YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮለኔል ገመቹ አያና የታሰሩበትን ሁኔታ ቀርቦ እንዲያስረዳ ቢታዘዝም ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ቀረ!

የኦሮሚያ ፖሊስ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር የሆኑት ኮለኔል ገመቹ አያና የታሰሩበትን ሁኔታ ቀርቦ እንዲያስረዳ በጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት የታዘዘ ቢሆንም ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ቀረ።የኦሮሚያ ፖሊስ በሰበር ሰሚ ችሎቱ ቀርቦ የኮለኔል ገመቹን የእስራት ሁኔታ በጽሁፍና በአካል እንዲያብራራ ባሳለፍነው ሳምንት አርብ በነበረ የችሎት ቀጠሮ መታዘዙ ይታወሳል።

በትዕዛዙ መሰረት ዛሬ ረፋድ ላይ በነበረ በችሎቱ ቀጠሮ ጥሪ ቢደረግም ከኦሮሚያ ፖሊስ ማንም አካል ሳይቀርብ ቀርቷል።የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር የሆኑት ኮለኔል ገመቹ አያና በግንቦት 09 ቀን 2013 በስር ፍርድ ቤት ከተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ነጻ ከተባሉ በኋላ፤ በነጋታው ግንቦት 10 ቀን ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሲወጡ በኦሮሚያ ፖሊስ ተይዘው በገላን ፖሊስ ጣቢያ እና በወታደሪዊ ካንፕ እንዲሁም በአዋሽ መልካሳ በአንድ ጀነራል ዶሮ ዕርባታ ውስጥ ለ6 ወራት ታስረው እንደነበር እና ከስድስት ወር በኋላ ከህዳር 16 ጀምሮ ደግሞ በፌደራል ፖሊስ በእስራት ላይ መሆናቸውን ከዚህ በፊት ለፍርድ ቤት አስረድተው ነበር።

ኮለኔል ገመቹ አያና ነጻ በተባሉበት የሽብር ክስ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዓቃቢህግ ይግባኝ ጠይቆ የነበረ ሲሆን፤ ይግባኝ ሰሚ ችሎቱም ኮነሬል ገመቹ ታስረው በነበሩበት የእስራት ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙና አለመፈጸሙ ማረጋገጪያ ባልቀረበበት ሁኔታ ክርክር ማስቀጠል አይቻልም ሲል መዝገቡን መዝጋቱ ይታወሳል።

ይሁንና ዓቃቢህግ በድጋሚ ለሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ በጠየቀበት በዚህ መዝገብ፤ የኮነሬል ገመቹ አያና የእስር ሁኔታ ላይ ባሳለፈው አርብ ዕለት በነበረ ቀጠሮ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በኮነሬል ገመቹ አያና ላይ ምንም አይነት የተከፈተ የወንጀል ምርመራ መዝገብ እንደሌለው ምላሽ ሰጥቷል።

ሰበር ሰሚ ችሎቱም በኮነሬል ገመቹ የእስር ሁኔታ ላይ የኦሮሚያ ፖሊስ ቀርቦ እንዲያስረዳ ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም በዛሬው ቀጠሮ ሳይቀርብ መቅረቱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች።ጉዳዩን መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎቱ በይደር ቀጠሮ መያዙም ታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
መስከረም አበራ የአማራ ክልልን ከፌደራል መንግስት ለመነጠል ገንዘብ ተከፍሏት እየሰራች ነው ሲል ፖሊስ ገለፀ!

መስከረም አበራ ሚድያዎችን በመጠቀም ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ በማድረግ፣ የአማራ ክልልን ከፌደራል መንግስት ለመነጠል ገንዘብ ተከፍሏት በመስራት እንዲሁም በፋኖ እና በፌዴራል መንግስት መካከል እምነት እንዳይኖር አድርጋለች ሲል መርማሪ ፖሊስ ለችሎት አስረዳ።

መስከረም አበራ ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2014 ዓ.ም. በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ተኛ የጊዜ ቀጠሮ በዋለው የወንጀል ችሎት ከጠበቃዎቿ ጋር ቀርባለች።መርማሪ ፖሊስ የ14 ቀን ቀጠሮ የጠየቀ ሲሆን የመስከረም አበራ ጠበቃዎች ፖሊስ ተፈጸመ ያለው ወንጀል በመገናኛ ብዙሃን መደበኛው የጊዜ ቀጠሮ ሳይሰጥ ለዐቃቤ ሕግ ተመርቶ ክስ የሚመሰረትበት እንጂ የምርመራ ጊዜ የሚጠየቅበት ስርዓት የለም በማለት ተከራክረዋል።

በተጨማሪም ለተጨማሪ ጊዜ ያቀረባቸው ተባባሪ አባሪዎችን ለመያዝ ፣ የኤሌክትሮኒስ ማስረጃቸውን ምርመራ ለማከናወን እና ምስክሮችን ለማሰባሰብ የሚሉት ምክንያቶች ተፈፀመ ስለተባለው ወንጀል ማስረጃ እንደሌለ ያሳያል ብለዋል።መስከረም ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብታቸውን ተጠቅመው ስርዓቱን በመሞገታቸው ለማሸማቀቅ የቀረበ እስር እንጂ ለእስር የሚዳርግ ተግባር አልፈፀሙም ያሉት ጠበቆቿ የ7 ወር አራስ በመሆናቸው የዋስትና መብታቸው ይከበር ብለዋል።ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ለነገ ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠዋት 3፡30 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
በዛሬው ዕለት 1ሺህ 68 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ የመመለስ ስራ 1ሺህ 68 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ የተቻለ ሲሆን÷ ከእነዚህ ውስጥ አንድ ሕጻንና 1 ሺህ 67 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡እስካሁን በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ከ 26 ሺህ 868 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
#ፍልስፍና_ከዘርዓ_ያዕቆብ_እስከ_ሶቅራጥስ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

በአቴና ጎዳናዎች ላይ በባዶ እግሩ እየተጓዘ ከሰዎች ጋር መጨቃጨቅ የሚወድ አንድ ሰው አለ፤ “ምነው ቤት የለህምን? ስለምንስ እኛን ትጨቃጨቃለህ?” ቢሉት “ቤትማ አለኝ ከአስቀያሚዋ እና ነዝናዛዋ ሚስቴ ሽሽት ወደዚህ መጣሁ” ነበር መልሱ፤ ይህ ሰው ታላቁ ፈላስፋ ሶቅራጥስ ነው። የአቴና ሰዎች የሶቅራጥስን ስድብ እና ጭቅጭቅ አልችል ቢሉ፣ መርዝ አጠጥተው ገደሉት።

የእኛው ሀገር የባዶ እግር ፈላስፋ የሆነው ዘርዓ ያዕቆብንም በዙሪያው ያሉ ሰዎች ጠልተው አሳደዱት። እንደ ቀበሮም ዋሻ ምሶ ለብቻው ኖረ። ዋሻውንም በእሾህ እና በድንጋይ አጠረ፤ ድንገት እንኳ ሰው ቢመጣበት ማምለጫ እንዲሆነው በአጥሩ ላይ ቀዳዳን አበጀ።

ሶቅራጥስም፣ ዘርዓ ያዕቆብም የዘመናቸው ወፈፌዎች ነበሩ። እንኳን ሊጠየቁ፣ ሊታሰቡ እንኳ የከበዱ ጥያቄዎችን አንስተው መርምረዋል።

#ሶቅራጥስን_ያስገደለ_ዘርዓ_ያዕቆብንም_ከሀገር_ያሰደደ ፍልስፍና ምንድን ነው? እውቀት ምንድን ነው? ... እውነት ምንድነው? ... ፍትህ ምንድነው? የሕይወት ትርጉምስ ምንድን ነው? … እኛ ማን ነን? ... ከየት መጣን? ... ወዴትስ እንሄዳለን?... ስለምንስ እንኖራለን?...

#ፍልስፍና_ከዘርዓ_ያዕቆብ_እስከ_ሶቅራጥስ መጽሐፍ ጥያቄዎቻችን እየመለሰ መንገዱ በዚህ ነው ይለናልና ማሿችንን እንዳበራን ጥበብን ፍለጋ በጨለማ መሃል እንጓዝ...

#ፍልስፍና_ከዘርዓ_ያዕቆብ_እስከ_ሶቅራጥስ መጽሐፍ
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡
*
ቤተሰብ ይሁኑ
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/
Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun
ለቤትዎ ለቢሮዎ እንዲሁም ለድርጅትዎ ይተለያየ ውበት ያላቸውን የፍይበር ግላስ የአበባ መትከያ ከፈለጉ እኛ አለን የድርጅትዎን እርማም መትከያው ላይ እናትምሎታለን
👋👋እንዲሁም ይሄን አዋጭ ቢዝነስ
ለመጀመር ካሰቡ ሙሉ ስልጠና እንሰጣለን ይደውሉልን
https://tttttt.me/+xvCuMwxhK19kODg0
☝️☝️☝️Join our group
Phone number:0987414243
0913676664
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች ማኅበር መንግሥት ለመገናኛ ብዙኀን ችግሮች መፍትሄ እንዲሰጥ ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ደብዳቤ ማስገባቱን ዋዜማ ሬዲዮ ተረድቻለሁ ብላለች።

ማኅበሩ የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች ከቤታቸውና ከሥራ ገበታቸው በጸጥታ ኃይሎች መታፈናቸው እንዳሳሰበው ገልጦ፣ ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ከፍተኛ የሕግ ጥሰት ሰምተው እንዳልሰሙ መሆናቸው አሳዝኖኛል ብሏል።መንግሥት ጋዜጠኞችን በሕግ አግባብ ብቻ እንዲጠይቅ እና ጋዜጠኞችን ያፈኑ አካላትም ለሕግ እንዲቀርቡ ማኅበሩ ጠይቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት ለ200 ሺህ ሜትሪክ ቶን ስኳር ግዥ ላቀረበው ዓለማቀፍ ጥሪ አራት ስኳር አቅራቢ የውጭ ኩባንያዎች እንዳለፉ ካፒታል አስነብቧል።

ሌሎች ሁለቱ ኩባንያዎች ግን የፋይናንስ እና ቴክኒክ ሰነድ ባለማሟላታቸው ከስኳር አቅራቢዎች ዝርዝር ተሰርዘዋል። ለጨረታው ያቀረቡት ሰነድ ተገምግሞ ያለፉት፣ የሲንጋፖር፣ የብሪታንያ፣ የፈረንሳይ እና የአሜሪካ ኩባንያዎች ናቸው። በዘርፉ አዲስ እንደሆነ የተነገረለት የአሜሪካው ኩባንያ ከሁሉም ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ሲሆን፣ ስኳሩን ከብራዚል እንደሚገዛ ገልጧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በዋግኸምራ አበርገሌ ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ህፃናት እየሞቱ ነው ተባለ!

በአማራ ክልል ዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ ለጊዜው ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ የህፃናት ህይወት እያለፈ ነው ሲል የብሔረሰብ አስተዳደሩ አስታወቀ። ስለጉዳዩ የተጠየቁት የአማራ ክልል ጤና ቢሮና የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቱት አንዱ ሌላውን ይመለከተዋል የሚል ምላሽ ሰትተዋል፡፡የአበርገሌ ወረዳ በህወሓት ቁጥጥር ስር ከሚገኙ የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አንዱ ሲሆን የተወሰነው የወረዳው ህዝብ ተፈናቅሎ በሰቆጣ አካባቢ ሲኖር ቀሪው ደግሞ ቀየውን ሳይለቅ በዛው እንደሚኖር የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አመልክቷል፡፡

ተፈናቅለው በሰቆጣ ከተማ የሚገኙት የአበርገሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓለሙ ክፍሌ ከአካባቢው በተለያዩ መንገዶች ሪፖርት እንደሚደርሳቸው ጠቁመው ከግንቦት 7/2014 ዓም ጀምሮ ምንነቱ በውል ያልታወቀ በሽታ ተከስቶ 9 ህፃናትን እገሏል፣ በሽታው አሁንም እየተስፋፋ ነው ብለዋል፡፡አበርገሌ ወረዳ በህወሓት ቁጥጥር ስር ቢሆንም እንደሌሎቹ አካባቢዎች ምግብና መድኃኒት እየቀረበለት ባለመሆኑ በበሽታና በርሀብ ሰዎች ህይወታቸው እያለፈ እንደሆነ የብሔረሰብ አስተዳደሩ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ከፍያለው ደባሽ ተናግረዋል፡፡

የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ኪዳት አየለ ወደ ወረዳው ባለሙያ መላክ አስቸጋሪ መሆኑን ጠቁመው በወረዳው እየተፈጠሩ ያሉ የጤና ችግሮች መፍትሔ እንዲያገኙ የሚመለከታቸው አካላት እንዲያውቁትና መፍትሔ እንዲፈለግ ለክልሉ ጤና ቢሮ ደብዳቤ መፃፋቸውን ለዶቼ ቬሌ አስረድተዋል፡፡

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ስቡህ ገበያው በበኩላቸው ዓለም አቀፍ የጤና ባለሙያዎች ወደ ቦታው ተንቀሳቅሰው በሽታውን የሚቆጣጠሩበት መንገድ እንዲፈለግ ለክልሉ ጤና ቢሮ በደብዳቤ እንደተገለፀለት ገልጠዋል።የሚመለከታቸው አካላት ተረባርበው ዓለም አቀፍ የጤና ድርጅቶች ወደ ቦታው የሚደርሱበት ሁኔታ ሳይውል ሳያድር እንዲደርሱ ያሳሰቡት የብሔረሰብ አስተዳደሩ ኃላፊዎች ያ ካልሆነ ግን ከፍተኛ የጤና ቀውስ ሊደርስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡

ስለጉዳዩ የተጠየቁት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊና የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጉዳዩ አንዱ ሌላውን እንደሚመለከት ምላሽ በመስጠታቸው በክልሉ በኩል ተከስቷል በተባለው በሽታ ዙሪያ እየተደረገ ያለውን ተጨባጭ እንቅስቃሴ ማካተት አልተቻለም፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
#ሉባር መጽሐፍ
ሁለተኛው ዕትም በገበያ ላይ

ሊከድኑት የሚሳሱለት ተወዳጁ ሉባር መጽሐፍ ለሁለተኛ ጊዜ ታትሞ በገበያ ላይ ዋለ።

ድርሰቱ ከጎንደር ፋሲለደስ እስከ ዘጌ ጊዮርጊስ፤ ከዘጌ ጊዮርጊስ እስከ ዳጋ እስጢፋኖስ፤ ከዳጋ እስጢፋኖስ እስከ ጣና ቂርቆስ፤ ከጣና ቂርቆስ እስከ ዲማ ጊዮርጊስ የተዘረጋ መሳጭ ታሪክ፡፡

ታሪክን- ከወቅታዊ ክስተት፣ ፍልስፍናን- ከነባራዊ ሁነት፣ እውቀትን - ከጥበብ፣ ስልጣኔን - ከባህልና ወግ ጋር አግባብቶና አጣጥሞ በፍቅር ቅኝት ሞሽሮና ገምዶ የያዘ መጽሐፍ፤

እንደ ስሙ ቅዱስና ከፍ ያለ የሀሳብ ልዕልናን የተጎናፀፈ መጽሐፍ ነው። ቢያነቡት በርካታ ህይወት ቀያሪ ተሞክሮዎችን ከተሟላ እርካታ ጋር ያገኙበታል።

#ሉባር
#ለትውልድና_ለሀገር

“ደራሲው በቁጭት የሀገራችንን የከፍታ ዘመን እያነሳ ወደ ኋላቀርነትና ድኅነት የተንደረደርንባቸውን ምክንያቶች እየጠቀሰ፣ ከችግሮች የምንላቀቅባቸውን መንገዶች በዝርዝር ያስረዳል፡፡ ቢያነቡት አስተማሪ ተሞክሮዎችንና በርካታ ጭብጦችን ያገኙበታል።”
ዶ/ር ሞገስ ሚካኤል
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ የዐባይ የቋንቋና የባህል ጥናት ተቋም ኃላፊ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/
Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun
👉 ለጤናው ቅድሚያ እንሰጣለን


መሪጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን
በተሰጠንና ባገኘነው ልምድና ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሔወችን እንሰጣለን።፦

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም

👉 የኪንታሮት መድኀኒት በሚቀባ ታማሚው
ወደቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላሳይነካ
ሳያቆስል ስራ ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛ እንዳይተካ አድርጎ የፈውሳል።
👉 የእሪህ መድአኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉 ገብያ ለገረገረው ለገብያ
👉 ለመፍትሔ ስራይ
👉 ለአይነ ጥላ (ለገርጋሪ)
👉 ለስንፈተ ወሲቢ ለሚቸኩልበት
👉 የአስም (የሳይነስ)
👉 ለማይስማሙ (ለመስተፋቅር)
👉 ገንዘብ ለሚበተንበት
👉 ስራ አልሳካለት ላለ
👉 ለቡዳ
👉 ለሚጥል በሽታ
👉 ለማህጸን እንፌክሽን
👉 ህይወቱ ለሚመሰቃቀልበት
👉 ለአዕምሮ ጭንቀት
👉 ሌሊት ለሚሸና
👉 ለነገረ በትን
👉 ለሆድ ሀህመም
👉 ለስኳር መቀነሻ
👉 ለነርብ
👉 እራሱን ለሚያመው

እነዚህንና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን

መዳኒቱን ባሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል

በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዪ ክፍያ ይፈጽማሉ

አድራሻ
ባህርዳር ቀበሌ 11
ዲያስፖራ በኮብሉ

ለበለጠ መረጃ
☎️ 0917040506
📞 0912718883

ይደውሉ👍

መፍትሔ ሥራይ ወአይነ ጥላ ለጤናወ
መፍትሔ ከመሪጌታ ጥበቡ
የሚፈልጉትን ለማግኔት ይሄን ቻናል ይቀላቀሉ
🩺
https://tttttt.me/meritibe
https://tttttt.me/meritibe👇
👇
ኢትዮጵያ በመጪው ሐምሌ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ልትጀምር ነው!

ከአሥር ዓመት በፊት ውል የተፈጸመበትና ለዓመታት የዘገየው የኢትዮጵያና የኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ፣ በመጪው ሐምሌ 2014 ዓ.ም. እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡የስምምነቱ ተግባራዊነት መዘግየት ተከትሎ በተነሱ ጉዳዮች ላይ የሁለቱ አገሮች ስምምነት ክለሳ የተደረገበት ሲሆን፣ ኬንያ መጀመርያ ውል የገባችበት የሽያጭ ዋጋ እንዲቀነስላት ያቀረበችውን ጥያቄ በተመለከተ ግን፣ እስካሁን ስምምነት ላይ አልተደረሰም፡፡በሁለቱም አገሮች በኩል ለኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታና ለሌሎች ሥራዎች 1.3 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ፣ የስምምነት ክለሳ ተደርጎበት የመጨረሻ ፊርማ ለማኖር በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. ቀጠሮ እንደተያዘለት ታውቋል፡፡

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
የውጭ የሞባይል ገንዘብ ኦፕሬተሮች ወይም የዲጂታል ፋይናንሺያል አገልግሎት ሰጪዎች የባንክ አዋጁ ማሻሻያ ከመደረጉ በፊትም ቢሆን በኢትዮጵያ እንዲሰሩ ይፈቀድላቸዋል ተባለ።

የዲጂታል ክፍያ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በመዘጋጀት ላይ ሲሆን አዋጁ ሲጠናቀቅ የውጭ ባለሀብቶች የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት እንዲሰጡ ያስችላቸዋል።የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ /ዶር / የባንክ አዋጁን ማሻሻል እና የሞባይል ገንዘብ ኦፕሬተሮችን መፍቀድ የተለያዩ መሆናቸውን ገለፀው የውጭ የሞባይል ገንዘብ ኦፕሬተሮች ሀገር ውስጥ እንዲሠሩ የሚፈቅደው ህግ ለብቻ አንደሚሠራ ጠቁመዋል።በዚህም የውጭ የዲጂታል ፋይናንሺያል አገልግሎት ሰጪዎች ነባሩ የፋይናንሻል አዋጁ ከመሻሻሉ በፊትም ሊፈቀድ እንደሚችል ተናግረዋል።

አሁን በሥራ ላይ ባለው የባንክ አዋጅ መሠረት የዲጂታል ፋይናንሺያል አገልግሎት ተቋማት ማለትም ክፍያ፣ ሬሚታንስ እና ኢንሹራንስን በዲጂታል አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን የውጭ ባለሀብቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መያዝ አይችሉም።ባለፈው አመት የቴሌኮም ጨረታ አሸንፎ የገባው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኬንያ በሰፊው አገልግሎት የሚሰጠውን ኤም-ፔሳን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ዝግጅት ላይ መሆኑን ሲገልፅ ቆይቷል።እየተዘጋጀ ያለው ህግ ሲፀድቅ ኤም-ፔሳን ጨምሮ ሌሎች የውጭ ሀገር የፊንቴክ ኩባንያዎች እንዲሰሩ ይፈቀድላቸዋል ብለዋል ገዢው።

መንግስት የባንክ ኢንዱስትሪውን ለውጭ ውድድር ለመክፈት ዝግጅት ላይ መሆኑ ሚታወስ ነው። ለዚህም ይረዳ ዘንድ የፋይናንሻል ህጉን ለማሻሻል ኮሚቴ አዋቅሮ እየሠራ እንደሚገኝ ገዢው ገልጸዋል።"ዘርፉን መከፈቱ ኢኮኖሚውን እና የሀገር ውስጥ ባንኮችን በይበልጥ ተጠቃሚ ያደርጋል፣ ብዙ ኢንቨስትመንት ያስፈልገናል ኢንቨስትመንቱን ያሳድጋል" ሲሉ ዶር ይናገር ይገልፃሉ።አሁን ላይ ብዙ የአፍሪካ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለመግባት ፍላጎት እያሳዩ መሆኑን እና መከፈቱ የሚካሄደው ሁሉን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ የሀገር ውስጥ ባንኮችን እና ኢኮኖሚውን ሳይጎዳ እንደሚሆን ገዢው አክለዋል።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የሚገኙ የሲሚንቶ አምራች ድርጅቶች ከማምረት አቅማቸው 60 በመቶ ብቻ እያመረቱ መሆኑ ተነገረ!

በኢትዮጵያ ከሚገኙ ሲሚንቶ አምራች ድርጅቶች መካከል ከዳንጎቴ የሲሚኒቶ ፋብሪካ ውጪ ሁሉም የሲሚንቶ አምራቾች ከማምረት አቅማቸዉ ከ60 በመቶ በታች እያመረቱ ስለመሆኑ በማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የማዕድን ልማት ኢንስቲዩት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ጉታ ለገሰ ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰአት በሲሚንቶ ገበያው ላይ እየታየ ያለው የዋጋ መወደድ በተጨማሪ በአምራች ድርጅቶች ዘንድ ያለዉ የግብአት እጥረቶች በአቅርቦት ላይ ችግሩን መፍጠሩን አንስተዋል፡፡እንዲሁም ደግሞ ከሲሚኒቶ ፋብሪካዎች የሚወስዱ ነጋዴዎች ማትረፍ ከሚገባቸው 30 በመቶ በተጨማሪ ከአምርች ድርጅቶቹ በላይ እስከ 80 በመቶ ድረስ እያተርፉ መሆናቸውም ችግሩን እንድባባሰው ተናግረዋል::

በዚህም በኢትዮጲያ ውስጥ ያሉት የሲሚንቶ አምራች ድርጅቶች የማምረት አቅማቸው ከ60 በመቶ እንዳይበልጥ ምክንያት መሆኑን አክለዋል፡፡አምራች ድርጅቶች የሚያነሱትን የግብአት እጥረትን፣በተረካቢዎቹ በኩል ያለውን ክፍተት እንዲሁም ፖሊሲ ከማስተካከል ጀምሮ እጥረት የታየባቸውን ግብአት የሚቀርብባቸውን ሁኔታዎች የማመቻቸት ስራዎች እየተሰራ እንደሚገኝ ዶ/ር ጉቱ ጨምረው ተናግረዋል።

[ዳጉ ጆርናል/ብስራት ኤፍ ኤም]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የትላልቅ ሆቴል ባለቤቶች መቋቋሚያ ብድር ባለማግኘታቸው ሆቴላቸውን ለመሸጥ እንቅስቃሴ አያደረጉ ነው ተባለ።

በኮቪድ-19 አስከፊ ተጽእኖ የሆቴል ኢንዱስትሪውን ለመታደግ መንግሥት ለሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ብድር ለመስጠት በወሰነው መሠረት በአንድ አመት የሚመለስ 3.3 ቢሊዮን ብር በንግድ ባንኮች አማካኝነት አበድሮ ነበር።ሆኖም በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሁኔታዎች ባለመሻሻላቸው የአዲስ አበባ ሆቴል ባለንብረቶች የንግድ ዘርፍ ማኅበር የንግድ ባንኮች የብድር መክፈያ ጊዜያቸውን እንዲያራዝሙ ለብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ውሳኔ እንዲሰጥ ቢጠይቅም፣ ጥያቄ በአየር ላይ የቀረ ይመስላል።

የማህበሩ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ አስቴር ሰለሞን እንደገለፁት የመክፈያ ጊዜው 3 ወር ብቻ የቀረው ሲሆን ብዙ የሆቴሎች ባለቤቶች በደረሰባቸው ችግር ምክንያት ሆቴላቸውን ለመሸጥ እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል። በጎን በኩል ደግሞ ባንኮች ብድራቸውን ያልከፈሉ ሆቴሎችን በጨረታ የመሸጥ ሂደት እየጀመሩ ነው።

መንግሥት የወሰደው እርምጃ ዘርፉን በወቅቱ የታደገው ቢሆንም አሁን ላይ ግን የብድር ጊዜ ካልተራዘመ በስተቀር በሆቴሉ ላይ ያለው ሥጋት አሁንም ሊፈታ አይችልም ሲሉ ወ/ሮ አስቴር አስረድተዋል አክለውም አበዳሪዎች የሆቴሎችን ችግር ተረድተው የመክፈያ ጊዜውን ማራዘም ቢፈልጉም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ ውጭ ማድረግ አይችሉም በማለት አስረድተዋል።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
ኮለኔል ገመቹ አያና ከእስር እንዲለቀቁ ተወሰነ!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር የሆነት ኮለኔል ገመቹ አያና ከእስር እንዲለቀቁ የፌደራልጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ወሰነ።

ኮለኔል ገመቹ አያና በግንቦት 9 ቀን 2014 በተከሰሱበት በሽብር ወንጀል በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረሽብርና የህገመንግክት ጉዳዮች ወንጀል ችሎች በነጻ ከተሰናበተ በኋላ፤ በነጋታው  ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በር ላይ ሲወጡ በኦሮሚያ ፖሊስ ተይዘው ለ6 ወር በገላን ፓሊስ ጣቢያና በወታደራዊ ካንፕ እንዲሁም በአዋሽ መልካሳ በአንድ ጀነራል ዶሮ እርባታ ውስጥ ታሶሮ እንደነበርና ከህዳር 16 ጀምሮ ደግሞ በፌደራል ፖሊስ በእስር ላይ እንደነበሩ ለፍርድ ቤት አስረድተው ነበር።

በኮለኔል ገመቹ አያናን በአደራ ከመቀበል ውጪ ምንም የወንጀል  የምርመራ መዝገብ እኖዳልተከፈተበት የፌደራል ፖሊስ ቀርቦ ማብራሪያ መስጠቱን መዘገባችን ይታወሳል።

ሰበር ሰሚ ችሎቱ የኦሮሚያ ፖሊስ  ቀርቦ በኮለኔል ገመቹ የእስራት ሁኔታን እንዲያስረዳ ታዞ በትናንትናው የችሎት ቀጠሮ አለመቅረቡን ተከትሎ መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ችሎቱ ለዛሬ በይደር ቀጥሮ የነበረ ሲሆን፤ መርምሮ ኮለኔል ገመቹ አያና ከእስር እንዲፈቱ መወሰኑን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች።

@YeneTube @FikerAssefa
በወረባቦ ወረዳ በህግ ቁጥጥር ስር የነበረ ግለሰብን ለማስፈታት በተደረገ ሙከራ አራት ሰዎች ተገደሉ!

ቅዳሜ ግንቦት 13 በወረባቦ ወረዳ በተለምዶዉ 02 ቀበሌ በተባለዉ አካባቢ በህግ ቁጥጥር ስር የነበረን ግለሰብ ለማስፈታት በተደረገ ሙከራ አራት ሰዎች መገደላቸዉን የወረዳዉ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ መስዑድ መሀመድ በተለይ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

በሙከራዉ ሌሎች 11 ሰዎችም ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸዉ እና በደሴ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ሀላፊዉ አስረድተዋል። በእለቱ በቁጥጥር ስር የዋለው ግለሰብ ግጭት ለመቀስቀስ ባደረገዉ ሙከራ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ሀላፊዉ ተናግረዉ ግለሰቡን ለማስለቀቅም በግምት ከምሽቱ ሶስት ሰዓት በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ግለሰቦች እስረኛዉን ለማስመለጥ ሙከራ አድርገዋል ብለዋል።

ግለሰቡን ከፖሊስ ጣቢያ ለማስወጣት ከመጣዉ ሀይል ዉስጥ መሳሪያ የታጠቁም ነበሩ ያሉት ሀላፊዉ ሙከራዉን ያደረገዉ ሀይል ከከተማዋ አምስት ኪሎሜትር ርቆ ተሰባስቦ የነበረ ነዉ ብለዋል።

በፖሊስ አባላት እና በንብረት ላይ ጥቃት ለማድረስ የተደረገዉ ሙከራም ሳይሳካ መቅረትን ገልፀዋል። ወረባቦ ወረዳ በእለቱ ከነበረዉ አለመረጋጋት በኋላ ወደቀደመው እንቅስቃሴ መመለሷን አስታዉቀዋል።በሙከራው ተሳትፎ የነበራቸዉ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር የማዋሉ ስራ እየተከናወነ እንሚገኝ አቶ መስዑድ መሀመድ ጨምረው ተናግረዋል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
"ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ትደግማላቸሁ" በሚል የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

በ2014 የትምህርት ዘመን ማጠቃለያ ላይ ተማሪዎች ለትምህርታቸው ትኩረት ሰጥተው ማጠቃለያ ፈተናዎችን ለመውስድ እየተዘጋጁ ባለበት ወቅት፣ ማኅበራዊ ኃላፊነት በጎደላቸው አካላት ሆን ተብሎ ተማሪዎችን ለማዘናጋት በዘንድሮ ዓመት ከክፍል ወደ ክፍል መዘዋወር የለም ተብሎ በማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች የሚናፈሰው ወሬ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የወረደ አቅጣጫ የሌለ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ያሳወቀ ሲሆን የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተማሪዎች "ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ትደግማላቸሁ" በሚል አሉባልታ ሳይጠለፉ እና ሳይምታቱ ለትምህርታቸው ትኩረት ስጥተው ለተሻለ ውጤት እንዲተጉ እንዲያደርጉ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
#ፍልስፍና_ከዘርዓ_ያዕቆብ_እስከ_ሶቅራጥስ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

በአቴና ጎዳናዎች ላይ በባዶ እግሩ እየተጓዘ ከሰዎች ጋር መጨቃጨቅ የሚወድ አንድ ሰው አለ፤ “ምነው ቤት የለህምን? ስለምንስ እኛን ትጨቃጨቃለህ?” ቢሉት “ቤትማ አለኝ ከአስቀያሚዋ እና ነዝናዛዋ ሚስቴ ሽሽት ወደዚህ መጣሁ” ነበር መልሱ፤ ይህ ሰው ታላቁ ፈላስፋ ሶቅራጥስ ነው። የአቴና ሰዎች የሶቅራጥስን ስድብ እና ጭቅጭቅ አልችል ቢሉ፣ መርዝ አጠጥተው ገደሉት።

የእኛው ሀገር የባዶ እግር ፈላስፋ የሆነው ዘርዓ ያዕቆብንም በዙሪያው ያሉ ሰዎች ጠልተው አሳደዱት። እንደ ቀበሮም ዋሻ ምሶ ለብቻው ኖረ። ዋሻውንም በእሾህ እና በድንጋይ አጠረ፤ ድንገት እንኳ ሰው ቢመጣበት ማምለጫ እንዲሆነው በአጥሩ ላይ ቀዳዳን አበጀ።

ሶቅራጥስም፣ ዘርዓ ያዕቆብም የዘመናቸው ወፈፌዎች ነበሩ። እንኳን ሊጠየቁ፣ ሊታሰቡ እንኳ የከበዱ ጥያቄዎችን አንስተው መርምረዋል።

#ሶቅራጥስን_ያስገደለ_ዘርዓ_ያዕቆብንም_ከሀገር_ያሰደደ ፍልስፍና ምንድን ነው? እውቀት ምንድን ነው? ... እውነት ምንድነው? ... ፍትህ ምንድነው? የሕይወት ትርጉምስ ምንድን ነው? … እኛ ማን ነን? ... ከየት መጣን? ... ወዴትስ እንሄዳለን?... ስለምንስ እንኖራለን?...

#ፍልስፍና_ከዘርዓ_ያዕቆብ_እስከ_ሶቅራጥስ መጽሐፍ ጥያቄዎቻችን እየመለሰ መንገዱ በዚህ ነው ይለናልና ማሿችንን እንዳበራን ጥበብን ፍለጋ በጨለማ መሃል እንጓዝ...

#ፍልስፍና_ከዘርዓ_ያዕቆብ_እስከ_ሶቅራጥስ መጽሐፍ
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡
*
ቤተሰብ ይሁኑ
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/
Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun
Forwarded from YeneTube
ለቤትዎ ለቢሮዎ እንዲሁም ለድርጅትዎ ይተለያየ ውበት ያላቸውን የፍይበር ግላስ የአበባ መትከያ ከፈለጉ እኛ አለን የድርጅትዎን እርማም መትከያው ላይ እናትምሎታለን
👋👋እንዲሁም ይሄን አዋጭ ቢዝነስ
ለመጀመር ካሰቡ ሙሉ ስልጠና እንሰጣለን ይደውሉልን
https://tttttt.me/+xvCuMwxhK19kODg0
☝️☝️☝️Join our group
Phone number:0987414243
0913676664
በብሄራዊ ባንክ አግልግሎት እንዲያቆም ተደርጎ የነበረው ዓለም አቀፍ የሃዋላ አገልግሎት እና ድጋፍ ማሰባሰቢያ የሞባይል መተግበሪያ ካሽ ጎ አገልግሎቱን ዳግም መስጠት እንዲችል ውሳኔ ተላለፈ፡፡

የብሄራዊ ባንክ ከፍተኛ አመራሮች ካሽ ጎ በኢትዮጵያውን የተሰራ ከመሆኑ ጋር በተገናኘ እና ለሃገር የሚሰጠውን ፋይዳ ከግምት በማስገባት ዳግም ወደ አገልግሎቱ እንዲመለስ መወሰናቸውን ነው ምንጮች የተናገሩት፡፡
ከወራት በፊት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ካሽ ጎ አገልግሎት መስጠት እንዲያቆም ትዕዛዝ ማስተላለፉን ይታወሳል፡፡

በወቅቱም ብሄራዊ ባንክ አገልግሎቱን ሙሉ ለሙሉ ዘግቶ ይቆያል ማለት እንዳልሆነ እና ከስራው ባለቤቶች የሚደረጉ ንግግሮች ይኖራሉ ብሎ ነበር፡፡

ከብሄራዊ ባንክ ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋር በተደረጉ ተደጋጋሚ ውይይቶች ካሽ ጎ ለሀገር ያለው ፋይዳ እና እየሰጠ ያለው ጥቅም መተማመን ላይ በመደረሱ ዳግም ወደ ስራ እንዲገባ እና ተጥሎበት የቆየው እገዳ እንዲነሳለት ተደርጓል፡፡

ከአርብ ግንቦት 12 2014 ጀምሮም ሲሠጥ የነበረውን አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የካሽጎ ባለቤት አቶ ቴዎድሮስ ሽፈራው ገልፀዋል፡፡

ምንጭ - ናሁ ቴሌቪዥን
@Yenetube @Fikerassefa