YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሩሲያ ዶንባስ የተሰኘ ሮኬት ወደ አለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ አመጠቀች

ሩሲያ ትናንት አርብ ዶንባስ የተሰኘ ሮኬት ወደ አለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ አስወንጭፋለች ፡፡
ስያሜው በዩክሬን ዶንባስ ግዛት ውስጥ ለሚገኙ ተገንጣይ ሪፐብሊካኖች (የዶኔትስክ እና የሉሃንስክ ህዝባዊ ሪፐብሊኮች) ክብር ለመስጠት በማሰብ የተሰጠ ነው፡፡
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት 100 ቀናትን አስቆጥሯል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የመንግስትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ እና ስልጠና የወሰዱ ኃይሎች በተለያየ የልማት ስራ ላይ መሰማራት መጀመራቸውን የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋሹ ዱጋዝ ገልፀዋል።

ፅንፈኛ አመለካከት ይዘው ሲዋጉ የነበሩት ታጣቂ ኃይሎች የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባከናወኑት የፀጥታ ስራ አብዛኞቹ የመንግስትን ጥሪ የተቀበሉና ስልጠና የወሰዱ አባላት በእርሻ በማዕድን ዘርፍ እና ቀደም ሲል በነበሩት የስራ መስክ ላይ ተሰማርተዋል።

ከ 4 እና 5 ወራት በፊት የነበረው የፀጥታ ችግር በመቀረፉ አሁን ላይ የመተከል ዞን ፊቷን ወደልማት ማዞር ጀምራለች ያሉት አስተዳዳሪው አቶ ጋሹ በእርሻ ስራ ለመሰማራት ለተደራጁ አባላት በቅድሚያ 6 የእርሻ ትራክተሮች መንግስት 30 ከመቶ ቅድመ ክፍያን በመሸፈን ለርክክብ ዝግጁ ሆነዋል ብለዋል።

ትራክተሮቹ በሁሉም የመተከል ዞን ወረዳዎች የሚታደሉ ሲሆን 11ተጨማሪ ትራክተሮችም በግዥ ሒደት ላይ እንዳሉ ገልፀዋል።

የተሃድሶ ስልጠና ከወሰዱት ተመላሽ ታጣቂዎች መካከል 17 በማዕድን ስራ 92 በንግድ ስራ ወደነበሩበት የመንግስት ስራ የተመለሱ 43 እንዲሁም 493 አባላት ደግሞ በፀጥታ ስራ ላይ ተሰማርተዋል።

ወደፀጥታ ስራ እየተሰማሩ ላሉት በቂ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን የገለፁት ደግሞ በመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት የዳንጉር ወረዳ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሻለቃ ደምስ ዳኜ ናቸው።

አሁን ላይ የፀጥታ ስራው በአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች ጭምር እየተከናወነ በመሆኑ ዜጎችን ወደቀያቸው የመመለስ ስራም ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ደመቀ ህወሓት ለጥፋት ዓላማ ሊጠቀምባቸው የሚችሉ ቁሳቁሶች እንዳያልፉ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰቡ!

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለጥፋት ዓላማ ሊጠቀምባቸው የሚችሉ ቁሳቁሶች ለህወሓት እንዳይተላለፉ አሳሰቡ፡፡አቶ ደመቀ በአፋር ክልል ሰርዶ ኬላ ተገኝተው የሰብዓዊ ድጋፎችን ትግራይ ክልል ለማድረስ የሚደረጉ ጥረቶችን ከሌሎች የፌዴራል እና የክልሉ ባለስልጣናት ጋር በመሆን ጎብኝተዋል፡፡አቶ ደመቀ የአፋር ህዝብ በህወሓት ወረራ ምክንያት ከ1 ሚሊየን በላይ ተፈናቃዮችን ይዞ መንግስት ለትግራይ ህዝብ ሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ እያደረገ ለሚገኘው ጥረት ያሳየውን ቀና ትብብር አድንቀዋል፡፡

በየደረጃው ያሉትን የክልሉን ነዋሪዎች ያመሰገኑም ሲሆን ሰብዓዊ እርዳታዎችን በሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ወደተጎዱ ወገኖች ለማድረስ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑንም አብራርተዋል፤ ከዚህም ውስጥ ለትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሚደረገው ድጋፍ አንዱ መሆኑን በመጠቆም፡፡በሰርዶ ኬላ ተገቢው የፍተሻና ተያያዥ ቁጥጥር ከተደረገበት በኋላ በቀን እስከ 200 ኮንቮይ ተሽከርካሪዎች ሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ እንደሚያቀኑም ተናግረዋል አቶ ደመቀ፡፡ይሁንና በተደረገዉ ፍተሻ ለሽብር ቡድኑ የጥፋት አላማ ማስፈጸሚያ ሊውሉ የሚችሉ ከተፈቀደው የነዳጅ መጠን በላይ ተጨማሪ ነዳጅና አንዳንድ ያልተፈቀዱ ቁሳቁሶች ለማሳለፍ ሙከራዎች አንዳሉ መገንዘባቸውን ነው የተናገሩት፡፡

https://am.al-ain.com/article/demeke-mekonnen-warned-to-be-careful-not-to-pass-on-materials-that-could-be-used-by-tplf


@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ጃዋር መሐመድ በእስር ላይ በቆዩባቸው ጊዜያት ለሳቸው እና አብረዋቸው ለታሰሩ ሰዎች ከእስር እንዲለቀቁ ደጋፊዎቻቸው አድርገዋል ላሉት ጥረት ዛሬ ምስጋና አቀረቡ።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አቶ ጃዋር መሐመድ ምስጋናውን ያቀረቡት ዛሬ በጀርመን ኑርንበርግ ከተማ አቅራቢያ በተዘጋጀ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ በአካል ተገኝተው ነው። ይህ የጉዟቸው አንደኛው አላማ ሲሆን ሌላኛዋ አላማ በብዙ ውጥንቅጥ ውስጥ የምትገኘው ኢትዮጵያ ላይ ሰላም እንዲሰፍን ለማስቻል በሚደረግ ጥረት ውስጥ ደጋፊዎቻቸው የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ለማሳሰብ ነው ተብሏል። ጉብኝታቸው አውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካን የሚያካልል ሲሆን በቀጣይ ደግሞ ፈረንሳይ፣ ኔዘርላንድስ እና ቤልጄም ከመሳሰሉ የአውሮፓ ሀገራት ከደጋፊዎቻቸው ጋር ከተገናኙ በኋላ ወደ ሰሜን አሜሪካ እንደሚያቀኑ ዶይቸ ቬለ ዘግቧል።አቶ ጃዋር መሐመድ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ለሁለት ዓመት ገደማ ያህል በእስር ላይ መቆየታቸው ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት አለፈ!

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ቀርሳ ወረዳ ከቀኑ 8፡30 አካባቢ የጭነት አይሱዙ ተሽከርካሪ ባደረሰው አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጐሹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ፥ አደጋው የደረሰው ተሽከርካሪው ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ ሲሚንቶ ጭኖ እየተጓዘ ባለበት ወቅት ቀርሳ ከተማ ሲደርስ ፍሬን አልታዘዝ ብሎት ወደ ገበያ በመሄድ ላይ የነበሩ መንገደኞችን በመግጨቱ መሆኑንም ተናግረዋል።

በዚህም 8 ወንዶችና 6 ሴቶች ህይወታቸው አልፏል።በአደጋው ህይወታቸው ካለፈው በተጨማሪ ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ለከፍተኛ ህክምና ወደ ድሬዳዋ ከተማ ተልከዋል።የአደጋው መንስኤ ከፍጥነት ወሠን በላይ ማሽከርከርና ፍሬ ለመያዝ አለመቻል መሆኑንም ገልጸዋል።ተሽከርካሪው በእግረኞች ላይ ጉዳት ካደረሰ በኋላ መገልበጡን የገለፁት ኢኒስፔክተር ቶሎሳ አሽከርካሪው ጉዳት ደርሶበት በቁጥጥር ስር መዋሉን ጠቁመዋል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሰሜናዊ ኬንያ የዋጅር አውራጃ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩ ዘጠኝ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን በአካል መጌብኘቱንና ፍልሰተኞቹ በምን አኳኋን እንደታሰሩ ቃላቸውን መቀበሉን በድረገጹ ገልጧል።

ፍልሰተኞቹ በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደ ኬንያ በሕገወጥ መንገድ በመግባት የታሰሩ ሲሆኑ፣ ሁሉም እድሜያቸው ከ18 በታች እንደሆነ እና አራቱ ሴቶች እንደሆኑ ኮሚሽኑ ጠቅሷል። በእስር ቤቱ ሌሎች ከ18 ዓመት በላይ የሚሆናቸው 18 ሕገወጥ ፍልሰተኛ ኢትዮጵያዊያን ታስረው እንደሚገኙ ማረጋገጠንም ኮሚሽኑ ገልጧል። ኮሚሽኑ ከጎረቤት አገራት አቻ ተቋማት ጋር በመተባበር፣ ፍልሰት መደበኛ፣ ሥርዓት ያለውና ደኅንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን እየሰራሁ ነው ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የተቃዋሚ ፓርቲዎች የምክክር ቤት (caucus) ተቋቋመ።

በሀገራዊ የምክክር መድረክ አካሄድ ላይ መሰረታዊ ቅሬታ አለን ያሉ 10 የሚደርሱ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች
"እውነተኛ የዴሞክራሲ ስርአትን የሚያስገኝ ሀገራዊ ውይይት አማራጭን ለማቅረብ የሚያስችል የምክክር ቤት (Caucus) አቋቁመናል" ሲሉ በዛሬው ዕለት ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

ሀገራዊ ምክክር በምን መልኩ ይካሄድ በሚለው ላይ ክርክሮች እየተደረጉ ባለበት ወቅት " መንግስት ሂደቱን የሚቆጣጠር ረቂቅ ህግ በማዘጋጀት በአንድ ፓርቲ የበላይነት ባለው ፓርላማ በኩል የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጥያቄ እና የግብአት ሀሳብ ችላ በማለት እንዲፀድቅ ማድረጉን ያስታወሰው የፓርቲዎቹ መግለጫ የኮሚሽነሮቹን ምርጫም "የተድበሰበሰ" ነበር ሲል ኮንኗል።
በትጥቅ እየተፋለሙ የሚገኙ አካላትን ወደ ምክክሩ ለመጋበዝ የተቀመጠ ድንጋጌ አለመኖሩን የነቀፈው የምክክር ቤቱ መግለጫ "አማራጭ" በተባለው አዲስ የምክክር ቤት (Caucus) በኩልም
ለመንግስት በርከት ያሉ ምክረሀሳቦችንም አቅርቧል።

በምክረሀሳቦቹም ላይ:-
-አፋጣኝ እና አለም አቀፍ ተቋማት የሚቆጣጠሩት የተኩስ ማቆም በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ላይ እንዲደረግ
-የምክክር ኮሚሽኑ በድጋሜ እንዲቋቋም እና ኮሚሽነሮቹም ገለልተኛ በሆነ መንገድ እንዲመረጡ
- የውይይት አጀንዳዎቹ ሁሉንም ባሳተፈ መልኩ እንዲቀረፁ እንዲሁም
-ውይይቶቹ አለም አቀፍ ታዛቢ በተገኘበት እንዲደረጉ
አሳስቧል።

የምክክር ቤቱን የመሰረቱት ፓርቲዎችም
1- መድረክ
2- ህብር ኢትዮጵያ
3- የአፋር ህዝብ ፓርቲ
4- የአፋር ፍትህ እና ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
5- የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)
6- የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ
7-የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር
8- የዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ
9- ዓረና ትግራይ
10- የዶንጋ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
መሆናቸው ተገልፃል።

ስለ ምክክር ቤቱ ለሚዲያችን አስተያየታቸውን የሰጡት የአፋር ህዝብ ፓርቲ መሪ እና የምክክር ቤቱ ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ ሙሳ አደም "ፓርቲዎቹ በተለያየ ጉዳይ ላይ የተለያየ አቋም ቢኖራቸውም ሀገራዊ ምክክሩ በሀቀኛ መንገድ መከናወን አለበት የሚለው ላይ ግን የማያወላዳ የጋራ አቋም አላቸው፤ አማራጭ የምክክር ቤት ለማቋቋም የወሰነውም ለዚህ ነው"
ብለዋል።

[Ubuntu News]
@YeneTube @FikerAssefa
የታለመ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ተሸከርካሪዎች መለያ ይፋ ሆነ!

የታለመ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የሚሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪዎች የድጎማው ተጠቃሚ መሆናቸውን የሚገልፅ መለያ ይፋ መሆኑን የትራንስፓርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር አስታወቀ።

መለያው ሁለት አይነት ሲሆን ለመደበኛ ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት ተሸከርካሪዎች እና በክልል ለሚገኙ ተሸከርካሪዎች የሚያገለግል ነው።

መለያው ተሸከርካሪዎቹ የታለመ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ መሆናቸውን ለነዳጅ ማደያዎችና ለሚመለከታቸው ሌሎች አካላት መረጃ የሚሠጥ ነው።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የታለመ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ተሸከርካሪዎች መለያ ይፋ ሆነ! የታለመ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የሚሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪዎች የድጎማው ተጠቃሚ መሆናቸውን የሚገልፅ መለያ ይፋ መሆኑን የትራንስፓርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር አስታወቀ። መለያው ሁለት አይነት ሲሆን ለመደበኛ ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት ተሸከርካሪዎች እና በክልል ለሚገኙ ተሸከርካሪዎች የሚያገለግል ነው። መለያው…
ሙሉ ሰማያዊ ቀለም ያለው መለያ ለሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት ተሸከርካሪዎች የሚያገለግል ሲሆን በነጭ መደብ የተዘጋጀው መለያ ደግሞ በክልል ለሚገኙ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎ ሰጪ ተሸከርካሪዎች የሚያገለግል ነው፡፡

በቅርቡ ተግባራዊ ለመሆን በዝግጅት ላይ የሚገኘው የታለመ የነዳጅ ድጎማ ስርዓት ተጠቃሚ የሚሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተሸከርካሪዎችን የመለየትና መረጃ የማጥራት ስራ እየተከናወነበት እንደሚገኝ ይታወቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ አራት የማጣሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ ማላዊ ጋር አቻዉ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2 - 1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ አቡበከር ናስር ማስቆጠር ችሏል ። የማላዊውን የማሸነፊያ ሁለት ግቦች ጋባዲንሆ ምህንጎ አስቆጥሯል።

የዛሬውን ውጤት ተከትሎ ዋልያዎቹ ያለ ምንም ነጥብ ምድብ አራት ላይ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ሀሙስ ምሽት 1:00 በማላዊ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከግብፅ ብሄራዊ ቡድን ጋር የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ የማጣሪያ ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ይሆናል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሩሲያ ከአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን የተለገሱ የጦር መሳሪያዎችን አወደምኩ አለች!

ሩሲያ ከአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን የተለገሱ የጦር መሳሪያዎችን ማውደሟን አስታወቀች።ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር ይፋዊ ጦርነት ከጀመረች 102 ቀናት ሆኖታል።

በዚህ ጦርነት ምክንያት ከ6 ሚሊየን በላይ ዩክሬናዊያን ዜጎች መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው ሲሰደዱ 20 በመቶ የዩክሬን ክፍልም በሩሲያ ጦር ቁጥጥር ስር ወድቋል።

ጦርነቱን ተከትሎም አውሮፓ ህብረት፣አሜሪካ እና ሌሎች ሀገራት በሩሲያ ላይ ከስድስት ሺህ በላይ ማዕቀቦች የተጣሉባት ሲሆን፤ ሩሲያም የአጸፋ እርምጃ በመውሰድ ላይ ትገኛለች።ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን በመለገስ ላይ ሲሆኑ፤ ሩሲያም የተለገሱትን የጦር መሳሪያዎች በማውደም ላይ መሆኗን ገልጻለች።

ከሰሞኑ ከአውሮፓ ሀገራት ለዩክሬን የተለገሱ የጦር ተሽከርካሪዎችን እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን ማውደሟን የሀገሪቱ ዜና ወኪል ታስ ዘግቧል።

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ እንዳይለግሱ አሳስበው ልገሳቸውን ከቀጠሉ ግን እርምጃ መውሰዴን እንደሚቀጥሉ አስጠንቅቀዋል።

ሩሲያ “ዚርኮን” የተባለ አዲስ ሃይፐርሶኒክ ክሩዝ ሚሳዔል ሞከረች
በተለይም ምእራባዊያን ሀገራት ረጅም ርቀት ተወንጫፍ ሚሳኤሎችን እንዳይለግሱ የተናገሩት ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ ደህንነቷን ለመጠበቅ ስትል እርምጃ ትወስዳለች ብለዋል።

አሜሪካ፣ ስፔን እና ሌሎች የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ለዩክሬን ሚሳኤሎች እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን ለግሰዋል ተብሏል።
እንደ ሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ ከሆነ ምዕራባዊያን ለዩክሬን የጦር መሳሪያ በመለገስ ጦርነቱን የማራዘም እቅድ እንዳላቸው ተገልጿል።

Via Alain
@Yenetube @Fikerassefa
ሦስተኛው ዙር የህዳሴው ግድብ ሙሌት በሐምሌ ወር እንደሚጀመር ታወቀ!

የሁለተኛው ተርባይን ፍተሻ ተጀምሯል
ለመጀመሪያ ጊዜ ኃይል ማመንጨት ከጀመረ ሦስት ወራት ያለፉት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር ሙሌት፣ ከመጪው ሐምሌ ወር አንስቶ መከናወን እንደሚጀምር ታወቀ፡፡ከክረምቱ መግባት ጋር ተያይዞ ወደ ግድቡ የሚፈሰው የውኃ መጠን ከሰኔ አጋማሽ ጀምሮ ከፍ እያለ ከሄደ በኋላ ወደ ግድቡ የሚገባውን ውኃ በመያዝ፣ በሐምሌ ወር ሙሌቱ እንደሚጀመር ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የህዳሴ ግድብ ከፍተኛ ኃላፊ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በዚህ ዓመት ወደ ግድቡ እንዲገባ የሚጠበቀውን የውኃ መጠን ለመያዝ የግድቡን ቁመት የመጨመር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ የውኃ ሙሌቱ ሲጀመር የግድቡ ቁመት በሚፈለገው መጠን እንደሚደርስ አስረድተዋል፡፡ከክረምቱ መግባት በኋላ ባሉት ወራት የሚኖረው የውኃ መጠን የሚለያይና እየጨመረ የሚሄድ በመሆኑ፣ ከፍተኛው የውኃ መጠን የሚታየው በነሐሴ ወር ነው ብለዋል፡፡ በዚህም መሠረት ከሐምሌ ጀምሮ የሚፈለገው የውኃ መጠን ተይዞ፣ በነሐሴ ወር ውኃው በግድቡ ላይ ይፈሳል ሲሉ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በትላንትናው እለት በደረሰ የጎርፍ አደጋ በዘጠኝ መኖሪያ ቤቶች ውድመት ደርሷል!

በአዲስ አበባ በጎርፍ አደጋ ከአንድ ነጥብ ሶስት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙንም የእሳት አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ጎርፉ በሁለት አካባቢዎች ከፍተኛ ውድመት አድርሷል።

የመጀመሪያው የጎርፍ አደጋ የደረሰው በዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ላዩ ቦታው አየር ጤና አካባቢ ከቀኑ10፡30 ነው። ሁለተኛው አደጋ በኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ ስልጤ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከቀኑ 11 ሰዓት ከ20 ላይ መሆኑን የኮሚሽነ የህዝብ ግንኙነት ባላሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

በደረሱት የጎርፍ አደጋዎች ዘጠኝ መኖሪያ ቤቶች ጉዳት ሲደርስባቸው አንድ ነጥብ ሶስት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ውድማል። የድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ቡድን በስፍራው በመድረስ ከመኖሪያ ቤቶቹ በፓንፕ ውሃ የማውጣት ስራ የሰራ ሲሆን ባደረገውም ርብርብ ከሰባት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማትረፍ መቻሉን አቶ ንጋቱ ጨምረው ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ በመጪው የክረምት ወራት 148 ቦታዎች ለጎርፍ ተጋላጭ መሆናቸውን ያሳወቀው ኮሚሽኑ ችግሮች እንዳይፈጠር እየተሰራ መሆኑን ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
በቡርጂ ወረዳ ተነስቷል በተባለ ግጭት 9 ሰዎች ሲሞቱ 17ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን አስተዳደሩ ተናገረ፡፡

በደቡብ ክልል በቡርጂ ወረዳ ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ.ም አንድ አርሶ አደር ከጉጂ የተነሱ ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች ጥቃት መድረሱን ተከትሎ በተነሳ ግጭት የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 17 ሰዎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የአካባቢው ነዋሪና የወረዳው አስተዳደር ለአሻም ተናግረዋል፡፡

አሻም እንዳነጋገረቻቸው የአካባቢው ነዋሪ ከሆነ ”ይህ ግጭት የተነሳው ጉዳት የደርሰበትን አርሶ አደር ይዘው ወደ አምቡላንስ በመሄድ ላይ ሳሉ ነበር፡፡”

የወረዳው አስተዳደር ያወጣው መግለጫ ”በወረዳችን የተፈፀመው ድርጊት ሰብዓዊነት የጎደለው በመሆኑ በጥብቅ እናወግዛለን፡፡” በማለት ይጀምራል፡፡

”ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ.ም የገበያን ቀን ጠብቆ የፀረ ሰላም ኃይሉ በማሳቸው በነበሩ አርሶ አደሮች ላይ ጥቃት እና ግዲያ በመፈፀሙ ምክንያት የቡርጂን ባሕል እና ዕሴት በፍጹም በማይወክል አግባብ የሰላም መኖር የሚያንገሸግሻቸው ጥቂት ቡድኖች በገበያተኞች ላይ አሰቃቂ ግዲያ እና ጉዳት አድርሷል፡፡” ሲል ወንጅሏል፡፡

የቡርጂ ወረዳ አስተዳዳሪ ማሬ አለማየሁ ለአሻም እንደገለፁላት ”ድርጊቱ በሁለቱ ብሔረሰቦች መካከል የተከሰተ አይደለም”፡፡

አክለውም ”በዚህ አረመኒያዊ” ሲል በጠሩት” ተግባር ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ለህግ ለማቅረብ መንግስት ጠንካራ” ያሉትን ” አቋም ይዞ እየሰራ ይገኛል፡፡ ”

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
በመዲናዋ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ ተሸከርካሪዎች የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሊደረግ ነው!

በመዲናዋ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሊደረግ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስና ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች አዲስ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ነገ እለተ ማክሰኞ ከቀኑ 8፡30 ላይ ለሚዲያ ተቋማት ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

የታሪፍ ማሻሻያው ከሰኔ 01 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን አፈፃፀሙ በተገቢው እንዲከወን የህግ አስከባሪ አካላት ሚና የጎላ በመሆኑ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ቢሮው አሳስቧል፡፡

ህብረተሰቡም የሚወጣውን ትክክለኛ ታሪፍ አውቆ በመክፈልና ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎችን በማጋለጥ በኩል ጥቆማ በመስጠት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ቢሮው መልዕክት አስተላልፏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
977 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ!

በዛሬው ዕለት በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 977 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ከእነዚህ ውስጥ ስድስት ህጻናትና 971 ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ 33 ሺህ 298 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በቡርጂ ወረዳ ተነስቷል በተባለ ግጭት 9 ሰዎች ሲሞቱ 17ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን አስተዳደሩ ተናገረ፡፡ በደቡብ ክልል በቡርጂ ወረዳ ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ.ም አንድ አርሶ አደር ከጉጂ የተነሱ ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች ጥቃት መድረሱን ተከትሎ በተነሳ ግጭት የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 17 ሰዎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የአካባቢው ነዋሪና የወረዳው አስተዳደር ለአሻም ተናግረዋል፡፡ አሻም…
በደቡብ ክልል ቡርጂ ልዩ ወረዳ ከተነሳው ግጭት እና ሞት ጋር በተያያዘ 10 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል፡፡

የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አለማየሁ ማሞ የሶማያ ከተማ ህዝብ በተፈጸመው አጸያፊ ድርጊት ተቆጥቷል ብለዋል፡፡

ይህንን ተከትሎም የአከባቢው ነዋሪዎች ለተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽነር አለማየሁ በግጭቱ የተጠረጠሩ ከ10 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡

በአከባቢው በሚፈጠሩ ግጭቶች ፤አብዛኛው ተሳታፊ ወጣት በመሆኑ፤ይህን ወጣት ወደ ጥፋት እንዳይነዳ ፤ውይይት ከማድረግ አኳያ ክልሉ ምን እየሰራ ነው ስንል ለጠየቅናቸው ጥያቄ ኮሚሽነር አለማየ ማሞ፣ ጥረቶች እንዳሉ እና ክልሉም ሆነ የፌደራሉ መንግስት ለአከባቢው ወጣቶች ትኩረት እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡

የአከባቢው ነዋሪዎች ቦታው አዋሳኝ ድንበር እና ስጋት ያለበት በመሆኑ መንግስት አስፈላጊውን ሃይል በቦታው ቢያሰፍር መልካም ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ 19 ሰዎች ተገደሉ!

በቤኒሻንጉል ክልል፣ በካማሺ ዞን በምትገኘው ምዥጋ ወረዳ በክልሉ ልዩ ኃይሎችና በታጣቂዎች መካከል በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ ሳቢያ 19 ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ የፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ሀሩን ኡመር ለቢቢሲ ገለጹ።ባለፈው ሳምንት ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ. ም. የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ታጣቂዎች ጥቃት ሰንዝረው፣ በምላሹ ከልዩ ኃይል ጋር በተደረገው የተኩስ ልውውጥ የምዥጋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ መሞታቸውንም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

ከዋና አስተዳዳሪው ውጪ የሞቱት ሰዎች ተኩስ የከፈተው የታጣቂው ቡድን አባላት እንደሆኑም አቶ ሀሩን ገልጸዋል።ጥቃቱ በክልሉ በልዩ ኃይል አባላት ላይ መከፈቱን የተናገሩት ኮሚሽነሩ፣ በተደረገው የተኩስ ልውውጥም በርካታ የታጣቂው ቡድን አባላት መገደላቸውን አመልክተዋል።በክስተቱ ከልዩ ኃይሉ የሞተ የለም ያሉት ኮሚሽነሩ “ታጣቂዎቹ የሚጠቀሙበት መሣሪያ” በቤታቸው የተገኘ የተባሉ ባለሀብትም እንደሞቱ ተናግረዋል።

ግለሰቡ ቤት ውስጥ “ዲሽቃ ጥይቶች፣ 5 ክላሽና ሌላም በርካታ ታጣቂዎች የሚጠቀሙባቸው ሌሎች ነገሮች" መገኘታቸውን ኮሚሽነሩ ለቢቢሲ አስረድተዋል።በግለሰቡ ቤት የተገኘውን “ለታጣቂዎች የተዘጋጀ መሣሪያ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

የምዥጋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በአጋጣሚ በስፍራው እንደነበር የተናገሩት ኮሚሽነር ሀሩን በተኩስ ልውውጡ ሕይወታቸው እንዳለፈ አመልክተዋል።የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) በአካባቢው የሚንቀሳቀስ ታጣቂ ቡድን ሲሆን፣ ከክልሉ መንግሥት ጋር ዕርቅ ለመፈፀም ስምምነት ላይ ደርሰው እንደነበር ይታወሳል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የ"ፍትህ" መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተር እና ባለቤት ተመስገን ደሳለኝን ጉዳይ ለግንቦት 30 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ቤተሰቦቹ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል። መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪው ሁከት እና ብጥብጥ እንዲነሳ በዩትዩብ ንግግሮችን አድርጓል የሚለውን ቅድመ ክስ ሃሳቡ በማንሳት፣ በ"ፍትህ" መጽሄት ሁከት እና ብጥብጥ ቀስቅሷል በሚል ክስ እንዲቀየርለት ጠይቋል። ጠበቃም ችሎቱ አዲሱን ክስ ውድቅ አድርጎ ለተጠርጣሪው ዋስትና እንዲፈቅድ ጠይቀዋል። ችሎቱ ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠው፣ በአዲሱ ክስ እና በተጠርጣሪው ላይ ባለፈው ሳምንት በተፈጸመው ድብደባ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ነው።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በአንድ ግለሰብ ቤት የሞርታር ተተኳሽ ተደብቆ መገኘቱ ተገለጸ!

በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ልዩ ስሙ 02 ቀበሌ ጢሳ አባሊማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በግለሰብ መፀዳጃ ቤት ውስጥ 23 የሞርታር ተተኳሽ መገኘቱን የአምባሰል ወረዳ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።ተተኳሹ ከኀብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በተደረገ ፍተሻ መገኘቱንም ነው የገለጸው።

የተገኘው የሞርታር ተተኳሽ አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን ከአካባቢው ሽሽቶ ሲሄድ ጥሎት የሄደ ሊሆን እንደሚችል የሚገመት ሲሆን፥ ተተኳሹ የተገኘበት ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ መጠቆሙን ከአምባሰል ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa