወጣት ብርቱካን ተመስገን ደረሰብኝ ባለችው ጥቃትና ሰቆቃ ፍፁም ሰብአዊነት በተሰማው መንገድ ያቀረበችልን መረጃ ተንተርሰን ይህችን ወጣት ወደ አዲስ የህይወት ምዕራፍ ለማሸጋገር ጥረት አድርገናል። ሆኖም በባለታሪክዋ ላይ እየወጡ ያሉ መረጃዎች የሚያሳዩት የተለየ ሆኖ አግኝተነዋል።
ይህ ስህተት እንዲፈጠር ክፍተት የፈጠረ አካል ተገቢው ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ጣቢያችን ከህግ አካላት ጋር ይተባበራል።

ጉዳዩን ለማጣራት ለሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ አካል ሚድያችን ተባባሪ እንደሆነም ይገልፃል ። ቀጣይ መሰል ስህተቶች እንዳይፈጠሩ ለማድረግ የሚያስችል ስርአት ለማጠናከር ቃል እየገባን ፤ ለተፈጠረው የመረጃ መዛባት ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ይቅርታ ይጠይቃል።

ተጨማሪ መረጃዎች እንዳገኘን በድጋሚ እናሳውቃለን።

ከ ኢቢኤስ ቴሌቭዥን ማኔጅመንት
@Yenetube @Fikerassefa
👎173👍102😁146👀5
YeneTube
Photo
በEBS TV የቴሌግራም ገፅ ትላንት ለሊት የለቀቀውን መግለጫ ከገፁ ላይ አጥፍቷል።

ምን ያመለክታል ?
ያለ እውቅና የተለቀቀ ይሆን ?
👀35😁22👍11👎6😭51
ለትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንትነት ጥቆማ እንዲደረግ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ጥሪ አቀረቡ

ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ ማለዳ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መረጃ መላው የትግራይ ህዝብ ግዝያዊ እስተዳደሩን በፕሬዝዳንትነት ሊያገለግል ይገባል የሚለውን ሰው እንዲጠቁም ጠይቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስተሩ በፅሑፋቸው በኢፌድሪ ህገ መንግስት 62(2)፣ እንዲሁም በፕሪቶርያ ስምምነትና በክልሎች የሚኖርን የፌደራል መንግስት ጣልቃ ገብነት ለመደንገግ በወጣ አዋጅ ቁጥር 359/1995 መሰረት፤ እምዲሁም አሳታፊ የትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር መመስረታት በተመለከተ የተደነገገ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደምብ ቁጥር 533/2015 መሰረት የቆመው የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ለሁለት ዓመታት በስራ ላይ መቆየቱ ይታወቃል ብለዋል።

በዚህም መሰረት የአቶ ጌታቸዉ ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዚዳንትነት ያበቃ መስሏል።
👍41😁27🔥41
Forwarded from YeneTube
እንኳን ለፊቼ ጨምበላላ በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ ለበዓሉ ድምቀት ይሆናሉ ያልናቸው መነፅሮች ሀዋሳ አስገብተናል።

በማንኛውም ሰዓት ፒያሳ አዋሽ ባንክ በመምጣት መግዛት ይችላሉ ወይንም ብዛት የሚወስዱ ከሆነ ያሉበት እናደርሳለን።

+251701319932
@Fikerassefa
ይደውሉ
👎121😁10👍91
🇸🇴🏦 ሶማሊያ አፍሪ ኤግዚም ባንክን ተቀላቀለች

በዚህም የኢንቨስትመንት ዕድሎች፣ የተመቻቸ ንግድ እና የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞችን በቀላሉ ማግኘት እንድትችልና ኢኮኖሚዋን መልሳ እንድትገነባ ይረዳታል ሲል ባንኩ ገልጿል።

የሶማሊያ ሚኒስትር ዴኤታ ሂርሲ ጃማ ጋኒ ለሀገሪቱ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው ያሉት ሲሆን ሶማሊያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ሥር በክልላዊና አህጉራዊ ንግድ ውስጥ ለሚኖራት ሚና ቁርጠኝነቷን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል።

የአፍሪ ኤግዚም ባንክ ሰብሳቢ ቤኔዲክት ኦራማ የሶማሊያ አባልነት ለመንግሥት እና የግል ዘርፎች አዲስ የገንዘብ ድጋፍ አማራጮችን የሚፈጠር ነው ብለዋል።

የሶማሊያ የንግድና የፋይናንስ ዘርፎች ከባንኩ የልማት ተነሳሽነቶች ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋገጡ ውይይቶች ከወዲሁ መካሄድ እንደጀመሩም ተጠቁሟል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍14
👍 ተከታዮችን በፍጥነት ማግኘት ይፈልጋሉ?

Boostgram Promo ይጠቀሙ - ተከታዮችዎን በአጭር ጊዜ ይጨምሩ!

ጀማሪ ኢንፍሉዌንሰር ከሆኑ
ተከታዮችን በፍጥነት ማሳደግ ከፈለጉ
ተጽዕኖዎን ለማሳደግ ከፈለጉ


Boostgram Promo መፍትሄው ነው!

👉 ዛሬውኑ ይሞክሩት: https://tttttt.me/boostgramPromoBot/boostgram
ከሌሎች ጀማሪዎች ልዩ ይሁኑ - የማህበራዊ ሚዲያ ተከታታዮችዎን በቀላሉ ያሳድጉ!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍51
ብሔራዊ ባንኩ በአገሪቱ ያለው የዋጋ ግሽበት በኢኮኖሚ እድገቱ ላይ ተጽእኖ አይኖረውም አለ

🔸የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ በአገሪቱ ያለው የዋጋ ግሽበት በኢኮኖሚ እድገቱ ላይ ተጽእኖ አይኖረውም አለ፡፡

🔸የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ትናንት ባወጣው ምክረሃሳብ የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየረገበ በመሄድ አሁን ላይ 15 በመቶ መድረሱን አረጋግጫለሁም ብሏል።

🔸ምግብ ነክ የዋጋ ግሽበት በየካቲት ወር 14 ነጥብ 6 በመቶ መሆኑን የጠቆመው ባንኩ ይህም ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረበት 31 በመቶ በእጅጉ የቀነስ መሆኑን ነው የተናገረው።

🔸ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች ደግሞ 15 ነጥብ 6 በመቶ መሆኑን ያመለክተው የባንኩ መረጃ ይህም ከባለፈው ዓመት አንፃር ቅናሽ ቢኖረውም ባለፉት ጥቂት ወራት ጭማሪ የማሳየት አዝማሚያ ማሳየቱ ነው የተመለከተው።

🔸የየካቲት ወር ወርሃዊ የዕድገት መጠን 0 ነጥብ 5 መሆኑን ያሳወቀው የባንኩ መረጃ ይህም ለ4 ተከታታይ ወራት የተመዘገበ ዝቅተኛ የዕድገት መጠን እንደሆነ ነው የተነገረው።

🔸ይህም ሊሆን የቻለው ብሔራዊ ባንኩ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ ከመከተሉ ባሻገር የግብርና ምርት መጨመሩና አስተዳደራዊ ዋጋዎች ላይ የተወሰዱ ማሻሻያዎች ቀስ በቀስ በመተግበራቸው እንደሆነ አመልክቷል።

🔸የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ኮሚቴ ሁለተኛ ስብሰባውን በትላንትናው ዕለት ማድረጉ የተገለፀ ሲሆን  የዋጋ ንረትን ጨመሮ በተለያዩ  የገንዘብ ፖሊሲ ግምገማዎችን እና ምክረ ሃሳቦችን  አቅርቧል፡፡

ሙሉ መግለጫውን ከላይ አያይዘንላችኋል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
😁37👎23👍20🔥1
ለ2ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርቧል

ዛሬ ለ2ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረበው ድምፃዊ አንዱዓለም ፖሊስ አንዳንድ ምርመራ ውጤቶች ስላልደረሱልኝ ተጨማሪ ቀናት ይሰጠኝ ባለው መሰረት ተጨማሪ 12 ቀን ተፈቅዶለታል።

የድምፃዊ አንዱዓለም ጠበቃ በበኩሉ የዋስ መብት ይፈቀድለት ብሎ ቢጠይቅም

ፖሊስ ማስረጃዎችን ያጠፋብኛል መፈቀድ የለበትም በማለቱ ሳይፈቀድ ቀርቷል።

መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓም ቀጠሮ ተሰርቷል።

#ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
👍38👎32😭2
3👍1
YeneTube
Photo
በወጣቷ ላይ የደረሰው ሰቆቃ በቅርብ ጊዜያት በአገራችን ለተፈጸሙ ግፎች በቂ ማሳያ ነው።

🗣 እናት ፓርቲ

(በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመኢአድ፣ ኢሕአፓ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄና እናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ)

ከምትማርበት ዩኒቨርስቲ ከዓመታት በፊት ከሌሎች ጓደኞቿ ጋር ታፍና ተወስዳ እጅግ አሰቃቂ በደል ከደረሰባቸው አንዷ እንደሆነች የገለጸችው ወጣት ብርቱካን ተመስገን የደረሰባትን ግፍና አኹን እየመራች ያለችውን እጅግ ፈታኝ የሕይወት ውጣ ውረድ የዚህ ዓይነት ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሰዎች በማይደፍሩት መልኩ በድፍረት በሚዲያ ቀርባ አስረድታለች። ይኼ በሕዝባችን ዘንድ በከፍተኛ ኹኔታ ሲጠየቅ የነበረና አንዳች መፍትሔ ሳይሰጠው ይባስ ብሎ በመንግሥት አካላት ዘንድ እጅግ የተጣረሱና የተድበሰበሱ መረጃዎች ሲቀርብበት የኖረ ግፍ ነው። ብርትኳን ላይ የደረሰው ግፍ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጸሙ መዋቅራዊና ሥርዓታዊ በደሎች ማሳያ ተደርጎ የሚወሰድ እንጂ ብቸኛው አይደለም። በዚኹ አጋጣሚ የልጅቷ ደህንነት ተጠብቆና መቋቋሚያ አግኝታ ስለሌሎች ደብዛቸው ስለጠፋ ተማሪዎች አንዳች ፍንጭ የሚሰጡ መረጃዎችን ለማገጣጠም መጣር ሲገባ ልጅቷ ጋር ያለውን እውነት ለማዳፈን ሙከራ ማድረግ የግፉ ተባባሪ ከመኾን ተለይቶ አይታይም። በትብብር የምንሠራ ፓርቲዎች በወጣቷ ጉዳይ የቅርብ ክትትል እንደምናደርግ ቃል እንየገባን ሕዝባችን ችግሮቹ ሥርዓት ወለድ መኾናቸውን በውል ተገንዝቦ እርስ በእርስ ጣት ከመጠቋቆም እንዲወጣና በጋራ እንዲታገል ከከፋው ሰቆቃም በአንድነት እንድንወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።   

መንግሥት የብርቱካንና መሰል ጓደኞቿን እገታ ቢያንስ ለችግሩ እውቅና ሰጥቶና ሕዝብን አስተባብሮ ወደ መፍትሔው መሔድ ሲገባው ማድበስበስን በመምረጡ እስከዛሬዋ ቀን ድረስ ችግሩ ሥር ሰዶ ከእለት እለት እየከፋ ሄዷል፡፡ መጋቢት ፰ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል እየተጓዘ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ላይ በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ወረ ጃርሶ ወረዳ፣ ልዩ ስሙ አሊዶሮ በተባለ ቦታ አሽከርካሪውን ጨምሮ መላ ተሳፋሪዎች መታገታቸውንና ለማስለቀቂያ የሚኾን በነፍስ ወከፍ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እየተጠየቀባቸው መኾኑን ሰምተናል፡፡

በተመሳሳይ መጋቢት ፲፬ ቀን በዚኹ ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ ጎርፎ ከተማ አካባቢ የታጠቁ ቡድኖች ከቀኑ ፲ ሰዓት ገደማ በኹለት ተሽከርካሪዎች ላይ በፈጸሙት እገታ አርባ ያኽል ሰዎች መታፈናቸውን ሰምተናል፡፡ ለጊዜው ለኹለቱም እገታዎች በይፋ ኃላፊነት  የወሰደ አካል ባይኖርም በአካባቢው መሰል ድርጊት ፈጻሚዎች ያለምንም ከልካይ ባሻቸው ወቅትና በተደጋጋሚ ጊዜያት እገታ እየፈጸሙ አሰቃቂ ግድያ የሚፈጸምበትና ብዙ ሚሊዮን ብር ካሳ የሚጠየቅበት መሥመር አካባቢው ደግሞ “የሞት ቀጠና” ከኾነ ውሎ አድሯል፡፡

በተደጋጋሚ እንደገለጽነው መንግሥት ተቀዳሚ ተግባሩ የኾነውን የዜጎችን ወጥቶ የመግባት ዋስትና ማስጠበቅ አለመቻል፣ ፍትሕ አለመስፈን በአገር ደረጃ መግደልና ማገት ቀላል እንዲኾን አልፎ ተርፎም ለእነዚኽና መሰል ቡድኖች የገቢ ምንጭ ጭምር ተደርጎ እንዲታይ አድርጎታል፡፡ በትብብር የምንሠራ ፓርቲዎች በእገታው የተሳተፈ የትኛውም ቡድን በንጹሓን ሕይወት መቆመሩን እንዲያቆምና የታገቱ ዜጎች ያለምንም ቅድመ ኹኔታ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
                
እግዚአብሔር አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

@Yenetube @Fikerassefa
👍97😭12👎73😁1👀1
የሱዳን ጦር የካርቱምን አየር ማረፊያ መቆጣጠሩን አስታወቀ

የሱዳን ጦር ሃይል (SAF) እኤአ ከሚያዝያ 2023 አጋማሽ ጀምሮ በፓራሚትሪ ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች (RSF) ተይዞ የነበረውን የካርቱም አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መቆጣጠሩን የካርቱም አካባቢ ወታደራዊ ምንጮች ገለፁ። 


#ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
👍145
የአማራ ክልል መንግስት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአድማ መከላከል እና መደበኛ ፖሊሶችን እያሰለጠነ መሆኑን ተገለጸ!

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው በብር ሸለቆ መሠረታዊ የውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ተገኝተው በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአድማ መከላከል እና የመደበኛ ፖሊስ ምልምል ሠልጣኞችን “አበረታትተዋል”።

ደሳለኝ ጣሰው በጉበኝቱ ወቅት “የክልልሉን ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ እና የሕዝብ እና የመንግሥትን ፍላጎት” አስመልክተው ለሠልጣኞች ማብራሪያም ሰጥተዋል። በተጨማሪም “የሥልጠናውን ዓላማ፣ አስፈላጊነት እና ግቦች በተመለከተም ለሠልጣኞች ግልጽ አድርገዋል” ሲል የክልሉ ሚዲያ ዘግቧል።

ሥልጠናው “በዋናነት ነጻ፣ ገለልተኛ፣ ወታደራዊ ሥነ ምግባር የተላበሰ፣ በሥነ ልቦናው ያደገ እና በራስ አቅም የክልሉን ሰላም ማረጋገጥ የሚችሉ ሠልጣኞችን ማፍራት እንደኾነም” አቶ ደሳለኝ ገልጸዋል።

ሠልጣኞች “የክልሉን ሰላም በዘላቂነት በማረጋገጥ ሕዝቡን ከገባበት ፈተና ለማላቀቅ እና ፊቱን ወደ ልማት እንዲያዞር በማድረግ ረገድ ትልቅ ኀላፊነት እንዳለባቸው” ተናግረዋል። ሰልጣኞች “ከክልሉ አልፎ የሀገርን ደኅንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ዝግጁነት ላይ መሆናቸውም” ተገልጿል።አቶ ደሳለኝ ጣሰው አክለውም ሠልጣኞቹ “በጥሩ ቁመና፣ ቁርጠኝነት እና የሥነ ልቦና ዝግጁነት” ላይ መኾናቸውን አረጋግጠዋል ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
😁35👍139👎2
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖን በአዲስ አበባ ልታዘጋጅ ነው!

ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላትን አቅም ለአለም ለማሳየት እና የአፍሪካ የቴክኖሎጂ ማዕከል ለመሆን የሚያስችላትን ጉዞ ያጠናክራል የተባዉ አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ETEX 2025) በአዲስ አበባ  ልታዘጋጅ መሆኑ ተገለፀ።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት (EAll) በጋራ የሚያዘጋጁት ይህ ኤክስፖ ከ100 በላይ የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች፣ ከ50 በላይ ስታርታፖች እንዲሁም ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች የሚሳተፉበት ነው።

ከግንቦት 8 እስከ 10 ፤2017 ዓ.ም. በሚካሄደዉ ኤክስፖው ላይ የቴክኖሎጂ ውጤቶችና አገልግሎቶች የሚቀርቡበት ዓውደ ርዕይ፣ ወርክሾፖች፣ ጥናታዊ ወረቀቶች፣ የፓናል ውይይቶች፣ የሃካቶን እና የ AI ሮቦቲክስ ውድድሮች እንደሚቀርብ ካፒታል ሰምቷል።

ኤክስፖው በሳይበር ደህንነት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት(Al)፣ ፋይናንስ ቴክኖሎጂ (FinTech)፣ ስማርት ከተማ (Smart City)፣ እንዲሁም በቴክኖሎጂ ትምህርት (Tech Education) ላይ እንደሚያተኩር ተነግሯል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👍28👎14😁71
ሕወሓት "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀጣይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳዳሪነት በኢሜል ጥቆማ ስጡኝ" ማለታቸውን ተቃወመ

"ብቻቸውን መሾም አይችሉም" ብሏል።
እኛ ጄኔራል ታደሰ ወረደን ፕሬዚዳንት አድርገን ሾመናል ነገር ግን የፌደራል መንግሥቱ ችላ ብሎታል ብሏል።
መንግሥት የፕርቶሪያን ስምምነት በመጣስ የትግራይን ህዝብ ትዕግሥት እየተፈታተነ ነው ብሏል።

ድርጅቱ አሁን ባወጣው መግለጫ እንዲህ ብሏል "የኢትዮጵያ መንግስት አሁንም የተኩስ አቁም ስምምነቱን መንፈስ እና ይዘት ወደ ጎን በመተው በተዋዋይ ወገኖች የጋራ ስምምነት ሳይሆን ተገቢ ባልሆኑ ህጎች (አዋጅ 359/1995፣ ደንብ 533/2015) ብቻውን ለመወሰን እየሰራ ነው። በፕሪቶሪያ ስምምነት አንቀፅ 10 መሰረት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተመሰረተው በህወሓት እና በኢትዮጵያ መንግስት ድርድር ነው።

ስለዚህ በትግራይ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር የፕሪቶሪያ ስምምነት ውጤት እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት ብቸኛ ውሳኔ አይደለም። ሆኖም ይህንን የሚጥስ ግልጽ እንቅስቃሴ አለ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ህወሓት ከስልጣን መወገዱን ተከትሎ በጊዜያዊው ፕሬዝደንት መተካት ላይ ውይይት አድርገዋል። በጉባኤው የእስካሁኑን ጊዜያዊ አስተዳደሩ የስራ አፈጻጸም የገመገመ ሲሆን፥ ጊዜያዊ አስተዳደሩን ፕሬዝዳንት ለመቀየር ተስማምቷል። ስለሆነም የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ጄኔራል ታደሰ ወረዳን በፕሬዝዳንትነት እንዲሾም ወስኗል። ነገር ግን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የቀረበው የአስተያየት ጥሪ ስምምነቱን ችላ ብሎታል። ፕሬዚዳንቱን የመሾም ስልጣን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቸኛ ውሳኔ መስሎ የፕሪቶሪያን ስምምነት ስለሚጥስ ተቀባይነት የለውም"ብሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍57👎10😁87