300 ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብትና የፕሬስ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግሥት በአማራ ክልል ላይ የጣለውን የኢንተርኔት እገዳ እንዲያነሳ ባወጡት የጋራ መግለጫ ጠይቀዋል።
መንግሥት በክልሉ ላይ የጣለው የኢንተርኔት እገዳ፣ "ዓለማቀፍ ሕጎን የሚጻረር" መኾኑን ድርጅቶቹ ገልጸዋል። "በግጭት ወቅት ኢንተርኔት ማቋረጥ "የሰዎችን ሕይወት አደጋ ላይ ይጥላል" ያሉት ድርጅቶቹ፣ በግጭት ቀጠና የሚገኙ ሰዎች "እጅግ አስፈላጊ መረጃዎችን እንዳያገኙ መሰናክል እንደሚኾንም" ገልጸዋል። ድርጅቶቹ፣ በክልሉ ግጭቱ እየተባባሰና የጸጥታው ኹኔታ እያሽቆለቆለ በሄደበት ወቅት ሰዎች ከውጭው ዓለም ጋር በመገናኘት "በግጭቱ ስለደረሱ ጉዳቶችና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሪፖርት ማድረግ መቻል አለባቸው" ብለዋል።
@YeneTube @FikerAssefa

👍42❤5👎2🔥1
ሰሜን ኮሪያ በዩክሬን ጦርነት ለሩሲያ ሙሉ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች!
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ የሩሲያን ፕሬዚዳንት “ሙሉ በሙሉ እና ያለቅድመ ኹኔታ” እንደሚደግፉ አስታወቁ።በምሥራቅ ሩሲያ የተገናኙት ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ስብሰባ፣ ሞስኮብ ዩክሬን ላይ ለከፈተችው ጦርነት መሣርያ የምታገኝበት መድረክ ሊኾን ይችላል፤ ስትል አሜሪካ በማስጠንቀቅ ላይ ናት፡፡
በምሥራቅ ሩሲያ በሚገኝ የመንኮራኩር ጣቢያ ውስጥ መሪዎቹ ለአራት ሰዓታት ባደረጉት ስብሰባ፣ የሁለቱ ሀገራት ፍላጎቶች አንድነት እንደተንጸባረቀበት ተመልክቷል።ፑቲን፣ ድኻ ብትኾንም የሮኬት እና የጦር መሣሪያ ከፍተኛ ክምችት ካላት ሰሜን ኮሪያ የሚፈልጉት አለ።
ከኀምሳ ዓመታት በፊት በነበረው የኮሪያው ጦርነት፤ ሞስኮብ፣ ደቡብ ኮሪያን ለወረረችው ሰሜን ኮሪያ መሣሪያ ለግሳ ነበር። አሁን ደግሞ፣ ሰጪ እና ተቀባዩ ቦታ እንደተቀያየሩ ተዘግቧል።
በምትኩ ኪም ጁንግ ኡን፣ የወታደራዊ ሳተላይትን በማበልጸግ ረገድ የሩሲያን ርዳታ ይሻሉ። ይህም፣ በተደጋጋሚ ለከሸፈባቸውና ወታደራዊ ሳተላይትን ወደ ህዋ ለማምጠቅ የሚያደርጉትን ጥረት እንዲያግዝ ነው፤ ተብሏል።
“ሩሲያ፣ ፍትሐዊ ጦርነት እያካሔደች ናት፤” ያሉት ኪም ጆንግ ኡን፣ ሰሜን ኮሪያ፥ የሩሲያ መንግሥት፣ “በጦርነቱ የሚወስዳቸውን ማንኛውንም ርምጃዎች፣ ሙሉ በሙሉ እና ያለቅድመ ኹኔታ ትደግፋለች፤” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
Via VoA

👍104❤9🔥5
Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።
በማንኛውም Social Media Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::
ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።
Telegram: @adsommar
📞0929334267

👍7🔥1
የአለም ባንክ የግል ዘርፍ አጋር የሆነው የአለም አቀፉ የገንዘብ ኮርፖሬሽን/IFC ኢንቨስትመንትን ጨምሮ ድጋፍ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያን ባለስልጣን ጋር ስምምነት አደረገ!
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከአለም አቀፍ የገንዘብ ኮርፖሬሽን ጋር ለአራት ዓመታት የሚቆይ ፕሮጀክት ስምምነት መፈራረማቸው አሳዉቀዋል።በስምምነቱ መሰረት IFC ሁሉን አቀፍ ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን።የካፒታል ገበያው ስራ በሚጀምርበት ወቅት ገበያ ውስጥ ኢንቨስት በማድረግ ጭምር የተገበያዮችን በገበያው ላይ መተማመን እንዲፈጥሩ ለማድረግ የሚረዳ ሚና ይጫወታል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ልማት ፕሮጀክት ለአራት ዓመታት እንደሚቆይና በተመሳሳይ መልኩ በሌሎች የአፍሪካ ሃገራት የካፒታል ገበያዎችን በመደገፍ ለገበያ የሚቀርቡ የመንግስት ሰነዶች ዉጤታማ እንዲሆኑ የበኩሉን ከመጫወት በዘለል የካፒታል ገበያ ግብይት አቅርቦት የማሳደግ ሚና መጫወት ችሏል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት " የአለም አቀፍ የገንዘብ ማህበር የግል ዘርፉን በማነቃቃት እና ዋስትና በመስጠት አስፈላጊዉን የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም በመንግሥት ቦንድ ላይ ኢንቨስት በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለዉ" ብለዋል።ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) እና የአለም አቀፍ የገንዘብ ማህበር የአፍሪካ ዳይሬክተር አሊዩ ማይጋ ናቸው።
Via Capital

👍22❤1
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከመስከረም 7 ጀምሮ መደበኛ የመማር ማስተማር ስራዉ እንደሚጀመር አስታወቀ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ "የጋራ መግባባት ለዉጤታማ መማር ማስተማር" በሚል መሪ ቃል የ2016 ትምህርት ዘመን አጀማመርን በሚመለከት በከተማዋ ከሚገኙ ከሁሉም ትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን ጋራ ዉይይት እያካሄደ ይገኛል።
መስከረም 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ዉይይቱን ያደረገዉ ትምህርት ቢሮው በ2016 ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራዉ በማስቀጠል በትምህርት ቤቶች ብዝሃነትን በማስተናገድ እንዲሁም በ2015 ዓ.ም. የተስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን ከመከላከል አንፃር ሊደረግ የሚገባዉን ቀጣይ አቅጣጫ አስመልክቶ ሰነድ ቀርቧል።
የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር እንደተናገሩት "በ2016 ዓ.ም. መደበኛ የመማር ማስተማር ስራዉ ከመጪው ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ይጀምራል" ብለዋል።

👍30👎7❤3🔥2
ብሔራዊ የሠራተኞች ዲጂታል መታወቂያ በመንግሥት ተቋማት ሊተገበር ነው!
ብሔራዊ የሠራተኞች ዲጂታል መታወቂያ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ የመንግሥት ተቋማት ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንና የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ሥራውን በጋራ ለማከናወን መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የቴክኒካል ዳይሬክተር ኢዮብ ዓለሙ እንዳሉት÷ የዲጂታል መታወቂያ የመንግሥት ተቋማት የሰው ሃብት አስተዳደር ሥርዓትን ለማዘመን እና ለመንግሥት ውሳኔዎች መረጃ ለማደራጀት ያግዛል፡፡
እንዲሁም ወጥ የሆነ የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራሙ የአሠራር ክፍተቶችን እንደሚቀንስ አንስተው÷ ከሙስናና ብልሹ አሠራር የጸዳ አገልግሎትን ለመስጠት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የመንግስት ሠራተኞችን ሠነዶች ትክክለኝነት እና ተዓማኒነት በማረጋገጥ ረገድም ሚናው የላቀ ነው ብለዋል፡፡የኮሚሽኑ የዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ እና የመረጃ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ይርጋ (ዶ/ር)÷ ሁሉንም የመንግሥት ሠራተኞች መረጃ በብሔራዊ ቋት በመመዝገብ ሠራተኞቹ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ነው ያሉት።የሠራተኛ ቁጥርን በአግባቡ ለማወቅና ቀልጣፋ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ እንደሚያግዝም አመላክተዋል፡፡
Via FBC

👍24👎2❤1
ፀሐይ ባንክ የክሬዲት ካርድ አገልገሎት መስጠት መጀመሩን ተናገረ።
ባንኩ ይህን የክሬዲት ካርድ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የተናገረው በዛሬው እለት በዋና መስሪያ ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።ፀሐይ ባንክ ዛሬ የጀመረው የክሬዲት ካርድ አገልግሎት ከተለመደው የዴቢት ካርድ የሚለየው ደንበኞች በተፈቀደላቸው የብድር መጠን የብድር ዘመኑ እስከሚያበቃ ድረስ እንደፈለጉ መጠቀም የሚችሉ ሲሆን፤ ይህም ደንበኞቻች ለሚገጥማቸው ጊዜያዊ ወይም አስቸኳይ የገንዘብ ችግር ትልቅ መፍትሄ የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡
ደንበኞች የክሬዲት ካርዱን ለመጠቀም ምንም አይነት ማስያዣ ማቅረብ አይጠበቅባቸውም ሲባልም ተሰምቷል።የሚከፍሉት የአገልግሎት ክፍያም እጅግ ተመጣጣኝና በተጠቀሙት የገንዘብ መጠን ልክ ብቻ ይሆናል ሲሉ የባንኩ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ያሬድ ተናግረዋል፡፡
ፀሐይ ባንክን ይህንን አገልግሎት መስጠት የጀመረው ከባንኩ ጋር የስራ ግንኙነት ላላቸው ተቋማት ሰራተኞች እና የባንኩ ቀዳሚ ደንበኞች ሲሆን፣ አግልግሎቱ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞችን ያካትታል ተብሏል።
የክሬዲት ካርድ አገልግሎቱ ደንበኞች የሚገጥማቸውን ጊዜያዊ የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ ያግዛል፣ከባንኩ በብድር የሚያገኙትን ገንዘብ በካርድ ጠቀም ያስችላቸዋል፣ለግብይት የሚያስፈልጋችውን ገንዘብ ወዲያው ተጠቅመው ቆይተው እንዲከፍሉ ያስችላቸዋል ተብሏል።
የፀሐይ ባንክ የክሬዲት ካርድ አገልግሎት ከባንክ ብድር ማግኘት ላልቻሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመድረስ ከፍተኛ አቅም ይፈጥራል ሲሉ ስራ አስፈፃሚው አስረድተዋል።ከዚህ በተጨማሪም የክሬዲት ካርድ ተጠቃሚ ደንበኞች ብድር ታሪክ መመስረትና መሰነድ የሚያስችላቸው ሲሆን ወደፊት ለሚኖራቸው ማንኛውም ዓይነት የብድር አገልግሎት ጥያቄ ትልቅ ውሳኔ መረጃ ግብዓት በመሆን እንደሚያገለግል ታምኖበታል፡፡
ደንበኞች የወሰዱትን ብድር ተጠቅመው ሲመልሱ የብድር መጠናቸው እያደገ እንደሚሄድ ተነግሯል።የክሬዲት ካርድ ብድር መመለሻ ጊዜው ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት ሲሆን የደንበኞች መመለስ አቅምና ፍላት እየታየ አገልግሎቱ እንደሚራዘም አቶ ያሬድ አስረድተዋል።
የፀሐይ ባንክ ደንበኞች ሒሳብ ወደ ከፈቱበት ቅርንጫፍ በመሄድ የክሬዲት ካርድ ባለቤት መሆን ይችላሉ ተብሏል፡፡ሓምሌ 16/2014 ስራ የጀመረው ፀሐይ ባንክ የቅርንጫፎቹ ብዛት 82፣ የደንበኞቹ ብዛት ደግሞ ከ280 ሺህ በላይ እንደደረሱለት ተናግሯል።የተከፈለ ካፒታሌ 1.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል ያለው ባንኩ አጠቃላይ ሀብቱ ደግሞ 3.5 ቢሊየን ብር እንደሆነ ተሰምቷል።
Via Sheger FM

👍58❤10🔥2
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን ሁኔታ የተመለከተ ዓመታዊ ባለ 29 ገጽ ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡
ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ በተጨማሪነት ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ላይ በማተኮር የታዩ መልካም እመርታዎች፣ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ አሳሳቢ ጉዳዮች እና ምክረ ሐሳቦችን አካቷል።

👍19❤7
ትላንት ምሽት በተከሰተው ጎርፍ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ!
ትላንት ምሽት በተከሰተው ጎርፍ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ፡፡በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ዳርፉር ወንዝ አካባቢ ትላንት ምሽት ከ3 ሰዓት ጀምሮ በጣለው ዝናብ በተፈጠረ ጎርፍ ሁለት ሴቶች መወሰዳቸውንና ሕይወታቸውን ማለፉን ተከትሎ አስከሬናቸው በተደረገው ፍለጋ ዛሬ ጠዋት መገኘቱን አመላክቷል፡፡
የሟቾቹ አስከሬን ዛሬ ጠዋት 2:30 እስከ 4 ሰዓት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ጥቁር አባይ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ በእሳትና አደጋ ስጋት ሰራ አመራር ኮሚሽን ጠላቂ ዋናተኞች ፍለጋ መገኘቱን የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ አስታውቀዋል።
በ2015 ዓ.ም በተለያዩ ጊዜያት በተፈጠረው የጎርፍ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉንም ባለሙያው አስታውሰዋል፡፡ሕብረተሰቡ በአካባቢው ከባድ ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ከጎርፍ አደጋ ራሱንና ቤተሰቡን እንዲጠብቅም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
Via Walta

👍9❤5🔥1
በደቡብ አፍሪካ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ፤ የራሳቸውን ዜጋ በማገት ወንጀል በቁጥጥር ስር ዋሉ!
በደቡብ አፍሪካ በፖሎክዋኔ ግዛት ሊምፖፖ ከተማ የሚኖሩ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ሌላ አንድ ኢትዮጵያዊን በማገት በከተማዋ ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተዘግቧል።
የ 20 አመት ወጣት የሆነዉን ታጋች ለማስለቀቅ ቤተሰቦቹን 80 ሺህ የደቡብ አፍሪካ ራንድ መጠየቃቸዉንም የሊምፖፖ ፖሊስ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ማሌስላ ለደዋባ ተናግረዋል። አጋቾቹ የ 20 እና የ 22 እድሜ ያላቸዉ ወጣቶች መሆናቸዉም ተነግሯል።
ታጋቹን ፖሊስ አፈላልጎ ሲያገኝም ከሌሎች ስምንት ሰዎች ጋር ነዉ የተገኘዉ ተብሏል። እገታ የግለሰቦቹ ዋነኛ ስራ ይሆናል ተብሎ የታሰበ ሲሆን ሌላ ከሶስት ወራት በፊት የታገተ ግለሰብ መገኘቱም ተነግሯል።
የተቀሩት ስምንት ሰዎችም ፖሊስ ደርሶ እስኪያስለቅቃቸዉ በትንሹ ከ 10 እስከ 15 ቀናት ታግተዉ ቆይተዋል ነዉ የተባለዉ። ግለሰቦቹ በደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በህገወጥ የሰዎች ዝዉዉር የተለያዩ 9 ክሶች ይቀርብባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

👍36❤5
በአዲስ አበባ የግል ትምህርት ቤቶች በሚያስከፍሉት ክፍያ ላይ የተማሪ ወላጆች ቅሬታ አቀረቡ!
በአዲስ አበባ የሚገኙ የግል ትምህት ቤቶች ለተማሪዎች የሚያስከፍሉት ክፍያ አሁን ያለውን የኑሮ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው ሲሉ የተማሪ ወላጆች ለአዲስ ማለዳ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ለአብነትም በዚሁ ዓመት አንደኛ ክፍል ለመማር ለተመዘገበ ልጃቸው የመመዝገቢያ፣ የጥናት እና የአንድ ተርም ክፍያ 9 ሺሕ 250 ብር መክፈላቸውን የገለጹት አንድ ወላጅ፤ ይኸው ክፍያ ባለፈው ዓመት 6 ሺሕ 500 ብር እንደነበር ተናግረዋል።
“ከከፈልኩት 9 ሺሕ 250 ብር ተጨማሪ ደግሞ ለመጽሐፍ፣ ለሶፍትና ለሳሙና ሌላ ተጨማሪ ገንዘብ ይጠብቀኛል፡፡” ካሉ በኋላም፤ “ልጄ የተሻለ ትምህት ያገኝ እንደሆን ብዬ እንጂን ዋጋው ለአንደኛ ክፍል ልጅ ፈጽሞ የተጋነነ እና አሁን ያለንበት ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ያላገናዘበ ነው፡፡” ብለዋል።
እንዲሁም ሥማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ ሌላ የተማሪ ወላጅ፤ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ለሚማር ልጃቸው የመመዝገቢያ እና የአንድ ተርም ክፍያ 7 ሺሕ 150 ብር መክፈላቸውን ገልጸው፤ ባለፈው ዓመት ይኸው ክፍያ 4 ሺሕ 900 ብር እንደነበር ጠቁመዋል።
አንድ ሌላ ወላጅ እንዲሁ ለዘንድሮው የትምህርት ዘመን 10ኛ ክፍል ለተመዘገበ ልጃቸው የአንድ ወር ክፍያ 2 ሺሕ 495 ብር መክፈላቸውን በመጥቀስ፤ ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከአንድ ሺሕ ብር በላይ ጭማሪ ማሳየቱን እና ተጨማሪ የጥናትና የመጸሃፍት ክፍያ እንደሚጠብቃቸው ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
ባለፈው ዓመት መዋዕለ ሕጻናት ለሚማር አንድ ልጃቸው በተርም 8 ሺሕ ብር ይከፍሉ እንደነበረ የገለጹ አንድ ወላጅ በበኩላቸው፤ ለዘንድሮው የትምህርት ዘመን ይኸው ክፍያ 14 ሺሕ ብር መድረሱን ተናግረዋል።
ያለፈው ዓመት ግማሽ ላይ የሚኖሩበት ቤት በመፍረሱ ልጃቸው ትምህርት ማቋረጧን ያነሱት አንድ ወላጅ ደግሞ፤ ለዘንድሮ የትምህርት ዘመን ልጃቸውን ሌላ ትምህርት ቤት ለማስገባት መሸኛ ሲጠይቁ፣ ውዝፍ ዕዳ የመሸኛ ብር እንዲከፍሉ መጠየቃቸውን ገልጸዋል።
“መክፈል እንደማልችል እና ችግር ዉስጥ መሆኔን ባስረዳቸውም በምንም መልኩ ሊተባበሩ ፍቃደኛ አልሆኑም፡፡” ሲሉም ተደምጠዋል።
የግል ትምህርት ቤቶች እየጠየቁት ያለው ክፍያ በጣም የተጋነነ ነው በማለት ቅሬታቸውን ያቀረቡት ወላጆቹ፤ “የግል ትምህርት ቤቶች ዓላማቸው ማስተማር መሆኑን በመዘንጋት እንደ አንድ የገቢ ምንጭ ነው የሚያስቡት፡፡” የሚል ሀሳብ ሰንዝረዋል።
የግል ትምህርት ቤቶች በሚያደርጉት የክፍያ ጭማሪ ላይ 51 በመቶ የሚሆኑ የተማሪ ወላጆች በተገኙበት ውይይት የማድረግ እና ተስማምቶ የመወሰን ግዴታ እንዳለባቸው፤ እንዲሁም የመጀመሪያው ውይይት ላይ የሚገኙ ወላጆች ከተጠቀሰው ቁጥር በታች ከሆኑ ስብሰባው መበተን እንዳለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በአሰራሩ ላይ አስቀምጧል።
ሆኖም ለኹለተኛ በሚጠራው ስብሰባ ላይ ሊደረግ የታሰበው ጭማሪ በሥፍራው በተገኙ ወላጆች መጽደቅ እንደሚችል አሰራሩ ይደነግግጋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ላይ የግል ትምህርት ቤቶቹ የክፍያ ጭማሪ ለማድረግ ፕሮፖዛል አቅርበው እንደነበር አውስቶ፤ ሆኖም ከወላጅ ጋር በቂ መግባባት ላይ ሳይደርሱ ጭማሪውን መተግበር እንደማይችሉ ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር ዘመናይ ኀይለጊዮርጊስ፤ በክፍያ ጭማሪ ላይ መስማማት ያልቻሉ ትምህርት ቤቶች እና ወላጆች ባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ በማወያየት ችግሩ እንዲፈታ ማድረጉን ገልጸዋል።
እንዲሁም አሁን ወቅቱ ትምህርት የሚጀመርበት እና የምዝገባ ጊዜ የተጠናቀቀ በመሆኑ የቀረበው ቅሬታ ወቅቱን ያላገናዘበ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን አስመልክቶ ትናንት መስከረም4/2016 ባወጣው መግለጫ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ ተማሪዎች 40 በመቶ የሚሆኑትን እንደሚያስተምሩ የሚገለጸው የግል ትምህርት ቤቶች፤ በተማሪዎች ወርሃዊ ክፍያ ላይ ከ20 እስከ 100 በመቶ የሚደርስ ጭማሪ ለማድረግ እቅድ ማቅረባቸውንና “ይህም በወላጆች ዘንድ በቂ ውይይት ያልተደረገበት እና መስማማት ያልተደረሰበት ነው፡፤” የሚል ቅሬታ ማስነሳቱን ገልጿል።
Via Addis Maleda

👍52❤7👎1
ዛሬ የሚደረጉ የአምስቱ ታላላቅ ሊጎች የተመረጡ ጨዋታዎች የቤቲንግ ግምትና መረጃዎች
ሆፈንሃይም፣ ዶርትመንድ፣ ፉልሃም ፣ አስቶንቪላ እና ኒውካስትልን የተመለከቱ የቤቲንግ መረጃዎች እና ግምቶች በቤትስኬት
ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ👇👇
http://www.betsket.com/ዛሬ-የሚደረጉ-የአምስቱ-ታላላቅ-ሊጎች-የተ/
ሁል ጊዜ የሚለቀቁ መረጃዎችን በአንድ ላይ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።👉 @betskett

👍12🔥2
ፀሐይ ባንክ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እግርኳስ ክለብ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማሙ!
መስከረም 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ስምምነት ያደረጉት ፀሐይ ባንክ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ እግርኳስ ክለብ ለአምስት ዓመታት እንደሚቆይ ባንኩ ለካፒታል አስታዉቋል።
ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር የተደረገው ስምምነት በባንኩ በኩል "የክለብ ደጋፊዎች የአባልነት ክፍያቸውን እንዲከፍሉ ፣ ለተጨዋችም እንዲሁም ለሰራተኞቹ የደመወዝ ሂሳብ በባንኩ በኩል ተፈፃሚ እንደሚሆን ፣ የስታዲየም መግቢያ ትኬቶች እና የክለቡ ቲሸርቶች በተቋሙ እንደሚሸጥ ገልጿል።
ፀሐይ ባንክ ለክለቡ በስፖንሰርሺፕ መልኩ በየዓመቱ 10 በመቶ የሚያድግ የ5 ሚሊዮን ብር ገቢ የሚያደርግ ሲሆን እስከ 40 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የረጅም ጊዜ ብድር እንደሚያመቻች ስምምነቱን ባደረገበት ወቅት አስታውቋል።

👍38👎6❤4
የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት ሀገር አቀፍ የትምህርት ካላንደር ይፋ ሆነ!
ትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ የትምህርት የ2016 ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት ሀገር አቀፍ የትምህርት ካላንደርን ይፋ አድርጎል።
መስከረም 14 2016 ዓ.ም የአንደኛው ወሰነ ትምህርት መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት ይጀምራል፡፡
ክልሎች በብሔራዊ ፈተናና በተለያዩ ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ የተወሰኑ የቀናት ለውጦች ሊያደርጉ ይችላሉም ብሏል።
ከመስከረም 2 እስከ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ለመምህራንና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ትውውቅይ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ ባወጣው ካላንደር ተመላክቷል።
ከመስከረም 7 እስከ 11/ 2016ዓ፣ም የትምህርት ሳምንት ሆኖ እንደሚከበርም ገልጿል።

👍35👎11❤4
በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች “የጦር መሳሪያ ደብቃችኋል አምጡ” በሚል ግድያዎች መፈጸማቸው ተገለጸ!
በመንግሥት የጸጥታ አካላት የታሰሩ ሰዎች “ለታጣቂ ቡድኑ ድጋፍ ታደርጋላችሁ” እንዲሁም “የጦር መሳሪያ ደብቃችኋል” በሚል ምክንያት እንደሆነም ኢሰመኮ ገልጿል። በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ ከተለያዩ ክልሎች የመጡ ህጻናት እና ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ውሏቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ነዋሪዎች ተይዘው የሚቆዩበት ጊዜያዊ ማዕከል እንዳለም ተመልክቷል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው፤ ሙሉውን ለማንበብ:
https://bbc.in/3PJten6

👍38❤7👎6
የ2016 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል መስከረም 26 እና 27 ይከበራል!
የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 26 ቀን በሆረ ፊንፊኔ እና መስከረም 27 በሆረ ሀርሰዲ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 26 ቀን በሆረ ፊንፊኔ እና መስከረም 27 በሆረ ሀርሰዲ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
👎89👍21❤8
በሰሜን ሸዋ ሙሉ ወረዳ ከኹለት ዓመት በላይ በዘለቀው የታጣቂዎች እገታ ነዋሪዎች ቀያቸውን ለቀው ለመውጣት መገደዳቸውን ገለጹ!
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሙሉ ወረዳ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው እና በመንግሥት ኦነግ ሸኔ በመባል በአሸባሪነት የተፈረጀው ታጣቂ ቡድን፤ ከኹለት ዓመት በላይ እያደረሰ ባለው ተደጋጋሚ ጥቃት የተማረሩ ነዋሪዎች መኖሪያ አካባቢያቸውን ለቀው እስከመውጣት መድረሳቸውን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
ታጣቂ ቡድኑ በአካባቢው ማህብረሰብ ላይ እገታና ጥቃት ማድረስ ከጀመረ ከኹለት ዓመት በላይ እንደሆነው የተናገሩት ነዋሪዎቹ፤ በተለያዩ ጊዜያት በሚያደርገው የአፈና እና ዝርፊያ ምክንያት ቤት ንብረታቸውን ጥለው ወደ ዱበር፣ ጫንጮ፣ ሱሉልታ እና ሌሎች አጎራባች አካባቢዎች ተፈናቅለው እየሄዱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ታጣቂ ቡድኑ ለአብነትም ባለፈው ቅዳሜ ጳጉሜ 04/2015 በወረዳው ውስጥ ድሬ ከተባለ አካባቢ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ሰዎችን አፍኖ መውሰዱን ነው የገለጹት።
ቡድኑ በተለይም ከኹለት ወራት ወዲህ በነዋሪው ላይ የሚፈፅመውን ጥቃት አጠናክሮ መቀጠሉን በመጥቀስም፤ "ይህ ኹሉ ሲፈጸም የሚያስቆም የመንግሥት አካል የለም።" ሲሉ አክለዋል።
ነዋሪዎች ከዚህ ባለፈው በእጅ ስልካቸው እየተደወለ “ይህን ያህል ብር ካላመጣችሁ እንገላችኀለን፣ ቤታችሁንም እናቃጥላለን” በሚል ዛቻና ማስፈራሪያ መማረራቸውን ተናግረዋል።
የሽብር ቡድኑ በሚያደርገው እንቅስቃሴ በተለይም በወረዳው ዋና ከተማ ዕሮብ ገበያ እና በተወሰኑ የገጠር ቀበሌዎች የትምህርት፣ የጤና እና ሌሎች አገልግሎት ሰጭ ተቋማት አገለግሎት መስጠት እንዳልቻሉ ተመላክቷል።
በተመሳሳይ በዞኑ ወረጃርሶ ወረዳ ጎሃፅዮን ከተማ እና በተለያዩ የወረዳው የገጠር ቀበሌዎች የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ነዋሪዎችን አፍነው እንደሚወስዱ እና ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደሚጠይቁ መረዳት ተችሏል።አዲስ ማለዳ በጉዳዩ ዙሪያ የሙሎ ወረዳ ሠላም እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት የጠየቀች ሲሆን፤ "በአካል መጥታችሁ ጠይቁን" በማለታቸው ምላሹን ማካተት አልቻለችም።

👍31❤5
የአፍሪካ ባለ ልዩ ጣዕም የቡናዎች ጉባሄና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነዉ!
20ኛዉ የአፍሪካ ባለ ልዩ ጣዕም የቡናዎች እና የኢንተር አፍሪካን ኮፊ ኦርጋናይዜሽን ጉባሄና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ
ባለስልጣኑ ይህን አስመልክቶ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ በመጪዉ ጥር ወር ላይ የሚካሄደው ጉባሄ የኢትዮጵያ ቡና በአፍሪካ እና በዓለም ገበያ ይበልጥ ለማስተዋወቅ እድል እንደሚፈጥር ገልጿል።
"Speciality Coffee at Origin" በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው ጉባሄዉ ላይ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ የዓለም አቀፍና የቀጠናዊ የቡና ቆይዎች ነጋዴዎች አምራች ገዥዎች እና የዘርፉ ባለሞያዎች በአንድ ጣሪያ ስር ለማሰባሰብ ታቅዷል።
የአፍሪካ ባለ ልዩ ጣዕም የቡናዎች ጉባሄና የኢንተር አፍሪካን ኮፊ ኦርጋናይዜሽን "IACO" ከጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በዚሁ ጊዜ የመጀመሪያዉ የአፍሪካ ቡና ሳምንት የሚካሄድ መሆኑ ካፒታል ሰምቷል።

👍17❤8👎2🔥1
የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ!
በሪያድ በመካሄድ ላይ ባለው 45ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል።
ኢትዮጵያ እስካሁን ካስመዘገበቻቸው ዘጠኝ ቅርሶች በተጨማሪ ይሄንኛው አስረኛ ሲሆን ለአፍሪካ ደግሞ 100ኛ ሆኖ ተመዝግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
በሪያድ በመካሄድ ላይ ባለው 45ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል።
ኢትዮጵያ እስካሁን ካስመዘገበቻቸው ዘጠኝ ቅርሶች በተጨማሪ ይሄንኛው አስረኛ ሲሆን ለአፍሪካ ደግሞ 100ኛ ሆኖ ተመዝግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
👍35❤7
አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ5 ሺህ ሜትር ሩጫ ክብረ ወሰን በመስበር አሸነፈች!
አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ5 ሺህ ሜትር ሩጫ በኬንያዊቷ አትሌት ፌይዝ ኪፕዬጎን የተያዘውን ክብረ ወሰን በመስበር የዲያመንድ ሊግ አሸናፊ ሆነች።
አትሌቷ ክብረ ወሰኑን የሰበረችው 14:00.21 በሆነ ሰዓት በመግባት መሆኑን ዎርልድ አትሌቲክስ አስታውቋል።

❤98👍44🔥4