YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አፍሪካ ኅብረት በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞኖች በንጹሃን ዜጎች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ላይ ምርመራ እንዲደረግ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አድርጓል።

የኅብረቱ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ዛሬ ባወጡት መግለጫ፣ በጥቃቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ስለመገደላቸው የደረሷቸው መረጃዎች እንዳሳሰቧቸው ገልጸዋል። ኅብረቱ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና ክልል መንግሥታት አናሳ ሕዝቦችን ጨምሮ ሁሉንም ሰላማዊ ሰዎች ከጥቃት እንዲከላከሉ እና እንዲህ ያሉ ጥቃቶችን ለመከላከል የሚያስችሉ ርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ አድርጓል። ኅብረቱ ምርመራ እንዲካሄድ የፈለገው በኢትዮጵያ መንግሥት አማካኝነት ይሁን ወይስ በሌላ ገለልተኛ አካል መግለጫው ግልጽ አላደረገም።

@YeneTube @FikerAssefa
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ምክነያት የነገዉ የጋራ መኖሪያቤት እጣ ስነስርዓት ለአርብ ተዘዋወረ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ14ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ስነስርዓት ለማካሄድ በበነገው እለት ፕሮግራም ተይዞ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ነገር ግን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠራው ስብሰባ ምክንያት የእጣ አወጣጥ ስነስርዓት ወደ ፊታችን አርብ ሃምሌ 1/2014 የተዛወረ መሆኑን ከታላቅ ይቅርታ ጋር ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

ታዛቢዎች ባለእድለኞች እና ሌሎችም በክብር እንግድነት የምትገኙ እንግዶችና የሚድያ አካላት በሙሉ ለተፈጠረው የፕሮግራም ለውጥ ይቅርታ እየጠየቅን በተለዋጩ ፕሮግራም መሰረት እንድትገኙልን ከወዲሁ እናሳስባለን ሲል ከተማ መስተዳድሩ አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ብራቮ፣ በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን የተሰራ የግል ፋይናንስ አስተዳዳሪ መተግበሪያ

በጀቶን በብቃት ለማውጣት ፣ የገንዘብ ልውውጦን በቀላሉ ለመከታተል ፣ የፋይናንስ እውቀቶንም ለመጨመር አሁኑኑ መተግበሪያውን አውርደው ይጠቀሙ።

ወቅታዊ መረጃዎችንም ቻናላችን በመቀላቀል በቀለላሉ ያገኙ
https://tttttt.me/birravo
መፍትሔ ስራይ ወአይነ ጥላ
መርጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድሀኒቶች ፍቱን ህክምናወችን እንሰጣለን።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረበትን
👉ሆዱን ለሚአመው
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ሁሉም ቦታ ላይ ላሉ ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለአቃቤ እርእስ ለጥላት መጠበቂያ
👉ለማንኛውም አይነት ቁስል
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ በሄደበት ሁሉ ሰው እንዲወደው
👉ለአይነ ጥላ
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉የሚአስቡት ሁሉ አልሳካ ላለ
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ለእራስ ህመም
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉ፍቅረኛ ላጣ
👉የሌባ ገትር ሌባ እማያስነካ
👉ለሚጥል በሽታ
👉ገንዘብ ለሚበተንበት
👉ስራ አልሳካለት ላለ
👉ለቡዳ
👉ለመስተፋቅር
👉ገበያ ለሚገረግረው ለገብያ
👉ለመፍትሄ ስራይ
👉ለስንፈተ ወሲብ ሲገናኝ ለሚቸኩልበት
👉ለአስም (ሳይነስ)
👉ለትዳር ለማይስማሙ ለመስተዋድድ

እንዲሁም የተለያዩ
መድኀኒቶችን እንቀምማለን

እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ ።

እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
መድሀኒቱን ባሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል

👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
0912718883

https://tttttt.me/meritibe

👉ቻናሉን በመቀላቀል ጥንታዊ የአባቶች ጥበብ እንደወረደ ያገኙታል በየስሀቱ የምንለቃቸውን ተደብቀው የቆዪ የብራና መጽሀፍ በሚፈልጉት አይነት ይለቀቃሉ የሚፈልጉትን ለማግኔት ይቀላቀሉ ሼር ሼር ሼር ያድርጉ
#ከማን_ጋር_ነህ?
#የስኬት_ቀመር መጽሐፍ 4ተኛው ዕትም በገበያ ላይ

'ሁልጊዜ ከሁለት ነገሮች በስተቀር በአምስት አመት ውስጥም ልክ እንደዛሬው ነህ’ ይላል፡፡” አለና በክላንድ ለረጅም ጊዜ እንግዳውን አፍጥጦ ተመለከተ፡፡

ፀጥታውን ለመስበር ይህ አዲሱ አስተዋይ ተማሪ “የትኞቹ ሁለት ነገሮች?” ሲል ጠየቀ፡፡

በክላንድ በፈገግታ ጠረጴዛው ላይ ወዳለው መጽሀፍ እየጠቆመ “ሁለቱ ነገሮችማ የምታገኛቸው ሰዎችና የምታነባቸው መጻህፍት ናቸው፡፡ አስበው እኛ ያለን እውቀትና አብረናቸው የምንሆናቸው ሰዎች ድምር ውጤት ነን፡፡ ከጋዜጣ በስተቀር ምንም ነገር የማታነብ ከሆነ፣ የምታውቀው ያንን ብቻ ይሆናል፡፡ የምታነበው የታላላቅ ሰዎችን የህይወት ታሪክና መንፈስን የሚቀሰቅሱ መፃህፍትን ከሆነ የምታውቀው ያንን ብቻ ይሆናል፡፡” አለ፡፡

“እሺ ገባኝ፡፡ ‘የምናገኛቸው ሰዎች’ የሚለውም ነገር እውነት እንደሆነ አስባለሁ፡፡” አለ ግሬግ፡፡

“ትክክል ነህ፡፡ ቻርሊ ሁልጊዜ ‘በተመራማሪዎች ዙሪያ ስትሆን የተሻለ ተመራማሪ ትሆናለህ፡፡ በአሸናፊዎች ዙሪያ ስትሆን የተሻለ አሸናፊ ትሆናለህ፡፡ በሚያማርሩና ችክ ባሉ ሰዎች ዙሪያ ስትሆን የተሻለ አማራሪና ችክ ያልክ ትሆናለህ’ ይላል፡፡” ሲል ነገረው፡፡

ከመቶ ሚሊየን ኮፒ በላይ በተሸጠው ቲንክ ኤንድ ግሮው ሪች #አስበህ_ሀብታም_ሁን መጽሐፍ ላይ የተመሰረተ የናፖሊዮን ሂል ድንቅ ስራ። #የህይወት_መመሪያ በተሰኘው መጽሐፍ የምናውቃት ሀኒም_ኤልያስ ተርጉማዋለች፡፡

ለመሆኑ መቶ አመታትን ያስቆጠረው እና #አሁንም_ድረስ_የሚሰራው ይህ የስኬት ቀመር ምን ይሆን?

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡
*
ቤተሰብ ይሁኑ
https://tttttt.me/teklu_tilahun
አስደሳች ዜና ለስኮላር ሽፕ ዝግጅት ፈላጊዎች
+251921-309530

ለHigh School | Collage | University ተማሪዎች ታስቦ የተዘጋጀ

IELTS | TOFEl | SAT | GRE ማስተማር ጀምረናል።

ወደ #አሜሪካ#ካናዳ#እንግሊዝ#አውስትራልያ#አውሮፓ#ቻይና
ወቅቱ የስኮላርሽ ጊዜ ስለሆነ ተማሪዎች ይህንን አጋጣሚ ይጠቀሙ።

ወደ መደበኛ ትምህርታችሁ ከመመለሳችሁ በፊት ጊዚያችሁን ተጠቀሙበት

የክረምት ክላስ

ENGLISH. FRENCH. CHINESE. GERMAN. AFAN OROMO

አድራሻ

Mexico:+251919913021/23
Hayahullet:+251919913023/24

Admission Open Now

Get free PDFs, Audio and different references from our Channel
JOIN US
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
T.me/SCHOOLOFAMERICAN
👍1
በወቅታዊ ጉዳዮችና በ2015 የፌደራል መንግስት ረቂቅ በጀት ላይ የሚመክረው የምክር ቤቱ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተገኙበት እየተካሄደ ነው!

በወቅታዊ ጉዳዮች እና በ2015 የፌደራል መንግስት ረቂቅ በጀት ላይ የሚመክረው የምክር ቤቱ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በአሁኑ ወቅትም የምክር ቤቱ አባላት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ።ምክር ቤቱ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚወያይ ይጠበቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በወቅታዊ ጉዳዮችና በ2015 የፌደራል መንግስት ረቂቅ በጀት ላይ የሚመክረው የምክር ቤቱ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተገኙበት እየተካሄደ ነው! በወቅታዊ ጉዳዮች እና በ2015 የፌደራል መንግስት ረቂቅ በጀት ላይ የሚመክረው የምክር ቤቱ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተገኙበት እየተካሄደ ነው። በአሁኑ ወቅትም የምክር ቤቱ አባላት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ።ምክር ቤቱ ማኅበራዊ፣…
በምክር ቤቱ ስበሰባ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል

6ኛዉ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ አመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በተገኙበት ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያየ ይገኛል።

ከምክር ቤቱ አባላትም ለ ጠ/ሚኒስትሩ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። ከቀረቡት ጥያቄዎች ዉስጥም

- የጸጥታ ችግር ከመፈጠሩ በፊት አስቀድሞ መከላከል አይገባም ነበር ወይ? የንጹሀንስ ሞት መቼ ያቆማል? በቀጣይስ እንዳይከሰት መንግስት ምንድነዉ እቅዱ? የሚሉት ይነሳሉ።

- በቀጣይ አመት በኦንላይን ይሰጣል ለተባለዉ ሀገር አቀፍ ፈተና ይገባሉ የተባሉ 1 ሚሊዮን ታብሌት ኮምፒውተሮች ሂደት ተስተጓጉሏል ፤ ለ 2015 ፈተና ለዚህስ መንግስት ምን እያከናወነ ነዉ?

- ከትግራይ ክልል ህዝቡ ለሚያሰማዉ ሰቆቃ መንግስት ምን እገዛ እያደረገላቸዉ ነዉ?

ጠ/ሚኒስትሩ በእነዚህ እና ሌሎች በሚቀርቡላቸዉ ጥያቄዎች ላይ ምላሽና ማብራርያን የሚሰጡ ይሆናል።

✍️ዳጉ ጆርናል
@YeneTube @FikerAssefa
ስፖርት!

ኢትዮጵያ ቡና እና ካሳዬ አራጌ ዛሬ በይፋ ተለያይተዋል።

Via Ethio Kickoff
@YeneTube @FikerAssefa
“መንግስት አሸባሪ አይደለም፤ አሸባሪን የሚፋለም ኃይል ነው!!”፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እየሰጡ በሚገኘው ምላሽ “መንግስት አሸባሪ አይደለም፤ አሸባሪን የሚፋለም ኃይል ነው!!” ብለዋል።

የአሜሪካን ልምድ እንደ ምሳሌ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት ስድስት ወራት ከ1 ሺህ በላይ አሜሪካውያን በሽብር ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ "አልቃይዳ ትይዩ ህንፃዎችን በአሜሪካ ሲያፈነዳ ሚስቱ ልጁ ወንድሙ የሞተበት አሜሪካዊ ከመንግስት ጎን ሆኜ አሸባሪን እንፋረዳለን ይላል፤ እኛ ጋር ደግሞ ይሄ መንግስት ይላል። ይሄ ትክክል አይደለም። መንግስት አሸባሪ አይደለም፤ አሸባሪን የሚፋለም ሃይል ነው።" ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የመንግስት መዋቅር ዉስጥ ያለዉን ችግር አሁንም ማስተካከሉ ይቀጥላል -ጠ/ሚ አብይ አህመድ

በተከታታይ በዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በተመለከተ በመንግስት መዋቅር ዉስጥ ያለ ሀይል ጥቃቶቹ እንዲፈጸሙ እያመቻቸ እና አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን በብዙዎች ይነሳል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በምክርቤቱ ስብሰባ ወቅት ጠ/ሚ አብይ ለምክርቤቱ አባላት የመንግስት መዋቅርን የማጽዳቱ ስራ አሁንም ይቀጥላል ብለዋል። ከዚህ ቀደም መንግስት በሰራዉ ስራ እስከ አምስት ሺህ የሚጠጉ አመራሮች ከእስር እስከ አመራር እርከን ዝቅ መደረግ ድረስ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን አስታዉሰዋል።

"መዋቅር ዉስጥ ችግር አለ ፤ የሽብር ቡድኖቹ በመዋቅር ዉስጥ ሰዉ ይገዛሉ ፤ አብረዉ ያቅዳሉ አብረዉ ያደራጃሉ ፤ እነዚህን የማጥራት ስራ ከዚህ ቀደም ሲሰራ ቆይቷል አሁንም ይቀጥላል ማለታቸዉን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚደርሱ ጥቃቶች ላይ የመንግስት መዋቅር ዉስጥ ያሉ አመራሮች ተሳትፎ እንዳለሰቸዉ ይሰማል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ከነሀሴ ጀምሮ የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ!

ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ከነሀሴ ጀምሮ የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።የድርጅቱ የውጭ ጉዳዮች እና ቁጥጥር ሀላፊ ማቲው ሀሪሰን እንዳሉት ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከአንድ ወር በኃላ የቴሌኮም አገልግሎት ለደንበኞች መስጠት ይጀምራል።

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስተር ቦሪስ ጆንሰን ከካቢኔ ሚኒስትሮቻቸውና ከምክር ቤት አባላት ድጋፍ ሳያገኙ በመቅረታቸው ከወግ አጥባቂው ፓርቲያቸው መሪነት ሊለቁ ነው።

በዚህም ለፓርቲው መሪነት የሚደረገው ፉክክር በቅርቡ የሚደረግ ሲሆን፣ በቀጣይ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ደግሞ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስተር ይሰየማል።

አስከዚያው ድረስ ግን ቦሪስ ጆንሰን በአገሪቱ የጠቅላይ ሚኒስትር መንበር ላይ ይቀጥላሉ።

ጆንሰን በአመራራቸው ላይ በርካታ ትችቶች ሲቀርብባቸው ቆይቶ በርካታ ባለሥልጣኖቻቸው በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ ነው ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት።

ከእነዚህም መካከል ቻንስለር ናዲም ዛሃዊን ጨምሮ ከፍተኛ ካቢኔ አባሎቻቸው “በክብር የሥልጣን መንበራቸውን እንዲለቁ” ለጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጥያቄ አቅርበው ነበር።


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት ሪሺ ሱናክን ጨምሮ በርካታ ሚኒስትሮቻቸው አመራራቸውን በመቃወም በ48 ሰዓታት ውስጥ በፈቃዳቸው ሥልጣን ከለቀቁ በኋላ ነው።

በተመሳሳይ ቦሪስ ጆንሰን ሥልጣን እንዲለቁ የቀረበላቸውን ጥያቄ እስከ ሐሙስ ረፋድ ድረስ ሳይቀበሉት ቆይተው፣ የፓርላማ አባሎቻቸውን ድጋፍ ማግኘት ሳይችሉ በመቅረታቸው በመጨረሻ ወስነዋል።

ሚኒስትሮቻቸው በፈቃዳቸው ሥልጣን በመልቀቃቸውና የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ከፓርላማ አባላት ማግኘት ያልቻሉት ቦሪስ ጆንሰን ከፓርቲው መሪነት ስለመልቀቃቸው መግለጫ እሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዚህም ከወራት በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ያስረክባሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በፓርቲያቸው ውስጥ የተደረገውን ውድድር በማሸነፍ በ2019 ነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት። ከአምስት ዓመት በኋላ በከፍተኛ የድምጽ ብልጫም ምርጫ አሸንፈዋል።

ምርጫውን ሲያሸንፉ የብሬግዚት (ዩናይትድ ኪንግደም ከአውሮፓ ኅብረት የመውጣት) ሂደትን እቋጫለሁ ብለው ቃል ገብተው አሳክተዋል።

ቢሆንም ግን መንግሥታቸው ባለፉት ወራት በብዙ አወዛጋቢ ጉዳዮች ውስጥ ቆይቷል። በኮሮናቫይረስ የእንቅስቃሴ ገደብ ወቅት በጽህፈት ቤታቸው ውስጥ በርካታ ሰዎች የታደሙበት ድግስ ማካሄዳቸው እና በፖሊስ መመርመሩም በቀላሉ የሚታይ አይደለም።

በበዚህ ሳምንት ደግሞ የቀድሞው ምክትል የፓርቲያቸው ተጠሪ ክሪስ ፒንቸር ላይ የቀረበውን ተገቢያ ያልሆነ ፆታዊ ድርጊትን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያያዙበት መንገድ ነውጥ ቀስቅሶባቸዋል።

Via :- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
በነዳጅ እና የተሽከርካሪ መለዋወጫ ጭማሪ ምክንያት የትራንስፖርት ታሪፍ ማስተካከያ እንደተደረገ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ከሰኔ 29/2014 ዓ.ም ጀምሮ የተደረገውን የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ መሰረት በማድረግ÷ የአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሸከርካሪዎች ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ አድርጓል፡፡

የተደረገው የታሪፍ ማስተካከያ ከዚህ በታች ቀርቧል፡-
- በደረጃ አንድ በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5360 ሲሆን አዲሱ ታሪፍ 0.5600 ብር በኪሎሜትር ሆኗል፡፡ ጭማሪ በኪሎ ሜትር 0.0240 ሳንቲም ነው፡፡

ደረጃ አንድ በጠጠር መንገድ በሰው በኪሎሜትር ነባር ታሪፍ 0.6150 ሲሆን አዲስ ታሪፍ 0.6464 ነው፡፡ ጭማሪ በሰው በኪሎሜትር 0.0314 ሳንቲም ይሆናል፡፡

- ደረጃ ሁለት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5120 ሲሆን አዲስ ታሪፍ 0.5420 ነው፡፡ ጭማሪ 0.0300 ሳንቲም፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የ2015 የፌዴራል መንግስት በጀት 786 ነጥብ 61 ቢሊየን ብር ሆኖ ፀደቀ

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባው የ2015 የፌዴራል መንግስትን በጀት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።የምክር ቤቱ አባላት በበጀቱ ላይ ያላቸወን ጥያቄዎች ያቀረቡ ሲሆን፤ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የፕላን ፋይናንስና በጀት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመቀጠል ምክር ቤቱ በፕላን ፋይናንስና በጀት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አማካኝነት በበጀቱ ዙሪያ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ ከመረመረ በኋላ በአራት ድምጸ ተዐቅቦ በአብላጫ ድምጽ የውሳኔ ቁጥር 1275 /2014 አድርጎ አጽድቆታል። የ2015 በጀት አመት የፌዴራል መንግስት በጀትም 786 ነጥብ 61 ቢሊዮን ብር መሆኑ ታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከስልጣናቸው ለመልቀቅ መወሰናቸውን አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሰልጣናቸው ለመልቀቅ የወሰኑት ባለፉት ሁለት ቀናት ከ50 በላይ የሚሆኑ ሚኒስትሮች ስልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ለፓርቲው መሪነት ውድድር ተካሂዶ እስከሚተኩ ድረስ አገሪቱን ለተወሰኑ ወራት በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመምራት እቅድ እንዳላቸው መግለጻቸውን ቢቢሲ አስበብቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
Photo
አሐዱ ባንክ ሐምሌ 9 ቀን 2014 ወደ ሥራ እንደሚገባ አስታወቀ!

ታኅሳስ 30 ቀን 2012 አንድ ብሎ ጀምሮ፣ 10 ሺሕ የሚደርሱ ባለአክስዮኖችን ያሰባሰበውና በ564 ሚሊዮን የተከፈለ ካፒታል የተመሠረተው አሐዱ ባንክ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ሐምሌ 9 ቀን 2014 ወደ ሥራ እንደሚገባ አስታወቀ።ባንኩ ዛሬ ሰኔ 30 ቀን 2014 በማርዮት ሆቴል በሰጠው መግለጫ፤ በኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎት ተደራሽነት ውስንነት እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ክፍተት መኖሩን አውስቷል። ከዚህ አንፃርም የተሻለ የባንክ አደረጃጀት ይዞ ወደ ገበያ የሚገባ መሆኑን አስታውቋል።

በባንኮች ካለው አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ውስጥ፤ 50 በመቶ እንዲሁም ለተበዳሪዎች ከተሰራጨ የብድር ክምችት 3/4ኛ የሚሆነው በአዲስ አበባ እና አካባቢው ካለ አስቀማጭና ደንበኛ የሚገኝ እንደሆነ ባንኩ በመግለጫው አንስቷል። አሐዱ ባንክ ይህንን ክፍተት ለመሙላትና በገጠር ላለው ማኅበረሰብም አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ የሚሠራ እንደሆነ ተገልጿል።

ባንኩ በተጨማሪም የብድር አቅርቦት፣ የወኪል ባንክ አገልግሎት፣ የገጠር ባንክ አገልግሎት ለአርሶ እና አርብቶ አደሩ ከማድረስ ጎን ለጎን ወረቀት አልባ አሠራርን ከማጠናከር አንፃር አዲስና የተሻሉ አካሄዶችን እንደሚያስተዋውቅ በመግለጫው ተጠቅሷል።

አንድ ቅርንጫፍ ለአንድ ልጅ የሚል መርህም እንዳለው በመግለጫው ተነስቷል። የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አንተነህ ሰብስቤ ይህን በሚመለከት ሲያስረዱ፤ ባንኩ ከተለያዩ የሕፃናት ማሳደጊያ ድርጅቶች ጋር እንደሚሠራ ጠቅሰዋል። በዚህም መሠረት አንድ ቅርንጫፍ በተከፈተ ቁጥር ለአንድ ወላጅ አልባ ልጅ ኹሉንም ወጪ በመሸፈን እንደሚያሳድግ ተናግረዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ፤ ባንኩ ወደሥራ ከሚገባበት ዕለት ዋዜማ ባሉት ቀናት የተለያዩ መሰናዶዎች እንዳሉት አዲስ ማለዳ ሰምታለች። ከዚህም መካከል የደም ልገሳ አንደኛ ሲሆን፤ ለተስፋ የካንሰር ሕሙማን መርጃ፣ ለጌርጌሴኖን የአእምሮ ሕሙማን መርጃ እንዲሁም ለስለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት የተለያዩ ስጦታና ድጋፎችን እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ለቅዱስ ላሊበላ ገዳም እድሳት ሥራም ድጋፍ እንደሚደረግ ተጠቅሷል።ባንኩ የንግድ ምልክት ወይም ብራንዱን በአዲስ መልክ ያሠራ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለትም ምልክቱን ይፋ አድርጓል።አሐዱ ባንክ ከምርቃቱ ዕለት ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ድረስ በተከታታይ ቅርጫፎቹን 50 ለማድረስ ማቀዱም ተነግሯል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
በጀሞ አንበሳ ገራዥ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ውስጥ የአንድ ሰው ህይወት አልፎ ተገኘ!

በአዲስ አበባ ዛሬ በሚገባደደዉ ሰኔ ወር ዉስጥ ብቻ አምስት ሰዎች ወንዝ ውስጥ በመግባት ህይወታቸዉ ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው ጀሞ አንበሳ ጋራዥ አካባቢ እሮብ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ገደማ አንድ የ35 ዓመት ወጣት ወንዝ ዉስጥ ህይወቱ አልፎ መገኘቱን እና አስክሬኑ መዉጣቱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ነጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

በሰኔ ወር ወንዝ ዉስጥ ገብተዉ ህይወታቸዉን ካጡ ሰዎች መካከል ሁለት ታዳጊዎች ኳስ ለማውጣት በሚል ወንዝ ውስጥ የገቡ እና አንድ ታዳጊ ለመዋኘት በሚል ነበር፡፡በተጨማሪም በተያዘዉ ሳምንት ሁለት ሰዎች ወንዝ ዉስጥ ገብተዉ ህይወታቸዉ ያለፈ ሲሆን የአሟሟታቸዉ ሁኔታ ተመሳሳይ በመሆኑ በፖሊስ ምርመራ ላይ እንደሚገኝ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል፡፡የተያዘው የክረምት ወቅት እየጣለ ያለዉ ዝናቡ ከፍተኛ በመሆኑ ከጎርፍ ጋር ተያይዞ የሚደርሰዉ የሞት መጠን እየጨመረ እንደሚገኝ በማንሳት ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡

[ዳጉ ጆርናል/ብስራት ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ብራቮ፣ በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን የተሰራ የግል ፋይናንስ አስተዳዳሪ መተግበሪያ

በጀቶን በብቃት ለማውጣት ፣ የገንዘብ ልውውጦን በቀላሉ ለመከታተል ፣ የፋይናንስ እውቀቶንም ለመጨመር አሁኑኑ መተግበሪያውን አውርደው ይጠቀሙ።

ወቅታዊ መረጃዎችንም ቻናላችን በመቀላቀል በቀለላሉ ያገኙ
https://tttttt.me/birravo