YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ጴጦሮስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አድርጎ መረጠ!

ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት 2014 ርክበ ካህናት እያከናወነ የሚገኘው ጉባኤ የቀጠለ ሲሆን፤ ጉባኤው ዛሬ ባካሄደው ምርጫ የባሕርዳር እና አካባቢው አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ እንዲሁም የኒዮርክ እና አካባቢው አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በማድረግ መርጧል።

ጉባኤው በዛሬው ዕለት ግንቦት 24 ቀን 2014 በተካሄደው ምርጫ አርባ አምስት ሊቃነ ጳጳሳት የተገኙ ሲሆን፤ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅነት ከተወዳደሩት ውሰጥ ብፁዕ አቡነ አብርሃም 26 ድምጽ በማግኘት ሲመረጡ፤ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ 20 ድምጽ በማግኘት መመረጣቸውን ከኢኦአተቤ ቴቪ ( EOTC TV) ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
በዋግ ኽምራ አለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች አፋጣኝ እርዳታ ካላደረጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት ሊያልፍ እንደሚችል ተገለጸ!

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ስር የሚገኙ 4 ወረዳዎች በአሸባሪው የህወኃት ቡድን እጅ ስር በመሆኑ ነዋሪዎች ከፍተኛ ችግር ውስጥ ናቸው ሲሉ የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ ከፍያለው ደባሱ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡በአበርገሌ ወረዳ፣ባግብጂ ወረዳ፣ዝቋላ 6 ቀበሌ ፣ሰቋጣ ወረዳ 1 ቀበሌ አካባቢዎች አሸባሪው የህወኃት ቡድን በስፋት የሚንቀሳቀስበት በመሆኑ ተፈናቃዮች ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ማወቅ ባለመቻሉ በችግር ውስጥ በመሆናቸው አፋጣኝ እርምጃ እንደሚያሻቸው ተገልፆል፡፡

በየእለቱ የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን አሁን ላይ በዞኑ ከ88 ሺበላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡አለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች በተለያዩ ክልሎች ገብተው እርዳታ እንደሚያደርጉት ሁሉ በነዚህ አራት ወረዳች ገብተው አፋጣኝ እርዳታ ካላደረጉ በብዙ ሺ የሚቆጠር ህዝብ ልናጣ እንችላለብ ሲሉ አቶ ከፍያለው ደባሱ ተናግረዋል፡፡

በዞኑ የመጠለያ ጣቢያ ችግር ከፍተኛ እንደሆነ እና በዚህም የተነሳ ተፈናቃዮች በየበረንዳው ፣ ከዘመድ ተጠግተው እየኖሩ ሲሆን በዛሬው እለት ብቻ 20 መጠለያ ከተለያዩ እርዳታ ድርጅቶች መለገሱን ገልጸዋል፡፡ሆኖም መጪው የክረምት ወቅት በመሆኑ የተፈናቃዮች ቁጥር በየእለቱ እየጨመረ በመምጣቱ ደረጃውን የጠበቀ መጠለያ ስፍራ ሊዘጋጅ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በዞኑ አሁንም ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የተለያዩ ድጋፎች ቢደረግም የተፈናቃች ቁጥር በመጨመሩ እና የእለት ፍጆታ እንደመሆኑ በቂ አይደለም ድጋፍ ሊጨምር ይገባል ሲሉ አቶ ከፍያለው ደባሱ ጨምረዉ ተናግረዋል፡፡

[ዳጉ ጆርናል/ብስራት ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሐመርን ለአፍሪካ ቀንድ አገራት አዲሱ ልዩ መልዕክተኛዋ አድርጎ መሾሟን አስታውቃለች።

ይህንን ዛሬ በትዊተር ገጻቸው ይፋ ያደረጉት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ናቸው። ማይክ ሐመር ላለፉት ስድስት ወራት በቀጠናው የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩትን አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድን ይተካሉ።አሜሪካ ከዓመት በፊት ለአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ከሾመች ወዲህ አምባሳደር ማይክ ከአምባሳደር ፉልትማን እና ከአምባሳደር ሳተርፊልድ ቀጥለው ሦስተኛው ልዩ መልዕክተኛ ይሆናሉ። ተሰናባቹ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ በአሜሪካው ራይስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የቤከር ፐብሊክ ፖሊሲ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
10 ህገ ወጥ ናቸው የተባሉ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኀን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ!

የኢትዮጵያ ፌድራል ፖሊስ “በሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ መንግስትና ህዝብን ለመለያየት” ይሰራሉ ያላቸውን 111 የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኀን መለየቱን አስታወቀ።ከእነዚህ ውስጥም 10 ተጠርጣሪዎችን ሃይማኖትን ከሃይማኖት በማጋጨት የሀገርን ደህንነት ለማደፍረስ በመንቀሳቀሳቸው በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ ገልጿል።

በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 መሰረት ምንም ዓይነት የብሮድካስት ፍቃድ ሳይኖራቸው የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የሚያናጉ በብሄር እና በሀይማኖት ጉዳዮች ላይ ግጭት ቀስቃሽ መረጃ የሚያሰራጩ ናቸው ሲልም የፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

“በየትኛውም ሚዲያ ተጠቅመው መረጃን ለህዝብ ተደራሽ የሚያደርጉ ግለሰቦች የሀገሪቱን ህግና ሥርዓት አክብረው መንቀሳቀስ እና ህጋዊ መስመር በመከተል በተጠያቂነት መንፈስ መስራት ይኖርባቸዋል።” ሲልም ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። በተጨማሪም ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር የጀመረውን “ህግ የማስከበር” ዘመቻ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታዉቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከዛሬ ጀምሮ የሲሚንቶ ግብዓትና ምርት ስርጭትን በሚያስተጓጉሉ ህገ-ወጦች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ!

የሲሚንቶ ግብዓትና ምርት ስርጭትን በሚያስተጓጉሉ ህገ-ወጦች ላይ አስፈላጊን እርምጃ ከዛሬ ጀምሮ እንደሚወስድ የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ።የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዱና የመዓድንና ኢነርጂ ሚኒስትር ታከለ ኡማ የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዱ በመግለጫቸው፤ በክልሉ በሲሚንቶ ምርት ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር የሚያስችል እርምጃ ክልሉ ከዛሬ ጀምሮ እንደሚወስድ አስታውቀዋል።

በተለይም በአንዳንድ አካባቢዎች በሚገኙ ያልተገባ ክፍያ በመጠየቅ የግብዓትና ምርት ስርጭት ላይ እንቅፋት የሆኑ ኬላዎችን በማንሳት ግብዓቱ በቀጥታ ወደ ፋብሪካዎች የሚደርስበት አሰራር ተግባራዊ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

አክለውም ምርቱ ከፋብሪካዎች በ400 ብር እና በ500 ብር የሚወጣ ቢሆንም በርካታ ደላሎች በመሀል የምርቱን ዋጋ እስከ 1 ሺሕ ብር ከፍ እንዲል ማድረጋቸው በመግለጫው ተነስቷል።

በመሆኑም ክፍተቶችን በመፈተሽ ህጋዊ ማኅበራትን በማደራጀት የምርት ስርጭቱ በቀጥታ ወደ ተጠቃሚው የሚደርስበትን አሰራር ተዘርግቷል ብለዋል።

ከአምራች እንደስትሪዎች ጋር በተገናኘ የሚነሱ የፀጥታና የግብዓት ችግሮች ለመቅረፍ ክልሉ ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑና ችግሩንም ለመቅረፍ ቁርጠኛ መሆኑንም ተናግረዋል።

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሴት ፖለቲከኞች ጥምረት መንግሥት፣ ሕወሃት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሰላም አማራጮችን እንዲከተሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ጥሪ ማድረጋቸውን ተሰምቷል። ጥምረቱ ከየትኛውም ወገን የሚሰሙ የጦርነት ጉሰማዎችን አውግዞ፣ በሴቶች ላይ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፍትሄ እንዲሰጣቸው፣ በሕግ ማስከበር ዘመቻው የመብት ጥሰቶች እና ግልጽነት የጎደላቸው እስሮች እንዲቆሙ ጠይቋል። ጥምረቱ ሴቶች በአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ያላቸውን ዝቅተኛ ውክልና ለማስተካከል፣ ኮሚሽኑ በተዋረድ በሚያዋቅራቸው አዳዲስ አደረጃጀቶች ለሴቶች 70 በመቶ ውክልና እንዲሰጥ ለሚመለከታቸው አካላት ደብዳቤ ማስገባቱንም ገልጧል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለሥራ ጉብኝት ባሌ ሮቤ ገባ!

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለሥራ ጉብኝት ባሌ ሮቤ ገብቷል።በጉብኝቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ኡስማን ዲዮን እንዲሁም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ናቸው።

የልዑካን ቡድኑ በባሌ ዞን እየተከናወኑ ያሉ የግብርና ሥራዎችን ተዘዋውሮ ይመለከታል ተብሎ ይጠበቃል።

(EBC)
@YeneTube @FikerAssefa
ራሱን የሀይማኖት አባት ነኝ በማለት በአራት ህጻናት ላይ የተመሳሳይ ጾታ ጥቃት ያደረሰዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ!

በሶዶ ወረዳ በአማዉቴ ግፍትጌ ቀበሌ ጋቲራ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ገነት አሰፋ የተባለ ግለሰብ ራሱን የሀይማኖት አባት በማስመሰል በአራት ህጻናት ላይ የተመሳሳይ ጾታ ጥቃት ማድረሱን የሶዶ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የህዝብ እና ሚዲያ ግንኙነት ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ትግስት ወልዴ ተናግረዋል።

ግለሰቡ ራዕይ ታይቶኛል ፤ ሀይማኖታዊ መጽሀፍትንም ታነቡልኛላችሁ በማለት ህጻናቱን አብረዉት እንዲያድሩ ካደረገ በኋላ ልብስ አዉልቀዉ እንዲተኙ በማድረግ ጥቃቱን እንደፈጸመባቸዉ አብራርተዋል።

ህጻናቱ ከ 9 እስከ 20 አመት የሚገመቱ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ ትግስት ህዳር 14 / 2014 ዓ.ም ጥቃቱ የደረሰባቸዉ ህጻናት እና ወላጆች ክስ ማቅረባቸዉን ተናግረዋል።

ግለሰቡ ድርጊቱን አልፈጸምኩም በማለት ክዶ የተከራከረ እንደነበር እና የክስ ሂደቱ በነበረበት ወቅትም በዋስ ወጥቶ ጉዳዩን ሲከታተል መቆየቱንም ቡድን መሪዋ ገልጸዋል።

አቃቤ ህግም የህክምና እና ሌሎች መረጃዎችን በማሰባሰብ ግለሰቡ ድርጊቱን እንደፈጸመ ለሶዶ ወረዳ ፍርድ ቤት አረጋግጧል። ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ማስረጃ ላይ ተከሳሽ መከላከል ባለመቻሉ ጥፋተኛ ነዉ በማለት በ 13 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ወ/ሮ ትግስት ወልዴ ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
ኦባሳንጆ ስለመቀሌ ቆይታቸውና ስለ ሰሜን ኢትዮጵያ ምን አሉ?

ሁለቱ ወገኖች መቸ ስምምነት ያደርጋሉ ለሚለው ጊዜ ማስቀመጥ እንደማይቻል አንስተዋል

በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ከህወሃት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የቡድኑ ቃል አቀባይ መግለጻቸው ይታወሳል።

ቃል አቀባዩ፤ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ እና ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በ ``ቀጣናዊ ጉዳዮች” ላይ እንደተወያዩ ይግለጹ እንጅ ቀጠናዊ የተባሉት ጉዳዮች ምን እንደሆኑ በግልጽ አላስቀመጡም ነበር።

በአፍሪካ ቀንድ የሕብረቱ ከፍተኛ ተወካይ እንዲሁም የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ በመቀሌ ያረጉትን ጉዞ በተመለከተ ከቢቢሲ አፍሪካ የራዲዮ ፕሮግራም ጋር ቆይታ አድርገዋል።

ከፍተኛ ተወካዩ የአፍሪካ ሕብረት በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በተመለከተ ትኩረት ሰጥቶታል ወይ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ፤ ሕብረቱ እርሳቸው በቀጣናው ሰላምና መረጋጋትን እንዲያጎለብቱ መሾሙ ጉዳዩን በደንብ እንደያዘው እንደሚያመለክት ገልጸዋል።
በፌደራል መንግስቱ እና በህወሃት መካከል ሰላም እንዲፈጠር በዝግታም ነገር ግን ያልተቋረጠ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

አሁን ላይ ለሰብአዊነት ሲባል የተደረገው የተኩስ አቁም እንዳለ ያነሱት ኦባሳንጆ፤ አሁን ላይ ያለው ሁኔታ ከስድስት ወራት በፊት ከነበረው ሁናቴ የተሻለ እንደሆነም ገልጸዋል።
በሁለቱ ወገኖች መካከል መተማመን እንዲመጣና ወደ ንግግር እዲያመሩ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን ነው የአፍሪካ ቀንድ ተወካዩ ለቢቢሲ የተናገሩት።

አሁን እየተደረገ ያለው ጥረት ሁለቱ ወገኖች ወደ ተኩስ አቁም እንዲመጡ ማድረግ እንደሆነ ያነሱት ተወካዩ በትግራይ ክልል ቆይታቸው ዩኒቨርሲቲ መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ፤ በናይጀሪያ ከህወሃት ሰዎች ጋር እንደተገናኙ ተደርጎ በተገለጸው ጉዳይ ላይ መንግስት ምላሽ ሰጠ
የሕብረቱ የመጨረሻ ግብ መደበኛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ መሆኑን ያነሱት ኦባሳንጆ፤ መቼ የሰላም ስምምነት ሊፈራረሙ እንደሚችሉ ለቀረበላቸው ጥያቄ የጊዜ ገደብ ማስቀመጥ እንደሚያስቸግር ገልጸዋል። ነገር ግን መግባባት እንዲፈጠር ስራችንን እንቀጥላለን ሲሉም ነው የተናገሩት።
ድርድርን በተመለከተ ቁርጥ ያለ ቀን አልተቀመጠም ያሉት ኦባሳንጆ ሶስት፣ ስድስት ወር ወይም ዓመት ይሁን አይታወቅም ብለዋል።

በትግራይ የተቋረጡ እንደ የመብራት፣ የውሃ እና የባንክ አገልግሎቶችን የመሳሰሉ የመሰረተ ልማቶች ዳግም አገልግሎት መስጠት እንደጀምሩም ንግግር መደረጉን ተወካዩ አንስተዋል።

Via:- Al Ain
@Yenetube @Fikerassefa
ሸኔና የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) በፈፀሙት ጥቃት የኹለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሦስት ሠዎችን ታፍነው መወሰዳቸው ተገለፀ!

በጋምቤላ ወረዳ ጎሊ በሚባል አካባቢ ሸኔና የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ብሎ የሚጠራው ቡድን በፈፀሙት ጥቃት የኹለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሦስት ሠዎችን ደግሞ አፍነው መውሰዳቸውን የክልሉ መንግስት አስታወቀ።

የጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኡገቱ አዲንግ እንዳሉት፤ ትናንት ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ በጋምቤላ ወረዳ ጎሊ በሚባል አካባቢ በእርሻ ሥራ ላይ የነበሩ የኹለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሦስት ሠዎች ታፍነው ተወስደዋል።

ኃላፊው ሟቾቹ አንድ ወንድና አንድ ሴት መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ታፍነው የተወሰዱትም ኹለት ወንድና አንድ ሴት እንደሆኑ አስታውቀዋል።

ጥቃቱን ያደረሱት ራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ብሎ የሚጠራው ቡድን ከህወሓት ተላላኪው ከሸኔ ጋር በማበር እንደሆነ አስረድተዋል።

ጥቃቱ ቡድኖቹ ለዘመናት በህዝቦች መካከል የነበረውን ወንድማማችነትና ሠላም በማደፍረስ ግጭት ለመፍጠር ያደረጉት ጥረት እንደሆነ ጠቅሰው ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ሙከራ አድርገው እንዳልተሳካላቸው አመልክተዋል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ከዚህ በፊት የጀመራቸውን የአብሮነትና የሠላም እሴት አጠናክሮ በማስቀጠል ለክልሉ ዘላቂ ሠላምና ልማት የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ሲሉ ኡገቱ ማሳሰባቸውን ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

የመንግስት ሀይል ጥቃት አድራሾቹ ላይ እርምጃ ለመውሰድ የተጠናከረ ክትትል እያደረጉ እንደሚገኝ ጠቁመው ህብረተሰቡ ተገቢውን ትብብር እንዲያደርግም ኃላፊው ጠይቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሜቴክ የቀድሞ 4 አመራሮች ከተከሱሰበት የሙስና ወንጀል ክስ ከስር እንዲፈቱ ታዘዘ።

አራቱ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ከተወሰነባቸው የስራት ቅጣት በላይ በስር በመቆየታቸው የስር ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸው ነው ከስር እንዲፈቱ የታዘዘው።

የቀድሞ የብረታብረትና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን ሀላፊዎች ሌ/ኮ ሰጠኝ ካሳይ: ኮነሬል ፍጹም አብርሃ: ሻለቃ ዋልታንጉስ ተስፋው እና ሻለቃ ክንድያ ግርማይ የኃይል ትራንስፎርመር እና ባለ 3 ፌዝ ተርሚናል ኮኔክተር ለኢትዮጲያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ለማቅረብ የተገባ ውል ላይ ያለጨረታ ግዢ ፈጽመዋል ተብለው በዓቃቢህጥ ባቀረበባቸው የሙስና ክስ በወንጀል ህግ 32 /1 ሀ እና የሙስና ወንጀል አዋጅ. ቁ 881/2007 አንቀጽ 91 ሀና ለ ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት በየደረጃው እንዲከላከሉ ብይን መሰጠቱ ይታወሳል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ተከሳሾቹ ያቀረቡትን የመከላከያ ማስረጃ ከመረመረ በኋላ በዓቃቢህግ ያቀረበውን ማስረጃ በተገቢው አልተከላከላችሁም ሲል የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸው ነበር።ተከሳሾቹ የቀረቡትን የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን ለሀገር ያበረከቱት ሙያዊ አስተዋጾ እና የበጎ አድራጎት ስራ በቅጣት ማቅለያ አስተያየት ተይዞላቸዋል።

በዚህም ፍርድ ቤቱ ሻለቃ ኮንድያ ግርማይን 2 አመት ከ9 ወር እስራትና 400 ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ የወሰነ ሲሆን ቀሪዎቹ ሶስት ተከሳሾች ደግሞ በ3 አመት እስራትና 500 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።ይሁንና ተከሳሾቹ ከተወሰነባቸው የዕስራት ጊዜ በላይ ከጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ በእስር በማሳለፋቸው የስር ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸው ከስር እንዲፈቱ ታዟል።

[Tarik Adugna]
@YeneTube @FikerAssefa
መቀለ እና ባሌ የታዩት ኦባሳንጆ የሰላም ጥረቱ ‘ዘገምተኛ’ ነገር ግን ‘ወደፊት እየሄደ ያለ’ ነው አሉ!

የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በውይይት ለመቋጨት የሚደረገው ጥረት ‘ዘገምተኛ’ ነገር ግን ‘ወደፊት እየሄደ ያለ’ ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናገሩ።የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ከቀናት በፊት በመቀለ ከህወሓት ሊቀመንር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ጋር እየተነጋገሩ ታይተዋል።ዛሬ ደግሞ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕምድ ጋር በኦሮሚያ ክልል ባሌ ሮቤ ከተማ ላይ ተገኝተዋል።

ጦርነት ውስጥ የገቡትን የፌደራሉን መንግሥት እና ህውሓትን ለማደራደር በርካታ ጥረት ሲያደርጉ የቆዩት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፤ “ለውጥ አለ ግን ዘገምተኛ ነው።ዛሬ ያለው ሁኔታ ከስድስት ወራት በፊት ከነበረው የተሻለ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

“እያደረግን ያለነው፤ ማድረግም ያለብን መተማመን [በተዋጊዎች መካከል] መፍጠር የሚያስችል ስራዎችን መስራት ነው” ያሉት ኦባሳንጆ፤ እየመሩት ያለው የድርድር ጥረት ሁለት ውጤቶችን እንዲያስመዘግብ ፍላጎታቸው እንደሆነ ተናግረዋል።ኦባሳንጆ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲኖር እና በድርድር ተኩስ ማቆም የሚቻልበት ደረጃ ላይ መድረስ ፍላጎታቸው እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከአፍሪቃ ሕብረት ሊቀመንበርን በነገው ዕለት ተቀብለው እንደሚያነጋግሩ ተገለጸ።

ፑቲን እና የአፍሪቃ ሕብረቱ የበላይ ዋና የመነጋገሪያ ነጥብ እህል ወደ አፍሪቃ ማስገባት የሚቻልበትን መንገድ በተመለከተ ሲሆን የፖለቲካ ትብብር ላይ እንደሚያተኩሩ ይጠበቃል።ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮጳ ሕብረት በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ማዕቀቦች የጣሉባት ሩሲያ አፍሪቃ እና እስያ ውስጥ አዲስ የገበያ ዕድል እና ጠንካራ ግንኙነት እየፈለገች መሆኑ እየተነገረ ነው።

በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ምክንያት አፍሪቃ ውስጥ የእህል ዋጋ በጣም እየጨመረ ሄዷል። በነገው ዕለት ፕሬዝደንት ፑቲን በዚሁ ጉዳይ ለመነጋገር የሴኔጋል ፕሬዝደንት እና የወቅቱን የአፍሪቃ ሕብረት ሊቀመንበር ማኪ ሳልን ሶቺ ላይ ተቀብለው ያነጋገራሉ።ሳል ወደ ሩሲያ የሚጓዙት ከአፍሪቃ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ሙሳ ፋኪ ጋር እንደሚሆን የአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዜና ያመለክታል።

ሩሲያ እና ዩክሬን ውስጥ ከፍተኛ የስንዴ ምርት መከማቸቱ ቢነገርም በጦርነቱ ምክንያት በመርከብ የማጓጓዙ እንቅስቃሴ ተደናቅፏል።በዩክሬን ወደብ ላይም በርካታ ቶን ስንዴ እና በቆሎ መከማቸቱ እየተነገረ ነው። ፑቲን ሀገራቸው ተጨማሪ እህል ወደ ዩክሬን ወደብ ለማድረስ መንገድ እየፈለገች መሆኑን በማመልከት ከዚያ በፊት ግን ምዕራቡ ዓለም እገዳውን እንዲያነሳ ጠይቀዋል። የተመድ አፍሪቃ በጦርነቱ ምክንያት ያልተጠበቀ ቀውስ ለመጋፈጥ መገደዷን አመልክቷል። የአፍሪቃ ሕብረት ሊቀመንበር ማኪ ሳል ቀደም ብለው የአውሮጳ ሕብረት ቀውሱ የሚፈታበትን መንገድ እንዲፈልግ ጠይቀዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጦርነት የገቡ አካላትን ለማስታረቅ ጠየቀች!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጦርነት የገቡ አካላትን ማስታረቅ እንደምትፈልግ ገለጸች፡፡ቤተ ክርስቲያኒቷ ከግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታካሂድ የነበረውን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ማህበራዊና መንፈሳዊ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቃለች፡፡

የጉባኤውን መጠናቀቅ ተከትሎም ቤተ ክርስቲያኒቷ ውሳኔዎቿን የተመለከተ መግለጫን አውጥታለች፡፡በመግለጫው በኢትዮጵያ በጦርነት ውስጥ ያሉ ወገኖች ወደ ሰላም እና እርቅ እንዲመጡ ማስታረቅ እንደምትፈልግ አስታውቃለች፡፡

ምልዓተ ጉባኤው በአሁኑ ደረጃ በኢትዮጵያ ባለው የሰላም እጦት ላይ በሰፊው መወያየቱን ገልጻ በቀጣይ ጦርነትና የእርስ በርስ ግጭት ተወግዶ አጠቃላይ ሰላም በሚሰፍንበት መልኩ ተነጋግሮ ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት እንዲቻል፣ የአስታራቂነት ሚናዋን መጫወት እንድትችል ለማድረግ ለፌዴራል መንግሥት ጥያቄ አቅርቤያለሁ ብላለች፡፡

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://am.al-ain.com/article/eotc-request-to-mediate-waging-parties-in-ethiopia

@YeneTube @FikerAssefa
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2015 በጀት 786 ነጥብ 61 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ወሰነ፡፡

በጀቱ በአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ የተቀመጡ ግቦችን ለማስፈጸም ያለመ ነው፡፡ በተጨማሪም የሀገር ደህንነትን ለማስጠበቅ፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ከመርዳትና የወደሙ መሰረተ ልማቶችን እና አገልግሎቶችን መልሶ ማቋቋምን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

ከ2014 በጀት ዓመት በጀት ጋር ሲነጻጸር የብር 111.94 ቢሊዮን ወይም የ16.59 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ ምክር ቤቱም የፌዴራል መንግሥት የ2015 በጀትን ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡የ2014 ዓ.ም በጀት 561 ቢሊየን ብር እንደነበር ይታወሳል፡፡መረጃዉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ነዉ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የተለያዩ ሹመቶች ሰጥተዋል።

በዚሁ መሰረት፥

1. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን - የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር

2. አቶ ካሊድ አብዱራህማን - በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የፕሮጀክቶች ክትትል

3. አቶ ወንድሙ ሴታ - የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ

4. አቶ ሄኖስ ወርቁ - የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚከተሉትን ሸመቶች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲያጸድቅላቸው ጠይቀዋል፦

1. ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ - የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ዋና ኦዲተር

2. አቶ አበራ ታደሰ - የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር ሆነው ተሹመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ደንበኞች ግብራቸውን ኦንላይን እንዲከፍሉ ከባንኮች ጋር ስምምነት ላይ ተደረሰ!

የገቢዎች ሚኒስቴር ደንበኞች ግብራቸውን በኦንላይን እንዲከፍሉ ለማስቻል ከኦሮሚያ፤ ወጋገን እና ዘመን ባንክ ጋር ስምምነት ተፈራርሟል ተብሏል።ስምምነቱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የታክስ አሰባሰቡን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እና ደንበኛውም በኦንላይን በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ ሆኖ ግብሩን መክፈል ያስችለዋል ነው የተባለው።

የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ክፍያ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለማሰባሰብ በሚያደርገው ጥረት ንግድ ባንክን ጨምሮ ከአራት ባንኮች ጋር እየሠራ መሆኑንም ተመላክቷል።
በሚኒስቴሩ የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ መሠረት መስቀሌ፤ የታክስ አስተዳደር ሥርዓቱን ዓለም በደረሰበት ቴክኖሎጂ በመደገፍ የአገልግሎት አሰጣጡ ግልጽ፤ ቀልጣፋ እና ተደራሽ በሆነ መንገድ መስጠት ዋናው የተቋሙ ተልእኮ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም የግብር ሥርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን ሌሎች ባንኮችም ወደ ሥርዓቱ እንዲገቡ ጥሪ ማቅረባቸው ተዘግቧል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://addismaleda.com/archives/27774

@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ ሶማሊያ ውስጥ የአልሻባብ ታጣቂዎችን ኢላማ ያደረገ የአየር ጥቃት ፈጽማ በቡድኑ ላይ ጉዳት ማድረሷን የሶማሊያ መንግሥት አስታወቀ።

ከሶማሊያ የማስታወቂያ ሚኒስቴር የወጣ መግለጫ እንዳመለከተው “ከአገሪቱ መንግሥት ጋር በመቀናጀት” ትናንት አርብ በተፈጸመው የአየር ጥቃት አምስት የአልሻባብ ታጣቂዎች ተገድለዋል።

የሶማሊያ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የአየር ጥቃቱን በተመለከተ በትዊተር ላይ ባወጣው መግለጫ፣ እርምጃው የአልሻባብ ታጣቂዎች ከኪስማዮ ከተማ ደቡብ ምዕራብ በሚገኝ አካባቢ ያለ የሶማሊያ መንግሥት ኃይሎች ላይ ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ ነው።

ይህ ጥቃት የተፈፀመው አሜሪካ ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ መልሳ ለማስፈር ከወሰነች ከሳምንታት በኋላ ነው። ፕሬዝዳንት ባይደን 500 የሚሆኑ የልዩ ተልዕኮ ወታደሮቻቸው ወደ ሶማሊያ እንዲሰማሩ የወሰኑት በሶማሊያ ከተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በኋላ ነበር።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ራይድ የትራንስፖርት አገልግሎት በስሩ ያሉ ከ40ሺ በላይ የሚልቁ አሽከርካሪዎች መኪናዎቻቸውን በኤሌክትሪክ ሃይል ወደሚሰራ መኪና እንዲቀይሩ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

የራይድ መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ት ሳምራዊት ፍቅሩ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ ድርጅታቸው በስሩ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ከ40ሺ በላይ የሚሆኑ አሽከርካሪዎች ከባንክና ከመኪና አምራች ኩባንያዎች ጋር በማስተሳሰር መኪናዎቻቸውን ዘመናዊና በኤሌክትሪክ ሃይል ወደሚሰራ ተሽከርካሪ ለመቀየር እየሰራ ነው።

እንደዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ገለፃ፤ የተሽከርካሪዎቹ መቀየር ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የነዳጅና የተሽከሪካሪ መለዋወጫ ወጪን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። በተለይም አገሪቱ ለነዳጅና ለተሽከርካሪ መለዋወጭ የምታወጣው የውጭ ምንዛሬ በመታደግ ለሌላ የልማት ሥራ እንድታውለው ለማድረግ የጎላ ሚና አለው። በተጨማሪም በከተሞች የሚስተዋለውን ከፍተኛ የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመከላከል ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከነዳጁ ባሻገር መለዋወጫዎችን ከውጭ በበርካታ ቢሊዮን ዶላር በማውጣት እያስመጣች በመሆኑ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዲባባስ ምክንያት እንደሆነ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አስረድተዋል። ይህም ሀገሪቱ ለዘመናት የኢኮኖሚ ጥገኛ እንድትሆን ያደረጋት መሆንኑም አብራርተዋል። ‹‹በመሆኑም ጥገኝነታችንን እየቀነስን ለመምጣት ከውጭ የሚመጣውን እዚሁ የሚተካበትን መንገድ መፍጠር አለብን። አንደኛው ደግሞ በነዳጅ ከሚነዳው መኪና ወደ ኤሌክትሪክ መኪና መሸጋገር አዋጭ ነው›› ብለዋል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://www.press.et/?p=74326

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ የትምህርት ሥነ ሥርዓት /ካሪኩለም/ መስማት ለተሰናቸው ተማሪዎች አካታች አለመሆኑ ጫና እየፈጠረባቸው እንደሆነ ተነገረ፡፡

መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የሚገጥሟቸውን ችግሮች ለመቀነስ ROOTS & wings በመባል የሚጠራ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ከአልፋ መስማት የተሰናቸው ልዩ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ጋር በመተባበር ችግሮቻቸውን ለመቀነስ ፣ጥራት ያለው ትምህርት መስማት ለተሰናቸው ሴት ተማሪዎች በሚል ሀሳብ ሥራ መጀመራቸው ይፋ አድርገዋል፡፡

ሴት መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ከወንዶች የበለጠ ፍላጎቶች ስለሚያስፈልጓቸው ሴቶችን ላይ የበለጠ ትኩረት አድርገን የትምህርት ሥርዓት መፍጠር ላይ እንሰራለን ያሉት የ ROOTS & wings መስራቾች መካካል አንዷ የሆኑት ዶ/ር ሰርካለም ግርማ ናቸው፡፡

መስማት በተሳናቸው ተማሪዎች ላይ የተጠኑ ጥናቶች በተለይም የመማሪያ መሳሪያዎች ፈፅሞ ለተማሪዎች እንደማይመቹ ፣ ወላጆች ጋር ያላቸው የመግባቢያ ቋንቋ ችግር ፣ ለተማሪዎቹ ለመግለፅ የሚያዳግቱ ቋንቋዎች መኖራቸውን የጠቀሱት ዶ/ር ሰርካለም ግርማ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ROOTS & wings በተቻለ አቅም ይሰራል ብለዋል፡፡

የድርጅቱ ከፍተኛ ትምህርት አማካሪ ዶ/ር ስለሺ ይትባረክ አልፋ መስማት የተሰናቸው ልዩ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ድርጅታቸው ሲሰራ የተማሪ የመማሪያ መፅሐፍቶችን ወደ ምልክት ቋንቋ መቀየር ፣ ለመምህራኖች እና ለወላጆች ሥልጠና መስጠት ፣ለሴት ተማሪዎች ክበባት ማቋቋም ፣ግንዛቤ የመፍጠሪያ መድረኮች መጀመር እና መሰል ሥራዎችን እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡በተመሳሳይ ሥራቸው አንድ ት/ቤት ውስጥ ተወስኖ የሚቀር እንዳልሆነ ለወደፊት የተለያዩ ት/ቤቶች ጋር እንደሚሰሩ ተሰምቷል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa