YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ሀብት_ያለው_አእምሮህ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

የእለት ጉርስህን ለማግኘት እየተጣጣርክ ወይም ያለህ ሀብት እንዲበዛ የምታደርግበትን መንገድ እየፈለግክ ነው?

እንግዲያውስ ሀብት ያለው አእምሮህ የተሰኘው አዲሱ የዶ/ር ጆሴፍ መርፊ መጽሀፍ ይረዳሀል፡፡ መጽሐፉ “የሁሉም ሀብት መነሻ አእምሮ ነው” ይለናል፡፡

“የምትኖረው በአእምሮህ ውስጥ ነው፡፡ ሀብታም ወይም ደሀ፣ ለማኝ ወይም ሌባ የምትሆነው እዚያ ነው፡፡ በህይወት ውስጥ የምትፈልጋቸውን ነገሮች የመፍጠር ኃይል እንዳለህ ስትገነዘብ ታላቅ ዋጋ ያለው እንቁ እንዳለህ ታውቃለህ፡፡ በውስጥህ ያለው ሀብት እና ኃይል በጭራሽ የሚቀንስ ስላልሆነ አንተ ከምታስቀምጠው ገደብ በስተቀር የአእምሮህ ሀብት ገደብ አያውቅም፡፡”

ከዝቅታ ህይወት ወደ ከፍታ ህይወት ተሸጋግረህ አንገትህን ቀና ለማድረግም ሆነ፣ በሕይወትህ ውስጥ የሚገባህን ብልጽግና ለማግኘት ይህ መጽሐፍ እንዴት የድብቁን አእምሮህን ኃይል መጠቀም እንዳለብህ ያስተምርሀል፡፡

#ሀብት_ያለው_አእምሮህ መጽሐፍ
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun
የብዝሃ ሕይወት ብሄራዊ አማካሪ ምክር ቤት ልውጥ ዘረ መል የድንች እና ጥጥ ዘሮችን በኢትዮጵያ ለማስተዋወቅ እያሰበ እንደሆነ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በሁለቱ ልውጥ ዘረ መሎች ላይ የሙከራ ምርት እና ምርምር ለማድረግ እንዲፈቀድለት ለመንግሥት ጥያቄ እንዳቀረበ ዘገባው ጠቅሷል። መንግሥት ልውጦቹ የድንች እና ጥጥ ዘረ መሎች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲመረቱ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት ግን ሕዝብ በጉዳዩ ላይ እንዲወያይበት ይደረጋል ተብሏል። የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ልውጦቹን የድንች እና ጥጥ ዘረ መሎች ለማስተዋወቅ ያሰበው፣ በሽታን የመቋቋም እና ከፍተኛ ምርት የመስጠት አቅም አላቸው በሚል መነሻ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
ተመድ በኢትዮጵያ በጥቅምት ወር ታስረው የነበሩ 16 ሠራተኞቹ በሙሉ ከእስር እንደተፈቱ በቃል አቀባዩ ስቴፈን ዱጃሪች በኩል አስታውቋል። ከ16ቱ ሠራተኞች አብዛኞቹ ቀደም ባሉት ወራት የተለቀቁ ሲሆን፣ ሦስቱ ደሞ የተመድ ምክትል ዋና ጸሃፊ አሚና ሞሐመድ ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው በተመለሱ ማግስት እንደተፈቱ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በሶማሌ ክልል ሰሞኑን የክልሉ ገዢ ፓርቲ ብልፅግና ለሁለት ተከፍሏል በሚል በስፋት የሚናፈሰውን መረጃ በተመለከተ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኢብራሂም ዑስማን ከዶይቼ ቬሌ ጋር ባደረጉት ቆይታ ምላሽ ሰጥተዋል።

ከዚህ በፊት በክልሉ የሚከሰት ድርቅ ለአንዳንዶች የጥቅም ምንጭ ይሆን እንደነበር ያነሱት ምክትል ፕሬዝዳንቱ አሁን በክልሉ ለተከሰተው ድርቅ መንግስት እያከናወነ ያለው አሰራር ያልተመቻቸው ግለሰቦች የሶማሌ ክልል ብልፅግና ለሁለት ተከፍሏል በሚል ውዥንብሩን እንዲፈጥሩ ምክንያት ሊሆን ይችላል ብለዋል።በድርጊቱ እየተሳተፉ ባሉ አካላት ላይ የክልሉ መንግስት እርምጃ የመውሰድ ሀሳብ አለው ወይ በሚል ለቀረበው ጥያቄ እንቅስቃሴው የክልሉን ህዝብ በተለያየ መልኩ ወደ ግጭት የሚያስገባ እና ወደ ህግ ጥሰት ከተሸጋገረ የክልሉ መንግስት ህግ የማስከበር ኃላፊነቱን ይወጣል ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዛሬ ኃይል መስጠት ይጀምራል!

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሙከራ ሂደቱን አጠናቆ በይፋ የኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ መስጠት ይጀምራል።ግድቡ ወደ ኃይል ማመንጨት የገባው በአንድ ተርባይን ነው።ኃይል የማመንጫ ግድቡ ካሉት 13 ተርባይኖች ዩኒት ውሰጥ አንዱን በመጠቀም ነው ወደ መደበኛ ኃይል የማመንጨቱ ሂደት የተሸጋገረው፡፡አንዱን ተርንባይን በመጠቀም ወደ ስራ የሚገባው ግድቡ 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው የወጡት መረጃዎች ያመለክታሉ።

ይህ የሚመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል ብቻውን ከጊቤ ሶስት እና ጣና በለስ ኅይል ማመንጫዎች ቀጥሎ ሶስተኛው ከፍተኛ የሚመነጭ የኤልክትሪክ ኃይል ያደርገዋል።በተጨማሪነትም ሁለት ተርባይኖች በቅርብ ኅይል ለመስጠት የሚያስችላችው ስራም እየተጠናቀቀ ተመልክቷል።ግድቡ አሁን ላይ በሁሉም ስራዎች ፈጣን እድገት እያሳየ በመሆኑ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።እስካሁን ለግድቡ ግንባታ ከ163ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ወጥቶበታል፤ከዚህ ውስጥ 16.3 ቢሊየን ብሩ ከህዝብ ተሳትፎ የተገኘ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የግድቡን ኃይል ማመንጫ ቁልፍ ተጭነው ኃይል ማመንጨት አስጀምረዋል!

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በጉባ ይገኛሉ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዓባይ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችለውን ቁልፍ ተጭነው ዓባይ ለኢትዮጵያ ኃይል እንዲያመነጭ አድርገዋል።አሁን ዓባይ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ኃይል በአንደኛው ተርባይኑ ብቻ 375 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት ጀምሯል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ግብፅና ሱዳን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨቱን ተቃወሙ!

ግብፅ እና ሱዳን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመሩን ተቃውመዋል።ከዛሬ አስር ዓመት በፊት በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የግንባተው መሰረተ የተጣለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ዛሬ ኃይል ማመንጨት ጀምሯል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በጉባ ተገኝተው ግድቡ ካሉት 13 ተርባይኖች አንዱ ማለትም ዩኒት 10 በመባልየሚጠራው ተርባይን 375 ሜጋዋት ሀይል የማመንጨት ስራን አስጀምረዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሀይል ማመንጨት ተከትሎ የግብጽ እና ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምላሽ ሰጥተዋል።የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ እንዳሉት የኢትዮጵያ አካሄድ ግብጽ፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2015 በካርቱም ያደረጉትን የመርህ ስምምነት የሚጥስ ነው ብለዋል።

በሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የህዳሴው ግድብ ተወካይ አምባሳደር ኦማር አልፋሩቅ ለአል ዐይን ኒውስ እንደተናገሩት፤ ግድቡ ሀይል ማመንጨቱ ሶስቱ ሀገራት የተናጥል እርምጃ እንዳይወስዱ በሚል የፈረሙትን የካርቱም ስምምነትን የሚጥስ እና ወዳጅነታቸውን የሚጎዳ ነው።

ሙሉ ዘገባው:
https://am.al-ain.com/article/egypt-sudan-oppose-ethiopian-mega-dam-power-production

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
#የኢትዮጵያ_ታሪክ_ከንግስተ_ሳባ_እስከ_አዲስ_አበባ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

የኢትዮጵያን ታሪክ ከንግስተ ሳባ እስከ አዲስ አበባ የሚቃኘውና በአማዞን የምንጊዜም የኢትዮጵያ ታሪክ መጻህፍት ሽያጭ ከፍተኛ ደረጃን የተቆናጠጠው መጽሐፍ በአማርኛ ተተርጉሞ ቀረበ፡፡

ይህ አለም በጣም ያደነቀው መጽሐፍ ኢትዮጵያን በትናንት፣ በዛሬና በነገ መነጽር የሚያሳይ የ30 ዓመታት ምርምር ውጤት የሆነ በቅጡ ሊነበብ የሚገባው መጽሐፍ ነው፡፡

የአጼ ኃይለስላሴ የልጅ ልጅ ልጅ የሆኑት ልዑል አስፋ ወሰን አስራቴ ስለመጽሐፉ እንዲህ ነው ያሉት፡-

“አንብቤ ለመጨረስ ሶስት ሌሊቶች ብቻ ነው የወሰደብኝ፡፡ ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ጥንታዊ፣ ኃይማኖታዊ ልምምድ ላይ ባልተለመደና ቀልብን በሚያነሆልል ሁኔታ የተጻፈ ነው፡፡ መጽሐፉ በአፍሪካ ምድር ከሚገኙ መሳጭ ስልጣኔዎች መካከል አንዱ ስለሆነው የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለንን ግንዛቤ የሚያፋፋ እጽ ነው፡፡”

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun
Forwarded from YeneTube
🎁 #ArtLand_gifts 🎁

✿ "እማይረሱ ስጦታዎችን ለሚወዷቸው" 🎁

✔️የወደዱትን "ፎቶ ወይም ምስል" እንጨት እና ቆዳ(ሌዘር) ላይ እንሰራለን 👌

✔️እንዲሁም MUG, PUZZLE, ሀብል እና ፕላስቲክ MDF ላይ የወደዱትን ፎቶ ወይም ፅሁፍ ያሰሩ 🎁


🔘☎️contact us: 0931465618
🔘For Order @Artlandgifts

Join our telegram channel👇
@artlandengraving
Forwarded from YeneTube
https://youtu.be/sG0S6CNbmvw

Check out and subscribe to our youtube channel to get recommendations on amazing movies and tvshows.

የፊልሞች እና የቲቪ ምርጫዎችን ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን ይመልከቱ እና ሰብስክራይብ ያድርጉ።


https://youtu.be/5O1i0ZvTYMgb
🇬🇧 የስራ ጉዞ ወደ #UK 🇬🇧

👉 የሚሰራበት አገር - UK
👉 የስራው አይነት - Vegetables and fruits picker
👉 የስራ ቀናት - 5 - 6 ቀናት/ week
👉 የስራ ሰዓት - ከ8 - 10 hr/day
40/60 working hrs per week
👉 ደሞዝ - £8.91 per hr + bonuses for OT
👉 ፆታ - ወንድ እና ሴት
👉 ዕድሜ - 20 እስከ 45
👉 OT - ይቻላል
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ 2 ወር

Accommodation is provided by the employer (~£55 per week)

#Requirements
👉 Passport
👉 Photo

#Urgent
የምንፈልገው የአመልካች ብዛት 20 ሰው ብቻ::

Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
info@sabinaadvisor.com
http://Sabinaadvisor.com
https://tttttt.me/sabinaadvisor
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ በሚገኘው ልዩ ስብሰባ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ይሾማል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች ላይ ህብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ከዚህ በፊት ዝርዝራቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

የተገኘውን ግብዓት ምክር ቤቱ ከተመለከተ በኋላም መስፈርቱን በከፍተኛ ደረጃ አሟልተዋል ያላቸውን እጩ ኮሚሽነሮች በመምረጥ እንዲሾሙ ለምክር ቤቱ አቅርቧል፡፡

በዚህ መሰረትም ፡-

1. ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

2. ወይዘሮ ሂሩት ገብረስላሴ

3. ዶክተር ተገኘወርቅ ጌቱ

4. አምባሳደር ዶክተር አይሮሪት መሃመድ

5. ወይዘሮ ብሌን ገብረመድህን

6. ዶክተር ዮናስ አዳዬ

7. አቶ ዘገየ አስፋው

8. አቶ መላኩ ወልደማሪያም

9. አምባሳደር መሃሙድ ድሪር

10. አቶ ሙሉጌታ አጎ እና

11. ዶክተር አምባዬ ኦጋቶ እጩ ኮሚሽነር ሆነው ቀርበዋል፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ እያካሄደው በሚገኘው ልዩ ስብሰባ በእነዚህ እጩ ኮሚሽነሮች ላይ ከተወያየ በኋላ ይሾማቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ምክር ቤቱ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮችን ሹመት አፀደቀ!

የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽንን የሚመሩ 11 ኮሚሽነሮችን ሹመት በ5 ድምፀ ታአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

ምክር ቤቱ በዛሬ ልዩ ስብሰባው ዶ/ር መስፍን አርዓያ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አድርጎ ሾሟል፡፡

ዋና እና ምክትል ኮሚሽነሮችን ጨምሮ የ11 ኮሚሽነሮች ሹመት በምክር ቤት ፀድቋል፡፡

እነርሱም:-
1. ፕ/ሮ መስፍን አርዓያ ዋና ኮሚሽነር

2. ሒሩት ገብረሥላሴ ምክትል ዋና ኮሚሽነር

3. ዶ/ር ተገኘወርቅ ጌቱ

4. አምባሳደር ዶ/ር አይሮሪት መሐመድ

5. ብሌን ገብረ መድህን

6. ዶ/ር ዮናስ አዳዬ

7. ዘገየ አስፋው

8. መላኩ ወልደ ማርያም

9. አምባሳደር ማሕሙድ ዲሪር

10. ሙሉጌታ አጎ

11. ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ ሲሆኑ፤ የእጩ ኮሚሽነሮችን ሹመት ለምክር ቤቱ ያቀረቡት አፈ ጉባኤው ታገሰ ጫፎ ዕጩዎቹ የተመረጡበት መስፈርት ብዙኃነትን እና የፆታ ስብጥርን ከግምት ያስገባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሁሉም ኮሚሽነሮች ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው ማገልገል እንደሚጠበቅባቸውም አፈ ጉባዔው አስረድተዋል።

ሹመቱ የፀደቀላቸው ኮሚሽነሮች በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሃላ ፈፅመው ኃላፊነታቸውን ተረክበዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ባይደን ከፑቲን ጋር ለመምከር በመርህ ደረጃ መስማማታቸው ተሰማ

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በዩክሬን ስላለው ቀውስ ለመወያየት በመርህ ደረጃ መስማማታቸዉ ይፋ ተደርጓል፡፡ፈረንሳይ ያቀረበችው ውይይት የሚካሄደው ሩሲያ ጎረቤቷን ዩክሬንን ካልወረረች ብቻ ነው ሲሉ ዋይት ሀውስ አስታውቋል።

ውይይቱ ባለፉት አሥርተ ዓመታት በአውሮፓ ውስጥ ከታዩት አስከፊ የጸጥታ ቀውሶች አንዱ የሆነውን የዩክሬን ዉጥረት ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ለመስጠት ያስችላል ተብሏል፡፡የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት የስለላ መረጃ ሩሲያ ወታደራዊ ዘመቻ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ያሳያል ቢሉም ሞስኮ ግን የሀሰት ስትል ታስተባብላለች፡፡

የዉይይት ሀሳቡ ሊመጣ የቻለዉ በፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና በሩሲያ አቻቸዉ ፑቲን መካከል ሁለት የስልክ ጥሪ ከተደረገ እና በአጠቃላይ ሶስት ሰዓታት ከፈጀ ንግግር በኃላ ነዉ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ዋና ጸሀፊ አንቶኒ ብሊንከን እና የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሐሙስ ዕለት በሚያደርጉት ውይይት ስለየመሪዎች ጉባኤ ዝርዝር ጉዳይ እንደሚወያዩበት የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ባወጣዉ መግለጫ አስታዉቋል፡፡

Via:- Bisrat
@Yenetube @Fikerassefa
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የባልደራስ ጥያቄ ውድቅ አደረገ!

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲን የምክር ቤት አባል ማስነሳት ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን ዛሬ ባሰራጨዉ ደብዳቤ ገለጸ።

የምክር ቤት አባል ይውረድልኝ ጥያቄን ማቅረብ የሚችለው መራጩ ህዝብ በመሆኑ እና በምርጫ ክልሉ ተወዳዳሪ የነበረ ፓርቲ በጉዳዩ ላይ ድጋፍ እንዲደረግለት የሚፈቅድ የህግ አግባብ ባለመኖሩ ሲል ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ጥያቄን ውድቅ አድርጓል

ቦርዱ እንዳስታወቀው የማሟያ ምርጫ የሚደረገው በሁለት ምክንያቶች ሲሆን በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች የተጓደሉባቸውን አባላት ለማሟላት ጥያቄ ሲያቀርቡ እንዲሁም ተፈፃሚነት ባለው ህግ መሰረት የቀረበ የይውረድልኝ ጥያቄ ተቀባይነት ሲያገኝ ነው ብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የብልፅግና ፓርቲ ተወካይ የሆኑት እና የከተማው የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ከምክር ቤት አባልነታቸው እንዲነሱና የማሟያ ምርጫ እንዲደረግ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የካቲት 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ለቦርዱ ጥያቄ ማቅረቡ የሚታወስ ነው።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
ፕ/ር መሰፍን አርአያ ወልደተንሳይ ማናቸው?

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ሹመት አጽድቋል።የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ሆነው የተመረጡት ፕሮፌሰር መስፍን አርአያን ይተዋወቁ።

👉 በሕክምና የዶክተሬት ዲግሪ ( MD), ከፓቭሎቭ ዩኒቨርሲቲ ሩሲያ

👉 በሳይኮቴራፒ ፍልስፍና የፒኤች ዲ ዲግሪ (PhD), ከኦማያ ዩኒቨርሲቲ፣ ሰዊድን

👉 ስፔሻላይዝድ ድፕሎማ፤ በሳይኮሎጂካል ሜድስን እና ሳይካትሪ፣
ግሮኒጎኝ ዩኒቨርስቲ ኔዘርላንድስ፣

👉 በኤፒዲሞሎጂና ባዮስታትስቲክስ ሰርተፍኬት፤ ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የሥራ ልምድ

👉 ለ6 ዓመታት በአዲግራት በደሴ አና በአማኑኤል ሆስፒታሎች ሜዲካል ኦፊሰርና ዳይሬክተር፣

👉 ለ10 ዓመታት በአማኑኤል ሆስፒታል ሳይካትሪስት

👉 ለ 6 ዓመታት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ፕሮቮስት

👉 ለ6 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሳይካትሪ ዲፓርትመንት ዲን፣

👉 ለ12 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ሆነው የዲፓርመንት ሃላፊ እና ልክቸረር ሆነው ካገለገሉ በኋላ ሙሉ የፕፌሰርነት ማዕረግ አግኝተዋል፡፡

👉 ለ 11 ዓመታት የፌደራል ሆስፒታሎች አመራር ቦርድ አባል

👉 በአሁን ወቅት ከሙያዊ አገልግሎት በተጨማሪ በኢፌዴሪ የማንነትና የአስተዳር ወሰን ኮሚሽን አባል ሆነው ያገለግላሉ፤

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ነገ ለሕዝብ ተወካዮች ማብራሪያ እና ምላሽ ይሰጣሉ!

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነገው ዕለት በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት፣ ከተወካዮቹ ለሚነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ማብራሪያ እና ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከሕዝብ ተወካዮች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ረገድ ለሚነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ማብራሪያ እና ምላሽ እንደሚሰጡ ከምክር ቤቱ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሶማሊያ ከአሜሪካ ኩባንያ ጋር የተደረገውን የነዳጅ ምርት ስምምነት ሰረዘች!

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ነዳጅ ፈልጎ እንዲያመርት ‘ኮስትላይን’ ከተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ሰረዙ፡፡

መሃመድ አብዱላሂ መሃመድ ፋርማጆ እና መሃመድ ሁሴን ሮብል ከትናንት በስቲያ በኩባንያው እና በአገሪቱ የፔትሮሊዬም ሚኒስቴር መካከል የተፈረመውን ስምምነት መሰረዛቸው ይፋ ሆኗል።

የፔትሮሊዬም ሚኒስትሩ አብዲረሽድ መሃመድ አሕመድ ምርቱን እኩል በመጋራት መርሃ ግብር በ7 የተለያዩ የባሕር ዳርቻዎች ነዳጅ ፈልጎ እንዲያመርት ከ‘ኮስትላይን’ ጋር መስማማታቸውን አስታውቀው ነበር፡፡

እንደአል አይን ዘገባ ስምምነቱ ከሕግ ውጭ የተደረገ ነው በሚል በአገሪቱ መሪዎች ተሰርዟል፡፡ምክንያቱ ደግሞ “በምርጫ ወቅት ከውጭ አካላት ጋር ምንም ዓይነት ስምምነቶች እንዳይደረጉ በፕሬዝዳንቱ ተፈርሞ የወጣውን አዋጅ ይጥሳል”ም ነው የተባለው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኬንያ ፖሊስ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ በሕገወጥ መንገድ የገቡ 108 ኢትዮጵያዊያንን ኪያምቡ በተባለ የሀገሪቱ አውራጃ ውስጥ ባለፈው ዓርብ እንደያዘ የሀገሪቱ ዜና አውታሮች ዘግበዋል። ፓሊስ በደረሰው ጥቆማ መሠረት ኢትዮጵያዊያኑን ያገኛቸው አንድ በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪነት በሚጠረጠር ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተቆልፎባቸው ሲሆን፣ ወደ ኬንያ የገቡት በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ሳይሆን እንደማይቀር ፖሊስ ተናግሯል። ኢትዮጵያዊያኑ ዕድሜያቸው ከ13 እስከ 35 እንደሚገመት ተገልጧል። ፓሊስ በዕለቱ 4 ኬንያዊያን ተጠርጣሪ ሕገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎችን ጭምር በቁጥጥር ስር አውሏል።

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
ባልደራስ ፓርቲ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ምስረታ የከሸፈ ነው አለ!

“ብልጽግና ፓርቲ (መንግሥት) ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ዋና ዋና አካሎች፣ ማለትም የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የሲቪክ ተቋማትን እና የሃይማኖት ተቋማትን አግልሎ ሂደቱን ብቻውን በማን አለብኝነት” በማስኬዱ ሀገራዊ ምክክሩ ከሽፏል ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ገለፀ።

ፓርቲው አመሻሹን ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ፣ መንግስት እጩ ኮሚሽነሮችን ለማንም ዜጋ ግልጽ የሆኑ የመምረጫ መስፈርቶች ሳያስቀምጥ ለራሱ በሚመቸው መንገድ በማውጣት የኮሚሽነሮችን ምርጫ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፅድቆታል ያለ ሲሆን፣ ምርጫውም “አካሄዱ የብልፅግና ሴራ ነው” በማለት ተችቶታል።

“ለመላው የአገራችን ሕዝብ ግልጽ መሆን የሚገባው ብልጽግና (መንግሥት) ይህንን ታሪካዊ የሠላም እና የአገራችን የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ በእጅጉ ይጠቅማል ተብሎ ተስፋ የተጣለበትን የምክክር ኮሚሽን የምስረታ ሂደት አሳታፊ ባለማድረግ፣ ኮሚሽኑ ገና ሳይመሰረት እንዲመክን ማድረጉ ነው” ብሏል ባልደራስ።

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa