ትራምፕ እና ልጆቻቸው ወደ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የኒውዮርክ ፍርድ ቤት መወሰኑ ተገልጿል፡፡
ትራምፕ እና ልጆቻቸው ኒውዮርክ ወደ ሚገኘው ፍርድ ቤት የሚቀርቡት ቃለ መኃላ በመፈጸም ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡የኒውዮርክ አቃቤ ህግ ዶናልድ ትራምፕ የሚያስተዳድሩትን ተቋም የግብር እና ብድር እፎይታ ለማግኘት በሚል " የሚያሳስት እና ያልተገባ የንብረት ግምገማ" በማድረግ አጭበርብረዋል ሲል መክሰሱ የሚታወቅ ነው፡፡
በዚህም ዶናልድ ትራምፕ በ21 ቀናት ውስጥ ወደ ፍርድቤት ቀርበው ቃለ መሃላ እንዲፈጽሙ የኒውዮርክ ፍርድ ቤት ዳኛ ውሳኔ አሳልፏል፡፡የዳኛውን ውሳኔ ተከትሎ የዶናልድ ትራምፕ ተቋም ለቢቢሲ በላከው ምላሽ "አሰራሩ በሙሉ የተባለሸ ነው" በማለት ለቀረበለት ክስ ያለውን ተቃወሞ ገልጿል፡፡
ይሁን እንጅ በትናንትናው እለት ዶናልድ ትራምፕ፣ ወንድ ልጃቸው ትራምፕ እና ሴት ልጃቸው ኢቫንካን የፍርድ ቤትን ትእዛዝ ሊያከብሩ እንደሚገባ የኒውዮርክ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ አርተር ኢንጎሮ ተናግሯል፡፡ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው የተጀመረው የፍርድ ሂደት ፖለቲካዊ ዓላማ ያነገበ የማይረባ ነው ሲሉ አጣጥለውታል፡፡
ትራምፕ የፍርድ ሂደቱን ቢያጣጥሉትም የፍርድ ቤት ትእዛዝ ያከብራሉ ወይስ አያከብሩም ለሚለው እስካሁን ግልጽ ያደረጉት ነገር የለም፡፡ጠበቆቻቸውም ቢሆኑ ዶናልድ ትራምብ በፍርድ ቤት ሂደት ባለ ጉዳይ ላይ ምንም አይነት አስተያየት ከመስጠት ቢቆጠቡ የሚል ምክር እያቀረቡላቸው ነው፡፡
Via Alain
@Yenetube @Fikerassefa

ዓለም ባንክ ለሶማሌ ክልል 64.3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መደበ!
ዓለም ባንክ በሶማሌ ክልል ለተከሰተው ድርቅ አስቸኳይ ምላሽ ለመስጠት የሚያግዝ 64.3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መመደቡን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ገለጹ።ከተመደበው ድጋፍ ውስጥ 38 ሚሊዮን ዶላሩ አሁን የሚሰጥ መሆኑን አቶ ሙስጠፌ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል። የዓለም ባንክ በዚህ ወሳኝ ጊዜ ድጋፉን በማድረጉም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa

62 ሰዎችን አሳፍሮ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ የእሳት ቃጠሎ አደጋ አጋጠመው!
ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ 62 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ አንድ አገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ የእሳት ቃጠሎ አደጋ እንዳጋጠመው በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።የእሳት ቃጠሎው የንብረት ውድመት ቢያደርስም በሰው ህይወት ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱ ተገልጿል።
በጽህፈት ቤቱ የመንገድ ደህንነትና ትራፊክ ክፍል ባለሙያ ዋና ሳጅን ወንድ ወሰን ጌታሁን እንደገለጹት የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት ኮድ3-99319 አውቶቡስ አደጋው ዛሬ ረፋድ ላይ ያጋጠመው በዞኑ ጅሌ ጥምጋ ወረዳ ጎዳ ቀበሌ ሲደርስ ነው።በደረሰው አደጋ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለመመዝገብ ተሳፍረው ይጓዙ የነበሩ ተማሪዎችን ሻንጣና ዶክመንት ጨምሮ የሌሎችን ተሳፋሪዎች ንብረትም ሙሉ በሙሉ ከአውቶቡሱ ጋር መውደሙንም ገልጸዋል።
አውቶብሱ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ያጋጠመው በሞተሩ ላይ በተከሰተ የቴክኒክ ችግር እንደሚሆን ጠቅሰው፤ የቃጠለውን መንስኤ ለማጣራት ሙሉ የምርመራ ሥራ መጀመሩን አስረድተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ተሽከርካሪው ከሽዋ ሮቢት ጀምሮ የጭስ ምልክት ያሳይ እንደነበርና አሽከርካሪው ፍሬን ሸራ ነው በሚል ሲያሽከረክር እንደነበር ከተሳፋሪዎች መረጃ መገኘቱንም አመልክተዋል።
በተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች በሌላ መኪና ወደ ደሴ መላካቸውን አመልክተው፤ አሽከርካሪውና ረዳቱ በቁጥጥር ሥር ውለው የማጣራት ሥራ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።

የሩሲያ ባሕር ኃይል ልዑክ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጠቅላይ መምሪያን ጎበኘ!
የሩሲያ ፌዴሬሽን ባሕር ኃይል ልዑክ የሁለቱን አገራት የዘለቀ ትብብር መነሻ በማድረግ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጠቅላይ መምሪያን ጎበኘ፡፡ሁለቱ ሀገራት ለረጅም አመታት የዘለቀ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ያላቸው ሲሆን፤ የጉብኝቱ ዓላማም የትብብሩ አንድ አካል መሆኑ ተመልክቷል፡፡
የልዑኩ መሪና በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌደሬሽን ተልዕኮ ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ኦስትሪ ኮቭ በጉብኝታቸው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል በመዋቅራዊ አደረጃጀቱ ይበልጥ እየዘመነ እንዲመጣና ኢትዮጵያዊያን የሚኮሩበት ጠንካራ ተቋም ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን መገንዘባቸውን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ጠንካራ ባሕር ኃይል ኢንዲኖራትና የመከላከል አቅሟን ይበልጥ ለመገንባት በምታደርገው ሁሉ ዐቀፍ እንቅስቃሴ ውስጥ በተለያዩ የሥልጠና መስኮች ላይ ሩሲያ ሚናዋን መጫወት ትችላለች ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሞዶር ዋላፃ ዋቻ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የዛሬ ሦስት ዓመት መቋቋሙን ገልፀው በተማረ የሰው ኃይል ለማደራጀት እየተሰራ ስለመሆኑ ለልዑካን ቡድኑ ገልፀዋል፡፡
"ከሌሎች አገራት የባሕር ኃይሎች አደረጃጀት እና ቀደም ሲል ከነበረ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ልምድ በመውሰድ፤ የተሰጠንን አገራዊ ተልዕኮ በአግባቡ ለመፈፀም የሚያስችል የተሟላ አደረጃጀት ተሰርቶና በመከላከያ ፀድቆ ወደ ሥራ ተገብቷል"ም ብለዋል፡፡
ኮሞዶሩ አያይዘውም ኢትዮጵያ ከባሕር ኃይሏ ማግኘት የምትችለውን ጥቅምና ግልጋሎት እንድታገኝ ከሩሲያ ፌደሬሽን ባሕር ኃይል ጋር በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰናል ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ አመላክቷል፡፡

በ6ኛው የአፍሪካ እና አውሮፓ ህብረት የጋራ ጉባኤ ኢትዮጵያ ያነሳቻቸው በርካታ ሀሳቦች ተቀባይነት ማግኘታቸውን በቤልጂየም፣ ሉክሰንበርግና በአውሮፓ ተቋማት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ገለጹ።
አምባሳደሯ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከጉባኤው ጎን ለጎን የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይቶችን ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ በጋራ ጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ ያነሳቻቸው የትብብርና የአጋርነት ሁኔታ፣ በሰላምና ጸጥታ ጉዳይ የአፍሪካ ድምጽ ስለሚሰማበት እንዲሁም የወቅቱን የአፍሪካ ህብረት መሪ ቃል የተመለከቱ ጉዳዮች ተቀባይነት እንዳገኙ ጠቁመዋል።የአፍሪካና የአውሮፓ ህብረት ግንኙነት በእኩልነትና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትብብር እንዲሆን ኢትዮጵያ ማንሳቷን ተናግረዋል።
ከዚህ ባለፈም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከተለያዩ አገሮች መሪዎች ጋር በነበራቸው የጎንዮሽ ውይይት÷ በኢትዮጵያና በአውሮፓ ህብረት መካከል ያለው ግንኙነት መጠናከር ስለሚኖርበት ሁኔታ ምክክር ተደርጓልም ነው ያሉት።በዚህም ለስድስት ወር የአውሮፓ ህብረት ሊቀመንበር ከነበረችው ስሎቬኒያ እና አሁን ሊቀመንበርነቱን ከተረከበችው ፈረንሳይ መሪዎች ጋር ጠቅላይ ሚኒስትሩ መወያየታቸውን አስታውሰዋል።
በጉባኤው የአፍሪካ ድምጽ በሰላምና ጸጥታ፣ ድህነትን በመዋጋት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመቀነስ፣ የታዳሽ ሃይል ልማትን በማጠናከር እንዲሁም በስደተኞች ጉዳይ የአህጉሩንና የኢትዮጵያን መብት ባስጠበቀ መልኩ ተነስቶ የጋራ መግባባት እንደተደረገበት አምባሳደሯ አስረድተዋል።
Via ENA

በድርቁ ምክንያት ከብቶቻቸውን እስከ 500 ብር ለመሸጥ እንደተገደዱ የቦረና አርብቶ አደሮች ተናገሩ!
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የከብቶች ዋጋ ከ5መቶ እስከ 3ሺህ ብር ማሽቆልቆሉ ተዘግቧል። ድርቁ በተከሰተባቸው በዞኑ 13 ወረዳዎች እና 2 የከተማ አስተዳደሮች የሚኖሩ አርብቶ አደሮች ለመገናኛ ብዙኃን እንደተናገሩት እስከ 40ሺህ ብር ይደርስ የነበረው የከብት ዋጋ 5መቶ ብር ድረስ ወርዷል።
የዝናብ እጥረቱን ተከትሎ የሞት አፋፍ ላይ የደረሱት ከብቶች ቁጥር ከ7 መቶ ሺህ በላይ ደርሷል። የዞኑ የእንስሳት ሃብት 6.8 ሚልዮን እንደሚደርስ መረጃዎች ያመለክታሉ።
የውሃ ሽፋኑ ከ53 በመቶ ወደ 28.6 በመቶ በደረሰበት የቦረና የተጎዱትን እንስሳት ለሽያጭ ያቀረቡት አርብቶ አደሮች ከብቶቹ ሲደክሙባቸው መንገድ ላይ ጥለዋቸው ለመሄድ እንደሚገደዱ የፋና ብሮድካስቲንግ ዘገባ ያሳያል።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዲጂታል ት/ቤት ስኩል ኦፍ ከላውድ .እ.ኤ. አ በ 01 FEB, 2022 መመረቁ ይታወሳል።
የስኩል ኦፍ ከላውድ የመጀመሪያው ማስተር ክላስ በ ሀብት ምጣኔ እና በስራ ፈጠራው የሚታወቀው የ አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ክላስ ሲሆን በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ ቢዝነስ እና ኢንተርፕነርሺፕ ማስተር ክላስ ዛሬ አርብ እ. ኤ. አ በ 18 FEB , 2022 ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት እንደሚለቀቅ አሳውቀዋል።
አሁኑኑ ይመዝገቡ www.schoolofcloud.com
ለበለጠ መረጃ፡፟
ስልክ ቁ፡ +251973045545
ኢሜል፡ Contact@schoolofcloud.com

በኢትዮጵያ ድርቅ የተከሰተባቸው አካባቢዎች ከሚያዚያ በፊት ዝናብ አያገኙም ተባለ!
በኢትዮጵያ ድርቅ የተከሰተባቸው አካባቢዎች ከሚያዚያ በፊት ዝናብ እንደማያገኙ የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡በኢትዮጵያ በሶማሊ፣ ኦሮሚያ እና ደቡብ ክልሎች ከፍተኛ የውሃ እጥረት ያጋጠማቸው ሲሆን እጥረቱ ከክልሎቹ አቅም በላይ በመሆኑ ድርቁ በሰው እና በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡
ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የቤት እንስሳት መሞታቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ባሳለፍነው ሳምንት ማሳወቁ ይታወሳል።
በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተው ድርቅ መነሻው ባሳለፍነው ክረምት ወራት ውስጥ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ በመዝነቡ እና በተወሰኑ አካባቢዎች ደግሞ ምንም ዝናብ አለመዝነቡ ቢሆንም፤ ከጥቅምት እስከ ታህሳስ ባሉት ወራት ውስጥ ዝናቡ አለመዝነቡ ጉዳቱን አባብሶታልም ተብሏል።
በኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትት የአየር ሁኔታ እና ትንበያ ባለሙያው አቶ ታምሩ ለአል ዐይን አማርኛ እንገለጹት አሁን ላይ ድርቅ የተከሰተባቸው አካባዎች ከሚያዝያ በፊት ዝናብ እንደማያገኙ ተናግረዋል፡፡
ዝርዝሩን ለማንበብ :- https://am.al-ain.com/article/ethiopian-drought-stricken-areas-will-remain-arid-untill-march

የተመድ ስደተኞች ኮሚሽን በአፋር ክልል ባንድ የስደተኞች መጠለያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ አምስት ስደተኞች እንደተገደሉ አስታውቋል። ይኼው ጥቃት ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈጸመው እና አምስት ስደተኞች የተገደሉት የኤርትራ ስደተኞች በተጠለሉበት በርሃሌ መጠለያ ነው። ከመጠለያው በርካታ ሴት ስደተኞችም በታጣቂዎች ታፍነው እንደተወሰዱ ኮሚሽኑ ገልጧል። በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራዊያን ስደተኞች ጥቃቱን ተከትሎ ወደ ሠመራ፣ አፍዴራ እና ሌሎች የክልሉ ከተሞች ሸሽተዋል።
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
https://tttttt.me/sabinaadvisor
👇👇👇👇👇👇👇👇
🇹🇷#Turkey_visa
የቱርክ ኢምባሲ አሁን ላይ ስራ ስለጀመረ ፕሮሰስ ለመጀመር ለምትፈልጉ ደንበኞቻችን አሁኑኑ ያናግሩን
👇
የሥራ ቪዛ ወደ ቱርክ
የሆቴል ሥራዎች
ጾታ፡ ወንድ እና ሴት
1. Cleaners
2. Dishwashers
3. Janitors
#Benefits
1. Food and accommodation
2. One way flight ticket
3.Training
4. Salary
5. Service bus
#Process_time = 2 months
#Work_in_Turkey
#Requirements
👉 Passport
👉 Photo
Contact:
@Sabinavisa
@Sabinavisa2
+251118683939
0936363639
0936363680
https://tttttt.me/sabinavisaa

#የኢትዮጵያ_ታሪክ_ከንግስተ_ሳባ_እስከ_አዲስ_አበባ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ
የኢትዮጵያን ታሪክ ከንግስተ ሳባ እስከ አዲስ አበባ የሚቃኘውና በአማዞን የምንጊዜም የኢትዮጵያ ታሪክ መጻህፍት ሽያጭ ከፍተኛ ደረጃን የተቆናጠጠው መጽሐፍ በአማርኛ ተተርጉሞ ቀረበ፡፡
ይህ አለም በጣም ያደነቀው መጽሐፍ ኢትዮጵያን በትናንት፣ በዛሬና በነገ መነጽር የሚያሳይ የ30 ዓመታት ምርምር ውጤት የሆነ በቅጡ ሊነበብ የሚገባው መጽሐፍ ነው፡፡
የአጼ ኃይለስላሴ የልጅ ልጅ ልጅ የሆኑት ልዑል አስፋ ወሰን አስራቴ ስለመጽሐፉ እንዲህ ነው ያሉት፡-
“አንብቤ ለመጨረስ ሶስት ሌሊቶች ብቻ ነው የወሰደብኝ፡፡ ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ጥንታዊ፣ ኃይማኖታዊ ልምምድ ላይ ባልተለመደና ቀልብን በሚያነሆልል ሁኔታ የተጻፈ ነው፡፡ መጽሐፉ በአፍሪካ ምድር ከሚገኙ መሳጭ ስልጣኔዎች መካከል አንዱ ስለሆነው የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለንን ግንዛቤ የሚያፋፋ እጽ ነው፡፡”
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun

🎁 #ArtLand_gifts 🎁
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
✿ "እማይረሱ ስጦታዎችን ለሚወዷቸው" 🎁
✔️የወደዱትን "ፎቶ ወይም ምስል" እንጨት እና ቆዳ(ሌዘር) ላይ እንሰራለን 👌
✔️እንዲሁም MUG, PUZZLE, ሀብል እና ፕላስቲክ MDF ላይ የወደዱትን ፎቶ ወይም ፅሁፍ ያሰሩ 🎁
🔘☎️contact us: 0931465618
🔘For Order @Artlandgifts
Join our telegram channel👇
@artlandengraving

https://youtu.be/sG0S6CNbmvw
Check out and subscribe to our youtube channel to get recommendations on amazing movies and tvshows.
የፊልሞች እና የቲቪ ምርጫዎችን ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን ይመልከቱ እና ሰብስክራይብ ያድርጉ።
https://youtu.be/5O1i0ZvTYMgb

የየካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የሰማዕታት ሀውልት እየተከበረ ይገኛል።
በበዓሉ ስነ ስርዓት ላይ ጀግኖች አባት አርበኞች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች፣ የስካውት አባላት እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
በበዓሉ ስነ ስርዓት ላይ ጀግኖች አባት አርበኞች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች፣ የስካውት አባላት እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
በአፋር በከባድ መሣሪያ ጥቃት አስር የአንድ ቤተሰብ አባላት መገደላቸው ተነገረ!
ባለፈው ማክሰኞ የካቲት 08/2014 ዓ.ም ምሽት ላይ ተፈፀመ በተባለው የከባድ መሳሪያ ጥቃት አስር የአንድ ቤተሰብ አባላት መገደላቸውንና ሌሎች 13 ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱን ከአካባቢው የወጡ ሰዎችና የበጎ ፈቃደኛ ለቢቢሲ ገልጸዋል።በጥቃቱ አስር የቤተሰብ አባሎቻቸው የተገደሉባቸው አቶ ሁሞ እና ቤተሰባቸው ይኖሩ የነበረው በአፋር ክልል ውስጥ በምትገኘው አዳ የምትባል ትንሽ ከተማ ነበር።
ከተማዋ ከበርሃሌ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ እንደሆነች በሰመራ ከተማ ነዋሪ የሆኑት የአቶ ሁሞ የቅርብ ዘመድ አቶ ያሲን ከድር ለቢቢሲ ገልጸው፤ አጠቃላይ ዘመድ በከባድ ሐዘን ውስጥ መሆኑን ተናግረዋል።በጥቃቱ ልጆቻቸውን ይዘው በመሸሽ ላይ ከነበሩት የቤተሰብ አባላት መካከል አምስት ህጻናት፣ እናት፣ የእናት እናት [አያት]፣ የእናት ወንድም እና የአባት እህት ሁለት ልጆች መሆናቸው ተገልጿል።አባወራው አቶ ሁሞ ቀድመው ከአካባቢው ተፈናቅለው ወጥተው ስለነበር በቤተሰባቸው ላይ ከደረሰው አደጋ ሊተርፉ ችለዋል።ሙሉ ቤተሰባቸውን ያጡት አባት ሐዘኑን ሊቋቋሙ በማይችሉት ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።
Via BBC

የሕዳሴው ግድብ ነገ ዕሁድ የካቲት 13 ቀን 2014 ዓ.ም በይፋ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር ተነገረ።
በሁለት የኋይል ማመንጫ ተርባይኖች በውሀ የመሞከር ስራ በስኬት የተከናወነ ሲሆን አሁን ግድቡ የመጀመሪያ ዙር የኤሌክትሪክ ኋይል ማመንጨት የሚጀምርበት ዕለት በግድቡ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ይሆናል፤ዋዜማ ራዲዮና ካፒታል ጋዜጣ እንደዘገቡት።
@YeneTube @FikerAssefa
በሁለት የኋይል ማመንጫ ተርባይኖች በውሀ የመሞከር ስራ በስኬት የተከናወነ ሲሆን አሁን ግድቡ የመጀመሪያ ዙር የኤሌክትሪክ ኋይል ማመንጨት የሚጀምርበት ዕለት በግድቡ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ይሆናል፤ዋዜማ ራዲዮና ካፒታል ጋዜጣ እንደዘገቡት።
@YeneTube @FikerAssefa
የምግብ ዘይት በቅርብ ቀናት ውስጥ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አሳየ!
በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች አንድ ሊትር የምግብ ዘይት እስከ 170 ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል።የዋጋ ጭማሪው ከጥር ወር መግቢያ ጀምሮ የተከሠተ መሆኑን አዲስ ማለዳ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውራ ያነጋገረቻቸው የምግብ ዘይት ሻጮች ተናግረዋል።ከውጭ ገበያ ወደ አገር ውስጥ የሚገባው ከሱፍ የሚመረተው አንድ ሊትር የምግብ ዘይት በተለያዩ መሸጫ ቦታዎች የተለያዬ ዋጋ ያለው ሲሆን፣ በመገናኛ አካባቢ ከ150 እስከ 160 ብር ሲሸጥ፣ በአየር ጤና አካባቢ ደግሞ ከ150 እስከ 170 ብር እየተሸጠ መሆኑን አዲስ ማለዳ አረጋግጫለሁ ብላለች።

እየተደረገ ባለው የሰላም ጥረት ውስጥ ለድርድር በማይቀርቡት አምስት የትግራይ ሕዝብ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ሰጥቶ መቀበል እንደማይኖር የህወሓት ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ተናገሩ።
ደብረ ጽዮን ህወሓት የትጥቅ ትግል የጀመረበትን 47ኛ ዓመት በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ከመንግሥት ጋር በተለያዩ ወገኖች አማካይነት ንግግር እየተደረገ መሆኑን አመልክተው፣ ነገር ግን ለድርድር የማይቀርቡ ጉዳዮች እንዳሉ ገልጸዋል።
በዚህም መሠረታዊ የትግራይ ሕዝብ ጥያቄዎች ናቸው ያሏቸውን አምስት ጉዳዮችን ዘርዝረዋል።"በመጀመሪያ ደረጃ በሠራዊታችን ላይ አንደራደርም።
አሁን ያለው ብቻ ሳይሆን ገና እንጨምርበታለን ስለዚህ በሠራዊታችን ጉዳይ ላይ አንደራደርም።ከዚህ በኋላም ኃይላችንን ይዘን ነው የምንኖረው" በማለት ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በአገሪቱ ሕገ መንግሥት የታወቁ የትግራይ ክልል ወሰን ጉዳይ፣ የኤርትራ ሠራዊት ከትግራይ መውጣት፣ የትግራይ ሕዝብ የራሱን እድል በራሱ የመወሰን መብት ጉዳይ እና በትግራይ ሕዝብ ላይ በደል የፈፀሙ ግለሰቦች ተጠያቂነት ለድርድር አይቀርብም ብለዋል።
ደብረ ጽዮን (ዶ/ር) ጨምረውም እየተደረጉ ባሉት የድርድር ጥረቶች ውስጥ እነዚህ አምስት ቅድመ ሁኔታዎች ዋነኞቹና ሊጣሱ የማይገቡ የድርድር ነጥቦች መሆናቸውን ጠቅሰው "ሰጥቶ መቀበል የሚባለው ጉዳይ እዚህ ላይ አይሰራም" ብለዋል።
ነገር ግን ጦርነቱ በድርድር መፍትሔ እንዲያገኝ የተለያዩ ወገኖች የማሸማገል ጥረት እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ሊቀመንበሩ፤ የአፍሪካ ሕብረትን በመወከል የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት፣ በተመሳሳይ የኬንያው ፕሬዚዳንት፣ የአሜሪካና የአውሮፓ ሕብረት ልዑካን የበኩላቸውን እየሞከሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለ6 ወጣትና አንጋፋ ተመራማሪዎች የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ!
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ገምግሞ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ለስድስት አንጋፋና ወጣት ተመራማሪዎች የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታወቀ፡፡
የዩኒቨርሲቲው የሕዝብና ዓለም ዐቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አለምእሸት ተሾመ እንደገለፁት የዩኒቨርሲቲ ው አስተዳደር ቦርድ ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ገምግሞ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ለስድስት አንጋፋና ወጣት ተመራማሪዎቹ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡
በዚህም መሰረት ለማሽላ ደጀኔ ወልደሚካኤል (ዶ/ር) በዕፅዋት በሽታ ጥናት "ፕላንት ፓቶሎጂ"፣ ለዋሱ መሐመድ አሊ (ዶ/ር) በዕፅዋት ዝርያ ማሻሻል "ፕላንት ብሪዲንግ" እና ለንጉሴ ቡሳ ፌዳሳ (ዶ/ር) በ"ባዮኬሚስትሪ እና ፊዚዮሎጂ" የሙሉ ፕሮፌሴርነት ማዕረግ እንደተሰጠ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም ለአቢ ታደሰ (ዶ/ር) በ"ኢንኦርጋኒክ ኬሚስትሪ"፣ ለምትኩ እሸቱ ጉያ (ዶ/ር) በእንስሳት እርባታ እና ለተስፋሕይወት ዘሪሁን (ዶ/ር) በቨተርነሪ ክሊኒካል ፓቶሎጂ (ስነ ደዌ) የሙሉ ፕሮፈሴርነት ማዕረግ ሰጥቷል።
እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ ተመራማሪዎቹ ባከናወኗቸው የምርምር ሥራዎች፣ በዓለም ዐቀፍ ጆርናሎች ላይ የህትመት ውጤቶችን በማሣተማቸውና በማኅበረሰብ አገልግሎት ባበረከቱት አስተዋፅዖ የሙሉ ፕሮፌስርነት ማዕረጉ እንደተሰጣቸው ተገልጿል።