YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ከማን_ጋር_ነህ?
#የስኬት_ቀመር መጽሐፍ 4ተኛው ዕትም በገበያ ላይ

'ሁልጊዜ ከሁለት ነገሮች በስተቀር በአምስት አመት ውስጥም ልክ እንደዛሬው ነህ’ ይላል፡፡” አለና በክላንድ ለረጅም ጊዜ እንግዳውን አፍጥጦ ተመለከተ፡፡

ፀጥታውን ለመስበር ይህ አዲሱ አስተዋይ ተማሪ “የትኞቹ ሁለት ነገሮች?” ሲል ጠየቀ፡፡

በክላንድ በፈገግታ ጠረጴዛው ላይ ወዳለው መጽሀፍ እየጠቆመ “ሁለቱ ነገሮችማ የምታገኛቸው ሰዎችና የምታነባቸው መጻህፍት ናቸው፡፡ አስበው እኛ ያለን እውቀትና አብረናቸው የምንሆናቸው ሰዎች ድምር ውጤት ነን፡፡ ከጋዜጣ በስተቀር ምንም ነገር የማታነብ ከሆነ፣ የምታውቀው ያንን ብቻ ይሆናል፡፡ የምታነበው የታላላቅ ሰዎችን የህይወት ታሪክና መንፈስን የሚቀሰቅሱ መፃህፍትን ከሆነ የምታውቀው ያንን ብቻ ይሆናል፡፡” አለ፡፡

“እሺ ገባኝ፡፡ ‘የምናገኛቸው ሰዎች’ የሚለውም ነገር እውነት እንደሆነ አስባለሁ፡፡” አለ ግሬግ፡፡

“ትክክል ነህ፡፡ ቻርሊ ሁልጊዜ ‘በተመራማሪዎች ዙሪያ ስትሆን የተሻለ ተመራማሪ ትሆናለህ፡፡ በአሸናፊዎች ዙሪያ ስትሆን የተሻለ አሸናፊ ትሆናለህ፡፡ በሚያማርሩና ችክ ባሉ ሰዎች ዙሪያ ስትሆን የተሻለ አማራሪና ችክ ያልክ ትሆናለህ’ ይላል፡፡” ሲል ነገረው፡፡

ከመቶ ሚሊየን ኮፒ በላይ በተሸጠው ቲንክ ኤንድ ግሮው ሪች #አስበህ_ሀብታም_ሁን መጽሐፍ ላይ የተመሰረተ የናፖሊዮን ሂል ድንቅ ስራ። #የህይወት_መመሪያ በተሰኘው መጽሐፍ የምናውቃት ሀኒም_ኤልያስ ተርጉማዋለች፡፡

ለመሆኑ መቶ አመታትን ያስቆጠረው እና #አሁንም_ድረስ_የሚሰራው ይህ የስኬት ቀመር ምን ይሆን?

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡
*
ቤተሰብ ይሁኑ
https://tttttt.me/teklu_tilahun
አስደሳች ዜና ለስኮላር ሽፕ ዝግጅት ፈላጊዎች
+251921-309530

ለHigh School | Collage | University ተማሪዎች ታስቦ የተዘጋጀ

IELTS | TOFEl | SAT | GRE ማስተማር ጀምረናል።

ወደ #አሜሪካ#ካናዳ#እንግሊዝ#አውስትራልያ#አውሮፓ#ቻይና
ወቅቱ የስኮላርሽ ጊዜ ስለሆነ ተማሪዎች ይህንን አጋጣሚ ይጠቀሙ።

ወደ መደበኛ ትምህርታችሁ ከመመለሳችሁ በፊት ጊዚያችሁን ተጠቀሙበት

የክረምት ክላስ

ENGLISH. FRENCH. CHINESE. GERMAN. AFAN OROMO

አድራሻ

Mexico:+251919913021/23
Hayahullet:+251919913023/24

Admission Open Now

Get free PDFs, Audio and different references from our Channel
JOIN US
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
T.me/SCHOOLOFAMERICAN
'የፌደራል እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስታት በክልሉ እየደረሱ ያሉ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን በአቸኳይ ያስቁሙ'- ኢሰመጉ

በኦሮሚያ ክልል በሚንቀሳቀሰው የሸኔ ታጣቂ ቡድን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጥቃቶች እየደረሱ ይገኛሉ ብሏል ኢሰመጉ፡፡ በእነዚህም አሰቃቂ ጥቃቶች በርካታ ቁጥር ያላቸው ንጹሀን ሰዎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ ንብረት ውድመት እና ሌሎችም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈጸሙ ይገኛሉም ብሏል በመግለጫው፡፡

መንግስት መሰል ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ ቀድሞ የመከላከል እና የዜጎችን ደህንነት እና ሰብዓዊ መብቶች የማስከበር ተቀዳሚ ሀላፊነት ያለበት ቢሆንም ይህ ሳይሆን በመቅረቱ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በርካታ ቁጥር ያላቸው ንጹሀን ሰዎች ላይ አሰቃቂ ጥቃቶች እየደረሱ ይገኛሉ በማለትም በመግለጫው ተናግሯል፡፡ ሙሉ መግለጫዉ ከላይ ተያይዟል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገው ዕለት 3ኛ ዙር የ40/60 እና 14ተኛ ዙር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ስነ - ስርዓት ያካሄዳል!

የከተማ አስተዳደሩ በነገው ዕለት 3ኛ ዙር የ40/60 እና 14ተኛ ዙር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ስነ - ስርዓት እንደሚያካሂድ ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገው ዕለት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ የጋራ መኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ለመሆን ተመዝግበው ለሚጠባበቁ የህብረተሰብ ከፍሎች 3ኛ ዙር የ40/60 እና 14ተኛ ዙር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ስነ - ስርዓት እንደሚያካሂድ አስታውቋል፡፡

የዕጣ አወጣጥ ስነ- ስርዓቱም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤና የሚመለከታቸው የከተማው ከፍተኛ አመራሮችና ታዛቢዎች በተገኙበት እንደያሚካሄድም ከወጣው መርሀግብር ለመረዳት ተችሏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የተወካዮች ምክር ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ በልዩ ስብሰባ እየመከረ ነው::

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “በወቅታዊ የሀገሪቱ የጸጥታ ጉዳይ እና በንጹሃን ዜጎች ጭፍጨፋ” ላይ ለመወያየት ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 29፤ 2014 ልዩ ስብሰባ እያካሄደ ነው። ፓርላማው በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በኋላ “የውሳኔ ሃሳብ” ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ አንድ የፓርላማ አባል ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።የተወካዮች ምክር ቤት ቀደም ሲል ለዛሬ ይዞት የነበረው መርሃ ግብር በፓርላማ አባላት አማካኝነት የችግኝ ተከላ ማካሄድ ነበር። ነገር ግን ከአማራ ክልል የተወከሉ የምክር ቤት አባላት ኮሚቴ አዋቅረው ባቀረቡት ጥያቄ የዛሬው ልዩ ስብሰባ መጠራቱን የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የፓርላማ ምንጭ ተናግረዋል።

በኮሚቴው ውስጥ ከአማራ ክልል የተወከሉ የገዢው ብልጽግና ፓርቲ እንዲሁም የተቃዋሚው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካዮች መካተታቸውን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉት የፓርላማ አባል አስረድተዋል። በኮሚቴው ጥያቄ በተጠራው በዛሬው ስብሰባ የተወካዮች ምክር ቤት “ጭፍጨፋውን ያወግዛል ተብሎ እንደሚጠበቅ” እኚሁ የፓርላማ አባል ገልጸዋል።

ከትላንት በስቲያ ሰኞ ሰኔ 27 በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ዞን ውስጥ የሚገኙ ዜጎች “ጭፍጨፋ” እንደተፈጸመባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስታውቀው ነበር። በቄለም ወለጋ ዞን በሀዋ ገላን ወረዳ መንደር 20 እና 21 በተባሉ አካባቢዎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንም አረጋግጧል።

የተወካዮች ምክር ቤቱ ድርጊቱን ከማውገዝ ባለፈ “ጉዳዩን ገምግሞ ሪፖርት የሚያቀርብ ቡድን” ሊያወቅር እንደሚችልም የፓርላማ አባሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። ምክር ቤቱ ሊያሳልፈው በሚችለው የውሳኔ ሀሳብ መሰረትም “ብሔራዊ የሀዘን ቀን ሊታወጅ” የሚችልበት ዕድል እንዳለም ጠቁመዋል።በዚህ ጉዳይ ላይ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም። የዛሬውን የፓርላማ ልዩ ስብሰባን የመዘገብ ፍቃድ የተሰጠው ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ብቻ በመሆኑም ሂደቱን በተወካዮች ምክር ቤት አዳራሽ ተገኘቶ ለመከታተልም አልተቻለም።

የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢን ጨምሮ ዛሬ በፓርላማ ሊካሄድ የነበረን ሌላ ስብሰባ ለመዘገብ በስፍራው የተገኙ የግል መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች “መግባት አትችሉም” ተብለው ተመልሰዋል።የግል መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በፓርላማው የተገኙት፤ በተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የሚገመግምበትን ስብሰባ ለመዘገብ ነበር።

ይህ የቋሚ ኮሚቴ ስብሰባ በልዩ ውይይቱ ምክንያት መሰረዙን የፓርላ ምንጮች አስረድተዋል።የተወካዮች ምክር ቤት ትላንት ማክሰኞ ሰኔ 28፤ 2014 ሊካሄደው የነበረው 16ኛ መደበኛ ስብሰባ እንዲሁ ሳይካሄድ ቀርቷል። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው የፓርላማ አባላት፤ የትላንቱ መደበኛ ስብሰባ የተሰረዘበት ምክንያት አልተገለጽልንም ብለዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
በዜጎች ላይ የተፈፀሙ ጭፍጨፋዎችን የሚያጣራ ልዩ ኮሚቴ እንዲቋቋም ፓርላማው ወሰነ!

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች 6ኛው ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛው ልዩ ስብሰባ፤ በወቅታዊ የፀጥታ እና በንጹሐን ዜጎች ጉዳይ ላይ ተወያይቶ የውሳኔ ሐሳብ አሳልፏል፡፡

የዕለቱን መርሐ-ግብር በግፍ ለተጨፈጨፉት ዜጎች የአንድ ደቂቃ የኅሊና ጸሎት በማድረግ የጀመረው ምክር ቤት፤ የሚከተሉትን የውሳኔ ሐሳቦች ማሳለፉን አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ በዘንድሮው በጀት ዓመት 3 ነጥብ 95 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱንና ጠቅላላ የሀብት መጠኑን 114 ቢሊዮን ብር ማድረሱን አስታወቀ።

የባንኩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጋዲሳ ማሞ ዛሬ የባንኩን ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት፣ ባንኩ ኦዲት ከመደረጉና ከግብር፣ ከንብረት እርጅናና መጠባበቂያ በፊት ያገኘው ትርፍ 3 ነጥብ 95 በሊዮን ብር መሆኑን አስተውቀዋል።የዘንድሮ በጀት አመተ ትርፍ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 65 በመቶ እድገት አሳይቷል።

ባንኩ ዘጠኝ ሚሊዮን የቁጠባ ሂሳብ ያላቸው ደንበኞች በማፍራት 96 ነጥብ 77 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ብር መሰብሰብ መቻሉን አቶ ጋዲሳ አስታውቀዋል።የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመቅረፍ በተለይ ከዳያስፖራው ጋራ በተሰራው ሥራ ባንኩ ያገኘው የውጭ ምንዛሪ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ27 በመቶ እድገት ማሳየቱን ገልጸዋል።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
በዛሬው ልዩ ስብሰባ ብሔራዊ የሀዘን ቀንድ እንዲታወጅ ጥያቄ ቢቀርብም፤ ምክር ቤቱ ለጊዜው ይህን አካሄድ ሳይከተል ቀርቷል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ “መጀመሪያ በህገ መንግስቱ መሰረት ሂደቱን ጠብቆ መታወጅ ካለበት ህጉን እንመልከት እና ምንም ችግር የለውም። እዚሁ አምጥተን ጸድቆ ይታወጃል” ማለታቸውን በዛሬው ስብሰባ ላይ የተሳተፉ አንድ የፓርላማ አባል ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ፓርላማው ዛሬ ያቋቋመውን የልዩ ኮሚቴ አባላት ማንነት በተመለከተ ከ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ጥያቄ የቀረበላቸው በዛሬው ልዩ ስብሰባ ላይ የተሳተፉ አንድ የፓርላማ አባል፤ “ልዩ ኮሚቴው እንዲቋቋም ውሳኔ ከመተላለፉ በስተቀር ምንም የተነገረ ነገር የለም፤ ገና ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ኮሚቴው የሚቋቋምበትን ሂደት በተመለከተ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ “በቋሚ ኮሚቴም በአስተባባሪ ኮሚቴም ተመልክተን፤ ሁሉንም በሚያካትት መልኩ ብዝሃነትን ጠብቀን እናቋቁማለን። ከዛ እናቀርብላችኋለን” ማለታቸውን እኚሁ የፓርላማ አባል ገልጸዋል።

በዛሬው ልዩ ስብሰባ ላይ 17 የሚሆኑ የምክር ቤት አባል አስተያየት መስጠታቸውን የፓርላማ አባሉ ገልጸዋል። በልዩ ስብሰባው ላይ “መንግስት ኃላፊነቱን እየተወጣ አይደለም፤ መንግስት ኃላፊነቱን ይወጣ” እንዲሁም “የመንግስት ሹማምንት እጃቸው አለበት እና መንግስት ራሱን ያጥራ” የሚሉ ሀሳቦች ተደጋግመው መነሳታቸውን የምክር ቤት አባሉ አስረድተዋል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
በቄለም ወለጋ የጅምላ ግድያው ከመፈፀሙ አስቀድሞ ለስብሰባ ትፈለጋለችሁ በሚል ተጠርተን ነበር ሲሉ የዓይን እማኞች ተናገሩ፡፡

አሻም ያነጋገረቻቸው ከጅምላ ግድያው ያመለጡ የኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ፣ ለምለም ቀበሌ፣ መንደር 20 እና 21 ነዋሪዎች ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ”ጭፍጨፋው ከመፈፀሙ አስቀድሞ ለስብሰባ ትፈለጋላችሁ” በሚል በማስገደድ ጭምር ከየቤታቸው እንደተወሰዱ ተናግረዋል፡፡

የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ባነጣጠረው የጅምላ ግድያ 72 ሰዎች ሰርዓተ-ቀብራቸው መፈፀሙን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ደግሞ በመቶዎች የሚቆጠሩት የቀብር ስነ ሰርዓታቸው ሲፈፀም ጭምር መመልከታቸውን ለአሻም ነግረዋታል፡፡ ”አሁንም ድረስ የት እንዳሉ፣ ይሞቱ/ይኑሩ የማይታወቁ የአማራ ብሔር ተወላጆች እንዳሉም” ነዋሪዎቹ ገልፀዋል፡፡

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
ከሐምሌ 1 - 10 ቀን ከፍተኛ ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል በተዳፋት አካባቢዎች ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ኢንስቲትዩቱ አሳሰበ!

በሐምሌ ወር የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት ከፍተኛ ጎርፍ ስለሚኖር በተዳፋትና ገደላማ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ፡፡ኢንስቲትዩቱ ከሐምሌ 1 እስከ 10 ቀን 2014 ዓ.ም የሚኖረውን የአየር ፀባይ ሁኔታ ትንበያ በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል፡፡በመግለጫውም በሐምሌ ወር የመጀመሪያዎች አስር ቀናት በሀገሪቱ መደበኛ እና በአንዳንድ አካባቢዎች ነጎድጓዳማ እና በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ይጠበቃል ብሏል።

በትንበያው መሰረት በሚቀጥሉት አስር ቀናት የሚኖረው የዝናብ ሁኔታ ከባድ እና ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል መሆኑን ገልጿል።በዚህም በምዕራባዊ የሀገሪቱ አካባቢዎች አጋማሽ እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከ100 እስከ 200 ሚሊ ሜትር፤ በተወሰኑ ቦታዎች ከ200 ሚሊ ሜትር በላይ ዝናብ እንደሚጠበቅ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡በሐምሌ ወር በመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በትግራይ እና በደቡብ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ይጠበቃል ብሏል።

በአብዛኛው የአባይ፣ ባሮ-አኮቦ፣ ተከዜ፣ አዋሽ፣ ስምጥ ሸለቆ፣ ኦሞጊቤ፣ አፋር-ዳናከል፣ የላይኛውና መካከለኛው ዋቢ-ሸበሌ እንዲሁም ገናሌ-ዳዋ ተፋሰሶች ከፍተኛ እርጥበት ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።በታችኛው ገናሌ-ዳዋ፣ ስምጥ ሸለቆ እና ኦሞ-ጊቤ ተፋሰሶችም መጠነኛ እርጥበት ይኖራቸዋል ተብሏል።

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ፖሊስ ኮሚነሩ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እስከአሁን ከእስር ለምን እንዳልተፈታ እንዲያስረዱ ትዕዛዝ ተሰጠ!

የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 1ኛ የፀረ ሽብር ጉዳዮች ችሎት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽነር ሀሰን አርጋው በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጉዳይ ላይ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲፈጽሙ፤ ወይም ያልፈፀሙበት ምክንያት ካለ ቀርበው እንዲያስረዱ ትዕዛዝ ሰጠ።

ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ100 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ሰኔ 27 ቀን 2014 ትዕዛዝ መስጠቱ የሚታወስ ነው።

ሆኖም ትዕዛዙን እንዲፈጽም በፍርድ ቤት የታዘዘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሃላፊዎች የሉም በማለት ጋዜጠኛ ተመስገንን በሕገወጥ መንገድ አስሮ እንደሚገኝ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ገልጿል።

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ፤ የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለመፈጸሙን አስመልክቶ፤ በትናንትናው ቀን ያቀረቡትን አቤቱታ ችሎቱ በዛሬው ዕለት ሰኔ 29 ቀን 2014 መርምሮ ትዕዛዝ ሰጥቶበታል።

አቤቱታውን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የፀረ ሽብር ጉዳዮች ችሎት፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽነር ሀሰን አርጋው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲፈጽሙ፤ ወይም ያልፈፀሙበት ምክንያት ካለ ቀርበው እንዲያስረዱ፤ ለነገ ሰኔ 30 ቀን 2014 ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ቀጠሮ ተሰጥቷል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠየቀ።

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ ጉዳይ እና በድርጅቱ ቀጣይ የትግል አቅጣጫ መግለጫ ሰጥቷል።በምእራብ እና ምስራቅ ወለጋ በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ተደጋጋሚ አሰቃቂ ጥቃት ተፈፅማል ብሏል ንቅናቄው።ይህ ጥቃት በአማራ ሕዝብ ላይ ሲፈፀም አዲስ አይደለም ይልቁንስ የተሳሳተው ትርክት አንዱ ቅርንጫፍ መኾኑንም አብን አስታውቋል።አማራ ጠል ትርክት ከውጭም ከውስጥም ጠላት አፍርቶልናል እናም በዚህ ደግሞ እየተጎዳ ያለው ምስኪን ራሱን መከላከል የማይችል ሕዝብ ነው፤ የአሁኑን ጨምሮ ተከታታይ ችግሮችን ለማስቆም የሚመለከታቸው ሁሉ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ የንቅናቄው ሊቀመንበር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) አሳስበዋል።

በአማራ ሕዝብ ላይ እየተደረገ ያለውን ዘር የማጥፋት ጥቃት የሚመለከታቸው ሁሉ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ ዶክተር በለጠ አሳስበዋል።ንቅናቄው በአማራ ሕዝብ ላይ አየተፈፀመ ያለው ስልታዊ ዘር ማጥፋት ነው ብሎ አብን ያምናል ብለዋል ዶክተር በለጠ በመግለጫቸው።የአማራ ሕዝብ ተከታታይ ግድያ ግድ ሊለው የሚገባው የመንግስት መዋቅር ችላ ማለቱን እንዲያቆም እና ባስቸኳይ ሕዝብን እንዲጠብቅ ሲል አብን አሳስቧል።

ጥቃቱን እየተከታተለ እርምጃ ያልወሰደው መንግስት ይህንን ጥቃት እየሸፈኑ ያሉ እንዲሁም ሕዝብን መጠበቅ ያለባቸው ከክልል እስከ ፌደራል ቢሮዎች ተጠያቂ ናቸው ሲልም አብን አስታውቋል።ጥቃቱን ለማስቆም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅና የአካባቢው ነዋሪዎች በፀጥታ አካልነት ተካትተው ራሳቸውን እንዲጠብቁ የሚያስችል ሥራ እንዲሰራ አብን ጠይቋል።አጥቂዎች በግልፅ ፍርድ እንዲበየንባቸው፤ ይህን ችላ ያሉ፣ እንዲባባሱ ያደረጉ ሚዲያዎች፣ ፓለቲከኞች እና ግለሰቦችን መንግስት ተጠያቂ እንዲያደርግ አብን ጠይቋል።

ብሄራዊ የሀዘን ቀን እንዲታወጅም አብን ጠይቋል።አማራ የመጣበትን ችግር ለመመከት እንደ ሕዝብ በአንድነት ለመመከት አንድነቱን ጠብቆ የመጣውን የዘር ማጥፋት ጥቃት ለመመከት እንዲሠራ አብን ጥሪ አቅርቧል።በቀጣይ ሀሙስ የሀዘን ቀንን ለማሰብ የሻማ ማብራት፣ የፓናል ውይይት እና ሌሎች ዝግጅትን ለማከናወን ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አብን ገልጿል።

[AMC]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገው ዕለት 3ኛ ዙር የ40/60 እና 14ተኛ ዙር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ስነ - ስርዓት ያካሄዳል! የከተማ አስተዳደሩ በነገው ዕለት 3ኛ ዙር የ40/60 እና 14ተኛ ዙር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ስነ - ስርዓት እንደሚያካሂድ ተገለፀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገው ዕለት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ የጋራ መኖሪያ…
በአዲስ አበባ ከተማ በ3ኛው ዙር የ40/60 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ 24 ሺህ 491 ቤቶች ነገ ዕጣ እንደሚወጣባቸው ተገለጸ።

በዕጣ አወጣጥ ሥነ ስርአት ዙሪያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫው በዕጣ አወጣጥ ሥነ ስርአቱ 79 ሺህ 794 ተመዝጋቢዎች በዕጣ አወጣጥ ውድድሩ ውስጥ እንደሚካተቱ ተናግረዋል።ከ1997 ዓ.ም የ20/80 ተመዝጋቢዎች መካከልም 60 ወራት ሳያቋርጡ የቆጠቡ ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።ነገ ጠዋት 2 ሰአት ላይ በሚካሄደው የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ፣ የሚመለከታቸው የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮችና ታዛቢዎች እንደሚገኙም ነው የተገለጸው።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
#ኦርቶጵያ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ከኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያን ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነጥሎ ማየት ይከብዳል፡፡ ቤተክስርቲያኒቱ ለኢትዮጵያ ህልውና ዋጋ ብትከፍልም ለውለታዋ ጥርስ እንዲነከስባት ሆናለች፡፡

ለመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክስርቲያን በምን ምክንያት ጥርስ ተነከሰባት? ውለታዋና በደሏስ ምንድነው?

እስልምና፣ ወንጌላውያን እና ካቶሊክ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጋር የነበራቸው ሙግት በአስደናቂ ሁኔታ በመጽሐፉ ውስጥ ተዳስሷል፡፡ በሙግቱ ማን ረትቶ ይሆን?

ላሊበላ ሶስት ቀናት ሞቶ የተገለጠለት አስገራሚ ሚስጥርም ተካትቶበታል፡፡ ብዙም ያልተነገረለት ላሊበላ ሞቶ የተገለጠለት ምስጢር ምን ይሆን?

ታቦተ ፂዮንን በአይናቸው ያዩት አጼ ኢያሱን ጨምሮ የጥቂት ሰዎች ምስክርነት በሚገርም ሁኔታ በመጽሐፉ ላይ ሰፍሯል፡፡ ታቦተ ፂዮንን በአይናቸው ያዩ ሰዎች ምን ተናረው ይሆን?

ኦርቶጵያ መጽሐፍ የሚነግረን ብዙ አስገራሚ ታሪኮች አሉ፡፡

ሁሉም ሰው ሊያነበው፣ ብሎም ቅርስ ሊያደርገው የሚገባ ለትውልድ የሚተላለፍ መጽሐፍ።

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

*
ቤተሰብ ይሁኑ https://www.facebook.com/booklandbook/

https://tttttt.me/teklu_tilahun
Forwarded from YeneTube
🔵 0991203033 🔵 Fabulous mart
💥የወንዶች እና የሴቶች ፀጉር ማሳደጊያ
📌የወንዶች ፀጉር እና ፂም ማሳደጊያ
👉Imported from 🇺🇸USA🇺🇸
💎የ 1 ወር ዋጋ 999ብር
💎የ 3 ወር ዋጋ 2800ብር
💎የ 6 ወር ዋጋ 4900ብር
📌 ለሴቶች የቆዳ ውበትና የፀጉር ቁመት የሚጨምር
🇺🇸 BIOTIN 🇺🇸 💎2499 ብር
📌Neo hair lotion 💎2950 ብር
📌DERMAROLLER
👉 የቆዳን ቀዳዳ በመክፈት የፀጉርን ሴል የሚያነቃቃ
👉ለተሸበሸበ ቆዳ ጥርት ያለ ገፅታን የሚሰጥ
price💎950 birr 🚛free delivery 🚛🚛
☎️+251991203033 & 0904132709
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEpoRsmLNv7NNj3K_g
Forwarded from YeneTube
መፍትሔ ስራይ ወአይነ ጥላ
መርጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድሀኒቶች ፍቱን ህክምናወችን እንሰጣለን።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረበትን
👉ሆዱን ለሚአመው
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ሁሉም ቦታ ላይ ላሉ ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለአቃቤ እርእስ ለጥላት መጠበቂያ
👉ለማንኛውም አይነት ቁስል
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ በሄደበት ሁሉ ሰው እንዲወደው
👉ለአይነ ጥላ
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉የሚአስቡት ሁሉ አልሳካ ላለ
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ለእራስ ህመም
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉ፍቅረኛ ላጣ
👉የሌባ ገትር ሌባ እማያስነካ
👉ለሚጥል በሽታ
👉ገንዘብ ለሚበተንበት
👉ስራ አልሳካለት ላለ
👉ለቡዳ
👉ለመስተፋቅር
👉ገበያ ለሚገረግረው ለገብያ
👉ለመፍትሄ ስራይ
👉ለስንፈተ ወሲብ ሲገናኝ ለሚቸኩልበት
👉ለአስም (ሳይነስ)
👉ለትዳር ለማይስማሙ ለመስተዋድድ

እንዲሁም የተለያዩ
መድኀኒቶችን እንቀምማለን

እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ ።

እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
መድሀኒቱን ባሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል

👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
0912718883

https://tttttt.me/meritibe

👉ቻናሉን በመቀላቀል ጥንታዊ የአባቶች ጥበብ እንደወረደ ያገኙታል በየስሀቱ የምንለቃቸውን ተደብቀው የቆዪ የብራና መጽሀፍ በሚፈልጉት አይነት ይለቀቃሉ የሚፈልጉትን ለማግኔት ይቀላቀሉ ሼር ሼር ሼር ያድርጉ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን በነገዉ እለት ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በም/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚያካሂድ አስታዉቋል፡፡

የስብሰባው አጀንዳዎችም፡-

1. በ2015 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ እና በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚሰጡትን ምላሽና ማብራሪያ ማዳመጥ እና የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ረቂቅ በጀቱን አስመልክቶ የሚያቀርበው ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ የበጀት አዋጁን ማጽደቅ፣

2. የምክር ቤቱን 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 15ኛ መደበኛ እና 6ኛ ልዩ ስብሰባ ቃለጉባኤዎችን መርምሮ ማጽደቅ፣

3. የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች እና የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት እንደገና ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ ለማሻሻል ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ማጽደቅ፣


4. የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች እና የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የአፍሪካ፣ የካሪቢያንና የፓስፊክ አገራት ድርጅት /አካፓድ/ የተቋቋመበት የተሻሻለውን የጆርታውን ስምምነት አስመልክቶ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ማጽደቅ፣

5. የምክር ቤቱ የ2014 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ሪፖርት ላይ እንደሚወያይ ተገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በዛሬው እለት በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1ሺሕ 24 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ 1ሺሕ 19 ወንዶች እና አምስት ህጻናት መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ቁጥራቸው 47,408 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa