የግል ንግድ ባንኮች በገጠማቸው የጥሬ ገንዘብ እጥረት መክፈል ወደማቆም መድረሳቸውን ቢናገሩም ፤ የብሔራዊ ባንክ ም/ል ገዢ ችግሩ የለም ብለዋል
👉🏼 ባለሃብቶች ወደ ኋላቀር የካዝና ቁጠባ ዘዴ መመለሳቸዉን ተናግረዋል
የግል ንግድ ባንኮች የገጠማቸው የጥሬ ገንዘብ እጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ቀጥሎ ለደንበኞቻቸው መክፈል የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ዋዜማ ያሰባሰበችው መረጃ ያመለክታል። የጥሬ ገንዘብ ዕጥረቱን ተከትሎ፣ ባለሀብቶችና ነጋዴዎች ጥሬ ገንዘብ ወደ ባንክ ከማስገባት ይልቅ ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም እንደተገደዱ ነግረውናል ስትል ዋዜማ ራዲዮ ዘግባለች። ያነጋገርናቸው ነጋደዎች እና ባለሀብቶች፣ ገንዘባቸውን ቀስ በቀስ ከባንክ እያወጡ በግል ካዝናና ስውር ቦታዎች ማስቀመጥ መምረጣቸውን ይናገራሉ። የባለሀብቶቹ ስጋት በባንክ የተቀመጠ ገንዘባቸውን በፈለጉት ፍጥነት ለማግኘት በመቸገራቸውና የተለያዩ ገደቦች ስለተጣለባቸው ነው።
አንዳንድ ባንኮች ባለፉት ወራት አልፎ አልፎ ለተመረጡ ደንበኞች ሲፈቅዱ የነበረውን ከባንክ ወደ ባንክ የገንዘብ ዝውውር (RTGS) አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ወደማቆም እየመጡ መሆናቸው የባንክ ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡ ዋዜማ ከነጋገረቻቸው የግል ንግድ ባንክ የሥራ ኃላፊዎች አንዱ “ዛሬ አንድ ሚሊየን ብር አስገብቶ ነገ ሲመጣ የሚፈልገውን ያክል ወጪ እንደማልሰጠው እያወቀ እንዴት ይመጣል?” ሲሉ የነጋዴዎች ጥሬ ገንዘብ መከዘን ገንዘባቸውን በፈለጉበት ጊዜ ማንቀሳቀስ አለመቻል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ዋዜማ ያጋገረቻቸው የተለያዩ ባንኮች የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች፣ የሚመሩትን ቅርንጫፍ ከ50 ሺህ ብር ባነሰ አዳሪ ገንዘብ ዕለታዊ ሂሳባቸውን የሚዘጉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ጠቁመዋል፡፡ የባንክ ቀርንጫፎች ለደንበኞቻቸው የሚከፍሉት ገንዘብ ሲያጥራቸው ከዋና መስሪያ ቤት (ትሬዠሪ) ገንዘብ እንዲላክላቸው በስፋት ጥያቄ እያቀረቡ ቢሆንም፣ ዋና መስሪያ ቤት ቋት ላይ እጥረቱ ስለበረታ የጠየቁትን ያክል ማግኘት አንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡
በተለይ ለተርታ ለደንበኞቻቸው የሚፈቅዱት ዕለታዊ ወጭ አንዳንዶ ከ10 ሺሕ ብር ያልበለጠ ሲሆን፣ ከፍተኛ የደንበኞች ቅሬታ እያስተገዱ ነው፡፡ በብሔራዊ ባንክ ሕግ መሰረት አንድ የባንክ ደንበኛ በቀን እስከ 50 ሺሕ ብር ጥሬ ገንዘብ የማውጣት መብት አለው፡፡ ከተከሰተ ወራት ያስቆጠረው የጥሬ ገንዘብ እጥረት አሁን ላይ በተለይ የግል ባንኮችን በእጅጉ እየፈተነ መሆኑን ዋዜማ ከተለያዩ የባንክ ምንጮቿ ሰምታለች፡፡
ቀድም ሲል በተለይ አነስተኛ አቅም ካለቸው ባንኮች መካከል የሚመደቡት ላይ በርትቶ የነበረው የጥሬ ገንዘብ እጥረት፣ አሁን ላይ አንጋፋ የግል ንግድ ባንኮች ላይም መበርታቱን ዋዜማ ከራሳቸው ከባንኮቹ ምንጮቿ አረጋግጣለች። ችግሩ ከበረታባቸው የግል ባንኮች መካከል አንዱ በተለይ የነዳጅ ክፍያ በቴሌ ብር አማካኝነት እንዲሰበሰብ መወሰኑን ተከትሎ፣ በየቀኑ ከነዳጅ አዳዮች የሚያገኘውን በሚሊየን የሚቆጠር የጥሬ ገንዘብ ገቢ ማጣቱ ችግር ውስጥ እንዳስገባው የባንኩ ምንጮች ነገረውናል፡፡ የግል ንግድ ባንኮች በገጠማቸው የመከፈል አቅም ውስንነት በርካታ የባንክ ደንበኞቻቸው የሚያንቀሳቅሱትን ገንዘብ ወደ መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማዞራቸውን ከግል ባንኮች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እስካሁን የጥሬ ገንዘብ እጥረት ውስጥ ካለመግባቱም በላይ ከዚህ ቀደሙ የተሻለ ጥሬ ገንዘብ በስፋት እየሰበሰበ ነው፡፡ ባንኩ ደንበኞች ገንዘባቸውን በሚፈልጉበት ጊዜ ብሔራዊ ባንክ ባስቀመጠው ጣሪያ ልክ፣ ያለገደብ ጥሬ ገንዘብ ማውጣት የሚችሉበት ብቸኛ ባንክ ሆኗል፡፡ ዋዜማ በባንኮች በኩል ያገኘችውን የጥሬ ገንዘብ እጥረት ችግር የባንኮች ተቆጣጣሪ አካል እንዴት እንደሚመለከተው የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥን ፍቃዱ ደግፌን የጠየቀች ሲሆን፣ ባንኮች በሚሉት ደረጃ እጥረት መኖሩን የባንኩ መረጃ እንደማያመላክት ነግረዋታል፡፡
ፍቃዱ ጉዳዩን “እኔ ባለኝ መረጃ ባንኮች ላይ በሚባለው ደረጃ የጥሬ ገንዘብ እጥረት (ሊኪዩዲቲ) የለም” ብለዋል፡፡ ባንኮች ከነዳጅ አዳዮችና ከሌሎች የተለያዩ ደንበኞች በየእለቱ ያገኙት የነበረውን የጥሬ ገንዘብ ገቢ በግዴታ ወደ ቴሌ ብር ስርዓት መቀየሩን ተክትሎ ገጥሞናል ያሉትን ችግር በተመለከተ፣ ምክትል ገዥው ለዋዜማ በሰጧት አስተያየት፣ “እጥረት አለብን ካሉ ተወዳድሮ መሰብሰብ ነው የሚከለክል ሕግ የለም” በማለት ገልጸውታል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa

👍55❤5
አማራ ባንክ ከፋይናንሻል ቴክኖሎጂ አቅራቢዎች እና ኦኘሬተሮች ጋር ያለዉን ግንኙነት በማጠናከር የተለያዩ ዲጅታል ባንኪንግ ኘሮግራሞችን ለደንበኞቹ ለማቅረብ እቅድ ይዤ እየሰራሁ ነው አለ።
ባንኩ በዲጅታል የፋይናንስ እድገት ላይ አተኩሮ እየሰራ መሆኑን የተናገሩት የባንኩ ምክትል ቺፍ አቶ በፍቃዱ ሸሪፍ አዳዲስ ከቴክኖሎጂን ከሚያቀርቡ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት በእቅድ ላይ ነን ብለዋል።ባንኩ ባሳለፍነው በጀት ዓመት ከቴክኖሎጂ አቅራቢዎች(ፊንቴኮች)ጋር በመስራት የተለያዩ የዲጂታል ባንኪንግ ስርአትን ለደንበኞቼ አቅርቤአለሁ ብሏል።
በዚህም መሰረት ባንኩ ለ 50 ሺህ ደንበኞች በአጭር ጊዜ የክፍያ ካርዶችን ማቅረቡን የተናገረ ሲሆን ለማንኛውም የቢል ክፍያ የቴክኖሎጂ ትስስር በመፍጠር ክፍያዎችን በሞባይል ባንኪንግ እንዲከፍሉ ማስቻሉን ተናግሯል።
የትምህርት ቤት ክፍያ አባስኩል ፔይ የተሰኘ አገልግሎት፣ የሆቴል መያዝ፣ የሜትር ታክሲ ክፍያን ደንበኞች በሞባይል ባንኪንግ መፈፀም እንዲችሉ ማድረግ፣ የኦንላይን ግብይት፣ የኪው አር (QR) የተሰኘ የመክፈያ አማራጭ ለንግድ ተቋማት እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶችን ለደንበኞቹ ማቅረቡን ከባንኩ ሰምተናል።
ባንኩ በ2016 እሰራባቸዋለው ብሎ ካቀዳቸው መካከል የወኪል(ኤጀንሲ) ባንኪንግ መጀመር የሚለው ይገኝበታል።አማራ ባንክ ኦላይን ባንክ ተጠቃሚዎቼ 200 ሺህ ተጠግተዋል ያለ ሲሆን 1.3 ሚሊዮን ደንበኞች ማፍራት እንደቻለም ጠቅሷል፡፡
[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa

👍32❤3
በሞሮኮ በርዕደ መሬት ሳቢያ ቢያንስ 632 ሰዎች ሞቱ!
በሞሮኮ በመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ ቢያንስ 632 ሰዎች ሞቱ።የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳለው በ6.8 የተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል።
በዋነኛነት የመሬት መንቀጥቀጡ የተሰማው በአትላስ ተራራ አካባቢ ነው።ይህም ከማራኬሽ በደቡብ ምዕራብ 71 ኪሎ ሜትር ርቆ ይገኛል። ጥልቀቱም 18.5 ኪሎ ሜትር ነው።
በማራኬሽና በሌሎችም ደቡባዊ አካባቢዎች ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል።አል-ሀውዝ፣ ማራኬሽ፣ ኦራዛቴ፣ አዚል፣ ክሪቾዋ እና ታራውዳንት በተባሉት አካባቢዎች ነው ሰዎች የሞቱት።በመሬት መንቀጥቀጡ ሕንጻዎችና ጎዳናዎች ሲጎዱ የሚያሳዩ ቪድዮዎች ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ወጥተዋል።
[BBC]

👍19❤2
በጋምቤላ ክልል 13 አመራሮች ከኃላፊነታቸው ተነሱ!
ባለፈው ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር ምክንያት በማድረግ በተካሄደ ግምገማ 13 አመራሮች ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ አስታወቁ፡፡እንዲሁም 55 አመራሮች አዲስና የሽግሽግ ሹመት መሰጠቱን ነው አቶ ኡሞድ ያስታወቁት፡፡
ሙሉ በሙሉ ከኃላፊነታቸው የተነሱት አመራሮች በብልሹ አሰራር፣ በአፈፃፀማቸውና በፀጥታ ችግር ክፍተት የታየባቸው ናቸው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡አዲስና በሽግሽግ ወደ ሹመት የመጡ አመራሮች የክልሉን ህዝብ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ይፈታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡
በክልል ማዕከል የተጀመረው አመራሩን የማጥራት ተግባር በቀጣይ በዞንና በወረዳ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡ህዝቡ ለክልሉ ሰላምና ልማት ከዚህ በፊት ሲያደርግ እንደነበረው ሁሉ አሁንም ከመንግሥት ጎን በመሆን የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
Via FBC

👍16❤3
በሞሮኮ የመሬት መንቀጥቀጥ ሟቾች ቁጥር ከ1000 አልፈ!
ያልተለመደና እጅግ ክፉኛ የተባለው የሞሮኮ ርዕደ መሬት አርብ ምሽት ተከስቶ ከ1 ሽህ በላይ ሰዎችን ህይወት መቅጠፉ ተነግሯል።አደጋው በታሪካዊቷ ማራካሽ ከተማ ጥንታዊ ህንጻዎችን ዶግ አመድ ማድረጉ ታውቋል።
እስካሁን ድረስ የርዕደ መሬቱ ሙሉ የሟቾች ቁጥር ያልታወቀ ሲሆን፤ በአደጋው ክፉኛ በተጎዱ አካባቢዎች የነፍስ አድን ሰራተኞች መድረስ አለመቻላቸውን አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል። 6.8 ሬክተር ስኬል የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ በሞሮኮ ከ120 ዓመታት በኋላ በእጅጉ የከፋ ነው ተብሏል።
@YeneTube@FikerAssefa

👍14❤3
የ5 ጂ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በይፋ ተጀመረ!
ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛው ትውልድ (5 ጂ) የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በይፋ አስጀመረ።ኢትዮ ቴሌኮም የ5 ጂ አገልግሎትን በአዲስ አበባ በተለያዩ አካቢዎች በሚገኙ በ145 ስፍራዎች ማስጀመሩን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።
የ5 ጂ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት እስከ 10 ጊጋባይት በሰከንድ የሚደርስ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው መሆኑ ተመላክቷል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በይፋ ማድረጊያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የ5 ጂ አገልግሎት ስራ ላይ መዋሉ የማህበረሰባችንን ህይወት የሚያቀሉ ዲጂታል መፍትሄዎችን በቀላሉ በማቅረብ ተሞክሯቸውን የሚያሻሽል መሆኑን ተናግረዋል።ደንበኞች የ5 ጂ አገልግሎትን ለመጠቀም የሚያስችሉ መሳሪያዎችና ቀፎዎች ሊኖራቸው እንደሚገባም ተመላክቷል።
Via Walta

👍44👎24❤9
የህዳሴው ግድብ አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት ተጠናቋል - ጠ/ሚ ዐቢይ
የህዳሴው ግድብ አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ4ኛውን ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቅ አስመልክቶ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
“ኢትዮጵያውያን ተባብረን በመሥራታችን ፈጣሪ ረድቶናል፤ በገንዘባችሁ፣ በዕውቀታችሁ፣ በጉልበታችሁና በጸሎታችሁ በሥራው ውስጥ የተሳተፋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል።ኢትዮጵያውያን በግድቡ ግንባታ ያሳዩትን ህብረት በሌሎች ጉዳዮችም እንዲደግሙትም ጠይቀዋል።
በግድቡ ግንባታ ከውስጥን ከውጭም ጫናዎች እንደነበሩ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈተናዎችን በመቋቋም ለዚህ ስኬት ደርሰናል ብለዋል።“ለግድቡ የምናደርገውን ማናቸውንም ድጋፍ እስከ ፍጻሜው እንድንቀጥል በዚሁ አጋጣሚ አደራ እላለሁ” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

👎76👍61🔥4❤3
11ኛው የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል!
11ኛው የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል፡፡በስነ ስርዓቱም ላይ በ10 ዘርፎች ለሀገራቸውና ለህዝባቸው የተለያዩ ተግባራትን ላከናወኑ ሰዎችና ተቋማት እውቅና ተሰጥቷል።
በዚህም መሰረት የዓመቱ የበጎ ሰው እውቅና ከተሰጣቸው ውስጥ፡-
1. በመምህርነት ዘርፍ አዝማች ይርጋ ገብሬ፣
2. በባህል፣ቅርስ እና ቱሪዝም ዘርፍ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም፣
3. በንግድ ኢንዱስትሪና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ ኩሪፍቱ ሪዞርት እና ስፓ፣
4. በበጎ አድራጎት ዘርፍ እቴነሽ ወንድምአገኘሁ
5. በኪነ ጥበብ (ስዕል) ዘርፍ ሰዓሊ ወርቁ ጎሹ፣
6. መንግስታዊ የስራ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት ዘርፍ ያየህይራድ ቅጣው (ዶ/ር) እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡
ስነ ስርዓቱ አሁንም እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን በቀሪ 4 ዘርፎች የሚካሄዱ ሽልማቶች ተጠባቂ ናቸው፡፡

👍41👎17❤5🔥3
ለዘመን መለወጫ በዓል 21 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል!
ነገ የሚከበረውን የ2016 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ 21 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል። ነገ ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
ነገ የሚከበረውን የ2016 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ 21 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል። ነገ ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
👎13👍5🔥5❤3
በአዲስ አበባ ከተማ 24 ማዳበሪ ከበዓድ ነገሮች ጋር የተቀላቀለ ቅቤ ተያዘ!
በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ አየር ጤና ቻይና ካምፕ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተሰራ የቁጥጥር ስራ ለበዓል ሊሸጥ የነበረ ከባዕድ ነገር ጋር የተቀላቀለ ቅቤ መያዙን የኢትዮጲያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መመሪያ የጅማ በር ፖሊስ ጣቢያ ጋራ በጋራ በመሆን በሚቀርቡ የምግብ ምርቶች ላይ የቁጥጥርና የክትትል ስራዎች ሲከናወን መቆየቱን የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አበራ ደመቀ ተናግረዋል።
የህብረተሰብን ጥቆማ መሰረት በማድረግ በተወሰዱ እርምጃዎች ቅቤን ከበዓድ ነገሮች የሚያቀላቅሉና በስፋት በሚያከፋፍሉት ተቋማት ላይ በተካሄደ ቁጥጥር 24 ማዳበሪያ ወይም 1ሺ440 ኪሎ ግራም የሚሆን ግምታዊ ዋጋው ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ ከባእድ ነገር ጋር የተቀላቀለ ቅቤ ተይዛል።
በተጨማሪም ከቅቤ ጋር ለመቀላቀል የተዘጋጀ ንፃህናው ባልጠበቀ መልኩና ከቅቤ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር ርካሽ ዋጋ ያለው የአትክልት ቅቤ እና የፓልም ዘይት ተይዟል።210 ካርቶን 3ሺ360 ኪሎ ግራም የአትክልት ቅቤ እና ፓልም ዘይት ግምታዊ ዋጋው ከ650,000 ብር በላይ የሚያወጣ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ተቋማቱም እንዲታሸጉ መደረጉንም አቶ አበራ ጨምረው ተናግረዋል።
ህብረተሰቡ የምግብ ምርቶችን ሲገዛ ፍቃድ ካላቸው ተቋማት ገዝቶ እንዲጠቀም እንዲሁም አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች ሲያጋጥም በ8482 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡
Via Bisrat FM

👍42❤3
የዛሬ ጨዋታዎች የቤትስኬት ግምት
ጀርመን፣ ስፔን፣ እንግሊዝ፣ ቤልጅዬም እና ኢኳዶርን የተመለከቱ የቤቲንግ መረጃዎች እና ግምቶች በቤትስኬት
ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ👇👇
http://www.betsket.com/የዛሬ-ጨዋታዎች-የቤትስኬት-ግምት-2/
ሁል ጊዜ የሚለቀቁ መረጃዎችን በአንድ ላይ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።👉 @betskett

👍2
በሊቢያ ባጋጠመው የጎርፍ አደጋ ከአንድ ከተማ ብቻ የ1ሺህ ሰዎች አስክሬን ተነሳ!
በሊቢያ ባጋጠመ የጎርፍ አደጋ በምስራቅ የአገሪቱ ክፍል ከምትገኘው ደርና ከተማ ብቻ የሟቾች ቁጥር ከ1ሺህ በላይ መሆኑን አካባቢውን የጎበኙ ከፍተኛ ባለስልጣን አስታወቁ።“የሰዎች አስክሬን በየቦታው ወድቆ ይገኛል” ብለዋል መቀመጫውን ምስራቃዊ ሊቢያ ያደረገው መንግሥት ሚንስትር።
100ሺህ ነዋሪ ባላት ደርና ከተማ ውስጥ የነበሩ ሁለት ግድቦች እና አራት ድልድዮች ከተደረመሱ በኋላ ከተማዋ ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ በውሃ ተውጣለች።የቀይ መስቀል ማኅበር በወደብ ከተማዋ ደርና እስካሁን ድረስ 10ሺህ ነዋሪ የገቡበት አለመታወቁ ሪፖርት ተደርጓል ብሏል።
እሁድ ዕለት የዘነበው ከፍተኛ ዝናብ ቤንጋዚ፣ ሶውሳ እና አል-ማርጅ ከተሞችን ጨምሮ በምስራቅ ሊቢያ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል።“እስካሁን የ1ሺህ ሰዎች አስክሬን ተነስቷል። የከተማዋ ሩብ ክፍል ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል ብል ማጋነን አይሆንም። በጣም ብዙ ብዙ ሕንጻዎች ፈርሰዋል” ብለዋል የአቪዬሽን ሚንስትሩ እና የአስቿኳይ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ አባሉ ሂቼም ቻኪኦት።
በሊቢያ የቀይ መስቀል ኃላፊ የሆኑት ታሚር ራማዳን በጎርፍ አደጋው ምክንያት የሟቾች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።ኃላፊው ከጎረቤት አገር ቱኒዚያ ሆነው፤ “የሥራ ባልደረቦቻችን ተጎጂዎችን ለመርዳታ የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ ነው። አሁን የሟቾችን ቁጥር በተመለከተ ትክክለኛው አሃዝ የለንም። እስካሁን ድረስ ግን አድራሻቸው የጠፉ ሰዎች ቁጥር ከ10ሺህ ተሻግሯል” ብለዋል።
Via BBC

👍32❤3👎2🔥1
አፕል አይፎን 15ን ይፋ አደረገ!
አፕል የቀጣዩን ትውልድ አይፎን 15ን ዛሬ አስተዋውቋል። አዲስ ይፋ የተደረጉት ሞዴሎች ከዚህ ቀደሙ በተለየ የዩኤስቢ ሲ(USB Type-C) የቻርጀር መሰኪያ የሚኖራቸው እንደሆነ ተገልጿል። የአውሮፓ ህብረት አምና ባወጣው ህግ በአባለ ሃገራቱ የሚመረቱ ሁሉም ስልኮች ተመሳሳይ የዩኤስቢ ፖርት እንዲኖራቸው መባሉ ይታወሳል።

👍51👎14❤2🔥2
በመዲናዋ የዘመን መለወጫ በዓል ያለምንም አደጋ መከበሩ ተገለጸ!
የ2016 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል ያለምንም አደጋ በሰላም ተከብሮ ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።
የ2016 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በዋዜማውም ሆነ በበዓሉ ዕለት እሳትና መሰል አደጋዎች ሳያጋጥሙ በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽኑ በዓሉ ከመድረሱ በፊት በተለያዩ አማራጮች ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
በዚህም ህብረተሰቡ ከኮሚሽኑ የተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረጉ በዓሉ ያለ ምንም አደጋ ክስተት በሰላም መከበሩን አመልክተዋል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ህብረተሰቡና የሚዲያ ተቋማት አደጋን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ ላደረጉት አስተዋጽዖ ምስጋናውን በማቅረብ በቀጣይ በሚኖሩ በዓላትና በመደበኛ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ተመሳሳይ ጥንቃቄዎች እንዲደረጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

👍44❤2🔥1
የአሜሪካ ም/ቤት በባይደን ላይ የሙስና ምርመራ እንዲያካሂድ አፈ ጉባኤው አዘዙ!
ፕሬዝደንት ባይደን፤ ልጃቸው ሃንተር ባይደን በውጪ ሀገራት ካለው የንግድ ሽርክና ተጠቃሚ ናቸው በሚል ምርመራ እንዲደረግባቸው ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን የአሜሪካው የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ከቪን ማካርቲ ዛሬ አስታውቀዋል።በባይደን ላይ የቀረበው ክስ “የሙስና ባህል እንዳለ አመላካች ነው” ሲሉ ማካርቲ ለሪፖርተሮች ተናግረዋል።
“ፕሬዝደንት ባይደን የቤተሰባቸውን የውጪ ንግድ ሽርክና በተመለከተ የአሜሪካን ሕዝብ ዋሽተዋል። በርካታ የስልክ ውይይቶች፣ ግንኙነቶች፣ የእራት ግብዣዎች መደረጋቸውን እንዲሁም ተሽከርካሪዎች እና በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ወደ ልጃቸው እና የንግድ ሸሪኮቻቸው መላኩን የዐይን ምሥክሮች ቃላቸውን ሰጥተዋል” ብለዋል ማካርቲ።
“20 ሚሊዮን ዶላር ወደ ባይደን የቤተሰብ ዓባላት እንደተላከ የባንክ አካውንት መዝገቦች እንደሚያሳዩ እናውቃለን” ሲሉ አክለዋል ማካርቲ።ማካርቲ በተጨማሪም፤ የንግድ ግንኙነቱን ለማሳለጥ ባይደን ኦፊሴላዊ ቢሯቸውን ተጠቅመዋል፣ አስተዳደራቸውም ልዩ እገዛ አድርጓል ብለዋል።
የም/ ቤቱ በርካታ ኮሚቴዎች ለውንጀላው ማስረጃ ገና እንዳላቀረቡ የቪኦኤዋ ካትሪን ጂፕሰን ዘገባ አመልክቷል።በሴኔቱ አብላጫ ቁጥር ያለው የዲሞክራቲክ ፓርቲው መሪ ቸክ ሹመር ምርመራውን “አስቂኝ” ሲሉ አጣጥለውታል።

👍52❤2
ሚኒስቴሩ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓትን የተማሪዎች መለያ አድርጎ ሊተገብር ነው!
የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓትን በትምህርት ተቋማት መደበኛ የተማሪዎች መለያ አድርጎ ለመተግበር ወሰነ፡፡
ሚኒስቴሩ ሥርዓቱ መተግበሩ የተማሪዎችን ማንነት በወጥነት መለየት እንዲያስችለው ያግዛል ተብሏል።
ዲጂታል መታወቂያ በሁሉም የትምህርት ተቋማት ዋና የማንነት ማረጋገጫ ሥርዓት ሆኖ ማገልገል የሚያስችል መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

👍18❤13🔥2