YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በመቀሌ በሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ታሰሩ!

በመቐለ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ 6 የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ጨምሮ ሌሎች በፖሊስ ተይዘው ታሰሩ። "ኪዳን ለስር ነቀል ለውጥ" በሚል መሪ ቃል በመቐለ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያካሂዱ ሲገልፁ የቆዩት በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሱ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ የትግራይ ነፃነት ፓርቲ እና ባይቶና የተባሉ የፖለቲካ ድርጅቶች፥ ህወሓት ሰልፍ ለማደናቀፍ እየሰራ ነው በማለት ከሰዋል። ከሰልፉ ጋር በተገናኘ የመቐለ ከተማ አስተዳደር ለፖርቲዎቹ በላከው ደብዳቤ ፀጥታ የሚያስከብርበት አቅም እንደሌለው የገለፀ ቢሆንም ተቃዋሚዎቹ ግን በትግራይ ያሉ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ ችግሮች የሚንፀባረቁበት ሰልፍ በመጪው ሐሙስ ጳጉሜ 2 ቀን 2015 ዓመተምህረት በሮማናት አደባባይ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

በትግራይ ያሉ ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለማንፀባረቅ እንዲሁም ዓለም በትግራይ ያለው ሁኔታ እንዲረዳ የተለያዩ መፈክሮች በመያዝ ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅት ላይ ያሉት ሶስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ፥ በትግራይ ያለው 'ህወሓት መር አስተዳደር' ሕጋዊ መብት የሆነው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይካሄድ የተለያዩ እንቅፋቶች እየፈጠረ ነው በማለት ከሰዋል።

የፊታችን ጳጉሜ 2 ቀን 2015 ዓመተምህረት ይካሄዳል የተባለው የተቃውሞ ሰልፍ ለህዝብ ለማስተዋወቅ በመቐለ ከተማ ጎዳናዎች በመኪና እየተዘዋወሩ ይሰሩ የነበሩ ስድስ አባላቶቻቸው ጨምሮ ሌሎች መታሰራቸው የገለፁት ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ የታላቋ ትግራይ ብሔራዊ ሸንጎ ባይቶና እና የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ፥ የገዢው ሐይል አፈና እና ማደናቀፍ ቢቀጥልም ሰልፊ እንደሚደረግ ገልፀዋል።

"ኪዳን ለስር ነቀል ለውጥ" በሚል የተሰባሰቡት እነዚህ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በትግራይ የሚታይ ፖለቲካዊ ውድቀት፣ ሕገወጥነት፣ በሴቶች ላይ የሚደርስ ፆታዊ አመፅ፣ ዓይን ያወጣ ያሉት በመንግስት መዋቅር የሚደገፍ ዝርፍያና ማጭበርበር እንዲሁም ሌሎች ያልተገቡ ተግባራት እንደሚቃወሙ የገለፁ ሲሆን በትግራይ ስርነቀል ለውጥ ለማምጣት እንደሚታገሉም ዛሬ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ኮምኒኬሽን ሐላፊ አቶ ገብረስላሴ ካሕሳይ፥ ሰልፉ ለማስቀረት ህወሓት ሕገወጥ ተግባራት በመከወን ላይ በማለት ይከሳሉ።

ዛሬ በመቐለ ሮማናት አደባባይ አካባቢ እንደታዘብነው፥ የተለያዩ የሰልፊ መፈክሮች እያስተዋወቀ ሲንቀሳቀስ የነበረ ተሽከርካሪ፥ የደንብ አስከባሪ እና ሲቪል ልብስ በለበሱ ታጣቂ እንዲቆም ተደርጎ፥ ተሽከርካሪው እዛው ከነበሩ ስዎች ጋር ወደ ቀዳማይ ወያነ ክፍለከተማ ፖሊስ ጣብያ ተወስደዋል። ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ እንደተረዳነውም ስድስት የፖለቲካ ድርጅቶቹ አባላት ጨምሮ ሌሎች የቴክኒክ ስራ ይከውኑ የነበሩ ግለሰቦች ታስረዋል። ህወሓት ሰልፊ ለማደናቀፍ እየሰራ ነው ያሉት የባይቶና ከፍተኛ አመራር አቶ ዮሴፍ በርሃ በበኩላቸው ሰልፊችን ሰላማዊ ነው፣ አስተዳደሩ ግን ከዓመፅ ተግባራት ጋር እያስተሳሰረው ይገኛል በማለት ወቅሰዋል። አቶ ዮሴፍ "ከጠላት የተላከ ሐይል የለም። ዓመፅ እየጠራ ያለ ሐይል የለም።

ትግላችን፣ ሰላማዊ ሰልፋችን ወደ ዓመፅ እንዳይሄዱ አግዙን ነው እያልን እየጠየቅን ያለነው። ፀጥታ አናግዝም ስላሉ የሚቀር ሰላማዊ ሰልፍ ግን የለም። እነሱ እጃቸው ከሰበሰቡልን የትግራይ ህዝብ አመፀኛ አይደለም። እኛም ሰላማዊ ሰልፍ እንጂ ዓመፅ አይደለም የምናደርገው። ግልፅ መሆን ያለበት ይህ ሰልፍ ለውጥ ፈላጊ የትግራይ ልጆች የጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ መሆኑ ነው" ብለዋል።

ይህ የትግራይ ነፃነት ፓርቲ፣ ባይቶናና ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የጠሩት "ኪዳን ለስር ነቀል ለውጥ" የሚል መፈክር ያለው የተቃውሞ ሰልፍ፥ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ሌሎች ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችም ድጋፍ ተችሮታል። ዓረና ትግራይ ባወጣው መግለጫ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የማንም ፍቃድ የማያስፈልገው የህዝብ መብት ነው ያለ ሲሆን ከግጭት የፀዳ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉ ይወጣ ብሏል። ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲም እንዲሁ የተቃውሞው አካል እንደሚሆን በፖርቲው ከፍተኛ አመራር አቶ መሐሪ ገብራይ በኩል ገልጿል።«የትግራይ ነፃነት ፓርቲ» በህወሓት ላይ ያቀረበው ክስ የመቐለ ከተማ አስተዳደር ሰልፉ አስመልክቶ ለተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶቹ በላከው ደብዳቤ ሰልፊ የሚደረግበት ቀን ከበዓል ጋር የተቀራረበ በመሆኑ እና በቂ የፀጥታ ሐይል ባለመኖሩ ድጋፍ ለማድረግ እንደማይችል ገልፆ ነበር።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
👍36👎65
Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።

በማንኛውም Social Media  Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::

ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።

Telegram: @adsommar
📞0929334267
👍71
የዋግነር ቡድን በእንግሊዝ ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ ሊፈረጅ ነው!

የሩሲያው ዋግነር ታጣቂ ቡድን በእንግሊዝ ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ ሊፈረጅ ነው።በእንግሊዝ የቡድኑ አባል ወይም ደጋፊ መሆንን ህገወጥ የሚያደርግ ረቂቂ ህግ በዛሬው እለት በፖርላማ ይቀርባል።በዚህ ረቂቅ ህግ እስከ 14 አመታት እስራት የሚያስቀጡ አንቀጾች እንደተካተቱበት ስካይ ኒውስ ዘግቧል።በዚሁ ረቂቅ ህግ መሰረት የዋግነር ንብረቶች የአሸባሪ ድርጅት ንብረቶች ተብለው እንደሚመዘገቡ እና እንደሚወረሱ ተገልጿል።

በፕሪጎዥን ሲመራ የነበረው ይህ ቡድን ባለፈው ወር በአውሮፕላን አደጋ ህይወቱን እስካጣበት ጊዜ ድረስ ሩሲያ በዩክሬን ላይ እያካሄደችው ባለው ጦርነት ጉልህ ሚና ተጫውቷል።ቡድኑ ከዩክሬን በተጨማሪ በሶሪያ፣ በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ በሱዳን እና በሊቢያ እንደሚንቀሳቀስ ይነገራል።

እንግሊዝ ፍረጃው ለማድረግ ያሰበችው የቡድኑ ተፈጥሮአዊ ባህሪይ፣ የቡድኑ እንቅስቃሴ እንዲሁም በውጭ በሚኖሩ የእንግሊዝ ዜጎች ላይ የደቀነውን አደጋ ከግምት በማስገባት መሆኑን ገልጻለች።ዋግነር ከወራት በፊት በሩሲያ መንግስት ላይ አመጽ ከፍቶ የነበረ ቢሆንም በቤላሩስ አደራዳሪነት አመጹ ቆሙ፣ የቡድኑ መሪም ወደ ቤላሩስ እንዲሄድ ተደርጎ ነበር።

Via Al ain
@YeneTube @FikerAssefa
👍47👎65
🌼ቁንዶ በርበሬ
🌼ኮረሪማ
🌼መከለሻ
🌼የሻይ ቅመም l
🌼ቀረፋ
🌼ከሙን
እና ከ20 በላይ ሌሎች ቅመሞች
በሁሉም ሱፐር ማርኬት ያገኙናል።

ይደውሉ 0911664775 || 0911872827
👍92
ከአዲስ አበባ ሚመጣ መልዕክት አሎት? 
ከአዲስ አበባ ውስጥ ከፈለጉት ቦታ መልዕክቶን ተቀብለን ሀዋሳ ቤቶ ድረስ እናደርሳለን።

በ300 ብር ብቻ

0980526262 አዲስ አበባ
0962627762 ሀዋሳ
👍83
በኢንዶኔዥያ ሙሽራው በሰርጉ ቀን በመቅረቱ ሙሽሪትን የሙሽራው አባት ኃላፊነቱን ወስዶ አገባ

በኢንዶኔዥያ አንዲት ሙሽሪትን በህይወቷ ውስጥ በጣም ደስተኛ በሚያደርጋት ቀን ባለቤቷ መጥፋቱን ተከትሎ ይህ ደስታ ወደ አዋራጅ ቅዠት ተለውጧል።

በኢንዶኔዥያ መገናኛ ብዙሃን እንደተዘገበው ከሆነ ኤስኤ ብቻ የተባለችው ወጣቷ በደቡብ ሃልማሄራ ጂኮታሞ መንደር ነዋሪ ስትሆን ሲሆን ከሙሽራው ጋር የረጅም ጊዜ ግንኙነት እንዳላት ተነግሯል። ነገር ግን በነሀሴ 29 በሠርጋቸው ቀን ሙሽራው በመቅረቱ ለእንግዶች ስለ ሰርጉ መሰረዝ ለመናገር እጅግ አዳጋች ያደርገዋል።

ይህው ችግም በሁለቱም ቤተሰቦች ይሆናል ተብሎ የማይታሰብ የነበረ ሲሆን  ፣ ለሠርጉ ዝግጅት ገንዘብ የተከፈለ ሲሆን ለጥሎሽ ተገቢው በሙሉ በመደረጉ የሙሽራው አባት ሙሽሪትን በማግባት የስዎች ጥያቄ ዝም ለማሰኘት ሞክሯል።በኢንዶኔዥያ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተሰራጨ ምስል መሰረት የሙሽሪት እና የሙሽራዋ አባቶች በአስደናቂው የሰርግ ስነስርአት ላይ አንድ ላይ ዘና ብለው ሲጫወቱ ታይ

በሰርጉ ላይ ለመታደም አስቀድመው እንግዶቹ ተገኝተዋል። የሙሽራው ቤተሰቦች ልጃቸው እንደጠፋ እና ሊገኝ እንደማይችል በማሳወቃቸው የሙሽራዋ ወንድም ዊስቶ አህመድ ለጋዜጠኞች እንደተናገረው  አባታችን ሙሽሪትን አግብቷል ሲል አረጋግጧል።

የሙሽራዋ ቤተሰብ በሙሽራው መጥፋቱ በጣም ያዘኑ ቢሆንም፣ ለሠርግ ዝግጅት ወደ 25 ሚሊዮን ሩፒያ ወይም 1,700 ዶላር ያወጡት ወጪ ሌላኛው ጭንቀታቸው ሆኗል። ዝግጅቱ ቢሰረዝ ገንዘቡን መተካት የወንዱ ሙሽራ ቤተሰብ ውጪ በመሆነ የሙሽራው አባት ማግባቱን መርጠዋል።

ይህ ያልተለመደ ሰርግ በኢንዶኔዥያ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተደበላለቀ አስተያየት የተሰጠበት ሲሆን  የወጣቷን ሙሽራ እጣ ፈንታ በርካቶች አሳዛኝ ብለውታል።አንድ አስተያየት ሰጪ የአባቴ ሚስት የቀድሞ የሴት ጓደኛዬ ናት " ሲሉ በጉዳዩ ላይ ያጋራው መልዕክት አነጋጋሪ ሆኗል።

ይህው ጋብቻ ህጋዊ በመሆኑ ለሙሽራው እንጀራ እናቱ ሆናለች። በቀሪው ሕይወቷ ውስጥ በማትፈልገው የትዳር "ወጥመድ" ውስጥ መግባቷ የሚያስቆጭ ያሉም በርካቶች ናቸው።

@Yenetube @Fikerassefa
👍35👎65
የዓረና ፓርቲ ሊቀ መንበር ዓምዶም ገብረስላሴን ጨምሮ ዛሬ ብቻ ከ20 በላይ ሰዎች ታሰሩ!

በትግራይ ክልል 'ጥምረት ለስር ነቀል ለውጥ” በሚል የተሰባሰቡ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዛሬ እለት ከጠሩት ሠላማዊ ሰልፍ ጋር ተያይዞ ከጠዋት ጀምሮ ይህ ዘገባ እስከወጣበት ሰዓት ድረስ ቢያንስ ከ20 የሚበልጡ ሰዎች ታስረዋል ተባለ።

የሠልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል እና የውድብ ናፃነት ትግራይ (ውናት) ምክትል ሊቀ መንበር አለምሰገድ አረጋይ ለአዲስ ዘይቤ እንደገለፁት “ሰልፉን የሚያስተባብሩ ከተፎካካሪ ፓርቲዎቹ የተውጣጡ የኮሚቴ አባላቶች በሙሉ ከሁለት አስተባባሪዎች በስተቀር ታስረዋል”።

እንደ መረጃ ምንጮቹ ከሆነ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ብቻ ከፖለቲካ ፓርቲዎች አመራርና አባላት ብቻ ዓምዶምን ጨምሮ 13 ሰዎች የታሰሩ ሲሆን፣ ስድስት የቀድሞ የትግራይ ሠራዊት (ቲዲኤፍ) ሰዎች፣ አራት ለሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ንፁሃን ሰዎች በአጠቃላይ ከ20 በላይ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል።

ሰላማዊ ሰልፉ የተጠራበት ሮማናት አደባባይ አካባቢ “ከሰልፈኞች ቁጥር ያለተናነሰ የፀጥታ ኃይል” መኖሩ የተገለፀ ሲሆን አሁንም በሰልፈኞች እና በፀጥታ ኃይሎች መካከል ግብግብ ቀጥሏል።

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
👍25👎21
ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ባለሙያ ቡድን ኮሚሽን በኢትዮጵያ የሥራ ጊዜው በአንድ ዓመት እንዲራዘም 63 ድርጅቶች ጠየቁ፡፡

ሁለቱ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅቶች ሂዩውማን ራይትስ ዎችና አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ 63 ድርጅቶች ከቀናት በኋላ የሚጠናቀቀው የኮሚሸኑ የሥራ ጊዜ እስከ መስከረም 2024 እ.አ.አ. ወይም አንድ ዓመት እንዲራዘም ለተባባሩት መንግስታት ድርጅት 54ኛው የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ባለኩት ደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡

እነዚህ የሲቪልና የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች እንደሚሉት በኢትዮጵያ ያለው የከፋ የሰብኣዊ መብቶች አያያዝ፣ የኮሚሽኑን የሥራ ጊዜ እንዲራዘም የሚያስገድድ ነው፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የኮሚሽኑን ሥራ ደጋግሞ ለማደናቀፍ ቢሞክርም፣ ይህ የባለሙያዎች ቡድን እጅግ ጠቃሚ ስራዎችን መስራቱን ደብዳቤው አመልክቷል፡፡ መንግስት በኮሚሽኑ ላይ እንቅፋት ሆኗል ሲል ከተጠቀሳቸው ጉዳዮች መካከል ‹‹ ባለሙያዎቹ በአዲስ አበባ እንጂ በሌሎች ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች እንዳይሄድ፣ ለኮሚሽኑ በጀት እንዳይመደብና ስራው ሙሉ በሙሉ እንዲቀለበስ ደጋግሞ መሞከር ›› የሚሉት ይገኙበታል፡፡

እነዚህ ፈተናዎች ቢኖሩም ‹‹ ኮሚሽኑ በወርሃ መስከረም 2022 እ.አ.አ. ይፋ ባደረገው የመጀመሪያ ዙር ሪፖርት የሰሜን ኢትዮጵያ ሁሉም ተፋላሚ ሀይላት የጦር ወንጀል መፈፀማቸውን ሊያሳምን የሚችል ማስረጃዎችን አጋልጧል ›› ብሏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍353
"ግጭቶች ሳይፈጠሩ ቀድመን ወደ ውይይት መምጣት አለብን፣ እሣት ማጥፋት ላይ መጠመድ የለብንም" ሲሉ የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል /ካርድ/ ዋና ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ ሀይሉ ተናገሩ፡፡

የነበሩ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለምፍታት፣ እየመጡ ያሉ የሚታዩ ግጭቶችን ቀድሞ ለመከላከልና መልስ እንዲያገኙ ለማድረግ እና በሰላማዊ መንገድ የተፈቱ ግጭቶችን ዛላቂ ለማድረግ ሁሉን አካታች የውይይት መድረክ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡በሀገራችን እስካሁን ድረስ እየተደረጉ ያሉት ሙከራዎች እሣት የማጥፋት ሁኔታዎቸ ናቸው ያሉት ዋና ዳይሬከተሩ የውይይት መድረኮች ግጭቶች ሳይፈጠሩ ቀድመው መከናወን አለባቸው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በተለያዩ አቅጣጫዎች ግጭቶች ሲመጡ ቀድመው ይታያሉ ስለዚህም እነዚህን ግጭቶች ለመከላከል የሚያስችል የውይይት መድረክ ያስፈልጋል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በባለፈው ዓመት በተመሳሳይ በትግራይ የነበረው ጦርነት እንዲቆም ጥሪ አቅርበን ከመንግስት ከፍተኛ ውግዘትን ብናስተናግድም ከተወሰኑ ወራት ባኃላ የፕሪቶሪያው ውይይት ተካሂዷል ብለዋል አቶ በፍቃዱ ሀይሉ፡፡በመሆኑም መንግስት አሁንም ሁሉን አቀፍ የሆነና ዘላቂ የሆነ መድረክ አዘጋጅቶ ያሉበትን ችግሮች በውይይት መፍታት ያስፈልገዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
👍231
“ትንሣኤ 70 እንደርታ” የተሰኘ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀስ ፓርቲ፤ መስራች ጉባኤውን በነገው ዕለት ሊያካሄድ ነው!

በትግራይ ክልል “የተንሰራፋውን ጭቆና እና የአንድ ፓርቲ ስርዓት” ለመታገል መነሳቱን የገለጸው ትንሣኤ 70 እንደርታ ፓርቲ (ትሰእፓ) የተሰኘ ክልላዊ ፓርቲ፤ መስራች ጉባኤውን ነገ አርብ ጷጉሜ 3 በአዲስ አበባ ከተማ ሊያካሄድ ነው። በትግራይ ክልል “ህብረ ብሔራዊ ስርዓት እንዲፈጠር” እንደሚታገል የጠቆመው ፓርቲው፤ ይህ የማይሳካ ከሆነ የእንደርታ ህዝብ “ከሌሎች ህዝቦች ጋር በጋራ ወይም ለብቻው” “የራሱን ክልላዊ መንግስት” እንዲመሰርት እንደሚታገልም አስታውቋል።

ከሰባት ወራት በፊት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ ምዝገባ ፈቃድ ያገኘው ትሰእፓ፤ ጠቅላላ ጉባኤውን ከዛሬ ሐሙስ ጷጉሜ 2፤ 2015 ጀምሮ እንደሚያካሄድ አስቀድሞ ገልጾ ነበር። ይህንን ተከትሎም የፓርቲው አባላት እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ጠቅላላ ጉባኤው በሚካሄድበት የአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ ተገኝተው ነበር።

ሆኖም መስራች ጉባኤውን ለመታዘብ በቦታው የተገኙት ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተወካዮች፤ ስብሰባው ከመደረጉ አስቀድሞ መሟላት የሚገባቸው ነገሮች አለመሟላታቸውን በማስታወቃቸው ጠቅላላ ጉባኤው ለነገ መተላለፉን የፓርቲው አመራሮች በስፍራው ለተገኘው የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ ተናግረዋል። አመራሮቹ በምርጫ ቦርድ “ማሟላት ይገባችኋል” የተባሏቸውን ጉዳዮች ግን ከመናገር ተቆጥበዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
👍21👎43
በጋምቤላ ክልል ጥቃት አራት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ!

በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ብሔረሰብ ዞን ጎዳሬ ወረዳ ውስጥ ባለፈው ሳምንት እሁድ ነሐሴ 28 ቀን፣ 2015 ዓ.ም «ያልታወቁ» የተባሉ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉ እና 2 ሰዎች መቁሰላቸውን ዞኑ ዐስታወቀ። የአካባቢው ባለሥልጣናት በስልክ ለዶይቸ ቬለ እንደተናገሩት፦ በወረዳው በተከተሰው የፀጥታ ችግር ምክንያት ተቋማት እስከ ዛሬ ጠዋት ድረስ ተዘግተው ቆይተዋል።

በጋምቤላ ክልል ማጃንጃግ ብሔረሰብ ዞን ጎዳሬ ወረዳ ባለፈው ሳምንት እሁድ ደረሰ በተባለው ጥቃት የደረሰው ጉዳት መጠን ሊጨምር እንደሚችልም ነዋሪዎች ተናግረዋል። እሁድ ዕለት የደረሰው ጥቃት ወደ ዞን ዋና ከተማው መጢ ከተማ በመስፋፋቱ የፈዴራል ፀጥታ ኃይሎች ወደ ስፋራው መሰማራታቸውም ተዘግቧል።በዛሬው ዕለት በወረዳው አንጻራዊ ሰላም መስፈኑ፤ ዛሬ ከሰዓት የመንግስት ተቋማት በከፊል ሥራ መጀመራቸውም ተገልጿል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
👍301
Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።

በማንኛውም Social Media  Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::

ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።

Telegram: @adsommar
📞0929334267
👍101
ፓስፖርት ለማግኘት የሚጠባበቁ ከ 300 ሺህ በላይ ሰዎች መኖራቸውን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አሳወቀ!

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አዲስ አመራር ከተሾመለት ወዲህ ላለፈዉ አንድ ወር ያከናወነዉን የማሻሻያ ስራ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት በዛሬዉ እለት ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በአሁኑ ሰዓት በአገልግሎቱ ፓስፖርት ለማግኘት ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ከ 300 ሺህ በላይ ዜጎች መኖራቸዉን ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል። የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አዲሷ ዳይሬክተር ፤ ላለፈዉ አንድ ወር በተቋማቸዉ አሉ ያሏቸዉን ችግሮች ለመቅረፍ ምልከታ ማድረጋቸዉን ተናግረዋል።

በዚህም ተቋሙ የአጭር ፣ መካከለኛ እና የረጅም ጊዜ እቅድ ነድፎ እየሰራ ነዉ ብለዋል። በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የሚነሳዉን እና ዜጎችን ያማረረዉ የሌብነት እና ብልሹ አሰራር ለመቅረፍ አዲስ የአሰራር መንገድ በመዘርጋት ላይ መሆኑን ገልጸዋል። በርከት ባሉ የተቋሙ ዳይሬክተሮች ፣ ሰራተኞች  እና በጊቢዉ ዙሪያ ባሉ ማስረጃ በተገኘባቸዉ ደላሎች ላይ ከአስተዳደራዊ እስከ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የተከሰተዉን ከፍ ያለ የፓስፖርት እጥረት ለመቅረፍ በዉጪ ከሚገኝ አምራች ተቋም ጋር ከስምምነት መድረሳቸዉን ጠቅሰዋል። ለእጥረቱ የዉጪ ምንዛሬ እጥረት እና አለማቀፍ ምክኒያቶች መንስኤ ነበሩ ብለዋል። ችግሩ አሁን በመጠኑ በመቀረፉ 190 ሺህ አዲስ ፓስፖርት ማተም መቻሉን ገልጸዉ ፤ አንገብጋቢ ለሆኑ ጉዳዮች ማለትም በአረቡ አለም ለሚገኙና በተለያዩ የዉጪ ሀገራት ካለ ፓስፖርት ለሚኖሩ ዜጎች ቅድሚያ መሰጠቱን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ባለፉት 90 ቀናት ዉስጥ የፓስፖርት ቀጠሮአቸው በተለያዩ ምክኒያቶች ያለፋቸዉ ሰዎች ዘወትር ቅዳሜ አገልግሎት እንደሚሰጥ ጠቅሰዋል። ወደ ኢትዮጵያ  ከዉጭ በሚመጡ ሰዎች ላይም ቪዛ ለማግኘት በነበረዉ ሂደት ይፈጸም ነበር ያሉትን ሌብነት ለመቀነስ ዘመናዊ አሰራር ተዘርግቷል ነዉ ያሉት። ወደ ኢትዮጵያ በገቡበት ሰዓትም ወዲያዉኑ ቪዛ የሚያገኙበትን On Arrival Visa ከመስከረም 15 ቀን ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል ብለዋል።

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ፤ የቀጠሮ መያዣ ስርዓቱ የመሳስሎ ተሰርቶ ለደላሎች እና ሌቦች ተጋልጦ የነበረ መሆኑን ፣ አሰራሩ ዘመኑን ያልዋጀ እና ኋላ ቀር የነበረ መሆኑን ፣ እነዚህና ሌሎች ጥቃቅን ችግሮችን በተደራራቢነት የሚያመጡ ክፍተቶች ነበሩበት ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍242🔥1
አጎአን ጨምሮ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ለአንድ ዓመት አራዘመ!

- እ.ኤ.አ. መስከረም 2021 ከሁለት ዓመታት በፊት በአሜሪካ ኤግዚኪዩቲቭ ኦርደር 14046 መሰረት በብሄራዊ ደህንነት እና የውጭ ፖሊሲ ላይ የተደቀነ ስጋትን ለመቋቋም በሚል ከትግራይ ክልል ጦርነት ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የጣለውን ማዕቀብ ለአንድ ዓመት አራዝሟል።

- የኢትዮጵያ መንግስት እና ባለስልጣናት ማዕቀቡን በተደጋጋሚ “በውስጥ ጉዳይ ተገብቶ የተጣለ ማዕቀብ” በማለት የሚጠሩት ሲሆን በ2013 ዓ.ም. በድሬዳዋ ከተማ የተደረገውን ጨምሮ የአሜሪካ ማዕቀብ በኢትዮጵያ ላይ ሊያሳድር በሚችለው ጫና ላይ ያተኮሩ ውይይቶች ሲደረጉ ተስተውሏል።

- ማዕቀቦቹ የኢትዮጵያ እንዲሁም የኤርትራ ባለስልጣናት፣ ወታደራዊ ሰራተኞች እና ሌሎች ግለሰቦች የቪዛ እገዳ፣ በትግራይ ክልል እና በኢትዮጵያ ለተስፋፋው ብጥብጥ፣ ግፍ እና ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠያቂ የሆኑ አካላት እና ግለሰቦች ላይም ልዩ ማዕቀቦችን ያካተተ ነው።

- በተጨማሪም የመከላከያ አገልግሎቶችም ሆኑ መሳሪያዎች ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ የታጠቁ ኃይሎች፣ ለፖሊስ፣ ለስለላ ወይም ለሌሎች የውስጥ ደኅንነት ኃይሎች እንዳይላኩ እንዲሁም ኢትዮጵያ በዓመት እስከ 100 ሚልየን ዶላር ገቢ ታገኝበት የነበረው የአፍሪካ የዕድገትና ዕድል ሕግ (አጎአ) ከቀረጥ ነፃ የአሜሪካን ገበያ ተጠቃሚነትን ማሳጣት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት ከሚቀጥሉ ማዕቀቦች ዋነኞቹ ናቸው።

- ማዕቀቦቹ አሁን ለሁለተኛ ጊዜ የተራዘሙ ሲሆን እስከ መስከረም 2024 ይፀናሉ።

✍️Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
👍50👎142
በፀጥታ ችግር ፈተና ያልወሰዱ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ከመስከረም 8 ቀን ጀምሮ ይፈተናሉ!

በፀጥታ ችግርና በሌሎች ምክንያቶች ፈተና ያልወሰዱ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ለመፈተን መዘጋጀቱን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የ2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት (12ኛ ክፍል) ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በሁለት ዙር መሰጠቱን አገልግሎቱ አስታውሷል፡፡

ይሁንና በጎንደርና በጋምቤላ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ሙሉ በሙሉ እና በከፊል 14 ሺህ 891 ተማሪዎች እንዲሁም በሕህ ግ ጥላ ስር በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ 419 ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን ሳይወስዱ መቅረታቸው ተጠቅሷል፡፡

ተፈታኞችን ከመጪው መስከረም 8 እስከ መስከረም 11 ቀን 2016 ዓ.ም ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡ውጤታቸውም ከመጀመሪያው ዙር ጋር እንደሚገለጽም የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍154
የዛሬ ጨዋታዎች የቤትስኬት ግምት

ማሊ፣ ስፔን፣ ፖርቹጋልን እና ሌቫንቴን የተመለከቱ የቤቲንግ መረጃዎች እና ግምቶች በቤትስኬት

ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ👇👇

http://www.betsket.com/የዛሬ-ጨዋታዎች-የቤትስኬት-ግምት/

ሁል ጊዜ የሚለቀቁ መረጃዎችን በአንድ ላይ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።👉 @betskett
👍21
የሳኡዲ አረቢያው ፕሮሊግ ለተጨዋቾች ግዥ 1 ቢሊዮን ዶላር ወጭ አደረገ!

የሳኡዲ አረቢያው ፕሮሊግ ለተጨዋቾች ግዥ 1 ቢሊዮን ዶላር ወጭ አደረገ።የዘንድሮው የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ሲዘጋ የሳኡዲ አረቢያው ፕሮሊግ 1 ቢሊዮን ዶላር ወጭ አውጥቷል።

አዲስ የእግር ኳስ መናኸሪያ መሆኗን ያስታወቀችው የነዳጅ ባለጸጋዋ ሳኡዲ አረቢያ ትናንት በባቃው የተጨዋቾች ዝውውር 1 ቢሊዮን ዶላር ማውጣቷን ኤፒ ዘግቧል።በቅርቡ ስሙ የገነነው የሳኡዲ ፕሮሊግ በበርካታ የአውሮፖ ሊግ ታዋቂ ተጨዋቾች መዳረሻ እየሆነ መጥቷል።

ሳኡዲ አረቢያ እግር ኳስን ጨምሮ በጎልፍ፣ በቦክስ፣ ፎርሙላ ዋን ሬሲንግ እና በቴኒስ ላይ ኢንቨስት እያደረገች።ፕሮሊግ በተጠናቀቀው የዝወውር መስኮት ያለወጣው ወጭ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ካወጫው ወጭ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የሚቀመጥ መሆኑን ሮይተርስን ጠቅሶ አል-ዐይን ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍21👎21
ዛሬ ምሽት በተካሄደው በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በግብፅ አቻው 1 ለ 0 ተሸንፏል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ2023 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታ ከግብጽ አቻው ጋር አካሂዷል፡፡ሁለቱ ቡድኖች ጨዋታቸውን በካይሮ አየር ሃይል ስታዲየም ምሽት 1 ሰዓት ላይ አድርገዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ የግብጽ ብሄራዊ ቡድን ምድቡን በበላይነት አጠናቋል።በአንጻሩ ዋልያዎቹ የማጣሪያ ውድድራቸውን በአራቱ ተሸንፈው አንድ አቻ በመውጣት እና አንድ ጨዋታ በማሸነፍ በአራት ነጥብ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👎50👍232🔥1
የሻረግ ቅመማ-ቅመም 👌
#ምርቶቻችንን :-
🌼 በሸዋ ሾፒንግ
🌼 በክዊንስ
🌼 በሎሚያድ
🌼 በጋራ ማርት
🌼 በባምቢስ(ልዊስ)
🌼 በዴይሊ ሚኒማርት
እና በሌሎች ሱፐር ማርኬቶች ያገኙናል።

📲 0911 664775 / 0911 872827
👍51
ከአዲስ አበባ ሚመጣ መልዕክት አሎት? 
ከአዲስ አበባ ውስጥ ከፈለጉት ቦታ መልዕክቶን ተቀብለን ሀዋሳ ቤቶ ድረስ እናደርሳለን።

በ300 ብር ብቻ

0980526262 አዲስ አበባ
0962627762 ሀዋሳ
👍42