YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ቮልስዋገን ከሰሞኑ ቮልስዋገን ኩባንያ ID4 እና ID6 መኪኖቹን የገዙ ከቻይና ውጪ ያሉ ደንበኞች ለተሸከርካሪዎቹ የዋስትና መብት አያገኙም፣ ለሌሎች ሀገራት ተስማሚነታቸውም አልተረጋገጠም ብሎ ነበር።

እዚህ ጋር ዋናው ጥያቄው መሆን ያለበት ለሀገራችን ተስማሚነቱ ካልተረጋገጠ የሰው ህይወት ላይ ጭምር አደጋ ሊያስከትል የሚችል የተሽከርካሪ "ፍቃድ በሌላቸው ሻጮች" እንዴት ወደ ሀገር ሊገባ ቻለ? ጉዳዩ የሚመለከተው የመንግስት አካል ወደ ሀገር የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ የራሱ ምዘና የለውም?

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እግዱን ያስተላለፈው ቮልስዋገን ኩባንያ አስቁሙልን ብሎ ጠይቆ እንጂ የደህንነት ችግር ሊኖርባቸው ይችላል ብሎ በራሱ ወስኖ አይደለም።

ሚኒስቴሩ ስለጉዳዩ ሲጠየቅ "መኪኖቹን ያገድነው ለኢትዮጵያ መንገዶች ብቁ መሆናቸውን ማረጋገጥ ስለሚኖርብን ነው" የሚል ምክንያት ሰጥቷል፣ ታድያ ይህ ማረጋገጫ የሚሰጠው ዜጎች ሚሊዮኖችን ከፍለው ካበቁ እና መኪናው ሀገር ውስጥ በገፍ ከተሸጠ በኋላ ወይስ በፊት?

ለማንኛውም፣ የጀርመን ኤምባሲን በዚህ ጉዳይ መረጃ ጠይቄ "ዜናውን እስካሁን በሚድያ ያስነገረው የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ነው፣ ኤምባሲያችን በቮልስዋገን ኩባንያ እና በሚመለከታቸው የመንግስት አካላት መሀል ውይይት ለማስጀመር ጥረት እያረገ ይገኛል" የሚል ምላሽ አድርሶኛል።

በነገራችን ላይ እንደ ጆርዳን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ግብፅ ያሉ ሀገራት ይህን የመኪና ሞዴል እንደ ባትሪ እና ሌሎች የቴክኒክ ችግሮች እንዳሉበት በመጥቀስ ሀገራቸው እንዳይገባ ያገዱት ከበርካታ ወራት በፊት ነበር።
ኤሊያስ መሰረት የዘገበው 👆