በኦነግ ሸኔ ታግተው ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ለተጠየቁ ሹፌሮች ገንዘብ እየተሰበሰበ ነው ተባለ!
ከአምስት ቀን በፊት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ገርበ ጉራቻ ከተማ አካባቢ ለታገቱ ከ50 በላይ ሹፌሮች፣ እገታውን የፈጸሙት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የጠየቁትን ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ህዝቡ እየሰበሰበ መሆኑን አዲስ ማለዳ ከምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የሥራ ኃላፊዎች ሰምታለች።
በዚህም በደብረ ማርቆስ እና ደንበጫ መካከል አማኑኤል ከተማ ላይ የታገቱ ሹፌሮች ይለቀቁልን በሚል ለሦስት ቀናት ያህል መንገድ ተዘግቶ እንደነበር የተጠቀሰ ሲሆን፤ መፍትሔ ባለመገኘቱ የታጋቾቹ ቤተሰቦች በየቦታው ጨርቅ አንጠፈው የተጠየቁትን ገንዘብ በመለመን ላይ ናቸው ተብሏል።
"እኛም ግራ ገብቶናል" ያሉ አንድ የሥራ ኃላፊ፤ "አብዛኛው ሹፌሮች የታገቱት ከዚህ አካባቢ ስለሆነ ሕዝቡ ልጆቻችን ይፈቱልን በማለት መንገድ ተዘግቶ ነበር።" ካሉ በኋላ፣ "ሕግ እና መንግሥት ባለበት አገር ሰው ታግቶ በሚሊየን ክፈሉ እየተባለ ነው፣ አጣርታችሁ ለመንግሥት ይፋ አድርጉ የሚሰማ ካለ።" ሲሉ ተደምጠዋል።
አክለውም፤ "ከታገቱት ውስጥ ዕድል ቀንቶት ለአንድ ሰው አንድ ሚሊየን ከፍሎ የሚለቀቅ አለ። አልፎ አልፎ እየከፈሉ እየተለቀቁ ነው፣ ክፍሎ ያልተለቀቀም አለ" ብለዋል።
የሥራ ኃላፊው "ገርበ ጉራቻ አሊዶሮ አካባቢ ያለው የመንግሥት አካል በዚህ ጉዳይ ለምንድነው ማብራሪያ የማይሰጠው?" ሲሉ ጠይቀው፤ "የፀጥታ ኃይል፣ መንግሥትና ህግ ባለበት አገር በተደጋጋሚ ድርጊቱ መፈፀሙ ያሳዝናል።" ብለዋል።
ከ50 በላይ ሹፌሮች ታግተው ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ነው የተጠየቀው ያሉት የሥራ ኃላፊው፤ "በዚህ ኑሮ ውድነት ምንም የሌለው ድሃ ልጆቹን ለማትረፍ በየቦታው ጨርቅ አንጥፎ እየለመነ ነው። የሚመለከተው አመራር ማብራሪያ ይስጥ።" ሲሉ አሳስበዋል።
ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው እና በመንግሥት ኦነግ ሸኔ ተብሎ በአሸባሪነት የተፈረጀው ታጣቂ ቡድን በተለይ በኦሮሚያ ክልል ሰዎችን ከመግደልና ከማፈናቀል ባለፈ ንጹሃን ዜጎችን በማገት ከፍተኛ ገንዘብ እየጠየቀ ይገኛል።
አዲስ ማለዳ ባለፈው ሰኔ 10/2015 በሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ አቅራቢያ ከ50 በላይ የከባድ መኪና እና የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ተሽከርካሪዎች ሹፌሮች፣ እረዳቶችና ተሳፍሪዎች መታገታቸውን መዘገቧ የሚታወስ ሲሆን፤ ድርጊቱ ሲፈጸም በቅርብ እርቀት የነበሩ የመንግሥት የጸጥታ አካላት "ከበላይ አካል ትዕዛዝ አልተሰጠንም" በማለት የታገቱ ዜጎችን ሊታደጉ አለመቻላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች መግለጻቸው አይዘነጋም።
[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa

"በኢትዮጵያ እርዳታ ያቋረጡ ድርጅቶች ለማቋረጣቸው ምክንያት ያሏቸውን ጉዳዮች የሚያጣራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ ገብቷል" – መንግስት
ዩ ኤስ ኤይድ እና የአለም የምግብ ፕሮግራም ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ ለጊዜው ለማቋረጣቸው ምክንያት ነው ያሏቸውን ጉዳዮች የሚያጣራ የቴክኒክ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱ ተገለፀ፡፡የመንግስት ኮሙኒኬሸን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ የአለም የምግብ ፕሮግራም እና የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ ለጊዜው ማቆማቸውን አስታውሰዋል፡፡
ይህን ተከትሎ መንግስት ከእነዚህ አካላት ጋር በመሆን የአሰራር ክፍተት አለባቸው የተባሉት ላይ ማሻሻዎችን ለማድረግ እና ህገ ወጥ ተግባር ተፈፅመውም ከሆነ ማጣራቶችን በማድረግ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኑን ማሳወቁንም እንዲሁ አንስተዋል፡፡በዚህም በአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መሪነት ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ባለድርሻ ተቋማት ተወካዮችን ያካተተ እንዲሁም ከእነዚሁ ከሰብአዊ ድጋፍ አጋሮች የተውጣጡ አባላት የተካተቱበት የቴክኒክ ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራ መጀመሩን ገልፀዋል፡፡
ኮሚቴው የተለያዩ የመፍትሄ ሃሳቦችን እያቀረበ የአሰራር ማሻሻያ ያስፈልጋቸዋል ያላቸውን ዘርፎችን በመለየት የመፍትሄ ሃሳቦችን እያቀረበ ውጤታማ ውይይቶችን እያደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡የተቋቋመው የጋራ ቴክኒካል ኮሚቴም በዋናነት በአስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ፣ በሴፍቲኔት መርኃ ግብር እና በስደተኞች የሰብአዊ ድጋፍና አቅርቦት እና ስርጭት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
[FBC]

#ቮልስዋገን ከሰሞኑ ቮልስዋገን ኩባንያ ID4 እና ID6 መኪኖቹን የገዙ ከቻይና ውጪ ያሉ ደንበኞች ለተሸከርካሪዎቹ የዋስትና መብት አያገኙም፣ ለሌሎች ሀገራት ተስማሚነታቸውም አልተረጋገጠም ብሎ ነበር።
እዚህ ጋር ዋናው ጥያቄው መሆን ያለበት ለሀገራችን ተስማሚነቱ ካልተረጋገጠ የሰው ህይወት ላይ ጭምር አደጋ ሊያስከትል የሚችል የተሽከርካሪ "ፍቃድ በሌላቸው ሻጮች" እንዴት ወደ ሀገር ሊገባ ቻለ? ጉዳዩ የሚመለከተው የመንግስት አካል ወደ ሀገር የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ የራሱ ምዘና የለውም?
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እግዱን ያስተላለፈው ቮልስዋገን ኩባንያ አስቁሙልን ብሎ ጠይቆ እንጂ የደህንነት ችግር ሊኖርባቸው ይችላል ብሎ በራሱ ወስኖ አይደለም።
ሚኒስቴሩ ስለጉዳዩ ሲጠየቅ "መኪኖቹን ያገድነው ለኢትዮጵያ መንገዶች ብቁ መሆናቸውን ማረጋገጥ ስለሚኖርብን ነው" የሚል ምክንያት ሰጥቷል፣ ታድያ ይህ ማረጋገጫ የሚሰጠው ዜጎች ሚሊዮኖችን ከፍለው ካበቁ እና መኪናው ሀገር ውስጥ በገፍ ከተሸጠ በኋላ ወይስ በፊት?
ለማንኛውም፣ የጀርመን ኤምባሲን በዚህ ጉዳይ መረጃ ጠይቄ "ዜናውን እስካሁን በሚድያ ያስነገረው የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ነው፣ ኤምባሲያችን በቮልስዋገን ኩባንያ እና በሚመለከታቸው የመንግስት አካላት መሀል ውይይት ለማስጀመር ጥረት እያረገ ይገኛል" የሚል ምላሽ አድርሶኛል።
በነገራችን ላይ እንደ ጆርዳን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ግብፅ ያሉ ሀገራት ይህን የመኪና ሞዴል እንደ ባትሪ እና ሌሎች የቴክኒክ ችግሮች እንዳሉበት በመጥቀስ ሀገራቸው እንዳይገባ ያገዱት ከበርካታ ወራት በፊት ነበር።
ኤሊያስ መሰረት የዘገበው 👆

አዲስ ኤክስፕረስ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት።
ዛሬ ከአዲስ አበባ እቃ ይላኩ
ነገ በጠዋት ይቀበሉ።
✅አዳማ
✅ሀዋሳ
✅ሻሸመኔ
✅አዲስ አበባ
📞0962627762
🤳0980526262
T.me/Addisexpressdelivery
ዛሬ ከአዲስ አበባ እቃ ይላኩ
ነገ በጠዋት ይቀበሉ።
✅አዳማ
✅ሀዋሳ
✅ሻሸመኔ
✅አዲስ አበባ
📞0962627762
🤳0980526262
T.me/Addisexpressdelivery
አቶ ይርጋ ሲሳይ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መሥተዳድር የሕዝብ ግንኙነትና የአደረጃጀት ዘርፍ አማካሪ ኾነው ተሾሙ።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ሹመት ሰጥተዋል።
ርአሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር የሕዝብ ግንኙነትና የአደረጃጀት ዘርፍ አማካሪ ሹመት የሰጡ ሲሆን አቶ ይርጋ ሲሳይን ከሰኔ 17/2015 ዓ.ም ጀምሮ የዘርፉ ኃላፊ አድርገው ሹመዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ የሕዝብ ግንኙነትና የአደረጃጀት ዘርፍ አማካሪ አድርገው የሾሟቸው አቶ ይርጋ ሲሳይ በተለያዩ የሕዝብ፣ የመንግሥትና የፓርቲ አደረጃጀቶች የረዥም ጊዜ ልምድ ያላቸው መሆኑ ታውቋል።
Via AMC

👍1
የሥራ ቪዛ ቼክ ሪፐብሊክ
መሥፈርቶች
የታደሰ ፖስፖርት እድሜ ከ 19_49
ነርስ
የ ኮንስትራክሽን ስራዎች
የ ፊኒሽንግ ስራዎች
አጠቃላይ የብረታብረት ብየዳ ስራዎች
የስራ ሰአት በቀን ከ10 - 12 ሰአት
ደሞዝ ከ 1680_2000 dollar
Accommodation አለው
የፕሮሰስ ግዜ 2 - 3 ወር
Contact Us:
@Sabinavisa2
@Sabina_5757
@SabinaA58
☎️☎️☎️📞📞👇👇👇👇
🤳ስልክ ቁጥራችን 9445
Website
www.sabinaadvisors.com
👇👇 ለበለጠ መረጃ 👇👇👇
👉 ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 702
እና ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602
ከታላቅ አክብሮት ጋር !!!
https://tttttt.me/sabinaadvisor
https://www.facebook.com/sabinaadvisor
መሥፈርቶች
የታደሰ ፖስፖርት እድሜ ከ 19_49
ነርስ
የ ኮንስትራክሽን ስራዎች
የ ፊኒሽንግ ስራዎች
አጠቃላይ የብረታብረት ብየዳ ስራዎች
የስራ ሰአት በቀን ከ10 - 12 ሰአት
ደሞዝ ከ 1680_2000 dollar
Accommodation አለው
የፕሮሰስ ግዜ 2 - 3 ወር
Contact Us:
@Sabinavisa2
@Sabina_5757
@SabinaA58
☎️☎️☎️📞📞👇👇👇👇
🤳ስልክ ቁጥራችን 9445
Website
www.sabinaadvisors.com
👇👇 ለበለጠ መረጃ 👇👇👇
👉 ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 702
እና ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602
ከታላቅ አክብሮት ጋር !!!
https://tttttt.me/sabinaadvisor
https://www.facebook.com/sabinaadvisor
#ADVERTISEMENT
👉ምርጥ የ ኮንስትራክሽን ቻናል ጥቆማ
📜የ ግንባታ ጨረታዎች እና የ ስራ ቅጥር ማስታወቂያ ምታገኙበት
📄እጅግ ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ሌክቸር ትምህርቶች ሚሰጥበት🗒
💵የ ኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭ እና ገዢ በቀላሉ ሚገናኙበት
📐ውብ ውብ የ ቤት ዲዛይኖች🏠
💻ኮንስትራክሽን ሶፍትዌሮችና ሴታፖችን📀
📙 ኮንስትራክሽን መፅሃፍቶች📚
🎬የ ኮንስትራክሽን ቪድዮዎቾ ምታገኙበት ምርጥ ቻናል
💫እመኑኝ ታተርፉበታላቹ
ቻናልችን ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/ETCONp
https://tttttt.me/ETCONp
https://tttttt.me/ETCONp
👉ምርጥ የ ኮንስትራክሽን ቻናል ጥቆማ
📜የ ግንባታ ጨረታዎች እና የ ስራ ቅጥር ማስታወቂያ ምታገኙበት
📄እጅግ ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ሌክቸር ትምህርቶች ሚሰጥበት🗒
💵የ ኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭ እና ገዢ በቀላሉ ሚገናኙበት
📐ውብ ውብ የ ቤት ዲዛይኖች🏠
💻ኮንስትራክሽን ሶፍትዌሮችና ሴታፖችን📀
📙 ኮንስትራክሽን መፅሃፍቶች📚
🎬የ ኮንስትራክሽን ቪድዮዎቾ ምታገኙበት ምርጥ ቻናል
💫እመኑኝ ታተርፉበታላቹ
ቻናልችን ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/ETCONp
https://tttttt.me/ETCONp
https://tttttt.me/ETCONp
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው
Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy
Telegram : @Eyobtravel
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL
Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel

ኢትዮጵያዊ መጻሕፍትን በኢቡክ እና በትረካ ለማግኘት ቱባ መተግበሪያን ያውርዱ!
የሚወዷቸውን መጻሕፍት በተመጣጣኝ ዋጋ ቱባ ላይ ያንብቡ!
Download Tuba: https://tuba.et
@tuba_books @tuba_books
የሚወዷቸውን መጻሕፍት በተመጣጣኝ ዋጋ ቱባ ላይ ያንብቡ!
Download Tuba: https://tuba.et
@tuba_books @tuba_books
#የቻናል_ጥቆማ❗️
🏗በ እትዮጵያ ብቸኛ ቡዙ ተከታዮችን ማፍራት የቻለው የconstruction ዘርፍ መረጃዎችን ትምህርቶችን ምታገኙበት channel 👇
https://tttttt.me/ethioengineers1
~ ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣ የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ሌክቸር የምታገኙበት👇
https://tttttt.me/ethioengineers1
~ የኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭና ገዢ የሚገናኙበት ምርጥ ቻናል ለማገኘት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን👇
©️Telegram 👇

Telegram
Ethio Construction
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
“በማዳበሪያ ግብዓት እጥረት የበቆሎ ምርት በወቅቱ መዝራት አልቻልንም” -የአማራ ክልል አርሶ አደሮች
በአማራ ክልል በተከሰተው የአፈር ማዳበሪያ ግብዓት እጥረት ምክንያት የመኸር እርሻቸውን በአግባቡ ማከናወን እንዳልቻሉ የክልሉ አርሶ አደሮች ገለጹ። የክልሉ ግብርና ቢሮ በበኩሉ ያለውን ችግር ለመፍታት የሰብል ለውጥ አድርገው እንዲዘሩ እየሠራን ነው ብሏል።
በአማራ ክልል፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን አነደድ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር አቶ ባይነሳኝ እንዳወቀ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ በተከሰተው የአፈር ማዳበሪያ እጥረት ምክንያት በቆሎ መዝራት አለመቻላቸውን ተናግረዋል።
ሙሉውን ለማንበብ:
https://press.et/?p=103495

የደቡብ ሱዳኑ ብሔራዊ ዲሞክራቲክ ንቅናቄ መሪ ለደህንነታቸው በመስጋት ኢትዮጵያ መምጣታቸው ተሰማ፡፡
በደቡብ ሱዳን የሚንቀሳቀሰው የብሔራዊ ዲሞክራቲክ ንቅናቄ መሪ ዶክተር ላም አኮል አጃዊን በደህንነት ስጋት ምክንያት ኢትዮጵያ እንደሚገኙ ሱዳንስ ፖስት ዘግቧል፡፡
ላም አኮል በኢትዮጵያ ላልተወሰነ ጊዜ እንደሚቆዩ ለፖለቲከኛው ቅርበት ያላቸውና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ከፍተኛ ባለስልጣን ነግረውኛል ሲል ዘገባው አክሏል፡፡
ስማቸው እንዳይጠቀስ ያልፈለጉት እኚህ ባለስልጣን አኮል ባለፈው ሚያዝያ ወር በሱዳን የተቀሰቀሰውን ሁከት ተከትሎ ዋና ከተማዋን ካርቱምን ለቅቀው በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ይገኛሉ፤ ለደህንነታቸው ሲባል ወደ ደቡብ ሱዳን ሳይመለሱ ላልተወሰነ ጊዜ እንደሚቆዩ ተናግረዋል።
‹ ሊቀመንበሩ ዶ/ር ላም አኮል አጃዊን አሁን አዲስ አበባ ናቸው። በሱዳን ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ የሄዱ ሲሆን እዚያው ይቆያሉ። ለደህንነት ሲባል ወደ ደቡብ ሱዳን አይመለሱም” ብለዋል - ባለስልጣኑ።
ሱዳን ፖስት አስተያየታቸውን የጠየቃቸውና በዶክተር ላም አኮል አጃዊን የሚመራው የብሔራዊ ዲሞክራቲክ ንቅናቄ ቃል አቀባይ ማህሙድ ሰሎሞን፣ በዚህ ዙሪያ አስተያየት ለመስጠት ትክክለኛው ስፍራ ላይ አለመሆናቸውን በመጥቀስ፣ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
[Asham]

❤1👍1
አምቦ ከተማ ዛሬ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ።
በከተማዋ ተልተሌ በተባለ ስፍራ ዛሬ ጠዋት ሦሥት ሰዓት አካባቢ ወደ ጉደር ከተማ ይጓዝ የነበረ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ (ሚኒ ባስ) ከከባድ የጭነት ማጓጓዣ (ትራከር) በመጋጨታቸው አደጋው መከሰቱን የአምቦ ከተማ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት በፌስ ቡክ ገጹ ጽፏል።
በአደጋው ሕይወታቸውን ካጡ በተጨማሪ በስድስት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱም ተገልጿል።ለአደጋው መከሰት አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው ፍሬን ከቁጥጥር ውጭ ሳይሆን እንዳልቀረ በከተማዋ ፖሊስ የትራፊክ ደህንነት ባልደረባ ረዳት ኢንስፔክተር እመቤት ተሾመ ተናግረዋል።

በግብጽ ባለ 13 ፎቅ ህንጻ ተደረመሰ!
በግብጽ አሌክሳንድሪያ ከተማ ውስጥ ባለ 13ፎቅ ህንጻ መደርመሱ ተገለጸ።
በፍርስራሹ ውስጥ ያሉ ሰዎችን የማውጣት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን የሀገረመቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
በቦታው ላይ በርካታ የነፍስ አድን ሰራተኞች እና 18 አምቡላንሶች ተሰማርተዋል ተብሏል። በህንጻው ላይ የነበሩ ነዋሪዎች በፍርስራሹ ውስጥ ናቸው።
[Alain]

የሩስያ እና ዩክሬን የጥቁር ባሕር የእህል አቅርቦት ስምምነት ካበቃ በተለይ በአፍሪቃ ቀንድ የከፋ ቀውስ እንዳያስከትል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጠነቀቀ።
የስምምነቱ ማብቃት በምግብ ላይ ሌላ የዋጋ መናር አስከትሎ በ10 ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለረሃብ እንዳያጋልጥ ያሰጋል ሲሉ የረድኤት ባለሥልጣናት ዛሬ አስጠንቅቀዋል።የረድኤት ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ የተሰማው ሞስኮ ለዓለም ገበያ በምታቀርበው እህል እና ማዳበሪያ ላይ የተጋረጠው እንቅፋት ካልተነሳ በመንግሥታቱ ድርጅት አደራዳሪነት ከስምምነት ከተደረሰው የጥቁር ባሕር ውል ልትወጣ እንደምትችል ካስጠነቀቀች በኋላ ነው።
ሃገራቱ የፊታችን ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ/ም ሲገናኙ ሩስያ ከውሉ ለመውጣቷ ሙሉ ለሙሉ እርግጠኛ መሆናቸውን የዩክሬን ልዑክ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ነግረዋል።ሩሲያ ያለችውን ካደረገች ደግሞ ለአምስትና ተከታታይ ዓመታት ዝናብ አጥ የሆነው የአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ለከፋ ረሃብ ሊጋለጥ እንደሚችል አስግቷል።
ይህም በሰባት የአፍሪቃ ቀንድ ሃገራት የሚኖሩ 60 ሚሊዮን ሰዎችን ለምግብ ዋስትና እጦት እና አልፎም ለረሃብ ሊያጋልጥ እንደሚችል የረድኤት ድርጅቶች ባለሥልጣናት አስጠንቅቀዋል።ሩስያ እና ዩክሬን የጥቁር ባሕርን ውል ከተፈራረሙ ወዲህ ከ700 ሺህ በላይ ቶን እህል ወደ ኢትዮጵያ እና ኬንያ መጓጓዙን የመንግሥታቱ ድርጅት መረጃ ያመለክታል።
ይህም ለቀጣናው ሃገራት መቅረብ ከሚገባው ከሁለት በመቶ እምብዛም ፈቀቅ ያላለ ነው።የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመለክተው በቀጣናው 10.4 ሚሊዮን ሕጻናት ለከፋ የምግብ እጥረት መዳረጋቸውን አመልክቷል። ባለፉት ሦሥት ዓመታት በተለይ በሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኬንያ በዚሁ ችግር ወደ ህክምና የመጡ ሕጻናት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን መረጃው አክሏል።
[DW]
@YeneTube

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ከኃላነታቸው ለቀቁ!
ወ/ሪት ብርቱካን “በገዛ ፍቃዴ መልቀቄን ለተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ ጽህፈት ቤት ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም አሳውቄያለሁ” ብለዋል።ከኃላፈነታቸው የለቀቁበት ምክንየትም “ጤናዬን በሚገባ ለመጠበቅ የረጅም ጊዜ እረፍት የሚያስፈልገኝ” ነው ብለዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
ወ/ሪት ብርቱካን “በገዛ ፍቃዴ መልቀቄን ለተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ ጽህፈት ቤት ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም አሳውቄያለሁ” ብለዋል።ከኃላፈነታቸው የለቀቁበት ምክንየትም “ጤናዬን በሚገባ ለመጠበቅ የረጅም ጊዜ እረፍት የሚያስፈልገኝ” ነው ብለዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
በኤሌክትሪክ አደጋ እናትና ልጅን ጨምሮ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በአዲስ አበባ እና ደቡብ ክልል በኤሌክትሪክ አደጋ እናትና ልጅን ጨምሮ የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ትናንት ከቀኑ 9:10 ላይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አትላስ ፊትለፊት በሚገኝ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር ላይ ዕድሜው 35 ዓመት የሚገመት በኤሌክትሪክ አደጋ ሕይወቱ አልፏል።
አስከሬኑን ለፖሊስ ማስረከባቸውን ጠቁመው÷ በአዲስ አበባ በሁለት ወራት ውስጥ በኤሌክትሪክ አደጋ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስታውሰዋል፡፡
በሌላ በኩል በደቡብ ክልል ሀላባ ዞን አቶቴአሎ ወረዳ ጤፎ ጩፎ ቀበሌ ከኤሌክትሪክ ምሰሶ ላይ ተቆርጦ የወደቀ የኤሌክትሪክ ገመድ የእናትና ልጅን ሕይወት ቀጥፏል፡፡
በአደጋው የ23 ዓመቷ እናት ከ2 ዓመት ልጇ ጋር ሕይወታቸው ማለፉን የደቡብ ክልል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa

በዋግነር መሪ ላይ የተከፈተው ክስ ይቀጥላል ተባለ!
የታጠቁ ወንጀለኞችን በማደራጀት የተከሰሰው የዋግነር የግል ወታደራዊ ኩባንያ (PMC) መስራች በሆነው የቭጀኒ ፕሪጎዝኒ ላይ የተከፈተው የወንጀል ክስ ምርመራ አልተዘጋም ሲል የሩሲያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ ምንጭ ለሩሲያው የዜና ወኪል ታስ አረጋግጧል። "በፕሮጎዝኒ ላይ ያለው የወንጀል ክስ አልተዘጋም ምርመራው ቀጥሏል" ሲል ምንጩ ተናግሯል።
ኮሜርሳት የተሰኘው የሩሲያ ጋዜጣ በበኩሉ በሰኞ ማለዳ እትሙ ላይ ፕሪጎዝሂን እና የታጠቁ የቡድኑ አባላትን የሚመለከተው የወንጀል ክስ እንዳልተዘጋ እና በሩሲያ የፌደራል ደህንነት አገልግሎት (FSB) ምርመራ መጀመሩን እንደቀጠለበት ዘግቧል። ቅዳሜ እለት የሩሲያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጽ / ቤት የታጠቁ ወንጀለኞችን በማደራጀት በሩሲያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀጽ 279 በየቭጅኒ ፕሪጎዝሂን ላይ የወንጀል ክስ መከፈቱን አስታውቆ ነበር።
ጉዳዩ የተጀመረው ፕሪጎዝሂን በቴሌግራም ቻናል ላይ በወታደሮቼ ላይ ጥቃት ደርሶባቸዋል የሚል መግለጫን ካጋራ በኋላ ሲሆን የዋግነር ደጋፊዎች በሀገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎች ላይ እንዲነሱ ጥሪ በማቅረቡ የተነሳ ነው። በወንጀሉ ከ12 እስከ 20 ዓመታት እስራት ሊቀጣም እንደሚችል ተመላክቷል።
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቴሌቭዥን ባስተላለፉት መልዕክት አመፁን ከባድ ወንጀ፤ የአገር ክህደት እና ሽብርተኝነት ሲሉ አውጀው ነበር። ሆኖም ግን ከጥቂት ሰዓታት በኋላ፣ ከፕሪጎዝሂን ጋር በተደረገው ስምምነት፣ በዋግነር መሪ ላይ የተመሰረቱት ሁሉም የወንጀል ክሶች የተቋረጡ መሆናቸው ተገለጸ። በድጋሚ ደግሞ ክሱ ይቀጥላል መባሩ አነጋጋሪ አድርጎታል።
[ዳጉ ጆርናል]

በአዲስ አበባ ከተማ በአጠቃላይ 297 ያክል ቦታዎች ለጨረታ የቀረቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 4 ቦታዎች ለጨረታ ብቁ እንዳልሆኑ በባለሙያዎች መለየታቸው እና ሌሎች 6 ቦታዎች ደሞ በቂ ተጫራች ሳያገኙ መቅረታቸውን አቶ ሃብታሙ ተናግረዋል።
በድምሩ13 ሄክታር ገደማ ስፋት ባላቸው በቀሪዎቹ 287 ቦታዎች ላይ በቂ ተጫራቾች ተገኝተው አሸናፊዎች የተለዩ ሲሆን አሁን ላይ ወደ ውል ማሰር እና ሌሎች ሂደቶች እንደተገባ ገልጸዋል።
በሊዝ ለጨረታ ከቀረቡት ቦታዎች 7.7 ቢሊዮን ብሩን ተጫራቾች ቦታውን እንደተረከቡ ክፍያ የሚፈጽሙበት ሲሆን ቀሪው 4.5 ቢሊዮን ብር ደግሞ ከተማ አስተዳደሩ በሰጠው የሊዝ መክፈያ የ5 ዓመት የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚከፈል ነው።
በተደረገው ቦታዎችን በሊዝ ጨረታ የማስተላለፍ ሂደት በአራዳ ክፍለ ከተማ 1 ካሬ በ414 ሺህ ብር በከፍተኛ ዋጋ የተሸጠው ሲሆን ዝቅተኛው ደግሞ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ20 ሺህ ብር የተሸጠው መሆኑ ተነግሯል።
አቶ ሀብታሙ የጨረታ ሂደቱ ከዚህ በፊት ከነበረው የተሻለ ግልጽነት የተስተዋለበት እና ተጫራቾች እያንዳንዱን ሂደት በአካል እንዲከታተሉ የተደረገበት እንደሆነም ገልጸዋል።
ነገር ግን በጨረታው ሂደት ላይ ከቴክኖሎጂ ጋር በተያያዙ አሰራሮች ስህተቶች ተፈጥረው እንደነበር ጠቅሰው፤ በችግሮቹ ላይ ማስተካከያ መደረጉን ነው የተናገሩት።
ተጫራቾችም ምንም አይነት ቅሬታ ካላቸው መስሪያ ቤቱ ይህንን ለማስተናገድ ክፍት መሆኑን ገልጸዋል።
ላለፉት አምስት ዓመታት መሬትን በሊዝ የማስተላለፍ ሂደት ተቋርጦ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሀብታሙ፤ ለዚህ ምክንያቱ በመሬት አያያዝ ስረዓቱ ላይ ክፍተት እና ህገ ወጥነት ይስተዋል ስለነበር መሬት ኦዲት እየተደረገ በመቆየቱ ነው ብለዋል።

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጭንቅላት ቀዶ ህክምና ያለ ሪፈር እንደሚያስተናግድ ገለጸ።
የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለማህበረሰቡ ያለ ሪፈር የጭንቅላት ቀዶ ህክምና እየሰጠ መሆኑን የሆስፒታሉ የጭንቅላት ቀዶ ህክምና ክፍል አስታውቋል።
የክፍሉ ሀላፊ ዶ/ር አብዲ ኤርሜሎ እንደገለጹት የህጻናት ጭንቅላት ቀዶ ህክምና ብቻ ላይ ይሰጥ የነበረው አገልግሎት የአዋቂዎችንም የህክምና አገልግሎት ጨምሮ እየተሰጠ ይገኛል።
በህጻናት የህክምና አገልግሎት በኩል የሃይድሮሴፋለስ (የጭንቅላት ውሃ መቋጠር) ህመም ህክምና ፣ የኤምኤንሲ ቀዶ ህክምና፣ በአከርካሪ ላይ የሚወጡ ዕጢዎች ህክምና እና ከወሊድ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የተለያዩ የጭንቅላት ችግሮች ህክምና የሚሰጥባቸው ናቸው።
በአዋቂዎች ህክምና ደግሞ የአንጎልና አከርካሪ ዕጢዎች፣ የዲስክ መንሸራተት ከአደጋ ጋር በተገናኘ የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ህክምናዎች እየተሰጡ እንደሚገኙ ዶ/ር አብዲ ተናግረዋል።
#ከሁለት_ወር በፊት የኢንዶስኮፒክ ቀዶ ህክምና መጀመሩ በተለይ ለህጻናት የሚደረገውን ህክምና በማሻሻል የጭንቅላት ውሃ መቋጠርን ለማከም ከጭንቅላት ወደ ሆድ የሚሄድ ቱቦ (vp shunt) በመጠቀም ይሰጥ የነበረውን ህክምና የጎንዮሽ ጉዳቶች በኢንዶስኮፒክ ሰርጀሪ ማስቀረት እንደተቻለም ገልጸዋል።
የህክምና አገልግሎቱ በሳምንት አምስት ቀን እየተሰጠ በወር ከ50 እስከ 60 ቀዶ ህክምናዎች እየተሰሩ የሚገኙ ሲሆን በቀጣይ የሲአር ማሽን ግዢ ተጠናቆ ወደ ስራ ሲገባ ደግሞ የአከርካሪ አጥንት ስብራት ህክምናን ጨምሮ ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶች በሰፊው እንደሚሰጡ ዶክተሩ ተናግረዋል።
በሆስፒታሉ የጭንቅላት ቀዶ ህክምና በከፍተኛ ደረጃ እንዲሰጥ የሆስፒታሉ የማኔጅመንት አባላት ላደረጉት ከፍተኛ ጥረት ሊመሰገኑ ይገባቸዋል ያሉት ዶክተሩ ህብረተሰቡም የህክምና አገልግሎቶቹን ያለ ሪፈር እንደሚሰጡ አውቆ ህክምና ማግኘት እንደሚችል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።