YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ቀድሞ ይፋ ባልተደረገ ጉብኝት ኬንያ ገብተዋል።

የሞስኮ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የሚኒስትሩን ሰኞ ንጋት ላይ ናይሮቢ መግባት ይፋ ያደረገ ቢሆንም ለምን እንደመጡ ግን ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጠም።በናይሮቢ የሩሲያ ኤምባሲ በትዊተር ገጹ “ፍሬያማ የሁለትዯች ግንኙነት ለሩሲያና ኬንያ” የሚል መልዕክት አስፍሯል።የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ዛሬ ሰኞ የናይጄሪያው አዲሱ ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ በዓለ ሲመት ጉዟቸውን በላቭሮቭ ጉብኝት ምክንያት ሳይሆን አይቀርም፣ ሰርዘዋል።

ላቭሮቭ ወደ ኬንያ የመጡት የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲመትሪ ኩሌባ አዲስ አበባን ጨምሮ በአፍሪካ አገራት ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።ላቭሮቭ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ወደ አፍሪካ ሲመጡ ይህ የመጀመርያቸው አይደለም።በፈረንጆች በሐምሌ ወር 2022፣ ግብጽን የጎበኙት ላቭሮቭ ወደ ኮንጎ ብራዛቪል አቅንተው ከዚያ ኢትዮጵያን እና ኡጋንዳን ጎብኝተው ነበር።በጥር ወር 2023 ዓ/ም ደግሞ ኤርትራን መጎብኘታቸውና ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር መምከራቸው አይዘነጋም።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
1
የዲጂታል የነዳጅ ግብይት ላይ የሚፈጠሩ መስተጓጎሎችን ተከትሎ የጥቁር ገበያ የነዳጅ ግብይት እየተስፋፋ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል መገበያያ መንገዶች ብቻ እንዲሆን መደረጉ የሚታወቅ ቢሆንም በዚሁ ምክንያት የተፈጠሩ መስተጓጎሎችን ተከትሎ በህገ ወጥ መንገድ የጥቁር ገበያ መስፋፋቱን የትራንስፖርት ሚንስቴር የነዳጅ ድጎማ ፕሮጀክት አስተባባሪው አቶ ሰልማን መሃመድ ገልጸዋል፡፡

በተለይ በክልሎች ላይ ለአርሶ አደሮች እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት በጀሪካን እና በበርሜል እንዲገዙ ፈቃድ የሚሠጥ ሲሆን በዲጂታል ግብይት አጀማመር ላይ የነበረውን መስተጓጎል እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የጥቁር ገበያ የነዳጅ ግብይት እንዲስፋፋ ማድረጉን ነው የገለፁት።

ይህንንም ለመቆጣጠር ከክልል የንግድ ቢሮዎች እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ የክትትል ስርአት በመዘርጋት አስፈላጊው ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

አክለውም እየተሠሩ ባሉት የቁጥጥር እና የእርምጃ ስራዎች በጥቁር ገበያ የሚካሄደው የነዳጅ ግብይት መቀነስ እንደተቻለ ገልፀው ይህን ህገ ወጥ ግብይት ሙሉ ለሙሉ ማስቆም እስከሚቻልበት ጊዜ ድረስ የክትትል ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

[Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1😭1
#ScamAlert

"በአሁኑ ወቅት በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት የብድር አገልግሎት በመስጠት ላይ አይደለንም"--- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት አማካኝነት የብድር አገልግሎት እየሰጠ ነው በሚል የሀሰት መረጃ ስርቆት ለመፈፀም የሚሞክሩ አጭበርባሪ መልእክቶች እየተሰራጩ እንደሚገኙ ዛሬ አስታውቋል።ባንኩ እንዳለው እነዚህ የማጭበርበርያ መልዕክቶች ደንበኞች ብድር ለማግኘት እንዲጠቀሙበት ባስቀመጡት ሀሰተኛ ኮዶች አማካኝነት ከደንበኞች ሂሳብ ላይ ገንዘብ ለመስረቅ እየሞከሩ ነው፡፡

"ነገር ግን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአሁኑ ወቅት በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት የብድር አገልግሎት በመስጠት ላይ አይደለም። በመሆኑም ደንበኞች ከንደዚህ ዓይነት አጭበርባሪዎች እራሳችሁን እየጠበቃችሁ ባንኩ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች መረጃ ማግኘት ያለባችሁም ከግለሰቦች ሳይሆን ከባንኩ ቅርንጫፎች፣ ወደ 951 በመደወል እና ከባንኩ ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ብቻ መሆን እንዳለበት እንገልጻለን" ብሏል።

Via Commercial Bank of Ethiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ከ24 ሰዓት ውስጥ 16ቱን ሰዓት አገልግሎት መስጠት ጀምሬበታለሁ አለ፡፡

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የነዋሪውን ከፍተኛ የትራንስፖርት ፍላጎት ግምት ውስጥ በማስገባት የአገልግሎት ሰዓቱ ላይ ማስተካከያ አድርጌያለሁ ብሏል፡፡

ቀላል ባቡሩ ቀደም ሲል ከጠዋት 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ማለትም በየቀኑ ለ14 ሰዓታት የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት በአሁኑ ወቅት ማለትም ከግንቦት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰዓቱን እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት በማራዘም በየቀኑ ለ16 ሰዓታት ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ይፋ አድርጓል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በዛሬው እለት በተከሰተ የእሳት አደጋ በአምስት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ደረሰ!

በዛሬ  እለት ግንቦት 21 ቀን 2015 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በአንድ ንግድ ቤትና በአንድ መኖሪያ ቤት ባጋጠመ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ሲደርስ በአምስት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል።በእሳት አደጋዉ አንድ  የተሽከርካሪ ጌጣጌጥ ሙሉ በሙሉ ሲወድም በታፒሴሪዉ ለአገልግሎት ቆመዉ የነበሩ ሁለት ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል።

የእሳት አደጋዉ ለመቆጣጠር ጥረት ሲያደረጉ ከነበሩ ነዋሪዎች መካከል በአምስቱ ላይ ቀላል ላይ ጉዳት ደርሷል።የእሳት አደጋዉ ወደተሽከርካሪዎቹ በመዛመቱ በቀላሉ ሊስፋፋ ችሏል።የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 7 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ የተሰማራ ሲሆኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እሳቱ ተዛምቶ ከዚህ የከፋ አደጋ ሳያደርስ መቆጣጠር መቻሉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

[ዳጉ ጆርናል/Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ እየሱስ በጋምቤላ ክልል ባንድ የቤተክርስቲያኗ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ግንቦት 12 ቀን ባደረሱት ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች እንደተገደሉ ዛሬ ባወጣችው መግለጫ አስታውቃለች።

ጥቃቱ 11 ሰዓት ገደማ የተፈጸመው፣ በምዕራብ ጋምቤላ ቤተል ሲኖዶስ አገልግሎት ክልል "ማታራ" በተባለ ቀበሌ ውስጥ መኾኑን መግለጫው አመልክቷል። ከ2 ሺህ 700 በላይ የመንፈሳዊ ጉባዔው ተሳታፊ ወጣት ሴቶች፣ እናቶችና ሕጻናት የዕለቱን መንፈሳዊ መርሃ ግብር አጠናቀው ለእራት በተቀመጡበት ወቅት፣ ድንገት የደረሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ሕጻናትን አፍነው ለመውሰድ በሞከሩበት ወቅት በተፈጠረ ግብግብ፣ መንፈሳዊያኑ ላይ ተኩስ እንደከፈቱ ቤተክርስቲያኗ ጨምራ ገልጣለች። ከተገደሉት መካከል አንዲት ሕጻን እንደምትገኝበትና፣ በጥቃቱ የቆሰሉ በርካታ ምዕመናን ጋምቤላ ሆስፒታል ውስጥ ሕክምና ላይ እንደኾኑም በመግለጫው ላይ ተገልጧል።

[ዋዜማ]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
Photo
"በሕገ መንግስት ማሻሻያ ስም ሀገሪቷ እንድትፈርስ መደላድል እየተዘጋጀ ነው" - ኦፌኮ

የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት ማሻሻያ ተብሎ በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢኒስቲቲዩት የቀረበውን ጥናት አስመልክቶ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ግንቦት 21ቀን 2015 ዓ.ም መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው "በህገመንግሰት ማሻሻያ ስም የሕብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም ስርዓት እንዲናድ እና ሃገሪቱ እንድትፈርስ መደላድል እየተዘጋጀ ነው" ሲል ከስሷል።ይህ በሦስት ገፅ የተቀነበበው መግለጫ የተቋሙን ጥናት በብርቱ ተችቷል።

ለአብነትም "የኢትዮጲያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት የኢፌዲሪ ሕገ መንግሰት ምሰሶ የሆኑትን ለይቶ በመምረጥ የህገመንግስቱን መግቢያና አርማን ጨምሮ፣ የፌዴራል የስራ ቋንቋ (አንቀፅ 5)፣ የብሔሮች፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት (አንቀፅ 8) ጨምሮ ስድስት አንቀፆች መሻሻል እንዳለባቸው አረጋግጪያለሁ" ማለቱን ነቅፏል።

ኦፌኮ እንደሚለው "በጥናቱ ላይ የሚስተዋሉ የጥናት ዘዴ፣ የወቅታዊነት፣ በጉዳዩ ላይጥናት የማካሄድ ስልጣን አለመኖር የመሳሰሉ የጎሉ ችግሮችና የዚህ ጥናት የተሳሳቱ መደምደሚያዎች ሊያስከትሉ የሚችሏቸውን አደጋዎች በስፋት" ገምግሟል።

ኮንግረሱ በመግለጫው "ድርጅታችን የህግ፣ የፖለቲካ፣ የታሪክና መሰል ባለሙያዎች አስተያየት፣ እንዲሁም የሃገራችንን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ስሜትና ፍላጎትን ከመዘነ በኋላ ይህ ጥናት ተቀባይነት የለውም" ሲል አቋም ይዟል።

"መፍትሄ" ያላቸውን 7 ነጥቦች ዘርዝሯል።"ይህን ጥናት ያካሄደው አካል የተጠቀመበት የጥናት ዘዴ (Methodology) ከፍተኛ ስህተት አለበት ብዬ አምናለሁ" የሚለው ኦፌኮ "በመጀመሪያ ደረጃ ለጥናቱ የተወሰደው ናሙና ወካይነት እና ሽፋን ከፍተኛ ችግር ያለበትና ከጥናቱ የተገኘውን ውጤት ጥርጣሬ ውስጥ የሚከት ነው።" ብሎታል።

"የ120 ሚሊዮን ዜጎችን ችግር ለመረዳት የ1ሺህ123 ሰዎች ብቻ አስተያየት መቀበሉ እና ለ106,687 ሰዎች 1 ሰው ብቻ እንዲወክል መደረጉ፣ በመቶኛ ሲሰላም የ 0.0001% ሰዎች አስተያየት መሆኑ፣ የጥናት ውጤቱ ተዓማኒነት ወደ ዜሮ ዝቅ የሚያደርገው ሆኖ ተገኝቷል።" ባይ ነው።

የኦፌኮ ሲቀጥል "ከአማራና ሲዳማ ክልል በጥናቱ የተካተቱ መላሾች ህብረ ብሄራዊ የፌዴራል ስርዓቱን እንደማይደግፉ በማስመሰል የቀረበው ውጤት በተጨባጭ መሬት ካለው እውነታ ጋር የሚቃረን ነው።" ሲል ገልፆል።

ለዚህም እንደማሳያ ተከታዮቹን ነጥቦች በመከራከሪያነት አስቀምጧል።

"የአማራ ኃይሎች በአሁኑ ሰዓት በብሄር ማንነቱ ተደራጅቶ በምርጫ በመሳተፍ በፓርላማ በመታቀፍ ለመብቱ እየታገሉ ሳለ፣ ሌሎቹም የብሄር መብታቸው እንዲከበርና የአማራ ሃገር እንመሰርታለን በማለት ፋኖ በሚል ስም እንዲሁም በቅርቡ የአማራ ሕዝባዊ ግንባር የሚባል ድርጅት በማቋቋም ጫካ ገብተው የትጥቅ ትግል እያካሄዱ ሳለ፣ በብሄር መደራጀትን አይደግፉም ማለት ፌዝ ነው።" ሲል አጣጥሏል።

"የሲዳማ ሕዝብም በራሱ ክልል እራሱን ለማስተዳደር ለዘመናት ሲታገል ቆይቶ ከሁለት ዓመታት በፊት በሪፈረንደም ያስከበረውን መብቱን በሚቃረን መልኩ የብሄሮች መብት ከህገመንግሰቱ እንዲፋቅ የሚል ሃሳብ ደግፏል ማለት ከእውነት የራቀ ነው።" ብሏል -ኦፌኮ

የመግለጫው ሙሉ ይዘት በአባሪነት ተያይዟል።

@YeneTube @FikerAssefa
መርጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል በቲክቶክ መቷል።

የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ

👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።

    ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ

👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
                   👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
          0912718883

    ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah

👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ

tiktok.com/@u0917040506_0912718883
ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር

ላንጋኖ  ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች

✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

✔️  ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

✔️  ዘመናዊ ኪችኖች

✔️  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
       
       ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣

♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣

♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን

♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣

♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን

♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣

♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡

🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ

በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511

ይደውሉልን,ይጎበኙን!       
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት
👍1
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥

🌕ድርጅታችን ከታች በተዘረዘሩ የስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት ይፈልጋል። 

🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

💥NGO በማንኛውም

     🔹የት/ደረጃ:ዲፕሎማ/ድግሪ
     🔹የስራ ልምድ: 0 ዓመት
     🔹ደሞዝ: 18,500+

💥ሹፌር በሁሉም

     🔹የት/ደረጃ:መፃፍ ማንበብ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ:13,500+

💥ስልክ ኦፕሬተር

     🔹የት/ደረጃ: 10 ጀምሮ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ: 6500

💥ጉዳይ አስፈፃሚ

     🔹የት/ደረጃ:10
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ:7000

💥ባንክ ቤት ፅዳት ተላላኪ

    🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ፡4500

💥አካውንታንት

🔹የት/ት ደረጃ= ድግሪ/ድፕሎማ
🔹 ልምድ = 0-2 አመት
🔹ደሞዝ=8500

💥ካሸር አሰልጥኖ

🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500

💥ባርማን/ባሬስታ

🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት

💥 ዌተር የጧት እና የከሰዓት

     🔹የት/ደረጃ: 10 ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ: 3500


💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች

     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,000

💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)

🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
በ35 ባለ ኮከብ ሆቴሎች ላይ እርምጃ ተወሰደባቸው።

በአዲስ አበባ ከተማ በህገወጥ መንገድ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ሆቴሎች ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተብሏል።የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ጌታሁን አበራ፣ ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ያልተገባ አገልግሎት እየሰጡ በተገኙ ባለ ኮከብ ሆቴሎች ህጋዊ እርምጃ አየተወሰደባቸው ይገኛል ብለዋል።

ሆቴሎቹ ሺሻ ሲያስጠቅሙ የተገኙ ሲሆን በዚህ ህገወጥ ተግባር ተሳትፈው የተያዙ 1ሺህ 250 ሰዋች መያዛቸውንም ተናግረዋል።

በተያያዘ የህግ ማስከበር ዜና

ህገ-ወጥ በሆኑ ጫኝና አውራጆች ላይ እርምጃ እየተወሰደባቸው እንደሚገኝም ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

ለህብረተሰቡ ችግር የሆኑ በመዲናዋ በጫኝ እና አውራጅ ስራ ላይ በተሰማሩ ሰዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል።የቢሮው ሃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በማህበር ተደራጅተው ዜጎችን ያላግባብ በሚያስከፍሉት ላይ እርምጃ እየወሰድን እንገኛለን ብለዋል።እነዚህ ሰዎች ነዋሪዎች በሃገራቸው ተስፋ እንዲቆርጡ እያደረጉ ናቸውም ብለዋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረትና በታክስ ላይ የሚፈጸመውን ማጭበርበር ለመካለከል የቀረበው አዋጅ ጸደቀ!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት እና በታክስ ላይ የሚፈጸመውን ማጭበርበር ለመከላከል የቀረበውን አዋጅ አጸደቀ፡፡የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 23ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ፣ስዊዘርላንድ እና በግራንድ ዱቺ ኦፍ ሉዘምበርግ መንግስት መካከል በገቢ ላይ የሚከፈለውን ግብር በሚመለከት በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ መክሯል፡፡በሀገራቱ መካከል ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት እና በታክስ ላይ የሚፈጸምን ማጭበርበር ለመከላከል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አዋጁን አጽድቋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ከገንዘብ ሚኒስቴር የሕግ አማካሪ በተለያዩ መድረኮች በረቂቅ አዋጁ አስፈላጊነት ላይ እንደተወያየም የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡የምክር ቤቱ አባላትም÷ረቂቅ አዋጁ በታክስ ማጭበርበር የሚታዩ ግድፈቶችን ለማረም የሚያስችል እና የሀገራቱን ግንኙነት የሚያጠናክር አዋጅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa