YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#Scamalert

ከ50 እስከ 100 ዶላር ታገኛላችሁ በማለት በቴሌግራም እየተሰራጨ የሚገኘው ሊንክ ፍጹም ውሸት ነው። እንዲሁም ዌብሳይቱ ላይ ገብታችሁ ስልክ ቁጥራችሁን ስታስገብ ቴሌግራም የላከላችሁን ቁጥር አስገብ ይላሉ በምታስገቡበት ወቅት አካውንታችሁን የውስድባችኃል።

እውነተኛነታቸው የተረጋገጡ በይነ መረብን በመጠቀም ስራ መስራት የሚያስችሉ ገፆች ➡️ www.freelancer.com | www.upwork.com ታዋቂዎቹ እነዚህ ናቸው እኚህን በመጠቀም መስራት ይችላሉ።

@Yenetube @Fikerassefa
#ScamAlert

"በአሁኑ ወቅት በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት የብድር አገልግሎት በመስጠት ላይ አይደለንም"--- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት አማካኝነት የብድር አገልግሎት እየሰጠ ነው በሚል የሀሰት መረጃ ስርቆት ለመፈፀም የሚሞክሩ አጭበርባሪ መልእክቶች እየተሰራጩ እንደሚገኙ ዛሬ አስታውቋል።ባንኩ እንዳለው እነዚህ የማጭበርበርያ መልዕክቶች ደንበኞች ብድር ለማግኘት እንዲጠቀሙበት ባስቀመጡት ሀሰተኛ ኮዶች አማካኝነት ከደንበኞች ሂሳብ ላይ ገንዘብ ለመስረቅ እየሞከሩ ነው፡፡

"ነገር ግን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአሁኑ ወቅት በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት የብድር አገልግሎት በመስጠት ላይ አይደለም። በመሆኑም ደንበኞች ከንደዚህ ዓይነት አጭበርባሪዎች እራሳችሁን እየጠበቃችሁ ባንኩ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች መረጃ ማግኘት ያለባችሁም ከግለሰቦች ሳይሆን ከባንኩ ቅርንጫፎች፣ ወደ 951 በመደወል እና ከባንኩ ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ብቻ መሆን እንዳለበት እንገልጻለን" ብሏል።

Via Commercial Bank of Ethiopia
@YeneTube @FikerAssefa