ኢትዮጵያ ከ Djibouti 🇩🇯 ጋር ከ1 ሰዓት በኋላ የምታደርገውን ጨዋታ ለማየት ይህን አፕ ዳውን ሎድ አድርጉ። Cricfy TV በነፃ ነው። ለሌላ ጊዜም ይጠቅማችኋል።
Application ለማውርድ በዚህ ገፅ ላይ ካደረግን Copyright ሊዘጋብን ሰለሚችል አዲስ ቻናል ከፍተናል ለቀናል አፕልኬሽኑን
https://tttttt.me/+LMTodBBw8oI4MjY0

👍22😁11❤1
ነዳጅ
የግል ኩባንያዎች ነዳጅ እንዲያስመጡ ተፈቀደ
የግሉ ዘርፍ ከሽያጭ በተጨማሪ ነዳጅ ማስመጣት እንዲችል የሚፈቅደው አዋጅ ስራ ላይ ዋለ፡፡
የነዳጅ ግብይት አዋጅ ቁጥር 1363/2017 ላለፈው 11 አመት በስራ ላይ የነበረውን አዋጅ የቀየረ ሆኖ ባለፈው ጥር ነበር በፓርላማ የፀደቀው፡፡
ይህ አዋጅ በሳለፍነው ሳምንት በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ መውጣቱን ተከትሎ ወደ ስራ መግባቱ ነው የታወቀው፡፡
በዚህም እስካሁን በመንግስታዊው የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ብቻ ተይዞ የነበረውን የነዳጅ ከውጭ ገዝቶ የማስገባት ስራ ሌሎች ኩባንዎችም ማከናወን እንዲችሉ በር የሚከፍት ነው፡፡
የነዳጅ ንግድ የመንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ አካል ሆኖ እየተሰራበት የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa

👍29👀7😁2❤1⚡1
በማዕከላዊ ጎንደር እና በሰሜን ጎጃም ዞኖች በተካሄዱ ውጊያዎች በርካታ ሰዎች ተገደሉ!
በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር እና በሰሜን ጎጃም ዞን ከአርብ መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት ፀጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች በተካሄዱ ውጊያዎች በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
በጎንደር ከተማ “የፋኖ ታጣቂዎች” ተኩስ መክፈታቸውን ተከትሎ ግጭቶች መካሄዳቸውን የገለጹት ነዋሪው አክለውም ታጣቂዎቹ የጎንደር ዙሪያ ጠዳ ክፍለከተማ አከባቢውን ተቆጣጥረው መቆየታቸውን ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁ በማዕከላዊ ጎንደር ነዋሪ ተናግረዋል።
ሌላኛው ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁ በሰሜን ጎጃም ዞን መራዊ ከተማ ነዋሪ፤ በከተማዋ የፋኖ ታጣቂዎች “ለምን ትምህርት ታስተምራላችሁ” በሚል 11 መምህራንን ሀሙስ መጋቢት 11ቀን 2017 ዓ.ም ከቤታቸው አስወጥተው መግደላቸውን ገልጸዋል።
Via AS
@YeneTube @Fikerassefa

😭41👍25😁6👎3
“ኢትዮጰያን በ2026 የአለም የንግድ ድርጅት ሙሉ አባል ለማድረግ እየሰራን ነው” -የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር
ኢትዮጵያ 5ኛውን የአለም የንግድ ድርጅት የስራ ቡድን ስብሰባ በበቂ ዝግጅት ተሳትፋ በስኬት ማጠናቀቋን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ትላንት መጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
በመግለጫቸውም በቅርቡ ጄነቭ በተካሄደው 5ኛው የሀገራችን የአለም ንግድ ድርጅት የስራ ቡድን ስብሰባ በስኬት መጠናቀቁንና በቀጣይ በሚካሄደው 6ኛው የአለም ንግድ ድርጅት የስራ ቡድን ስብሰባ ኢትዮጵያን ሙሉ አባል ሆና ድርጅቱን መቀላቀል የሚያስችላትን ስራ መሰራቱን አስታውቀዋል፡፡
በካሜሩን በ2026 በሚካሄደው 14ኛው የአለም ንግድ ሚኒስትሮች ስብሰባ ኢትዮጵያ የአለም የንግድ ድርጅት አባል መሆኗን የሚያበስር ዜና የምንሰማበት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በ5ኛው የሀገራችን የአለም ንግድ ድርጅት የስራ ቡድን ስብሰባ በተለያዩ የድርድር ነጥቦች ዙሪያ ከ110 በላይ ጥያቄዎች ከተለያዩ ሀገራት ቀርበው ምላሽ የተሰጣቸው መሆኑንና የልኡካን ቡድናቸው በበቂ ዝግጅት ውጤታማ ድርድር ያካሄደ መሆኑን ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በትላንትናው እለት መግለጫቸው ኢትዮጵያ ከ17 ሀገራት መካከል ከ12ት ሃገራት ጋር የሁለትዮሽ ድርድር የተካሄደ መሆኑን አንስተው በተለይም ከአሜሪካና ከአውሮፓ ህብረት ጋር ውጤታ ድርድር መደረጉን ጠቁመዋል፡፡
የአለም ባንክ እና 19 ሀገራት ኢትዮጵያ ድርጅቱን እንድትቀላቀል ጠንካራ ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቁመው "ከተለመደው እና ከሚጠበቀው በላይ ድጋፍ" አግኝተናል ብለዋል።ከአለም የንግድ ድርጅት ጋር የሚካሄደው ቀጣዩ ድርድር በተያዘው አመት 2017 በሐምሌ ወረ መሆኑን አስታውቀዋል።
@YeneTube

👍17😁13👎8❤3
በኬንያ የጭነት አውሮፕላን በሶማሊያ ዋና ከተማ አቅራቢያ ተከሰከሰ
በውስጡ የነበሩ አምስቱም የበረራ ሰራተኞችህይወት አልፏል።
የአደጋው መንስኤ እስካሁን አልታወቀም።
አውሮፕላኑ አልሸባብ ታጣቂ ቡድን ጋር ለሚዋጉ የአፍሪካ ህብረት ኃይሎች ምግብና የተለያዩ ቁሳቀቁሶችን ጭኖ ነበር።
@Yenetube @Fikerassefa
በውስጡ የነበሩ አምስቱም የበረራ ሰራተኞችህይወት አልፏል።
የአደጋው መንስኤ እስካሁን አልታወቀም።
አውሮፕላኑ አልሸባብ ታጣቂ ቡድን ጋር ለሚዋጉ የአፍሪካ ህብረት ኃይሎች ምግብና የተለያዩ ቁሳቀቁሶችን ጭኖ ነበር።
@Yenetube @Fikerassefa
😭26👍5
ሰባራ ባቡር በደረሰ የእሳት አደጋ ሶስት የንግድ ሱቆች ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰ
ዛሬ መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 1ሰዓት 05 ላይ በአራዳ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 2 ሰባራ ባቡር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በተነሳ የእሳት አደጋ በሶስት የንግድ ሱቆች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ሶስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሀያ ሶስት የአደጋ መቆጣጠር ሰራተኞች የተማሩ ሲሆን የእሳት አደጋዉ በአቅራቢያዉ ባለዉ ባንክና የንግድ ሱቆች ላይ ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያስከትል መቆጣጠር መቻሉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል።
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣር ጥረት ሲያደርጉ ከነበሩ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች መካከል በሁለቱ ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱንም ኮሚሽኑ አስታውቃል።
(ብስራት ሬድዮ እና ቴለቪዥን)

👍15😭13❤5🔥1
ሸገር ከተማ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አደገ!
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ አንድ እየተሳተፈ የሚገኘው ሸገር ከተማ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።ዛሬ የምድብ 18ኛ ጨዋታውን ያደረገው ሸገር ከተማ እንጅባራ ከተማን 5 ለ 1 አሸንፏል።
ውጤቱን ተከትሎ ነጥቡን 45 ያደረሰው ሸገር ከተማ አራት ጨዋታ እየቀረው አስቀድሞ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል፡፡
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa

👍42😁28👎9❤7
ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ 28.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አገኘች!
ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳዋን ለመደገፍ ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ (AFD) 28.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አገኘች። ስምምነቱ 25 ሚሊዮን ዩሮ የበጀት ድጋፍ እና 3.5 ሚሊዮን ዩሮ የቴክኒክ ድጋፍን ያካትታል።
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ እንደገለጹት፣ ይህ ድጋፍ የኢትዮጵያን የህዝብ-የግል ሽርክና፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ማሻሻያ እና የፋይናንስ ዘርፍ ተደራሽነትን ለማጠናከር ይረዳል። እንዲሁም ውጤታማ ፖሊሲ ትግበራ ተቋማዊ አቅምን ለማሳደግ አስተዋፅኦ ብለዋል።
የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ (AFD) የሀገር ዳይሬክተር ሚስተር ሉዊስ-አንቶይን ሶሼት በበኩላቸው፣ ኤጀንሲው የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ለውጥ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ድጋፍ አስተዳደርን፣ ኢኮኖሚያዊ ዘላቂነትን እና የመንግስት ዘርፍ ቅልጥፍናን ለማጠናከር ያለመ መሆን ተጠቁሟል።

👍20❤5😁5
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቬንዚዌላ ላይ ነዳጅ በሚገዙ ሃገራ ላይ የ 25 በመቶ ታሪፍ እንደሚጥሉ አስታወቁ
ትራምፕ እንዳስታወቁት ከቬንዚዌላ ነዳጅ በመግዛት ወደ ሃገሩ በሚያስገባ ማንኛውም ሃገር ላይ የ25 በመቶ ታሪፍ ይጣልበታል ብለዋል፡፡
ትራምፕ በትሩዝ ማህበራዊ ድረገጻቸው ላይ በጻፉት መልዕክት ቬንዚዌላ ከአሜሪካ ጋር እጅግ ጠበኛ ሃገር ነች ስለዚህም ከቬንዚዌላ ላይ ነዳጅ የሚገዙ ሃገራት ከአሜሪካ ጋር በሚኖራቸው የንግድ ልውውጦች ላይ 25 በመቶ ታሪፍ ይጣልባቸዋል ይህም ከ ሚያዚያ 12 ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል፡፡
ስፔን ህንድ ሩሲያ ሲንጋፑር እና ቬተናም ከ ቬንዚዌላ ላይ ነዳጅ በመግዛት ከሚታወቁት ውስጥ ናቸው፡፡
እስከ ዛሬ ባለው ራሷ አሜሪካም ከቬንዚዌላ ነዳጅ ስታስገባ የቆየች ሲሆን ባለፈው ጥር ወር ብቻ 8 ነጥብ 6 ሚሊየን በርሜል ነዳጅ ከቬንዚዌላ አስገብታለች፡፡
ባጠቃላይ ከጥር ወር ወዲህ ሁለት መቶ ሁለት ሚሊየን በርሜል ነዳጅ አሜሪካ ከሃገሪቱ ገዝታለች ሲል የዘገበው ዩሮ ኒውስ ነው፡፡

👍22👎7😁5❤1
የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን በትግራይ ክልል የነዳጅ አቅርቦት መቋረጡን አላውቅም አለ!
-የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ ነዳጅ የሚያገኘው ከሕክምና ተቋማት ድርሻ መሆኑን አስታውቋል
የትግራይ ንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ ከመጋቢት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በክልሉ የነዳጅ አቅርቦት መቋረጡን የሚገልጽ ደብዳቤ፣ ለነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣንና ለንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ቢልክም፣ ባለሥልጣኑ በክልሉ የነዳጅ አቅርቦት መቋረጡን እንደማያውቅ አስታወቀ፡፡
የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የነዳጅ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዲበር ፉፋ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ባለሥልጣኑ በትግራይ ክልል ነዳጅ እንዲቋረጥ ምንም ዓይነት ምክንያት የለም ብለዋል፡፡ባለሥልጣኑ ባለፈው ሳምንት ባለሙያዎችን በመመደብ አዳዲስ የነዳጅ ማደያዎችንም ሆነ የበፊቶቹን በቀልጣፋ ሁኔታ እንዲሠሩ ማድረጉን፣ በክልሉም ነዳጅ መቋረጡን የሚገልጽ ደብዳቤ እንዳልደረሰው አክለው ገልጸዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.proworksmedia.com/139544/

👍21❤1👎1
አሜሪካ የሩሲያ የግብርና ምርት እና ማዳበሪያ ወደ ዓለም ገበያ እንዲመልስ እገዛ ታደርጋለች ሲል ኋይት ሀውስ በሪያድ የተካሄደውን ስብሰባ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ
የመግለጫው ተጨማሪ ነጥቦች፦
▪️ዩናይትድ ስቴትስ ለሩሲያ የማዳበሪያ እና ምግብ ኤክስፖርት ወደብ እና የክፍያ ስርዓት ለማመቻቸት አቅዳለች።
▪️አሜሪካ እና ሩሲያ በጥቁር ባህር ደህንነቱ የተጠበቀ ጉዞ ለማረጋገጥ እና ኃይል ከመጠቀም ለመቆጠብ ተስማምተዋል።
▪️አሜሪካ እና ዩክሬን በጥቁር ባህር የንግድ መርከቦች ላይ የሚወሰደውን የኃይል እርምጃ ለማስቀረት ተስማምተዋል።
▪️ዋሽንግተን እና ኪዬቭ በሩሲያ እና በዩክሬን የኢነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚደረጉ ጥቃቶችን የሚያስቀር መፍትሄ ለማዘጋጀት ተስማምተዋል።
@Yenetube @Dikerassefa

👍21❤3👀3🔥1😁1😭1
በትምህርት ዘርፍ አወቃቀር ላይ ቅሬታ አለን የሚሉ ተማሪዎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን በሕግ ሊጠይቁ ነው
‹‹ጉዳዩን የፈለጉበት ቦታ መውሰድ ይችላሉ››
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
በያሬድ ንጉሤ
በራስ ገዝነት ሒደት ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የነበሩትን ኮሌጆችና የትምህርት ፕሮግራሞች እየቀነሰና እያጠፈ በመምጣቱ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች በሕግ ሊጠይቁት መሆናቸውን ለሪፖርተር ተናገሩ፡፡ ዩኒቨርሲቲው ዕርምጃው ተገቢ እንዳልሆነ፣ የእነሱ አስተያየት ያልተጠየቀበትና ግልጽነት ያልታየበት ነው የሚሉ የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎች፣ ቅሬታቸውን በተለያዩ መንገዶች ለዩኒቨርሲቲው ቢያቀርቡም፣ ተገቢውን ምላሽ ባለማግኘታቸው በሕግ ለመጠየቅ የመጨረሻው ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡
ለሪፖርተር አስተያየታቸውን የሰጡ የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎች፣ ‹‹ራሱን ችሎ ያለውን የአገር ልማት ጥናት ኮሌጅ ወደ ሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ ሥር እንዲተዳደር ሲደረግ፣ ዩኒቨርሲቲው የሄደበት ርቀት፣ ግልጽነት የጎደለው ከመሆኑ ባሻገር፣ ኮሌጁ ለምን ፈረሰ በሚለው ጉዳይ ላይ ምላሽ የሚሰጥ...
ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/139575/

👍42😁5
አስደናቂ ፊቸሮችን ያግኙ!
- 4GB እስከሆኑ ፋይሎችን ይጫኑ
- በፍጥነት ያውርዱ
- የእርስዎን online status ከሌሎች ይደብቁ
- እስከ 4 accounts ድረስ ይጠቀሙ
- ልዩ ስቲከሮች እና ኢሞጂዎች🎭
- የድምፅ መልእክቶችን ጽሁፍ ያድርጉ
- ልዩ badges ያግኙ
- ማስታወቂያዎችን ያስወግዱ
አሁኑኑ ይቀላቀሉ እና የእርስዎን Telegram ተሞክሮ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግሩ!
https://tttttt.me/HuluPayOfficialBot/start?startapp እዚህ ሊንክ ጋር ያገኛሉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍16🔥9
YeneTube
Photo
"The consequences of this poll will be important. Please vote carefully."
ልክ የዛሬ ሶስት አመት፣ ቱጃሩ ኢሎን መስክ በምስሉ ላይ የምትመለከቱትን "ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ትርጉም ላለው ዴሞክራሲ ወሳኝ ነው። ትዊተር ለዚህ መርህ ተገዢ ይመስላቿል?" በማለት የትዊተር ተከታዮቹን "አዎን" ወይም "አይደለም" በማለት ምላሽ እንዲሰጡ ከጠየቀ በኋላ ተከታዮቹ የሚሰጡት ምላሽ "ወሳኝ ውጤት ይኖረዋል" በማለት አጽንኦት ሰጠ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ ግን ማንም ሰው የዚህ ትዊተር "ፖል" ውጤት የአሜሪካን፣ ብሎም የአለምን የወቅቱን "status quo" የሚቀይር ይሆናል ብሎ የጠበቀ ማንም አልነበረም።
ከዚህ የትዊተር ፖል ቀናት በፊት ግን አንድ ነገር ተፈጥሮ ነበር፣ ባቢሎን ቢ የተባለ ቀኝ ዘመም፣ በወግ አጥባቂዎች የሚነበብ የቀልድ ዜናውች የሚጽፍ ዌብሳይት በወቅቱ የትዊተር ሃላፊዎች ማህበራዊ ሚዲያውን እንዳይጠቀም ታገደ።ለእግዱም ምክንያት ተብሎ የተሰጠው የወቅቱን የአሜሪካ ጤና ሚንስትር በተሳሳተ ተውላጠ ስም መጥራቱና "የአመቱ ምርጥ ወንድ" በማለት መቀለዱ ነበር። እኝህ ግለሰብ ጾታቸውን ከወንድ ወደሴት ቀይረው ነበርና ይህ ቀልድ እንደ ጥላቻ ንግግር ተቆጥሮ ባቢሎን ቢ ከትዊተር ታገደ።
ይህን ከዳር ሆኖ ሲከታተል የነበረው ኢሎን በዚህ ድርጊት ብስጭቱን ሲገልጽ ከቆየ ከቀናት በኋላ ነበር እንግዲህ በምስሉ ላይ የምታዩትን ትዊት ያደረገው። ውጤቱም በ"አይደለም" አሸናፊነት እንደተጠናቀቀ ነበር 44 ቢሊዮን ዶላር አውጥቶ ትዊተርን ሽጡልኝ ያለው። በወቅቱ የትዊተር ዋጋ እሱ ካቀረበው ገንዘብ በግማሽ ገደማ ያነሰ ነበር፣ ይህም የማህበራዊ ሚዲያውን ኢንቬስተሮች አሻፈረኝ የሚያስብል አልነበረምና በወራት ጊዜ ውስጥ ኩባንያውን በቁጥጥሩ ውስጥ ማስገባት ቻለ።
ከዚህ በኋላ 80 በመቶ ሰራተኞቹን አባረረ፣ የታገዱ አካውንቶችን አስለቀቀ። ነገር ግን በዚህ አላበቃም፣ በወቅቱ የነበረውን የባይደን አስተዳደር መሞገቱን የእለት ተእለት ስራው አደረገው። ከዚህ ከዚህ በፊት የትዊተርን እስር ቤት ፈርተው ዝምታን የመረጡና የግዞቱ ሰለባ የነበሩ ቀኝ ዘመም የፖለቲካ አንቂዎች እንደ ልብ መፈንጨት ቻሉ። ይህም በዴሞክራቶች የተያዘውን የአሜሪካን የፖለቲካ የሃይል ሚዛን የመፈታተን አቅም መፍጠር ቻለለት።
ከዚህ በኋላ ነበር እንግዲህ ከ2020ው ምርጫና ከጥር ስድስቱ የአሜሪካ ህግ አውጭዎች መቀመጫ(ካፒቶል) ረብሻ በኋላ የፖለቲካ እድሜያቸው አብቅቶላቸዋል የተባለላቸው ዶናልድ ትራምፕ ነፍስ መዝራት የጀመሩት፣ ኢሎን ትዊተርን ከገዛበት እለት አንስቶ የአሜሪካ የፖለቲካ ሃይል ሚዛን ወደቀኝ ማጋደሉን አላቋረጠም።
ይህ ሁሉ ሲሆን ቱጃሩ በይፋ ትራምፕን እንደሚደግፍ አልተናግረም ነበር፣ በዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ የተደረገባትን ቅጽበት ግን ድጋፉን ይፋ ለማድረግ ተጠቀመበት።
የ2024 የምርጫ ውጤት ተከትሎ የመጡ የፖሊሲ ለውጦች አሜሪካም ሆነ አጋሮቿንና ጠላቶቿን በተመለከተ የተደበላለቀ ስሜት ውስጥ የከተተ፣ ምናልባትም ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ወዲህ የነበረውን የሃገራትን ግኑኝነት የማይገመት ያደረገ፣ በአሜሪካ ከወጭና እዳ ቅነሳ ጋር በተገናኘ በርካታ መስሪያ ቤቶችንና ፕሮግራሞችን እንዲዘጉ ያደረገ፣ በአጠቃላይ ከምን ጊዜውም በበለጠ የነገን ተገማችነት ያስቀረ ሆኖ ቀጥሏል። ይህ ሁሉ የተፈጠረው በሁለት ወራት ሲሆን የትራምፕ አስተዳደር ገና ሶስት አመት ከአስር ወር እንዳለው ስናውቅ ገና ምኑን አየነው የሚያስብል ነው።
ምናልባትም ስለዚህች ትዊት በወደፊት የታሪክ መማሪያ መጽሃፍ ላይ ብዙ ተብሎ ልናይ እንችል ይሆናል።

👍45❤4👎1
እንኳን ለፊቼ ጨምበላላ በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉን ምክንያት በማድረግ ለበዓሉ ድምቀት ይሆናሉ ያልናቸው መነፅሮች ሀዋሳ አስገብተናል።
በማንኛውም ሰዓት ፒያሳ አዋሽ ባንክ በመምጣት መግዛት ይችላሉ ወይንም ብዛት የሚወስዱ ከሆነ ያሉበት እናደርሳለን።
+251701319932
@Fikerassefa
ይደውሉ

😁18👍6❤3