YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የፌደራሉ መንግስት ”ከክንብንቡ ወጥቶ፣ ከእንቅልፉ ነቅቶ ዐብይና ቀዳሚ” ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲል ኢህአፓ አሳሰበ!

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ(ኢህአፓ) ለአሻም በላከው መግለጫ ”መንግስት የዜጎችን በህይወት የመኖር ዋስትና ማስጠበቅ፣ መንግስታዊ ግዴታው ነው፤ እንዲሁም ቀዳሚ ተግበሩ ነው” ሲል ሃላፊነቱን አስታውሷል፡፡ይሁንና ”አሁን አሁን እንደምናስተውለው ቅድሚያ የሚያገኘው ተግባር ሌላ ሌላው እየሆነ፣፣ የዜጎች አጉል ሞትን እያለማመደን ይሆን?” የሚል ጥያቄ እንዳጨረበት ፓርቲው በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

ፓርቲው አካሄዱን ’የልጆች ጨዋታ” ሲል በመጥራት ”መንግስት ከክንብንቡ ወጥቶ፣ ከእንቅልፉ ነቅቶ፣ ዐብይና ቀዳሚ ሚናውን እንዲወጣ አሳስቧል፡፡ኢህአፓ ለአሻም በላከላት መግለጫ በአፋር ክልል በሽብርተኛ ድርጅትነት በተፈረጀው ህወሓት ”ጥቃት የተከፈተባቸው ነዋሪዎች መንግስት ድርስልን ቢሉም፤ ጩኽታቸው ሰሚ አላገኝም’ ብሏል፡፡

ፓርቲው አክሎም ” ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት አገሩንና ሕዝብን በመታደግ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደረገውን “ፋኖ” መተናኮስ መጀመራቸው እያስተዋልን ነው፡፡”ሲል ከስሷል፡፡

”ሀገር አሁን የምትሻው እንደ ክፉ ጎረቤት ሲያልክፍ ሲያገድም የሚያሽሟጥጥ አመራር ሳይሆን በስክነትና በእርጋታ፣ በመርህና በቁርጠኝነት መውጫውን የሚተልም፣ ነገን የሚያልም ሰው ነው፡፡’” ሲል መንግስትን በፅኑ ተችቷል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ሌላኛው በሽበርተኝነት የተፈረጀው ድርጅት ኦነግ ሸኔ እያደረሰ ያለውን የጅምላ ግድያ ያስታወሰው ፓርቲው ” ፈላጊ መንግስትና ዘመድ የሌላቸው ወገኖቻችን ይሄው የጅምላ መቃብራቸው እየተገኘ እንደሆነ እየሰማን ነው፡፡” ብሏል፡፡ፓርቲው በመግለጫው ”እንዲህ ያለው አካሄድ ሰነባብቶ ብልጽግናና የሚመራውን መንግሥት ከባድ ዋጋ የሚያስከፍለው መሆኑን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡’ ሲል አስጠንቅቋል፡፡

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ

አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉 https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
Forwarded from YeneTube
Kdamie.com ንግድ እና አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ፡፡
#ጅምላና ችርቻሮ ንግዶችን አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ከጨረታና ፐርፎርማ እንዲሁም የስራ ማስታወቂያዎች እና መረጃዎች ጋር፣
#በጉዞዎ መዳረሻዎችን ከነ አስጎብኚዎች እና የጉዞ ወኪሎች ጋር
#የእንግዳ ማረፊያ ሆቴልና ሪዞርቶችን ፈርኒሽድ አፓርታማዎችን ገሰት ሀውሶችን እና ፔንሲዮኖችን
ለመኖሪያ የሚሆኑ ቪላ እና ኮንዲሚኒየሞችን
#በሁሉም የገበያ ማዕከላት ለሱቅ እና ለቢሮ የሚሆኑ ክፍሎችን ሳይዞሩ ሳይደክሙ የሚያገኙበት Kdamie.com
#በንግድ በቱሪዝም እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ለሆኑ ድጅቶችም ኑ አብረን እንስራ ይሎታል Kdamie.com

ከኛ ጋር መስራት ንግድና አገልግሎቶን ማዘመን፣ደንበኞችዎን ባሉበት ማግኘት ነው!! Kdamie.com
#በሁሉም የማህበራዊ ገፆች
Telegrame እና whatsup - +251-911705126
Kdamie.com - https://tttttt.me/+K7sPcHhHYy44NDI0
facebook - https://www.facebook.com/Kdamie-107188781818909
Instagram - https://www.instagram.com/p/CZkVH-FAd11/?utm_source=ig_web_copy_link
Email - kdamiesells@gmail.com
phone:- +251911705126/+251916821091 ያገኙናል፡፡
Forwarded from YeneTube
#የኢትዮጵያ_ታሪክ_ከንግስተ_ሳባ_እስከ_አዲስ_አበባ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

የኢትዮጵያን ታሪክ ከንግስተ ሳባ እስከ አዲስ አበባ የሚቃኘውና በአማዞን የምንጊዜም የኢትዮጵያ ታሪክ መጻህፍት ሽያጭ ከፍተኛ ደረጃን የተቆናጠጠው መጽሐፍ በአማርኛ ተተርጉሞ ቀረበ፡፡

ይህ አለም በጣም ያደነቀው መጽሐፍ ኢትዮጵያን በትናንት፣ በዛሬና በነገ መነጽር የሚያሳይ የ30 ዓመታት ምርምር ውጤት የሆነ በቅጡ ሊነበብ የሚገባው መጽሐፍ ነው፡፡

የአጼ ኃይለስላሴ የልጅ ልጅ ልጅ የሆኑት ልዑል አስፋ ወሰን አስራቴ ስለመጽሐፉ እንዲህ ነው ያሉት፡-

“አንብቤ ለመጨረስ ሶስት ሌሊቶች ብቻ ነው የወሰደብኝ፡፡ ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ጥንታዊ፣ ኃይማኖታዊ ልምምድ ላይ ባልተለመደና ቀልብን በሚያነሆልል ሁኔታ የተጻፈ ነው፡፡ መጽሐፉ በአፍሪካ ምድር ከሚገኙ መሳጭ ስልጣኔዎች መካከል አንዱ ስለሆነው የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለንን ግንዛቤ የሚያፋፋ እጽ ነው፡፡”

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun
🇭🇺የስራ ጉዞ ወደ #Hungary 🇭🇺
#Schengen_visa

👉 የሚሰራበት አገር - Budapest, Hungary
👉 የስራው አይነት - Construction work
👉 የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week
👉 የስራ ሰዓት - 8 - 10 hr/day
👉 የወር ደሞዝ - €1500 and more
👉 ፆታ - ወንድ
👉 ዕድሜ - 18 እስከ 45
👉 መኖሪያ ቤት - በነፃ
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 2 - 3 ወር ነው

#30_persons

#Requirements
👉 Passport
👉 Photo


Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
info@sabinaadvisor.com
http://Sabinaadvisor.com
https://tttttt.me/sabinavisaa
#ጅግጅጋ

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና ጅግጅጋን አስመልክቶ የክልሉ የኮሙኒኬሽን ቢሮ በተሰጠ መግለጫ!!

"በአሁኑ ወቅት ጅግጅጋ ከተማን ጨምሮ መላው የሶማሌ ክልል እንደ ወትሮው ሁሉ ሰላም እና መረጋጋት የሰፈነ ሲሆን፣ በአንዳንድ ቦታዎች ፀረ ለውጥ የሆኑና በሙስና እንዲሁም በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ለውጥ አደናቃፊ አካላት በድብቅ ግንኙነት ሲያደርጉ ተደርሶባቸው ከመንግስት መዋቅር የወጡ ሀይሎች ሰላም ለማደፍረስ ያደረጉት ሙከራ ከሰላም ወዳዱ ህዝባችን ጋር በመተባበር መክሸፉን እንገልፃለን። " ብሏል።

አመሻሹን ጅግጅጋ ከተማ ውስጥ ረብሻ፣ አለመረረጋጋትና መፈንቅለ መንግሥት እንዳለ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ግን ፍፁም ሀሰት መሆኑንም ክልሉ ገልጿል።

የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ በመግለጫ የሶማሌ ክልል መንግሥት ከሰላም ወዳዱ ህዝባችን ጋር በመሆን የህዝባችንን ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እንደማይታገስና አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ እንገልፃለን ብሏል።

ምንጭ፣ የሶማሌ ክልል ኮምዩኒኬሽን ቢሮ
@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
Photo
የጀርመኑ መራሂተ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ወደ ሩሲያ አቅንተዋል፡፡

ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ጦርን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ እና ሩሲያ ጉዳዩን እንደማትቀበል በማሳወቋ በምስራቅ አውሮፓ ጦርነት ይቀሰቀሳል የሚል ስጋት ተደቅኗል፡፡የሩሲያን ውሳኔ ተከትሎም የኔቶ አባል ሀገራት እንደ ተቋም እና እንደ አገር ከፍተኛ መጠን ያለው ጦር ወደ አካባቢው በማስፈር ላይ ሲሆኑ ሩሲያም ከ150 ሺህ በላይ ጦር ወደ ዩክሬን አስጠግታለች፡፡

በዚህ ምክንያትም በአካባቢው ጦርነት እንዳይቀሰቀስ የጠለያዩ አገራት ጉዳዩ በዲፕሎማሲ እንዲፈታ ግፊት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ባሳለፍነው ሳምንት የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ሞስኮ ተጉዘው ሩሲያ ዩክሬንን እንዳትወር ጉዳዩ በዲፕሎማሲ እንዲፈታ ለማግባባት ሞክረው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡

አሁን ደግሞ የጀርመኑ መራሂተ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ወደ ሞስኮ የተጓዙ ሲሆን የጉዟቸው ዓላምም ኔቶ እና ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ የገቡበትን ውጥረት ማርገብ እንደሆነ የጀርመን ዜና ወኪል ዘግቧል፡፡

ኦላፍ ሾልዝ በትናንትናው ዕለት ወደ ዩክሬን መጥተው የነበረ ሲሆን ከሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ዘለንስኪ ጋር በውጥረቱ ዙሪያ ተወያይተው ነበር፡፡

በዛሬው የሞስኮ የአንድ ቀን ቆይታቸውም ከሩሲያ ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር እንደሚወያዩ የሚጠበቁት ኦላፍ ሾልዝ ሩሲያ ዩክሬንን እንዳትወር እና ጉዳዩ በዲፕሎማሲ ብቻ እንዲፈታ ለማግባባት እንደሚሞከሩ ይጠበቃል፡፡

ጀርመን የሩሲያ ዋነኛ የንግድ አጋር ስትሆን በዩክሬን ጉዳይ የዲፕሎማሲ ጥረቱ ካልተሳካ ጀርመንን እና አሜሪካንን ጨምሮ የአውሮፓ አገራት ጠንካራ ማዕቀብ እንደሚጣልባት አገራት ከወዲሁ በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው፡፡

ሩሲያ በበኩሏ ዩክሬንን የመውረር ሃሳብ እንደሌላት ገልጻ ዩክሬን ኔቶን ከተቀላቀለች የጸጥታ እና ደህንነት ስምምነት ግን ይኑረን ስትል በተደጋጋሚ በማሳወቅ ላይ ትገኛለች፡፡

Via Al Ain
@Yenetube @Fikerassefa
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አነሳ

አዋጁ 63 ተቃውሞ እና 21 ድምፀ ተአቅቦ ቀርቦበታል !!


የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በአገሪቱ ተጥሎ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነስቷል፡፡

ምክር ቤቱ በስብሰባው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በ63 ተቃውሞ በ21 ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ እንዲነሳ ወስኗል፡፡

ይህን ውሳኔ ተከትሎ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ያላጠናቀቃቸው ጅምር ሥራዎች ካሉ ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት ከዛሬ ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንዲያደርግ መወሰኑን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ የፍትህ አካላት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ የጀመሯቸውን ጉዳዮች በመደበኛው የፍትህ አሰሰጣጥ ሥርዓት እንዲያጠናቅቁም ምክር ቤቱ ወስኗል።

#ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
በረሃ ላይ ብቻውን ምግብ እያበሰለ የነበረውን ታዳጊ ፎቶ ያነሳው ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ ከፎቶው ጀርባ ስላለው ታሪክ ለቢቢሲ ተናግሯል።

ፎቶውን በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች ብዙዎች ያጋሩት ሲሆን ለልጁ ገንዘብና የተለያዩ እርዳታዎችም ተሰባስበውለታል።ፎቶውን ያነሳው ጋዜጠኛ ቦሩ ኮንሶ ይባላል።በፎቶው ላይ ታዳጊው ብቻውን በረሃ ላይ ምግብ እያበሰለ የሚታይ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያም ለተመለከቱትም ከፍተኛ ኃዘኔታን አሳድሯል።

ፎቶውን ያነሳው ጋዜጠኛ በሞተር ሳይክል ሚዮ በተባለች ገጠራማ ሰፈር ሪፖርት ለመስራት እየሄደ በነበረበት ወቅት ነው ልጁን ያገኘው።በጣም መሽቶም ነበር።"ትንሽ ልጅ ነው ምናልባትም ዕድሜው ከ10 ዓመት በታች።ብቻውን እሳት አንድዶ ምግብ እያበሰለ ነበር።ብቻውን በረሃ ውስጥ እያበሰለ ሳየው ደነገጥኩ።

በ10 ኪሎሜትር ርቀት ካልሆነ በአካባቢው ምንም አይነት ቤት የለም።ሞተር ሳይክሌን አቁሜም ፎቶ አነሳሁት" ይላል ቦሩ።ልጁ ለጋዜጠኛው የገለጸለት ቤተሶቦቹ በሌላ ወረዳ ውስጥ እንደሚኖሩና ውሃና ግጦሽ ፍለጋም ከብቶቹን ይዞ ከቦታ ቦታ እንደሚንቀሳቀስ ነው።ቦሩ የልጁን ፎቶ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ማጋራቱን ተከትሎ በርካቶችም ታዳጊውን መርዳት እንደሚፈልጉም ነገሩት።

ህፃኑን ከጎበኙት መካከል ነጋዴዋ ሙና ባካሬ የምትባል ግለሰብ አንደኛዋ ስትሆን ለልጁ ፣ለቤተሰቦቹ እና ለጎረቤቶች የምግብና ሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጋለች።"የዚህን ትንሸ ልጅ ፎቶ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ማየቴ ልቤን ነክቶታል። መተኛት አልቻልኩም ነበር።ልጄ እንደሆነ ተሰማኝ፣ ስለዚህ እሱን መፈለግ ጀመርኩ" ብላለች ሙና።ሙና የልጁን የትምህርት ወጪ እንደምትሸፍን የተናገረች ሲሆን ኮሌጅ እስኪጨርስ ድረስ ለመክፈል ቃል ገብታለች።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ሞሮኮ ከእስራኤል ጋር የ500 ሚሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ስምምነት ተፈራረመች

እስራኤል ለሞሮኮ የአየር ጥቃት መከላከያ መሳሪያን ለማቅረብ የ500 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ላይ ደርሳለች፡፡

ከእስራኤል ኤሮስፔስ ጋር የተደረገው ውል ባለፈው ህዳር ወር ሁለቱ ሀገራት በመከላከያ ትብብር ዙሪያ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ ነው።

ሞሮኮ እ.ኤ.አ በ2020 መገባደጃ ላይ በአሜሪካ አደራዳሪነት የክፍለ ዘመኑ የሰላም ስምምነት(የአብራሃም ስምምነት) በተባለዉ ሂደት ከእስራኤል ጋር ይፋዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማድረግ መጀመሯ ይታወሳል፡፡

Via:- Al ain
@Yenetube @Fikerassefa
ለዜጎች መብት መከበር የሚሟገተው ጋዜጠኛ መብት ይከበር ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር አሳሰበ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር ከጋዜጠኞች መብት እና የሙያ ነፃነት ጋር በተያያዘ እየተፈፀሙ ያሉትን ጥሰቶች አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

የማህበሩ መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦

ለዜጎች መብት መከበር የሚሟገተው ጋዜጠኛ መብት ይከበር!

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት መሻሻል እያሳየ እንደነበር ማህበራችን እና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ሲመሰክሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ይሁንና ይህ መሻሻል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተሸረሸረ መሄዱን በብዙ ማሳያዎችን መግለጽ ይቻላል፡፡

ለአብነትም የሚከተሉትን ማሳያዎች መጥቀስ ይቻላል፡፡
1. በአንድ ወቅት የአሐዱ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ ታምራት አበራ ስቲዲዮ በሥራ ላይ እያለ ትጥቅ ባነገቱ የጸጥታ አካላት ወደ ሰንዳፋ ተወስዶ ታስሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በየትኛውም አግባብ የታጠቁ ኃይሎች ወደ መገናኛ ብዙኃን ስቱዲዮዎች ፈጽሞ መግባት እንደሌለባቸው እሙን ቢሆንም በኢትዮጵያ ግን ይህ ተደርጎ አይተናል፡፡

2. የአሐዱ ኤፍ ኤም ሬድዮ ባልደረባ የነበረው ጌጥዬ ያለው የታሰረ ባልደረባውን ለመጠየቅ ሰንዳፋ ፖሊስ ጣቢያ ባመራበት ወቅት የክልሉ ጸጥታ አካላት "ጋዜጠኞች መታሰር አለባቸው” በሚል እንዳሰሩት ሙሉ መረጃ አለ፡፡

3. የፍትሕ መጽሔት ማኔጅንግ ኤዲተር ተመስገን ደሳለኝ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከቢሮው ተወስዶ እና በእስር ቆይቶ ከቀናት በኋላ መለቀቁ ይታወሳል፡፡

4. የባላገሩ ቴሌቪዥን ጣብያ ባልደረባ ጋዜጠኛ አስናቀ ማርሸትም በኦሮሚያ ክልል አሌልቱ ከተማ "አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ቀለማትን የያዘ ልብስ ለበሳችሁ” በሚል ታስሮ ፍርድ ቤትም ሳይቀርብ መለቀቁ ይታወሳል፡፡

5. የአሐዱ ኤፍ ኤም ሬድዮ ባልደረባ ክብሮም ወርቁ በመንግስት ኃይሎች ተወስዶ የት እንዳለ ሳይታወቅ ቆይቶ ከወራት በኋላ ተለቋል፡፡ ይህ ጋዜጠኛን ማፈን እና መሰወር ከመንግስት የማይጠበቅ ድርጊት ነው።

6. የአውሎ ሚዲያ ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረውም ታስሮ ለወራት ከቆየ በኋላ ቢለቀቅም ንብረቶቹ ሙሉ በሙሉ በጸጥታ ኃይሎች እጅ ሥር ይገኛሉ፡፡

7. ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድም ታስራ ፍርድ ቤት ሳትቀርብ ከአንድ ወር በላይ ቆይታ ተለቃለች።

8. "የአሸባሪውን ሸኔ ቡድንን በዓለም አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅ ስራ ሲሰሩ ነበር" ያላቸውን ሶስት ተጠርጣሪ ጋዜጠኞች ማለትም አሚር አማን - የአሶሺየትድ ፕሬስ ጋዜጠኛ፣ ቶማስ እንግዳ - የካሜራ ባለሞያ እና አዲሱ ሙሉነህ የፋና ብሮድካስቲንግ ጋዜጠኛ በቁጥጥር ሥር አውሏል። በቅርቡም ጋዜጠኛ አዲሱ ሙሉነህ ከአንድ ወር ተኩል እስር በኋላ ሲለቀቅ ሌሎቹ በእስር ላይ ይገኛሉ።

ይሁን እንጂ በተጠርጣሪነት የተያዙት ጋዜጠኞች ወንጀለኛነታቸው በፍርድ ቤት ባልተረጋገጠበት ሁኔታና አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከሚደነግገው ውጭ አስቀድሞ እንደወንጀለኛ እንዲቆጠሩ በማድረግ ምስላቸው በሚዲያ እንዲሰራጭ በማድረግ ከፍተኛ የሥም ማጥፋት ተፈጽሞባቸዋል።

9. ሌላው የተራራ ኔትወርክ ዩትዩብ አዘጋጅ የሆነው ታምራት ነገራም ባልታወቀ ምክንያት ታግቶ እስካሁን ድረስ በገላን ከተማ እንደሚገኝ ማህበራችን ከቤተሰቦቹ አረጋግጧል። ንብረቶቹም በሙሉ በመንግስት ተወስደዋል፡፡ ታምራት ነገራ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ እስካሁን በእስር ላይ መቆየቱ እጅግ አሳዛኝ እና ተገቢነት የሌለው ተግባር መሆኑን ማህበራችን ያምናል፡፡

በአጠቃላይ ጋዜጠኞችን ካለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መያዝ እንዲሁም ይህንን ያህል ጊዜ እስር ቤት ማቆየት ከሕግም ከሞራልም ያፈነገጠ መሆኑ ግልጽ ቢሆንም በኢትዮጵያ ግን ይህ ጉዳይ የተለመደ ሆኗል፡፡

ጋዜጠኛ የህዝብ አንደበትና ጆሮ በመሆኑ የሚያራምዳቸው ሀሳቦችን ከተለያዩ ምንጮች ሊያገኝ ስለሚችል የግል አቋም ተደርጎ መወሰዱ ብቻውን አግባብ አይደለም።

ማንኛውም ጋዜጠኛ ወይም የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያ የሚታሰረው ለሕዝብ ባስተላለፈው መልዕክት ይዘት ከሆነ ያስተላለፈው ሀሳብ የእርሱ ወይም የሌላ ሰው ሊሆን ስለሚችል እርሱ ብቻ በሀሳቡ ብቻ ሊጠየቅ አይገባም።

ያም ሆኖ በዘገባ ወቅት የተፈጠረ የመረጃ እና/ወይም የእውነታ ስህተት ቢኖር እንኳን ተመጣጣኝ ማስተካከያ በዚያው ሚዲያ ላይ ማድረግ የሚችልበት አሰራር እያለ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደእስር መውሰድ ተገቢ አይደለም።

ከዚህም በተጨማሪ ማንኛውም ጋዜጠኛ የመረጃ ምንጩን ምስጢራዊነት የመጠበቅ ሙያዊ መብቱ ሊከበርለት እንደሚገባ መንግስት ማጤን ይኖርበታል።

ጋዜጠኞች በታፈኑ ቁጥር የሀሳብ የበላይነት እየከሰመ የአገሪቱ የፕሬስ ዕድገትም እየቀጨጨ ይሄዳል።

ማህበራችን ጋዜጠኞች በተደጋጋሚ ታስረው ሲፈቱ ችግሮች በሂደት ይስተካከላሉ የሚል ተስፋ የነበረው ቢሆንም ችግሩ ግን እየተባባሰ መሄዱን አረጋግጧል፡፡

ባለፉት አሰርት ዓመታት ጋዜጠኞች ሲታሰሩ፣ ሲሰደዱና ሲገደሉ ሁላችንም አዝነን ለሀገራችን የምንችለውን አድርገን ለውጥ መምጣቱ ቢታወቅም ለውጡ ግን ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች የተለየ ነገር ይዞ አልመጣም።

በመሆኑም ጋዜጠኞች ሙያዊ ነጻነታቸውን ሳያጡ እንዲሰሩ ሊፈቅድላቸው ሲገባ በተደጋጋሚ ማሰርና ማንገላታቱ መቆም እንዳለበት እናሳስባለን፡፡

መንግስት ጋዜጠኞችን መጠየቅና ማብራሪያ መጠየቅ ሲፈልግ በአገሪቱ ሕግ እንዲሁም አገሪቱ በተቀበለቻቸው ዓለም ዓቀፋዊ ስምምነቶች መሰረት የተፈራረመቻቸውን መብቶች ግምት ውስጥ አስገብቶ ሊሆን ይገባል፡፡ በመርህ ደረጃ አንድ ጋዜጠኛ፣ አንድ መሃንዲስ፣ አንድ ሚኒስትር እኩል መሆኑን ማመን ያስፈልገናል፡፡

ይህ ማለት ግን አጥፊ ግለሰቦችና ባለሙያዎች ሲኖሩ በሕግ አግባብ እንደማንኛውም ዜጋ ሊጠየቁ ይገባል።

ይህ ሲሆን ግን ፈጸሙት በተባለው ድርጊት በሕግ አግባብ ብቻ የሚጠየቁበት አግባብ ተከብሮ፣ በትክክለኛው ጊዜ ክስ ተመስርቶባቸው፣ በሕግ ጥላ ሥር ባረፉበት ቦታ በቤተሰቦቻቸው የመጠየቅ መብታቸው ተከብሮላቸው ሊሆን ይገባል።

ጋዜጠኞች አሁን ባለው ሁኔታ እየተሳደዱ የሚቀጥሉ ከሆነ አዲሱ ትውልድ የጋዜጠኝነትን ሙያ እንደወንጀል እየቆጠረ ከሙያው እንዲሸሽ የሚያደርግ፣ ባለሙያው በሚሰራው ስራ ነጻ ሆኖ ከመስራት ይልቅ እንዲሸማቀቅ የሚያደርግ፣ የምንናፍቀው የፕሬስ ነጻነትም ሆነ የአገር ብልጽግና ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ስለሚያደርግ ለብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ድምጽ ለሚሆነው ባለሙያ ክብር ይሰጥ እንላለን፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያዊቷ ሥራ ፈጣሪ አጊቱ ጉደታ ገዳይ የ20 ዓመት እስራት ተፈረደበት!

በጣሊያን የትሬንቶ ፍርድ ቤት ትናንት የካቲት 07 ቀን 2014 በዋለው ችሎት በኢትዮጵያዊቷ ሥራ ፈጣሪ አጊቱ ጉደታ ላይ አሰቃቂ ጥቃት በማድረስ ለህልፈተ ህይወት የዳረገው የ33 ዓመቱ ጋናዊ ሱሌማን አዳምስ ላይ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶበታል።

አጊቱ በትሬንትኖ ሊጠፉ የተቃረቡ የፍየል ዝርያዎችን ከመጥፋት በመታደግና ፍየል እርባታ፣ በአካባቢ እንክብካቤ፣ በወተትና ወተት ተዋፅኦ ምርት በጣም ውጤታማ የነበረች እና በጣሊያን ህዝብና መንግሰት እንዲሁም በዳያስፖራው ማህበረሰብ ዘንድ በውጤታማነቷ ሞዴል የነበረች ትጉህ ሴት ነበረች ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

ለዚህ ፍትህ መገኘት የአካባቢው የመንግስት ኃላፊዎችና ነዋሪዎች እንዲሁም የትሬንቲኖ የኢትዮጵያ ዳያስፓራ ኮሚኒቲ በጣሊያን የኢፌዲሪ ኤምባሲ ጋር በመስራት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ኤምባሲው ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ

አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉 https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
Forwarded from YeneTube
#የኢትዮጵያ_ታሪክ_ከንግስተ_ሳባ_እስከ_አዲስ_አበባ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

የኢትዮጵያን ታሪክ ከንግስተ ሳባ እስከ አዲስ አበባ የሚቃኘውና በአማዞን የምንጊዜም የኢትዮጵያ ታሪክ መጻህፍት ሽያጭ ከፍተኛ ደረጃን የተቆናጠጠው መጽሐፍ በአማርኛ ተተርጉሞ ቀረበ፡፡

ይህ አለም በጣም ያደነቀው መጽሐፍ ኢትዮጵያን በትናንት፣ በዛሬና በነገ መነጽር የሚያሳይ የ30 ዓመታት ምርምር ውጤት የሆነ በቅጡ ሊነበብ የሚገባው መጽሐፍ ነው፡፡

የአጼ ኃይለስላሴ የልጅ ልጅ ልጅ የሆኑት ልዑል አስፋ ወሰን አስራቴ ስለመጽሐፉ እንዲህ ነው ያሉት፡-

“አንብቤ ለመጨረስ ሶስት ሌሊቶች ብቻ ነው የወሰደብኝ፡፡ ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ጥንታዊ፣ ኃይማኖታዊ ልምምድ ላይ ባልተለመደና ቀልብን በሚያነሆልል ሁኔታ የተጻፈ ነው፡፡ መጽሐፉ በአፍሪካ ምድር ከሚገኙ መሳጭ ስልጣኔዎች መካከል አንዱ ስለሆነው የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለንን ግንዛቤ የሚያፋፋ እጽ ነው፡፡”

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun
Forwarded from YeneTube
🇭🇺የስራ ጉዞ ወደ #Hungary 🇭🇺
#Schengen_visa

👉 የሚሰራበት አገር - Budapest, Hungary
👉 የስራው አይነት - Construction work
👉 የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week
👉 የስራ ሰዓት - 8 - 10 hr/day
👉 የወር ደሞዝ - €1500 and more
👉 ፆታ - ወንድ
👉 ዕድሜ - 18 እስከ 45
👉 መኖሪያ ቤት - በነፃ
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 2 - 3 ወር ነው

#30_persons

#Requirements
👉 Passport
👉 Photo


Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
info@sabinaadvisor.com
http://Sabinaadvisor.com
https://tttttt.me/sabinavisaa
🎁 #ArtLand_gifts 🎁

✿ "እማይረሱ ስጦታዎችን ለሚወዷቸው" 🎁

✔️የወደዱትን "ፎቶ ወይም ምስል" እንጨት እና ቆዳ(ሌዘር) ላይ እንሰራለን 👌

✔️እንዲሁም MUG, PUZZLE, ሀብል እና ፕላስቲክ MDF ላይ የወደዱትን ፎቶ ወይም ፅሁፍ ያሰሩ 🎁


🔘☎️contact us: 0931465618
🔘For Order @Artlandgifts

Join our telegram channel👇
@artlandengraving
ሩሲያ በዩክሬን ላይ አሁንም ጥቃት ልትፈጽም ትችላለች ሲሉ ባይደን ተናገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እንደተናገሩት ሩስያ በዩክሬን ላይ አሁንም ጥቃት ልትፈጽም እንደምትችል በመግለጽ ሊደርስ የሚችለዉ ሰብዓዊ ኪሳራ እጅግ ግዙፍ ነዉ ሲሉ አስታዉቀዋል፡፡በአገር አቀፍ ደረጃ በቴሌቪዥን በተላለፈው የፕሬዝዳንቱ መልዕክት ዩናይትድ ስቴትስ ለእንደዚህ ዓይነቱ እርምጃ ቆራጥ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል ።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሩሲያ ከዩክሬን ጋር በሚያዋስናት ድንበር 150,000 ወታደሮችን አስፍራለች ሲሉ ገልጸዋል፡፡የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ አንዳንድ ሃይሎች አካባቢዉን ለቀዉ መውጣታቸውን ቢያሳዉቅም ባይደን ግን ይህ አልተረጋገጠም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ባይደን የሩሲያ ጦር መልቀቅ ጥሩ ነበር ነገርግን እስካሁን አላረጋገጥንም ሲሉ አክለዋል፡፡

ባይደን ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሞስኮ የጸጥታ ስጋት ትኩረት ሊሰጠው እና በቁም ነገር መታየት እንዳለበት ከተናገሩ ከሰዓታት በኋላ ነው።ፑቲን በተደጋጋሚ ዩክሬንን ለመዉረር አቅደዋል መባሉን ያስተባብላሉ፡፡ ፣ ሩሲያ በአውሮጳ ምድር ሌላ ጦርነት ሀገራቸዉ እንደማትፈልግ ቢናገሩም ከህዳር ወር ጀምሮ ያለዉ ውጥረት ግን እየጨመረ ይገኛል፡፡


#ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
ጄነራል ታደሰ ወረደን እና ሌ/ጄ ጻድቃን ገ/ተንሳይን ጨምሮ 54 ተከሳሾች በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይ ፍርድ ቤቱ አዘዘ።

ትዛዙን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

አጠቃላይ ክስ የቀረበባቸው ተከሳሾች 74 ሲሆኑ ጄነራል ታደሰ ወረደ እና ሌ/ጄ ጻድቃን ገ/ተንሳይን ጨምሮ 54 ተከሳሾች በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ሲሆን:

ቀሪዎቹ ኮነሬል መሐመድ ኑር እና ኮነሬል ባህሩ ታጀብን ጨምሮ 20 ተከሳሾች ግን በቁጥጥር ስር ውለው ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ የተደረጉ ናቸው።

በጥር 18 ቀን 2014 ዓ/ም በነበረው ቀጠሮ የተከሳሽ ጠበቆች በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት እየቀረቡ የሚገኙ ደንበኞቻችን የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብታቸው እንዲከበር ጉዳያቸው ተነጥሎ ይታይልን ሲሉ ፍርድ ቤቱን መጠየቃቸው ይታወሳል።

ከሳሽ ዓቃቢህግም በበኩሉ በቁጥጥር ስር ያልዋሉ እነ ጄነራል ታደረ ወረደን ጨምሮ 54 ተከሳሾች በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቆ የነበረ ሲሆን:

ፍርድ ቤቱም ላልቀረቡ 54 ተከሳሾች በኢትዮጲያ ፕሬስ ድርጅት የጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸው ትዛዝ በመስጠት የትዛዙን ውጤት ለመጠባበቅ ለዛሬ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቶ ነበር።

ይሁንና ፍርድ ቤቱ በትናንቱ ቀጠሮ 54ቱ ተከሳሾች በጥር 26 ቀን በጋዜጣ ጥሪ የተደረገላቸው መሆኑን አረጋግጧል።

በጋዜጣ ጥሪ ውጤት መሰረት ከ 54ቱ ተከሳሾች መካከል ችሎት የቀረበ ካለ ለማረጋገጥ ፍርድ ቤቱ የስም ጥሪ ያደረገ ቢሆንም በችሎት የቀረበ ግን አልነበረም።

በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ መዝገቡ ያልተያዙ ተከሳሾች በሌሉበት እንዲታይ ትዛዝ ሰቷል።

በዚሁ መዝገብ ተካተው ጉዳያቸው እየታዩ ያሉ የ20 ተከሳሾችን ክስ ለመመልከት ለየካቲት 22 ቀን ተለዋጭ ተሰቷል።

አጠቃላይ ተከሳሾቹ ከህውሐት የሽብር ቡድን ተልኮ በመቀበል :ወታደራዊ ቡድን በማደራጀት እና በመምራት በሰሜን ዕዝ መከላከያ አባላት በፌደራል ፖሊስ እንዲሁም በአማራና በአፋር ክልሎች ላይ ጥቃት በማድረስ ወንጀል በየደረጃው የተከሰሱ ናቸው።

ምንጭ: ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ
@Yenetube @Fikerassefa
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሀይል የማመንጨት ሙከራ መጀመሩ ተዘገበ!

ባለፉት ሁለት የክረምት ወቅቶች ውሀ በያዘው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኋይል ማመንጫ ተርባይኖችን በውሀ የመሞከር ስራ መጀመሩን ዋዜማ ራዲዮ ከምንጮቿ ሰምቻለሁ ብላለች።

የሚመነጨው ኋይልም ወደ ብሄራዊ የኋይል ቋት የሚገባ ሳይሆን ለሙከራ ያህል ብቻ የሚከናወን ነው።ሆኖም ሙከራው ግድቡ የኤሌክትሪ የኋይል አመንጭቶ ወደ ብሄራዊ ቋት ለማስገባት ለሚደረገው ጥረት ግን ወሳኝ ደረጃ ነው ተብሏል።

ዝርዝሩን ለማንበብ - https://bit.ly/3HNxpYt

@YeneTube @FikerAssefa