YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በሀሰተኛ ማስረጃ የ276 ሚሊዮን ብር የግልግል ዳኝነት ያልተገባ ውሳኔ ሰጥተዋል ተብለው የተከሰሱት ሁለት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ።

በሀሰተኛ ማስረጃ የ276 ሚሊዮን ብር የግልግል ዳኝነት ያልተገባ ውሳኔ ሰጥተዋል ተብሎ በከባድ የሙስና ወንጀል የተከሰሱት ሁለት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችና ግብረአበሮቻቸው ላይ የዐቃቤ ህግን ማስረጃዎች መርምሮ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጧል።

ተለዋጭ ቀጠሮውን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ፀረ ሙስና ወንጀል ችሎት ነው።
ዐቃቤ ህግ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በነበሩት አዱኛ ነጋሲ߹ አክሊሉ ዘሪሁንና ግብረ አበሮቹ ላይ በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት ጄነራል ክስ መመስረቱ ይታወሳል ።

ዐቃቤ ህግ በሀሰተኛ ማስረጃ የ276 ሚሊዮን ብር የግልግል ዳኝነት ያልተገባ ውሳኔ ሰጥተዋል ብሎ በከባድ የሙስና ወንጀል የከሰሳቸው ሁለት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችና ግብረአበሮቻቸው ላይ አስር (10) የምስክሮችን ቃል ሲያሰማ ሌሎች ገላጭ ማስረጃዎችን ደግሞ ዛሬ ግንቦት 15/2014 ዓ.ም በፅ/ቤት እንዲደርሳቸው ተደርጓል ።

በዚህ የዐቃቤ ህግ ክስ ላይ እንደተመላከተው 1ኛ ተከሳሽ አዱኛ ነጋሲ ሲመለከት ነበር በተባለው 11ኛ የፍታብሔር የአፈጻጸም ችሎት በዳዊት ገ/እግዛብሔርና በቱፋ ጣፋ መካከል በስራ ግንኙነት ሳይከፈል የቀረ 276 ሚሊዮን ብር እና 9 ከመቶ ወለድ 250 ሺህ የግልግል ዳኝነት ክፍያ በጥቅምት 10 ቀን 2009 ዓ/ም የተከፈተ መስሎ በሀሰተኛ ሥም በተዘጋጀ ሀሰተኛ የግልግል ዳኝነት መዝገብ ለአንደኛ ተከሳሽ ጥቅም ለማስገኘት በማሰብ ከዐቃቤ ህግ 1ኛ ምስክር ጋር በ2ኛ ተከሳሽ አክሊሉ ዘሪሁን አደራዳሪነት በተለያዩ ቀናትና ቦታዎች በመገናኘት 3 ሚሊዮን ብር እና የ2 ሚሊዮን ብር ቼክ ከ4ኛ ተከሳሽ በመቀበል እንዲሁም ዐቃቤ ህግ ጓደኛቸው ነው ባለው እስከዳር አሰፋ በተባለ ግለሰብ የንግድ ባንክ ሒሳብ 400 ሺህ ብር ገቢ እንደተደረገላቸው ዐቃቤ ህግ በክሱ ላይ መጥቀሱ ይታወሳል ።

በተጨማሪም በአቶ ዳዊት ገ/እግዛብሔር ሥም በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ የነበረ 276 ሚሊዮን ብር “ቱሉ ጣፉ” ተብሎ በሀሰት ሥም በተከፈተ ቡና ባንክ እንዲገባ ያለአግባብ ትዕዛዝ ሰጥተዋል ተብሎ በዐቃቤ ህግ ክስ መመስረቱ ይታወሳል ።

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ፀረ ሙስና ወንጀል ችሎት ዐቃቤ ህግ በክሱ ላይ የጠቀሳቸው ገላጭ ማስረጃዎችን ለመጠባበቅ ደግሞ ለዛሬ ግንቦት 15/2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር በዚህም መሰረት ዐቃቤ ህግ በክሱ ላይ የጠቀሳቸውን ገላጭ የሰነድ ማስረጃዎች በፅ/ቤት ለተከሳሾች እንዲደርሳቸው ተደርጓል ።

ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች በቀረበባቸው ማስረጃዎች ላይ አስተያየታቸውን ከቀጠሮ በፊት እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሲሰጥ ዐቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ ያቀረባቸውን ማስረጃዎች መርምሮ ብይን ለመስጠት ደግሞ ለግንቦት 30/2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት የዕለቱ ችሎት ተጠናቋል ።

(ፍትህ ሚኒስቴር)
@YeneTube @FikerAssefa
ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ በዋስትና እንዲለቀቁ የቀረበውን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አደረገ!

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ዛሬ ተመልክቷል።የመርማሪ ቡድኑ ምርመራውን ባለማጠናቀቁ እና የተለያዩ ማስረጃዎችን ከባንክ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት፣ ከኢሳት እንዲሁም ከሌሎች ተቋማት የሚሰበስባቸው መረጃዎች በመኖራቸው ለ14 ቀናት ተጨማሪ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

የተከሳሽ ጠበቃ በበኩላቸው አስፈላጊ ናቸው የተባሉት መረጃዎች የሚሰበሰብባቸው ተቋማት የመንግስት ስለሆኑ እና ጊዜ የሚወስዱ ስላልሆኑ ተከሳሽ በውጭ ሆነው እንዲከራከሩ በዋስትና እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

ይሁን እንጂ የምርመራ ቡድኑ የጠበቃውን በዋስትና ይለቀቁልኝ ክርክር በመቃዎም ተከሳሹ ከእስር ቢለቀቁ የተለያዩ ማስረጃዎችን ያጠፉብናል፤ በዚህ ምክኒያት በእስር ሊቆዩ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።ፍርድ ቤቱ ክርክሩን ካደመጠ በኋላ ከተጠየቀው 14 ቀን የ10 ቀናት ብቻ ተጨማሪ ቀጠሮ በመስጠት ለሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ቀጥሯል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
የቤንዚን፣ ናፍጣ እና ኬሮሲን የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተባለ!

በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም የቤንዚን፣ ናፍጣ እና ኬሮሲን (ነጭ ጋዝ) የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በግንቦት ወር ሲሸጥበት በነበረው እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የተጠቀሱት ምርቶች መሸጫ ዋጋ በዓለም ገበያ ቢጨምርም መንግሥት የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥሉ ለማስቻል የምርቶቹ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ያለምንም ለውጥ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ነገር ግን የአውሮፕላን ነዳጅ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዓለም ዐቀፍ ዋጋ ተሰልቶ የመጣው ልዩነት ሙሉ በሙሉ ወደ ተጠቃሚው እንዲተላለፍ መወሰኑን ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ አመላክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
በመጪው የክረምት ወቅት ጎርፍና መሰል አደጋዎች ሊያስከትል የሚችል ከባድ ዝናብ ስለሚኖር የጎርፍ ተጋላጭ አካባቢዎች ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ።

ሰሞኑን የታየው ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች የመጣ መሆኑ ተጠቁሟል።በኢንስቲትዩቱ የአየር ሁኔታና የአየር ጠባይ ትንበያ ባለሙያው ታምሩ ከበደ እንደገለጹት፤በቀጣዩ ክረምት ወቅት ከመደበኛው በላይ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ትንበያዎች ያመለክታሉ።

የላሊና የአየር ጠባይ ለውጥ ሳቢያ በአገሪቱ በበልግም ሆነ በመኸር ወቅቶች ደረቅ ወራት በዝተው መስተዋላቸውን የገለጹት ባለሙያው ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀጣይ ሓምሌና ነሀሴ ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር ይችላል ብለዋል።በተለይም በአገሪቱ በሰሜን ምስራቅና በምስራቅ አካባቢዎች ላይ ዝናቡ እየጨመረ እንደሚሄድ ጠቁመዋል።

ሰሞኑን ተከስቶ የነበረው ከፍተኛ የሙቀት መጠን የላሊኖ ተፅእኖ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች ጋር ተያያዥ መሆኑን ለጎርፍ አደጋ ሥጋት እንደሚሆንም አብራርተዋል።

እንደ ባለሙያው ገለጻ፤ የጎርፍ አደጋ ሥጋት ያለባቸው አካባቢዎች ከወዲሁ አደጋዎች እንዳይፈጠር ኅብረተሰቡም ሆነ ተቋማት ከወዲሁ የመከላከል ሥራ ሊሰሩ ይገባልም ብለዋል።በተለይ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በሆኑ፣በወንዞችና ተዳፋታማ አካባቢዎች የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተጠናከረ የጥንቃቄ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በአገሪቱ የተከሰተው ላሊና የመኸርና በልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑትን የቦረና፣ባሌ ሶማሌና ደቡባዊ የአገሪቱ ክፍሎች በቂ ዝናብ እንዳያገኙ ምክንያት መሆኑንም አስታውሰዋል።የአደጋ ሥጋትና አመራር፣ ጤና ሚኒስትር፣ ግብርናና ሌሎች መሰል የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላሊኖ የሚፈጥረውን አደጋ ለመመከት ከወዲሁ አስፈላጊ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ከግንቦት ወር መጀመሪያ ጀምሮ የሙቀቱ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረው በከተሞች መስፋፋትና የውኃ አካላት መመናመን ምክንያት መሆኑንም ነው ያነሱት።ኅብረተሰቡም የተለያዩ ተክሎችን በመትከልና በመንከባከብ የአየር ንብረት ለውጥን የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖዎች መቋቋም እንደሚገባ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ባለሀብቶችን በማገት እና በማስፈራራት ብር በጠየቁ የሰራዊቱ አባላት ላይ ክስ ተመሠረተ!

ባለሀብቶችን በመሰለል፣ በማገት እና በማስፈራራት 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በጠየቁ እና በተቀበሉ አራት የመከላከያ ሚኒስቴር አባላት እና ግብረ-አበሮቻቸው ላይ ሥልጣንን አላግባብ በመገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ስር ክስ መመሥረቱን ፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ክሱ የተመሠረተው የመከላከያ መኪና በመያዝ “ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሀብት ማስመለስ የመጣን ዐቃቤ ሕጎች ነን፤ ሕገ-ወጥ ዘይት፣ ስኳር እና የጦር መሣርያ ስለምትሸጡ በወንጀል ትፈለጋላችሁ” በማለት 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በጠየቁ የመከላከያ ሚኒስቴር አባላት እና ግብረ-አበሮቻቸው ላይ ነው።

የተለያዩ የምርምራ ሂዶትችን ከፖሊስ ጋር ሲያከናውን ቆይቶ በግለሰቦች ላይ ክሱን የመሠረተው ደግሞ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል መሆኑ ተገልጿል።

ወንጀሉን ፈጽመዋል በሚል ክስ የተመሠረተባቸው በመከላከያ ሚኒስቴር በ93ኛ እና 94ኛ እግረኛ ክፍለ ጦር አባል የሆኑት 1ኛ) መቶ አለቃ ሀጂ ቱሉ߹ 2ኛ) ኦፊሰር መንግሥቱ በቀለ߹ 3ኛ) ሻምበል ካህሊ መላክ߹ 4ኛ) ሻለቃ ዱጉማ ዲምሳ እና በተለያዩ የንግድ ሥራዎች ውስጥ ተሰማርተው የሚገኙት ግብረ-አበሮቻቸው ከ5ኛ-8ኛ ስማቸው በክሱ የተጠቀሰው ተከሳሾች ሹምበዛ ፍቃዱ፣ አዲስ ዓለሙ፣ ተስፋዬ ለሚ እና አሸናፊ ወልደ ሰማያት መሆናቸውን ከፍትሕ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ችሎቱ በቁጥጥር ስር ያልዋሉትን 7ኛ እና 8ኛ ተከሳሽን ፖሊስ አፈላልጎ አንዲያቀርብ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን ተከሳሾች በተመሰረተባቸው ክስ ላይ የመጀመርያ የክስ መቃወሚያና ባልተያዙ ተከሳሾች ላይ የፖሊስን ምላሽ ለመጠባበቅ ለግንቦት 29/2014 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዛሬ በሮሃ ሜዲያ የየትዩብ ብዙኀን መገናኛ አዘጋጅ መዓዛ ሞሐመድ የ7 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንደፈቀደ ሮሃ ሜዲያ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ገልጧል።

መርማሪ ፖሊስ መዓዛን "ሁከት እና ብጥብጥ በማስነሳት" ወንጀል እንደጠረጠራት ካስረዳ በኋላ፣ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ችሎቱን ጠይቋል። የተጠርጣሪዋ ጠበቆች በበኩላቸው፣ ተጠርጣሪዋ ከጋዜጠኝነት ሥራዋ ውጭ የሰራችው ወንጀል እንደሌለ በመጥቀስ ጉዳዩ በመገናኛ ብዙኀን አዋጁ መታየት አለበት ሲሉ ተከራክረዋል። ችሎቱ ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠው በሁለቱ ወገኖች ክርክር ላይ ውሳኔ ለመስጠት ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
1ሺህ 76 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ!

ዛሬ ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1ሺህ 76 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።ከእነዚህ ውስጥ ሶስት ህጻናትና 1073 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ 30 ሺህ 198 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተመላክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል መንግሥት የኤርትራ ሠራዊት ትናንት እና ከትናንት ወዲያ የሽራሮ ከተማን በከባድ ጦር መሳሪያ ደብድቧል ሲል ዛሬ ማምሻውን በኮምንኬሽን ቢሮው በኩል ባወጣው መግለጫ ከሷል።

የክልሉ መንግሥት መግለጫ በሽራሮው የከባድ መሳሪያ ድብደባው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል ብሏል።

የክልሉ መንግሥት መግለጫ ባለፉት ሁለት ቀናት የኤርትራ ጦር በሽራሮ በኩል ጥቃት የከፈተው፣ ባለፈው ግንቦት 16 በምዕራብ ትግራይ ዓዲ አውዓላ አካባቢ የከፈተው ጥቃት የትግራይ ኃይሎች በወሰዱት አጸፋ ከሽፎ ጦሩ ክፉኛ በመመታቱ ነው ብሏል። የትግራይ ኃይሎች በውጊያው አንድ የኤርትራ ጦር ብርጌድ አዛዥ እና ሦስት የሻለቃ አዛዦች የሚገኙባቸው 120 ወታደሮችን ገድለው 195 ያህሉን እንዳቆሰሉ እና አራት ወታደሮችን እንደማረኩ ገልጧል። አንድ ድሽቃ፣ አምስት የወታደራዊ ሬዲዮ መገናኛዎች እና በርካታ የጦር መሳሪያዎች ከኤርትራ ጦር እንደተማረከም መግለጫው ጨምሮ አውስቷል።

የክልሉ መንግሥት በዚሁ መግለጫው፣ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ የኤርትራን መንግሥት ድርጊት በቃ ለማለት እጅጉን ቢረፍድበትም፣ ፈጽሞ ግን አልመሸበትም በማለት መግለጫውን ቋጭቷል።

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
በደሴ በተከሰተ የእሳት አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ!

በደሴ ከተማ አስተዳደር በተለምዶ አራዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በድርጅትና መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የተከሰተ የእሳት አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ፖሊስ ገለጸ፡፡የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ የአንደኛ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ጥላሁን ፈንታው ለኢዜአ እንደገለጹት ፥ ከለሊቱ 6 ሰዓት ገደማ የተቀሰቀሰውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ርብርብ ሲያደርጉ በነበሩ ሰዎች ላይም ጉዳት አስከትሏል።

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በሰዓቱ ወደ ህክምና ተቋም ሄደው እርዳታ እንዲያገኙ እንደተደረገም ተናግረዋል።“የእሳት አደጋው የተነሳበት አካባቢ አሮጌ እቃዎች የሚከማቹበትና ያረጁ ቤቶች ያሉበት በመሆኑ በቀላሉ ለማጥፋት ፈታኝ ቢሆንም በህብረተሰቡ ርብርብ እሳቱ ሳይስፋፋ መቆጣጠር ተችሏል” ብለዋል፡፡የእሳት አደጋ ማጥፊያ ተሸከርካሪ ከኮምቦልቻ ከተማ ጭምር መጥቶ ለማጥፋት ርብርብ መደረጉን ጠቁመው ፥ በቅንጅት አደጋው የከፋ ጉዳት ሳያስከትል በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።የአደጋው መንስኤ፣ የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት፣ የተቃጠሉ ቤቶችና ሌሎችንም የሚያጣራ ቡድን ወደ ቦታው ተልኮ ስራ መጀመሩን ኃላፊው ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት፤ የህወሃት እና የኤርትራ ግጭት ወደ ኢትዮ- ኤርትራ ግጭት እንደማያመራ ገለጸ!

የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ቅዳሜ እና ዕሁድ ዕለት የኤርትራ ሠራዊት በሽራሮ በኩል ጥቃት ከፍቶ እንደነበር ቢገልጹም የኢትዮጵያ መንግስት ግን ቀድሞ ትንኮሳ ያደረገው ህወሃት እንደሆነና በዚህም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ብሏል፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ለአል ዐይን አማርኛ እንደተናገሩት ህወሃት የኤርትራ ጦር ጥቃት ከፈተ በሚል የሚያሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም፡፡

በአሸባሪነት የተፈረጀው ህወሃት ኤርትራን እየተነኮስ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት ገልጿል፡፡

የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ቅዳሜ እና ዕሁድ ዕለት የኤርትራ ሠራዊት በሽራሮ በኩል ጥቃት ከፍቶ እንደነበር ቢገልጹም የኢትዮጵያ መንግስት ግን ቀድሞ ትንኮሳ ያደረገው ህወሃት እንደሆነና በዚህም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ብሏል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ:

https://am.al-ain.com/article/ethiopia-says-eriterea-tplf-clash-won-t-evolve-into-ethio-eriterea-conflict

@YeneTube @FikerAssefa
በሰበታ የተገነባው የኮካኮላ ፋብሪካ ተመረቀ!

ፋብሪካው የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የተመረቀው።ዛሬ በሰበታ ከተማ የተመረቀው ፋብሪካ ኮካኮላ ምርት ከሚያመርትባቸው ፋብሪካዎች 5ኛው ቅርንጫፍ መሆኑም ተገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በኢድ አል ፈጥር በዓል ላይ ከፈነዳው የአስለቃሽ ጭስ ቦንብ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር የዋለው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ ለአንድ ሳምንት በር ተዘግቶበት መታሰሩን ለፍርድ ቤት አስታወቀ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል የመከላከል አድማ ብተና አባል የሆነው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ ሶስተኛ ጊዜ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀረቦ ጉዳዩ ታይቷል።

መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት ከግንቦት 10 ቀን ጀምሮ በተሰጠው የ13 ቀን የምርመራ ጊዜ ውስጥ የሰራውን የምርመራ ስራ ሪፖርት ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።

በዚህም የተጠርጣሪው ቃል የመቀበል ስራ መሰራቱን ለተጠርጣሪው የገንዘብ ድጋፍ መኖርና አለመኖሩን ለማጣራት ለ18 ባንኮች ደብዳቤ መላኩን :የግል ስልኩ ላይ ለኤሌክትሮኒክስ ምርመራ እንዲደረግ ለብሔራዊ መረጃ ደህንነት ተቋም ደብዳቤ ልከው ውጤት እየተጠባበቁ መሆናቸውን እና የስልክ ቁጥር በማን ስም እንደወጣ ለማጣራት በኢትዮ ቴሌኮም በኩል እንዲጣራ መጠየቁን እንዲሁም የፈነዳውን አስለቃሽ ጭስ ቦንብ ፍንጣሪ በፎረንሲክ ምርመራ እንዲደረግ መላኩንና የምስክር ቃል መቀበሉን ለችሎቱ አስረድተዋል።

በፍርድ ቤቱ ዳኛ በኩል የስንት ምስክር ቃል እንደተቀበለ ለመርማሪ ፖሊስ ለቀረበ ጥያቄ የአንድ ሰው ምስክር ቃል ተቀብለናል የ3 ምስክር ቃል ይቀረናል በማለት ምላሽ ሰቷል።

ምስክሮቹ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከሆኑ አስካሁን ለምን አልተቀበላችሁም ለሚለው ጥያቄ ደግሞ አንደኛው ምስክር ለስራ ሌላ ቦታ በመሄዳቸውና ሌሎቹም ስራ ላይ በመሆናቸው ምክንያት መቀበል አለመቻሉን መርማሪ መልስ ሰቷል።

ተጠርጣሪው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ በበኩሉ ከሻንጣዬ ጀምሮ ብርበራ ተደርጎል ነገር ግን ምንም ማስረጃ አላገኙብኝም እኔ ምንም ወንጀል አልሰራሁም ከታሰርኩበት ጊዜ ጀምሮ ውሃ እንኳን የሚሰጠኝ ጠያቂ የለኝም አንድ ሳምንት በር ተዘግቶብኝ ታስሬ ነበር ሲል ለችሎቱ ገልጿል።

በአሁን ወቅት ያለበት የስር ሁኔታ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ በችሎቱ ዳኛ የተጠየቀው ኮንስታብል አንቡላ አሁን አ/አ ፖሊስ ከሌሎች እስረኞች ጋር እንዲሆን መደረጉን መልስ ሰቷል።

ፍርድ ቤቱ የፖሊስ የምርመራ መዝገብ አስቀርቦ ከተመለከተ በኋላ ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ ማስረጃ ማሰባሰቡን እንዲሁም የ3 ሰዎች ምስክር ቃል መቀበልና ቀሪ ማስረጃ መሰብሰብ እንደሚቀረው ማረጋገጡን ገልጿል።በዚህ መልኩ የጀመረውን ምርመራውን ፖሊስ አጠናቆ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ የ10 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል።የምርመራ ውጤቱን ለመጠባበቆ ለሰኔ 3 ቀን 2014 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

Via Tarik Adugna
@YeneTube @FikerAssefa
ሶስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ በአማራ ክልል አለ ያሉት “አፈና” እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ!

ሶስት ተቃዋሚ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአማራ ክልል እየተደረገ ነው ያሉት “መንግስታዊ አፈና” እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ። ፓርቲዎቹ በጋራ ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 23፤ 2014 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ሌላ ውድመት እንዳያደርስ የሰላም አማራጮች ሁሉ እንዲተገበሩም ጠይቀዋል።

የጋራ መግለጫውን የሰጡት እናት ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ናቸው። ሶስቱ ፓርቲዎች በአዲስ አበባ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የመኢአድ ዋና ጽህፈት ቤት የሰጡት መግለጫ ዋነኛ ትኩረቱ መንግስት ከሰሞኑ እያካሄደው የሚገኘው “የህግ ማስከበር ዘመቻ” ነው።

ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ጋዜጠኞች፣ ማህበረሰብ አንቂዎች፣ የፋኖ አባላት፣ ምሁራን፣ ተመላሽ የጸጥታ አባላት እና የፖለቲካ አመራር አባላት “በህግ ማስከበር ሰበብ ታፍነዋል” ሲሉ ወንጅለዋል። መንግስት የህግ ማስከበር ዘመቻውን “የማህበረሰቡን ቅስም ለመስበር፣ የኃይል ሚዛንን ለማስጠበቅ፣ መሪ ለማሳጣት እና በዚሁ አጋጣሚ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን፣ ምሁራንን፣ ጋዜጠኞችን፣ የማህበረሰብ አንቂዎችን ከመከላከያና ልዩ ኃይል ተመላሾችን ለማሳደድ እየተጠቀመበት ነው” ሲሉም ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ከስሰዋል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
ኦባሳንጆ በመቀሌ ከህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ጋር ተወያዩ!

የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ መቀሌ መሆናቸውን አስታወቁ፡፡ቃል አቀባዩ በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ የህወሓት ሊቀ መንበር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ኦባሳንጆን ተቀብለው ማነጋገራቸውን ገልጸዋል፡፡

“በቀጠናዊ ጉዳዮች” ላይ መምከራቸውንም ገልጸዋል ቃል አቀባዩ፡፡ ሆኖም ”ቀጣናዊ” የተባለው ጉዳይ ምን እንደሆነ አቶ ጌታቸው በግልጽ አላስቀመጡም፡፡ የተወያዩባቸው ተጨማሪ ጉዳዮች እንዳሉም አልገለጹም፡፡የቀድሞውን የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት የመቀሌ ጉዞ በተመለከተ የፌዴራል መንግስቱ የሰጠው መግለጫም ሆነ ያለው ነገር የለም፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
የአፋር ሕዝብ ፓርቲ መንግሥት በአፋር ክልል ለተከሰተው ሰብዓዊ ቀውስ ትኩረት እንዲሰጥ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

ፓርቲው ፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልል መንግሥት የሚያደርጉት የሥልጣን ሽኩቻ በአፋር ክልል ላይ አለመረጋጋት እና በሰላማዊ ነዋሪዎች ሞትና መፈናቀል አስከትሏል ሲል ወቅሷል። ፓርቲው በአፋር ሕዝብ ላይ ለደረሰው ሰቆቃ ፌደራል መንግሥት ተጠያቂ መሆኑንም አውስቷል። በክልሉ በአፍዴራ እና ጉየህ የተፈናቃዮች መጠለያ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ያስታወቀው ፓርቲው፣ በክልሉ ሰብዓዊ ዕርዳታን ያላግባብ ጥቅም ላይ እንደሚውል ገልጧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ምዕራብ ጎንደር ዞን 4ሺህ ይህል ተፈናቃዮች ተመለሱ!

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በነበሩ የፀጥታ ችግሮች ተፈናቅለው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው የነበሩ 4ሺህ ያህል የመተማና የአገር አድን ጨቆ ወረዳ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆናቸውን የአካባቢው አመራር ዐስታወቁ፣ ተፈናቃዮች በበኩላቸው ወደ ቦታቸው መመለሳቸው ቢያስደስታቸውም አስፈላጊ ቁሳቁሶች እንዳልተሟሉላቸው ይናገራሉ። የዞኑ መንግስት ግን ተመላሾችን ለማገዝ የተቻለው ሁሉ ጥረት ይደረጋል ብሏል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የመንግሥት ሠራተኞች በኪራይ የተሰጣቸውን ቤት የራሳቸው ለማድረግ የሚያስችላቸውን ውል እየፈጸሙ ነው!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2010 ዓ.ም. በኪራይ የጋራ መኖሪያ ቤት የሰጣቸው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች፣ የቤቱ ባለቤት ለመሆን የሚያስችላቸውን ውል ከከተማ አስተዳደሩ ጋር እየፈጸሙ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የመንግሥት ሠራተኞቹ በኪራይ የተሰጣቸውን ቤት በባለቤትነት የሚወስዱት የቤት ማስተላለፊያ ዋጋው ድጎማ ተደርጎበት ሲሆን ውል የሚፈጽሙበት ዋጋ የከተማ አስተዳደሩ አሁን ላይ አንድ ካሬ ሜትር ቤት ከሚያስተላልፍበት ዋጋ በ43.5 በመቶ የቀነሰ ነው፡፡በዚህ መሠረት በአማካይ ከፍተኛው የአንድ ቤት ሙሉ ክፍያ 180 ሺሕ ብር ሲሆን ትልቁ የቅድመ ክፍያ ዋጋ ደግሞ 20 ሺሕ ብር ነው፡፡

ይኼንን ቅድመ ክፍያ አሁን ላይ መክፈል የማይችሉ የመንግሥት ሠራተኞች አንድ ዓመት የእፎይታ ጊዜ እንደሚሰጣቸውና በሚገቡት ውል መሠረት ሙሉ ክፍያውን ለመፈጸም የ20 ዓመት ጊዜ እንደሚኖራቸው የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጋሻው ተፈራ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://www.ethiopianreporter.com/article/25676

@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል እየተወሰደ ያለው የሕግ ማስከበር ዘመቻ የጠላትን ቅስም የሰበረ ነው ተባለ!

በአማራ ክልል እየተወሰደ ያለው የሕግ ማስከበር ዘመቻ የጠላትን ቅስም የሰበረ መሆኑን የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ግዛቸው ሙሉነህ በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ እየሰጡ ነው።በመግለጫቸው የአማራ ክልል ሕግ የማስከበር ሥራ እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል።የውስጥ ስርዓት አልበኝነትን የማስቆም ሥራ የወገንን ኃይል ያጠናከረ የጠላትን ኃይል ቅስም የሰበረ ነው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

የሕግ ማስከበሩ ተግባር ሕገ-ወጥነትንና ስርዓት አልበኝነትን መልክ የማስያዝ ተግባር መሆኑንም ተናግረዋል።የሕግ ማስከበር ሥራው ለውጭ ጠላት ከሚደረገው ዝግጅት አንዱና ዋነኛው ተግባር እንደሆነም አስገንዝበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የስኳር ኮርፖሬሽን የስኳር ግዢ ሂደትን ባጠረ ጊዜ ማከናወን እቀጥላለሁ አለ!

የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የስኳር የግዥ ሂደትን በማሳጠር ምርት በቶሎ የሚገባበትን አሰራር እከተላለሁ አለ፡፡ኮርፖሬሽኑ በአገር ውስጥ ከሚያመርተው በተጨማሪ ስኳርን ከውጭ በማስገባት ገበያውን እንደሚሞላ ይታወቃል፡፡ሆኖም ላለፉት ወራት ተደጋጋሚ ጨረታ ቢያወጣም ስኳርን በተፈለገው ፍጥነት ገዝቶ ማስገባት አልቻለም፡፡ለዚህም የጨረታ ሂደት እና የውሳኔ መጓተት አይነተኛ ጫናዎች ነበሩ ሲሉ የዘርፉ አካላት ይገልፃሉ፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ የግዥ ሂደት የጨረታ ህግጋትን እንዲሁም ጨረታ ከተከፈተ በኋላ ያሉ የግምገማ ሂደቶች ቀናት እንዲወስዱ የሚያስገድዱ ህጎች ግዥ በወቅቱ እንዳይከናወን ጫና እንዳላቸው ገልፀው፡፡ ሆኖም በተለይ የጨረታ ሰነድ ግምገማ ባጠረ ጊዜ መከወን ይቻላል ለዚህም በቅርቡ ለመግዛት የሄድንበት መንገድ ጥሩ ማሳያ ነው ሲሉ ገልፀውታል፡፡ከሳምንታት በፊት ከመንግስት በወረደ ትእዛዝ ምርቱን በአጭር ጊዜ ለመግዛት የተኬደበት መንገድ ውጤታ ነበር ተብሏል፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
በመቀለ የሚገኘው ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል አገልግሎት መስጠት ማቆሙ ተነገረ!

በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ የሚገኘው ዋነኛው ሪፈራል ሆስፒታል በገጠመው የግብዓት ችግር ምክንያት ለታካሚዎች ይሰጥ የነበረውን አግልግሎት ማቋረጡን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ተናገሩ።ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በገጠመው የመድኃኒት አቅርቦት ችግር፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጥ እና በሌሎች ተደራራቢ ችግሮች ምክንያት ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን አገልግሎት መስጠት ማቆሙን የሆስፒታሉ ቴክኒካል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ክብሮም ገብረሥላሴ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ትግራይ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ የእርዳታ አቅርቦቶችን ጨምሮ መሠረታዊ አቅርቦቶች በመቋረጣቸው ምክንያት በክልሉ ውስጥ በርካታ ሰዎች በምግብና በህክምና አቅርቦት እጦት ምክንያት ለችግር መጋለጣቸውን ዓለም አቀፍ ተቋማት መግለጻቸው ይታወቃል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ:
https://bbc.in/3GSiUTL

@YeneTube @FikerAssefa